Wednesday, 8 January 2014

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ

07 January 2014

በሀገራችን ላይ የተንሠራፋውን አምባገነናዊ ሥርዓት ገርስሶ ለመጣል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ የሚወስዳቸውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃዎች አጠናክሮ በመቀጠል በታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር በላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ ገራርዋ ባምብላ ወንዝ በተባለው ቦታ መሽጎ የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያሰቃይና ሲያንገላታ ከነበረው የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር እና ከፀረ-ሽምቅ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ባደረገው ውጊያ 24 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል የግንባሩ ሠራዊት አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል፡፡


 በዚሁ ዕለትም በተደረገው እልህ አስጨራሸ ውጊያ የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚደርስበትን የተኩስ ናዳ መቋቋም ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጡን ታውቋል::

ይህ በእንዲሀ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ ባስመዘገበው ከፍተኛ ወታደራዊ ድል መደሰታቸውና ወደፊትም ሀገራዊና ሕዝባዊ አላማን አንግቦ የህብረተሰቡን እምባ በማበስ ግንባር ቀደም በመሆን ለሀገርና ለወገን ደራሽነቱን እያስመሰከረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊትን በመደገፍ የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው ግንባሩ በተከታታይ ጊዜያቶች የሚወስዳቸው ወታደራዊ ጥቃቶችና የሚያስመዘግባቸው አንፀባራዊ ድሎች የወገንን አንጀት በማራስ በአንፃሩ ደግሞ የጠላትን አንገት በማስደፋቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡


 በመጨረሻም የአካባቢው ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የጀግና አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከግንባሩ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

January 8, 2014                                         

‹‹ግብፅ ስምምነት የተደረሰበትን ጉዳይ ለመቀልበስ እየጣረች ነው››
የታላቁን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ሦስተኛ ዙር ድርድራቸውን ለመቀጠል የተገናኙት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና ሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሳይግባቡ ቀሩ፡፡ ሦስተኛው ዙር ድርድር ያለውጤት ቢበተንም ውይይቱን በሌላ ጊዜ ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡
የሦስቱ አገሮች ሚኒስትሮች ከዚህ ቀደም ሁለት ዙር ድርድሮችን በማካሄድ በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ መሆኑን የሚከታተል ኮሚቴ ለማቋቋም መስማማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡


የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ቀሩ በተባሉ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሦስተኛ ዙር ድርድር ለማካሄድ በያዙት ቀጠሮ መሠረት ባለፈው ቅዳሜ ካርቱም የተገናኙ ቢሆንም፣ በግብፅ በኩል የቀረበው ሐሳብ ቀደም ባሉት ድርድሮች እልባት ያገኙ ጉዳዮችን የሚቀለብስ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አለማገኘቱን በኢትዮጵያ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅ አህመድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡


የሦስት አገሮች ሚኒስትሮች ከዚህ ቀደም በነበሩ ሁለት ድርድሮች ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግና ተግባራዊነቱን የሚከታተል ኮሚቴ ለማቋቋም ስምምነት የደረሱበት ጉዳይ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ፈቅ፣ በሦስተኛው ዙር ድርድር ይህንን ኮሚቴ የሚቆጣጠር ሌላ ዓለም አቀፍ አማካሪ ይቋቋም የሚል ሐሳብ ግብፅ ይዛ በመቅረቧ ላለመግባባቱ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


ቀደም ሲል እንዲቋቋም የተስማሙበት ኮሚቴ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ለመተግበርና ተግባራዊነቱን መከታተል መሠረታዊ ኃላፊነቱ ሲሆን፣ ሦስቱን አገሮች የሚወክሉ ዜጎች ብቻ የኮሚቴው አባላት እንደሚሆኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡


የኮሚቴው አባላት ስብጥርን በተመለከተ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተንፀባርቆ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን የኮሚቴው አባላት በሦስቱ አገሮች የሚወከሉ ዜጎች ብቻ ይሁኑ በሚለው የኢትዮጵያ አቋም ላይ ስምምነት ተደርሷል፡፡ ይህ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የውጭ አማካሪ ቅጥር የመፈጸምና አማካሪው የሚያቀርበውን ሐሳብ ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ የማቅረብ ኃላፊነት እንደሚኖረው፣ ለዚህና ለሌሎች ኃላፊነቶቹ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሦስቱ አገሮች ይሸፍኑ በማለት ተደራዳሪዎቹ ተስማምተው እንደነበር ይታወሳል፡፡


