ኢ.ኤም.ኤፍ – የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ከ30 አመታት በኋላ ለከፍተኛ ደረጃ እንዳደረሰ የሚነገርለት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከነበረበት ሃላፊነት መነሳቱን የስፖርት ፌዴሬሽን አሳውቋል። ይህን አስመልክቶ እስካሁን ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በኩል ምንም የተሰማ ነገር የለም። ሆኖም ከጥቂት ቀናት በፊት ስፖርት ፌዴሬሽኑ አድርጎት በነበረው ግምገማ ላይ፤ በኢትዮጵያ ላይ ሊገቡ የቻሉት ግቦችን አስመልክቶ፤ አሰልጣኝ ሰውነት ተጫዋቾቹን በመከላከል፤ “ሃላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ የምወስደው እኔ ነኝ” ማለቱ ይታወሳል።
ከተጠቀሱት ግቦች መካከል፤ ተከላካይ ደጉ ደበበ ሜዳው ላይ አዳልጦት ከወደቀ በኋላ የገባውን ግብ አስመልክቶ ሲናገር፤ “ደጉ ደበበ በጨዋታም በሩጫም ተበልጦ ሳይሆን፤ ሜዳው አዳለጠው ሌላኛው ተጫዋች አልፎት ሄደ ግብ ገባብን።” በማለት ይህን እና ሌሎችንም ግቦች በተመለከተ ሙያዊ ትንታኔውን ሰጥቶ ነበር። በዚያም ተባለ በዚህ ግን የዚያኑ ቀን እና ከዚያም በኋላ አሰልጣኝ ሰውነት ሃላፊነቱን እንዲለቅ ግፊት ሲደረግበት ቆይቶ ዛሬ ቦታውን ለቋል። ይህንን በተመለከተ እስካሁን ከአሰልጣኝ ሰውነት የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም፤ ሰዎች ግን አስተያየት መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ነው።
በአንድ በኩል ያለው ወገን… “ተጫዋቾቹን ለዚህ በማብቃቱ እራሱን ከምንም በላይ እላይ አድርሶ ነበር። የሚሰጡ አስተያየቶችን አይቀበልም። በራሱ መንገድ ብቻ ነው የሚመራው። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው።” ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ የሆነ አስተያየት ሰጥተዋል።
ሌላው ወገን… “ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ደረጃ አድርሷል። እያንዳንዱ አሰልጣኝ ቡድኑን የሚያዘጋጅበት የራሱ የሆነ መንገድ አለው። አሰልጣኝ ሰውነት ሙያውን ተምሮ እና በዚሁ የአሰልጣኝነት ሙያ የተመረቀ ኢትዮጵያዊ ነው። ቡድኑን ለዚህ በማብቃቱ ቢኩራራ ወይም ሌሎች ጉዳዩ የማይመለከታቸው ሰዎች የሚሰጡትን አስተያየት አለመቀበሉ አይስደንቅም። በራሱ የሚተማመን ሰው የሚሰጠውን ምላሽ ነው የሰጣቸው።” ይላሉ።
በመጨረሻም ከዚህ በፊት ስናደርግ እንደነበረው የራሳችንን አስተያየት በመስጠት ይህን ዘገባ እናጠናቅቃለን። አሁን የተደረገው ውሳኔ ትክክል መሆን እና አለመሆኑን ለታዛቢዎች እንተዋለን። ነገር ግን “አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተባረረ” የሚለው ዜና በራሱ የሚፈጥረው አሉታዊ ስሜት አለ። አሰልጣኙ ያበረከተውን መልካም ስራ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ፌዴሬሽኑ… “አባረርን” ከማለት ይልቅ፤ “በክብር አሰናበትናቸው” ማለት ይችላል። ማለት ብቻም ሳይሆን ማድረግም ይቻል ነበር።
አሰልጣኝ ሰውነት ከቦታው ሲነሳ፤ በምትኩ ቦታውን የሚወስደው ስዩም አባተ ሊሆን እንደሚችል እሙን ነው። ስለሆነም አሰልጣኝ ሰውነት እና አሰልጣኝ ስዩም (ወይም ሌላው ተራካቢ) በተገኙበት “የሃላፊነት ሽግግር ተደረገ” ቢባል፤ የተጫዋቹን፣ የደጋፊውንና የሌላውንም ኢትዮጵያዊ ክብር የሚጠብቅ ይሆን ነበር። አሁንም ቢሆን ርክክቡን በኦፊሴል አድርጎ፤ የቀድሞው አሰልጣኝ ለአዲሱ እንዲያስረክብ ማድረግ ይቻላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ላለነውም ደስ ይለናል፤ ለመጪውም አዲስ አሰልጣኝ ተስፋ ይሰጠዋል። በዚህ የስልጣኔ ዘመን ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን አዲሱም አሰልጣኝ ቢሆን፤ መቼ እንደሚባረር ስለማያውቅ በመሳቀቅ የስራ ዘመኑን ሊገፋ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ርክክቡን በሰላም እና በፍቅር አድርጉት። በፍቅር የተጀመረ ነገር በፍቅር ያልቃልና – ይህ ነው የዛሬው የኢ.ኤም.ኤፍ መልዕክት።
Wednesday, 5 February 2014
በሳንሆዜ፤ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች፤ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በህብረት የወያኔን ሴራ እናምክን!!
