May 22nd, 2014
በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን፤ በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በገዛ ወንዟ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል።
እንደሚታወቀው፤ ሰሞኑን በየድህረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፤ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው በኢትዮጵያ በመገንባት ስላለው ታላቅ የአባይ ግድብ ነው። ስለ ግድቡ የተንጸባረቁት የተለያዩ አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው፤ የአባይ ወንዝ ባለቤትነት የማን እንደ ሆነ፤ ውሱን በሆነ መንገድ ተነካ እንጂ በጥልቀት በተከናወነ ምርመራና በዓለም-አቀፍ ሕግ ላይ በተመሠረተ አስተማማኝ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ አልቀረበም። የዚች ጦማር ዓላማም ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር በምታከናውናቸው ውሎች ያሁኑንና የመጪውን ትውልድ ሁሉ መብት በሚጠብቅ ሥልት መጠቀሟን እንድታረጋግጥ ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅትና ጥንቃቄ እንድታደርግ ለማሳሰብ ነው። በዚህ አጋጣሚም፤ ተሞክሮው ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ስለሚመስለኝ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት፤ የለሶቶ (Lesotho) መንግሥት የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በነበርኩበት ጊዜ ስለዛች ሐገር ወንዝ፤ በዓለም ባንክ ድጋፍ፤ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር እኔ ራሴ በመራሁት የልዑካን ቡድን ስለ ተከናወነው ድርድርና ስለ ተገኘው ውጤትም ባጭሩ እገልጻለሁ።
የአባይ ወንዝ በረከት፤
አባይ፤ ኢትዮጵያ ካሏት እጅግ ታላቅና አኩሪ የተፈጥሮ ሐብቶች አንዱ ነው። ክልዩ ልዩ ወንዞች የተጠራቀመው ወደ 80 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር (cubic metre) ውሀ በአባይ አማካኝነት እየተዥጎደጎደ ሱዳንንና ግብጽን እያለማ አቋርጦ ከሚተነው ውሀ የተረፈው ሚዲቴሬኒያን ባሕር ይገባል። አባይ ከኢትዮጵያ ሰንቆ የሚጓዘው ውሀ ብቻ ሳይሆን ለም አፈር ጭምር ነው። ስለዚህ ግብጽና ሱዳን የሚታየው ለም መሬት፤ አብዛኛው በአባይ ወንዝ አማካኝነት ከኢትዮጵያ በሚጎርፍለት ውሀና ለም አፈር ችሮታ ነው። በተጨማሪም፤ እስካሁን ሳንጠቀምበት የቆየነው፤ ምናልባት በመሠራት ላይ ያለው ግድብ ለውጤት ከበቃ፤ ለኢትዮጵያና ለአካባቢዋ ከፍ ያለ የኃይል ማመንጪያ ሐብት ሊያስገኝ የሚችለው ሌላው የአባይ ወንዝ በረከት ሊሆን ይችላል።
በአባይ ወንዝ በረከት የተጠቀመው ማን ነው?
በእንግሊዝኛ Blue Nile (በአማርኛ፡ አባይ) ከተሰኘው፤ በዓለምና በታሪክ ታዋቂ ከሆነው ወንዝ ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ሱዳንና ግብጽ ናቸው። ከሌሎች ሐገሮች ጭምር ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚፈሰው ውሀ ሲታሰብ ከኢትዮጵያ የሚዘልቀው የአባይ ወንዝ አስተዋጽኦ ከጠቅላላው የውሀ መጠን 86% እንደ ሆነ ይታወቃል። የሚያሳዝነው ከባድ ጉዳይ ግን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ የሆነችው፤ ኢትዮጵያ፤ ለብዙ ዘመናት ተጠቃሚ ሳትሆን መቅረቷ ነው። ይህን ሁኔታ ከባድ የሚያደርገው፤ ባንድ በኩል አባይን የመሰለ
አኩሪ የውሀ ሐብት እያላት፤ ኢትዮጵያ በድርቀት ምክንያት በመደጋገም ረሀብና እልቂት የተፈራረቀባት ሐገር መሆኗ ነው።
በዚህ አጋጣሚ፤ አንድ የማልረሳው ነገር፤ በተባበሩት የዓረብ ኤሚሬትስ እሠራ በነበረበት ጊዜ፤ በዚያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ባዘጋጀልን አንድ ስብሰባ አንድ ግብጻዊ የውሀ መሐንዲስ ጎኔ ተቀምጦ ስለ ነበር፤ በውይይታችን መሀል የአባይ ወንዝ ጉዳይ ተነሳና አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚመነጭ መሆኑን ሳስታውሰው፤ ወዲያውኑ የሚያስቆጭ መልስ ሰጠኝ፤ “አዎን፤ እኛ (ግብጽ) እንጠቀምበታለን።” “እኛም (ኢትዮጵያም)” የምልበት ጊዜ በሕይወት እያለሁ ይደርስ ይሆን?!