በሦስተኛው ዙር ድርድር ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፣ የግብፅ ተደራዳሪዎች ተጨማሪ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት እንዲቀጠር መጠየቃቸውን አቶ ፈቅ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡


ግብፆች እንዲቀጠር የጠየቁት ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ከዚህ ቀደም ስምምነት የተደረሰበት ኮሚቴ ኃላፊነቶችን በበላይነት የመከታተል ድብቅ አጀንዳ እንዳለው መረዳት የተቻለ መሆኑን አቶ ፈቅ ገልጸዋል፡፡


‹‹አማካሪ ለመቅጠር ቅጥሩን የሚያማክር አማካሪ ድርጅት መቅጠር ተቀባይነት የሌለው አሠራር ነው፡፡ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ተግባራዊነት ለመከታተል የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች በቂ ናቸው፤›› የሚል አቋም  በኢትዮጵያ በኩል መያዙን፣ በዚህ ላይ መግባባት ባለመቻሉም ድርድሩ መቋረጡን አስታውቀዋል፡፡


‹‹በግብፅ በኩል ድብቅ ዓላማ ካልተያዘ በቀር አማካሪ ለመቅጠር ሌላ አማካሪ መቅጠር ታይቶ አይታወቅም፤›› ያሉት አቶ ፈቅ፣ ጉዳዩ ግን ተደጋጋሚ ውይይትን የሚጠይቅ በመሆኑ ለቀጣይ ውይይት በመስማማት መበተኑን ገልጸዋል፡፡ ቀጣዩ ውይይት መቼ እንደሚካሄድ ቀን ባይቆረጥም በግብፅ በኩል ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ድርድሩ የሚካሄደው በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ቢሆንም የሱዳን መንግሥት የህዳሴውን ግድብ ጠቀሜታ በመገንዘብ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋምን ማራመድ መርጧል፡፡ ይህ በመሆኑም ድርድሩ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው በዋናነት በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል መሆኑን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ ካቀረቡት ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በ45 ሰዎች ላይ ከሦስት ዓመት እስከ 12 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ፍርድ ሰጠ፡፡

January 8, 2014                                          

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በ45 ሰዎች ላይ ከሦስት ዓመት እስከ 12 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ፍርድ ሰጠ፡፡
ፍርዱ ከተላለፈባቸው መካከል በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የፓርላማ ወንበር የነበራቸው ይገኙበታል፡፡የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ዝርዝር አለው፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
http://amharic.voanews.com/audio/Audio/362865.html

ዛሬም ኢትዮጵያውያን በጅዳ መካ በከፍተኛ ስቃይና እንግልት ላይ ናቸው (በፎቶ የተደገፈ አዲስ መረጃ ከሳዑዲ)



Hello, world!
6000bc359d71474716d3500832e9d989






በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞት
ነብዩ ሲራክ (ከሳዑዲ አረቢያ)
ካሳለፍነው ወር ጀምሮ በመንግስት ጥሪ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ ” ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው! ” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
Screenshot_2014-01-08-01-29-06-1
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው !” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል። የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው ከአይን እማኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።
የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ ” በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።
Screenshot_2014-01-08-01-29-16-1
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል። “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።
ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው ” የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም? ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም ! ዜጎች አይደልንም? ” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።
Screenshot_2014-01-08-01-29-39-2
የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-
የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች ቅሬታ እያሰሙ ነው ። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው ። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች ” ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን ! ” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው ። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውረተውኛል።
Screenshot_2014-01-08-01-29-20-1
በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ -
በጀዛን ” ወደ ሃገር እንግባ !” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን !” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገን የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል። በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል! ” እያሉ ነው! በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም ” እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን።አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው። ” ይላል። የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም! ” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ ” በዲሲፕሊን! ” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!
Screenshot_2014-01-08-01-29-51-1
የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ -
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑ አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።
a97a08f471f6148ffe0ee14caac97504
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ” ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ !” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!” ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ !
ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ” ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !
\

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 07 2014 Ethiopia | ESAT Tube