February 5, 2014
እንዳለመታደል ታዲያ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የስልጣን መንበር ላይ የተፈናጠጠው ጎጠኛውና አምባገነኑ የወያኔው ቡድን ከህዝባችን ፍላጎት በተቃራኒው በመቆም፤ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ባለሙዋልና ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን፤ የሺ አመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ሃገራችንን፤ ህዝቦችዋን እና በውስጡዋ ያዘለችውን አኩሪ ባህል፤ በመናቅ፤ በመካድ፤ ብሎም በዘርና በጎሳ በመከፋፈል፤ በጎጥና በቁዋንቁዋ በመነጣጠል፤ በመንደር እና
በወንዝ በመለያየት፤ የሃይማኖት ልዩነትን ወዳልተፈለገ ጥግ በመግፋት፤ የጋራ የሆኑ ታሪካዊ እሴቶቻችንን፤ እንደ ህዝብ የሚያስተሳስር ሰንደቅ አላማችንን ሳይቀር በመለወጥ፤ ህልውናችንን ከመፈታተን አልፎ፤ ወደ ማጥፋት ግስጋሴ ላይ እንደሆነ የታወቀ ነው። በዚህ ጠባብና ጎጠኛ ቡድን የአገዛዝ ዘመን፤ ታሪካዊ ሃገራችን ወደብ አልባ፤ ትውልድ አልባ፤ እምነት አልባ፤ ጀግና አልባ፤ ብሎም በአጎራባች ሃገሮች ቸርነት ላይ ተስፋዋን የጣለች፤ መጻግኡ ሆናላች ብንል የተጋነነ አይደለም። ጀግኖች ኣባቶቻችን ኣጥንታቸውን ከስክሰው፤ ከባሩድ እና ከጥይት ጋር ተጠራምሰው፤ በመርዝ ጭስ ተጨርሰው፤ እነሱ አልፈው ያቆዩትን ሰነደቅ አላማ፤ ይሄ ዘረኛ ቡድን በበርሃ ስኩዋርና በሶ ሲሸከምበት፤ ከተማ ከገባ በሁዋላም ጨርቅ ነው እያለ ሲራቀቅ እና ሲመጻደቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ
ነው።
በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባረ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮመኛ ተናጋረ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፋው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባረነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታረካችን ታይቶ እማይታውቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲየዙ አድረጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተስጥቷል።
በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራረው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና ባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት ያገዛዝ አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታዎቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከር ከጀመሩ ሰንበትበት ብሎል በየሄዱበት ቢከሽፍም። ዛሬ ታድያ በዚህ ብምንኖርበት በሳን ሆዜ ከተማ ውህዳን የወያኔ ጀሌዎች የወያኔን ጭምብል ለብሰው “ልማታዊ” የልመና አኩፋዳቸውን አዘጋጅተው ለፌብሯዋሪ 8፣ በ770 ሞንታጊዩ ኤክስፕሬስ ዌይ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ (770 Montague Expressway San Jose CA 95134) በህዝባችን እንባ ሊሳከሩ እና በሃዘኑ ሊሳለቁበት ተዘጋጅተዋል። እኒኚህ ከሃዲዎች የወያኔን ሹማምንትም ጋብዘዋል። ከሃዲዎችን ማጋለጥ እና ቅስማቸውን መስበር ኢትዮጲያዊ ግዴታችን በመሆኑ ሁላችንም ኢትዮጲያውያን አንድ ላይ በመሆን በሌሎች ከተሞች እንደተደረገው ሳን ሆዜ ለባንዳዎች አይሆንም ልንላቸው ይገባል። እላይ በተጠቀሰው አድራሻ ክ3፡00PM በመገናኘት ድምጹን ማሰማት ላልቻለው ህዝባችን ድምጽ እንሆነው ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።
…በሳን ሆዜ ከተማ ውህዳን የወያኔ ጀሌዎች የወያኔን ጭምብል ለብሰው “ልማታዊ” የልመና አኩፋዳቸውን አዘጋጅተው ለፌብሯዋሪ 8፣ በ770 ሞንታጊዩ ኤክስፕሬስ ዌይ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ (770 Montague Expressway San Jose CA 95134) በህዝባችን እንባ ሊሳከሩ እና በሃዘኑ ሊሳለቁበት ተዘጋጅተዋል።