ለመሆኑ፤ የአባይ ወንዝ ባለቤት ማን ነው?
ዶር. ሚንጋ ነጋሽ፤ ዶር. ሰይድ ሀሰንና ዶር. ማሞ ሙጬ በቅርቡ ባበረከቱት “Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam” በተሰኘው ጽሑፋቸው፤ ክታዋቂው ከሪቻርድ ፓንከርስት (Richard Pnakhurst) በመጥቀስ፤ በጥንቱ፤ ቱርኮች ግብጽን በሚገዙበት ዘመን፤ የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ መሆኗ ታውቆ፤ 50000 (ሃምሳ ሺ) የወርቅ መሀለቅ (gold coins) ለሐገራችን በየዓመቱ ይከፍሉ እንደ ነበር ታውቋል።
ከላይ እንደ ተጠቀሰው፤ ምንም እንኳ ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚነጉደው የአባይ ወንዝ ምንጭ ኢትዮጵያ ብትሆንም፤ በቅርብ ዘመናት የታየው፤ ለጊዜው ተጠቃሚ የሆኑት ሐገሮች እያንጸባረቁት የቆየው ተጨባጭ ክስተት ባለቤትነቱ የነሱ እንደ ሆነ ዓይነት መሆኑ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ምሑራን እንደ ገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችባቸው ውሎች፤ (ሀ) እ.አ.አ በ1929 በእንግሊዝና በግብጽ መሀል በተፈጸመው ውል 48 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለግብጽ፤ 4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን እንዲመደብ፤ በኋላ ደግሞ (ለ) በ1959 በግብጽና በሱዳን መሀል በተከናወነው ውል 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ለግብጽ፤ 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን ተመድቧል። የሚያስገርመው፤ ዋናዋ የውሀው ምንጭ የሆነችው የኢትዮጵያ መብት ምንም ዋጋ አልተሰጠውም።
ባሁኑም ጊዜ ተከስቶ ያለው ሁኔታ፤ ግብጽ “የአባይ ስጦታ” (“Gift of the Nile”) መሆኗን ስለምታውቅ በተለይ በቅርቡ ዘመን የለመደችውን ልቅ የሆነ በአባይ ወንዝ የመጠቀም ችሮታ ያለገደብ እንድትቀጥል መብቷ እንደ ሆነ እያስመሰለች ኢትዮጵያ በመብቷ ከተጠቀመች እርምጃ የሚያስከትል መሆኑን በመጠቆም የማስፈራራት ሥልት እያናፈሰች፤ በሌላ በኩል የዚህ ዓይነት አጉል ዘዴ የማያዋጣ መሆኑን ግንዛቤ ያለው በሚመስል ሥልት ለመደራደር ፈቃደኛነት ትጠቁማለች። ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ለማስከበር በቁርጠኛነት ከወሰኑ፤ ማንም ሊገድባቸው እንደማይችል ግብጽም ብትገነዘብ መልካም ነው። በታሪክ እንደምናውቀው፤ ግብጽ፤ የሕልውናዋ ምንጭ የሆነውን አባይን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ፤ ከአሥር ጊዜ በላይ ኢትዮጵያን ወርራ፤ ሐረርን እስከ መያዝ ደርሳ፤ በመጨረሻው ግን ሳይሳካላት ቀርቷል። በተቃራኒው፤ ከታሪክ የምንማረው፤ ኢትዮጵያ ከኃያሎቹ ሐገሮች አንዷ በነበረችበት ዘመን፤ ግብጽንም ተቆጣጥራ እንደ ነበር ነው። ለዚህ ማስረጃ ካስፈለገ፤ የጥንት ግብጻዊ ነገሥታትን ታሪክ መመልከት ይበቃል። ስለዚህ፤ ግብጽ ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነት የምትከተለው ሥልት የትም ስለማያደርሳት፤ ይልቁንስ ሚዛናዊ በሆነ፤ የሁሉንም የወንዙን አካባቢ ሐገሮች መብት በትክክል ማስተናገድ የተሻለ ዘዴ ነው። መብቷን የማስከበሩ ዋናው ኃላፊነት ግን የኢትዮጵያ ነው።
3
ሱዳንን በተመለከተ፤ ምንም እንኳ፤ ከመገናኛ ብዙኃን መገንዘብ እንደሚቻለው፤ በመገንባት ላይ ስላለው ግድብ ደጋፊ መሆኗ ቢገለጽም፤ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ስላላት መብት አቋሟ ምን እንደ ሆነ በይፋ አልተገለጸም።
ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ፤ ከሚነጉደው ውሀ 86% የምታበረክተው፤ 100 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የኢትዮጵያ ድርሻ በትክክል እንዲታይ ያስፈልጋል። የውሀ ሐብቷ እያለ፤ ኢትዮጵያ በድርቅና በረሀብ መሰቃየቷ መቀጠል የለበትም። ኢትዮጵያም፤ የወንዝ ምንጮች እንደሆኑ እንደ ሌሎች ሐገሮች፤ በአባይ ወንዝ በረከቷ፤ በውሀዋ፤ በኃይል ማመንጫዋና በአፈሯ በስፋት እየተጠቀመች ልማቷን ማጣደፍና ማሳደግ መብቷ ነው። ይህም ሲባል ግን፤ የሌሎቹ ሐገሮች፤ ማለት የሱዳንና የግብጽ በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብት አይኑር ማለት አይደለም። የዓለም-አቀፍ ሕግ መመሪያዎችን መሠረት ባደረገ ሚዛናዊ በሆነ የጋርዮሽ አጠቃቀም ሥልት ይከናወን ማለት ነው። ይህንንም ለማስገኘት በጥሞናና በመከባበር ለዘለቄታው ተቀባይነት በሚያስገኝ ዘዴ መደራደርና መዋዋል ያስፈልጋል ማለት ነው።
የለሶቶ (Lesotho) በወንዟ ሐብት የመጠቀም ተሞክሮ፤
በመግቢያው እንደ ገለጽኩት፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ለሶቶ (Lesotho) አገልግዬ ነበር። እዚያች ሐገር የሠራሁትም እ.አ.አ በ1972-78 ሲሆን፤ ለአራት አመቶች በፖስታ፤ ቴሌኮሙኒኬሽንና ሲቪል አቭዬሽን ዋና ዲሬክተርነት ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመቶች ደግሞ የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በመሆን ነበር። የሥራ ሚኒስቴሩም የሚያጠቃልላቸው አገልግሎቶች፤ የመንግሥት ሕንጻዎችና መንገዶች ግንባታዎችና ጥገናዎች፤ የውሀ ልማትና አቅርቦት፤ የመብራት ኃይል አገልግሎትና፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ነበሩ። በነገራችን ላይ፤ ስለዚህ ሥራዬና ስለ ሌሎችም አገልግሎቶቼና ተያያዥ ጉዳዮች በቅርቡ በሚወጣ መጽሐፌ በሰፊው ለመግለጽ እየተዘጋጀሁ ነው።
ለሶቶ፤ ደቡብ አፍሪካ መሀል የምትገኝ አንድ ትንሽ ሐገር ናት። ትንሽ ብትሆንም፤ እንደ ኢትዮጵያ የውሀ ሐብት በረከት ያላት ሐገር ናት። እኔ ለሶቶ በነበርኩበት ጊዜ የለሶቶ ወንዝ የሚፈሰው ደቡብ አፍሪካ ለልማትና ሌላም ጥቅም ወደምትፈልገው አቅጣጫ ስላልነበረ፤ አስፈላጊው የማስተካከል ተግባር ተከናውኖ ሙሉ ተጠቃሚ እንድትሆን በለሶቶና በደቡብ አፍሪካ ድርድር ተጀምሮ ነበር። በዚህም ምክንያት በቋሚ ተጠሪነት ተግባሬ በድርድሩ ተካፍዬ ነበር። ከዚሁ በተለይ የማስታውሰው፤ እ.አ.አ. በ1977 በኔ መሪነት ኬፕ ታውን (Cape Town) በመጓዝ የለሶቶ ባለሥልጣኖችና ከየዓለም ባንክም ተወካይ የተገኘበት ልዑካን ከደቡብ አፍሪካ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣኖች ጋር ተደራድረን ነበር። የድርድሩ ጭብጥም ለሶቶ በውሀ ሐብቷ (ለኃይል ማመንጪያ ጭምር) የመጠቀም መብቷ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚፈሰው ውሀ ለሶቶ ተገቢውን ክፍያ እንድታገኝ ለማድረግ ነበር።
ያ ሁሉ ድርድር ውጤቱ አምሮ፤ የለሶቶን ተራራ በመሸንቆርና የወንዙን ፍሰት አቅጣጫ በማስለወጥ ለደቡብ አፍሪካ የሚያስፈልገው ውሀ በሚገባ እንዲቀርብ ለማድረግ ከቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሆነበት ሥራ ተጠናቆ፤ ባሁኑ ጊዜ ለሶቶ በያመቱ፤ በአማካኝ፤ $50 ሚሊዮን በደቡብ አፍሪካ እየተከፈላት ነው።
