አዲስ አበባ ፣ ጥር 2 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጨረታ ሂደት የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 6 ግለሰቦች ዛሬ ከ6 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ።
ተከሳሾቹ አቶ ያረጋል አይሸሹም የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና የክልሉ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ የነበሩት አቶ ሀብታሙ ሂካ ፣ የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌድዮን ደመቀ፣ አቶ አሰፋ ገበየሁ የአቶ ጌድዮን አማካሪ ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገ እና አቶ መክብብ ሞገስ በስራ ተቋራጭነት የሚሰሩ ናቸው።
በ1997 ዓ.ም ከክልሉና ከፌደራል መንግስት በተገኘ የ79 ሚሊዮን ብር በጀት የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ፣ የግልገል በለስ ማሰልጠኛ ኮሌጅና የጣና በለስ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት እንዲከናወን አቶ ያረጋል አይሸሹም የሚመሩት የክልሉ ካቢኔ ይወስናል።
በግልፅ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች ተወዳድረው ግንባታው መከናወን ሲገባው ፥ ባልተገባ መንገድ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በፈጠሩት የጥቅም ትስስር ፤ የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት እንዲያሸንፍ ይደረጋል።
የክልሉ መንግስት የግዥ ስርዓት መመሪያ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ግዥ ሲፈፀም የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማፅደቅ አለበት የሚል ቢሆንም ፥ ከተከሳሾቹ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካ ከባለሃበቶቹ ጋር በመመሳጠር ጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ያለግልፅ ጨረታ እንዲያሸንፍና ሶስቱንም ፕሮጀክቶች እንዲሰራ ያደርጋሉ። '
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ተጫራቹ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን ፥ በ13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ5 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል ፤ ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ድርጀትም በህገወጥ መንገድ እንዲያሸንፍ ከመደረጉም በላይ ደረጃው ፕሮጀክቶቹን ለመገንባት የሚያስችል አለመሆኑም በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል።
የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካን ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ሌሎች ባለሀብቶችን ደግሞ በመመሳጠር በዚህ ወንጀል በመሳተፋቸው ከሷቸዋል።
እንዲከሰሱ ካስቻሏቸው ነጥቦች መካከል በ13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ5 ዓመት በላይ መጓተታቸው ፣ በተጨማሪ 7 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለተቋራጩ መከፈሉ ፣ እነዚህ ባለሀብቶች በተለያየ ጊዜያት ለአቶ ያረጋል አይሸሹምና ለአቶ ሀብታሙ ሂካ ጉቦ መስጠታቸው ፣ የጨረታ መመሪያ ደንብ መጣስና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ ።
መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ህዳር 11 2006 አቶ ያረጋል አይሸሹም ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገና አቶ መክብብ ሞገስን በአቃቤህግ ከተመሰረተባቸው ክሶች በአንድ ብቻ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ፥ አቶ ሀብታሙ ሂካ ፣ ጌድዮን ደመቀና አቶ አሰፋ ገበየሁን በ3 ክሶች ነበር ጥፋተኛ ያላቸው።
በዚህ መሰረት ዛሬ ከሰዓት ችሎቱ የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ከግምት በማስገባት አቶ ያረጋል አይሸሹምን በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺህ ብር ፣ አቶ ሀብታሙ ሂካን በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ45 ሺህ ብር ፣አቶ አሰፋ ገበየሁን በ15 ዓመት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር ፣ አቶ ጌድዮን ደመቀን በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና 60 ሺህ ብር ፣ አቶ ገዛኧኝ አድገ እና አቶ መክብብ ሞገስን እያንዳንዳቸው በ 6 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ25 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።
በመዝገቡ በ7ኛ ተራ ቁጥር ተጠቅሶ የነበረው የአቶ ሀብታሙ ሂካ ወንድም አቶ ሀብተገብርኤል ሂካ ህዳር 11 ፣ 2006 ዓ.ም በዋለው ችሎት በብይን በነፃ መለቀቁ ይታወሳል።
Friday, 10 January 2014
የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!
January 10, 2014
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል የጋራ ኃይል አድርጎ ራሱን የሚጠራ አካል የዜጎችንና የተቋማትን ሕገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በመጣስ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ሳይወሰን ወንጀለኛ ሲያደርጋቸውና ስማቸውን ሲያጎድፍ ማየት እየተለመደ የመጣ ተደጋጋሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ተውጣጥቶም ይሁን ተቀናጅቶ የሚሰራ አካል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው ቆይቷል፡፡
ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል፡፡ በዚሁም መሰረት ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ፕሮፓጋንዳ አሸባሪ ያላቸውን ድርጅቶችና ግለሰቦች አድርሰውታል ያለውን ጥፋት በዝርዝር አቅርቧል፡፡ ፓርቲያችንን በዚሁ ዘገባ ከተጠቀሱት “አሸባሪ” ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ስም ለማጉደፍና ለማስፈራራት የተደረገውን መፍጨርጨር አይተናል፣ ሰምተናል፣ ተገርመናል በመጨረሻም አዝነናል፡፡
በዘጋቢ ፊልሙ የቀረቡ ፓርቲያችንን የማይመለከቱ ጉዳዮችን ትተን ከፓርቲያችን ጋር በማገናኘት የተጠቀሰው “ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳንጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎልናል፡፡ ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የፈለገውን አካል ለመፈረጅ፣ ለመክሰስና ለመፍረድ ሥልጣኑን ከየት እንዳገኘ የማይታወቅ ሲሆን የዚህች ሐገር ዜጎችም ሃሳባችንን የምንገልፅበትንና የማንገልፅበትን የመገናኛ ብዙሃን እየመረጠልንና እየወሰነልን ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ ዓይነቱን የእብሪት መልዕክት ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው ብሎ ያምናል፡፡
የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ነገር ግን ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፍ አይደለም፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት የለም፡፡ ማንም መልዕክት የሚያስተላልፍ አካል የሚያሰራጨው ሃሳብ የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ ከሆነ መልዕክቱ የተላለፈበት መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ይሁን ሌላ ህጋዊ የተባለ የመገናኛ ብዙሃን መሆኑ ብቻ መልዕክት አስተላላፊውን አካል ከተጠያቂነት ሊያድን እንደማይችልም ለማንም የተሰወረ ይሆናል የሚል እምነት የለንም፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ እያደረገ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል፡፡ በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)