ሐገራችን ኢትዮጵያ የአንጸባራቂ ታሪክ ባለቤት፤ ለአፍሪካና እንዲሁም በአለም ዙሪያ ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ እንደ አጥቢያ ኮከብ የምትታይ መሆኑዋ በወዳጅም በጠላትም የተመሰከረ ሃቅ ነው። ታሪካዊ ጠላቶች፤ የሀገራችንን ሉአላዊነት፤ የህዝባችንን በራስ መተማመን፤ ሀገር ወዳድነት፤ የራሱ የሆነ ባህል፤ ወግ እና እምነት ጠብቆ መቆየት እንቅልፍ ነስቷቸው፤ ሲቻላቸው ከመሃከላችን፤ ለጠላት ያደሩ ከሃዲ ባንዳዎችን በመመልመል፤ ሳይቻል ደግሞ በቀጥታ በመዝመት እኛነታችንን ለማክሰም፤ የነበራቸው ህልም፤ በጀግኖች አባቶቻችን እና ጀግኖች እናቶቻችን ቆራጥ ተጋድሎ የወራሪው ሃይል ህልም መክኖ ቀርቶዋል።እንዳለመታደል ታዲያ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የስልጣን መንበር ላይ የተፈናጠጠው ጎጠኛውና አምባገነኑ የወያኔው ቡድን ከህዝባችን ፍላጎት በተቃራኒው በመቆም፤ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ባለሙዋልና ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን፤ የሺ አመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ሃገራችንን፤ ህዝቦችዋን እና በውስጡዋ ያዘለችውን አኩሪ ባህል፤ በመናቅ፤ በመካድ፤ ብሎም በዘርና በጎሳ በመከፋፈል፤ በጎጥና በቁዋንቁዋ በመነጣጠል፤ በመንደር እና
በወንዝ በመለያየት፤ የሃይማኖት ልዩነትን ወዳልተፈለገ ጥግ በመግፋት፤ የጋራ የሆኑ ታሪካዊ እሴቶቻችንን፤ እንደ ህዝብ የሚያስተሳስር ሰንደቅ አላማችንን ሳይቀር በመለወጥ፤ ህልውናችንን ከመፈታተን አልፎ፤ ወደ ማጥፋት ግስጋሴ ላይ እንደሆነ የታወቀ ነው። በዚህ ጠባብና ጎጠኛ ቡድን የአገዛዝ ዘመን፤ ታሪካዊ ሃገራችን ወደብ አልባ፤ ትውልድ አልባ፤ እምነት አልባ፤ ጀግና አልባ፤ ብሎም በአጎራባች ሃገሮች ቸርነት ላይ ተስፋዋን የጣለች፤ መጻግኡ ሆናላች ብንል የተጋነነ አይደለም። ጀግኖች ኣባቶቻችን ኣጥንታቸውን ከስክሰው፤ ከባሩድ እና ከጥይት ጋር ተጠራምሰው፤ በመርዝ ጭስ ተጨርሰው፤ እነሱ አልፈው ያቆዩትን ሰነደቅ አላማ፤ ይሄ ዘረኛ ቡድን በበርሃ ስኩዋርና በሶ ሲሸከምበት፤ ከተማ ከገባ በሁዋላም ጨርቅ ነው እያለ ሲራቀቅ እና ሲመጻደቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ
ነው።
በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባረ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮመኛ ተናጋረ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፋው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባረነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታረካችን ታይቶ እማይታውቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲየዙ አድረጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተስጥቷል።
በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራረው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና ባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት ያገዛዝ አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታዎቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከር ከጀመሩ ሰንበትበት ብሎል በየሄዱበት ቢከሽፍም። ዛሬ ታድያ በዚህ ብምንኖርበት በሳን ሆዜ ከተማ ውህዳን የወያኔ ጀሌዎች የወያኔን ጭምብል ለብሰው “ልማታዊ” የልመና አኩፋዳቸውን አዘጋጅተው ለፌብሯዋሪ 8፣ በ770 ሞንታጊዩ ኤክስፕሬስ ዌይ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ (770 Montague Expressway San Jose CA 95134) በህዝባችን እንባ ሊሳከሩ እና በሃዘኑ ሊሳለቁበት ተዘጋጅተዋል። እኒኚህ ከሃዲዎች የወያኔን ሹማምንትም ጋብዘዋል። ከሃዲዎችን ማጋለጥ እና ቅስማቸውን መስበር ኢትዮጲያዊ ግዴታችን በመሆኑ ሁላችንም ኢትዮጲያውያን አንድ ላይ በመሆን በሌሎች ከተሞች እንደተደረገው ሳን ሆዜ ለባንዳዎች አይሆንም ልንላቸው ይገባል። እላይ በተጠቀሰው አድራሻ ክ3፡00PM በመገናኘት ድምጹን ማሰማት ላልቻለው ህዝባችን ድምጽ እንሆነው ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።
Subscribe to:
Posts (Atom)