4
ለሶቶ ብሔራዊ መብቷንና ጥቅሟን ከላይ እንደ ተገለጸው ማስከበር ከቻለች፤ በታሪኳም ነጻነቷንና ክብሯን በማስከበር የምትታወቀው ኢትዮጵያ ከዚያ ያነሰ ይጠበቅባታል?
ማጠቃለያ፤
የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ ታላቅ የተፈጥሮ ሐብት ነው። ኢትዮጵያ የሱዳንንና የግብጽን ተገቢ መብት እያከበረች የራሷንም ጥቅም መጠበቅና ማስከበር ይኖርባታል። ለዚህም፤ በወንዝ ውሀ አጠቃቀም መርሆ፤ ሥልትና እቅድ ባለሞያዎች በመታገዝ ዝርዝር ጥናቶች በማከናወን ከጎረቤት ሐገሮች ጋር የሚደረገው ድርድር የኢትዮጵያን የዘለቄታ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ማረጋገጥና ሒደቱም ግልጽነትና ቁጥጥር የሰፈነበት እንዲሆን፤ የአባይ ወንዝ ዋናው ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሙሉ መብቱ እንዲጠበቅ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
ቸሩ አምላክ፤ ኢትዮጵያ በሕዝቧ ያልተቆጠበ ጥረት መብቷን፤ ክብሯንና ጥቅሟን እንድትጠብቅ ይርዳ!
Thursday, 22 May 2014
ህዝባዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ እና የተቃዋሚዎች የቤት ስራ በናትናኤል
May 22nd, 2014
ከሰሞኑ ወያኔ መራሹ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያወጣው አዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሚያ ዞን ያካተተ ማስተር ፕላን እና የእዝ አስተዳደር ተግባራዊነትን በመቃወም በብዙዎች የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች ሰፊ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ ተቀስቅሶ በመንግስት ቅጥ ያጣ ግድያና እስር ለጊዜው ጋብ ቢልም አሁንም ቢሆን በህዝቡ ውስጥ ሞልቶ ሊገነፍል የደረሰ ቁጣ አለ፡፡ በሌላ በኩል በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ ሲደረግ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ አሁንም ቢሆን የቀጠለ ቢሆንም እስካሁን ድረስም ቢሆን በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ በሚፈለገው መልኩ ሊስፋፋ አልቻለም፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት ሁለት ሲሆኑ አንደኛው የመንግስት ህዝባዊ ተቃውሞን አቅጣጫ በማሳት እና በህዝቦች መካከል የተነሳ የዘረኝነት ወይም የሀይማኖት የበላይነት የተፈጠረ በማስመሰል በህዝቡ ውስጥ መከፋፈልን በመፍጠር “የእብድ ገላጋይ” እንደሚባለው እንዳስታራቂ መጥቶ በህዝቦችና በሀይማኖት መሀከል ለረጀም ግዜ የቆውን መዋደድ (ልብ አርጉ መቻቻል አላልኩም) እንዳልነበር አድርጎ የኢትዮጵያ ህዝቦች የተባበረ አንድነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ሲሆን ሁለተኛወ ደግሞ የተቃዋሚዎች ሀዝባዊ ንቅናቄውን በማጠናከርና የጋራ አጀንዳ የሆነውን የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት መገርሰስ የተለየ አትኩሮት በመስጠት እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄው ሰፊ ሽፋን አንዲኖረው እምብዛም የጠነከረና የተቀናጀ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ አጠናክረው ባለማስቀጠላቸው ነው፡፡
በአብዛኛው ህዝባዊ ተቃውሞዎች ውስጥ የሚሳተፉ የወያኔ ካድሬዎች (Under Cover) እንደሚባለው በማዘጋጀት ዋና ተልዕኮዋቸው በህዝቦች መሀከል መቃቃር ሊፈጥሩ የሚችሉ አጀንዳዎችን በሰፊው እንዲሰራጩ እና በህዝባዊ ጥያቄዎች ውስጥ እንደ አንድ አጀንዳ እንዲካተቱ በማድረግ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በማክሸፍ እንዲሁም ተቃውሞዎችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በመጠምዘዝ ውጤታማ እንዳይሆኑ በማድረግ ከጅምሩ የህዝብ ንቅናቄን ፈር ማሳት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የተቃዋሚወች በአቋም መግለጫ ብቻ መወሰን የተቃውሞ ንቅናቄዎቹ ስኬታማ እንደዳይሆኑ አስተዋጽዎ አድርጓል፡፡ ለዚህ በማሳያነት በቅርቡ የተደረጉት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ምን አይነት ሙከራ እንደተደረገበት እንመልከት፡፡
የመጀመሪያው የሙስሊሞች ህዝባዊ ጥያቄ ሲሆን በመሰረቱ እስካሁን ከታዩት ህዝባዊ ንቅናቄዎች በተሻለ መልኩ የተደራጀ ቢሆንም በሚፈለገው መልኩ ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል አላካተተም (የሀይማኖት ነጻነት ሁሉንም ዜጋ የሚመለከት ቢሆንም) እንደውም ተደጋግመው በሚቀርቡ የመንግስተ መሰረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳዎች (እስላማዊ መንግስት ማቋቋም በሚል ውሸት የታጨቀ) የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ሁኔታውን በጥርጣሬ የሚመለከቱበትና መንግስት የሚወስደውን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ በዝምታ ያለፉበት ሁኔታ የተፈጠረው፡፡ ለዚያውም ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በየአጋጣሚው ትክክለኛውን ጥያቄዎቻቸውን ለማስረዳት ጥረት እያደረጉ፡፡ በዚህ ረገድ ተቃዋሚዎች የመረጡት አካሄድ የጥያቄውን ትክክለኛነትና የገዠው ወያኔ መንግስት እርምጃ ትክክል አለመሆኑን አስመልክቶ መግለጫ መስጠት ብቻ ነው፡፡ጥያቄው የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ በማስረዳት በቂ የሆነ ቅስቀሳ ማድረግ እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ሲገባቸው የተለሳለሰ አካሄድን በመምረጣቸው ተቃውሞው ሰፊ ህዝባዊ ተሳትፎ ሳይኖረው ቀርቷል፡፡ አሁንም ቢሆን ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እድሉ ስላለ ተቃዋሚዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ቅርጽ በማስያዝ የጋራ አጀንዳ ወደሆነው የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት ገርስሶ ወደመጣል ሊመሩት ይገባል፡፡
በሁለተኛነት ማየት የፈለኩት የአሁኑ በኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና ንቅናቄ ሲሆን፡ ህዝባዊ ተቃውሞውን እንደተለመደው ዋነኛው ጥያቄ የኦሮሚያ ክልል ህዝብን ብቻ የሚመለከት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር ችግሩ የጨቋኙ ስርዐት ያመጣው ሆኖ ሳለ እንደተለመደው የጥቂት ሀገወጦች እንደሆነና ችግሩም ከሌሎች ብሄረ ተወላጆች ጋር የተፈጠረ ግጭት ተደርጎ ቀርቧል፡፡
እውነታው ግን ዛሬ በኦሮሚያ ላይ እየተወሰደ ያለው ህገ ወጥ አፈና እና ጭፍጨፋ በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ክልል (መሬት ተቀርሶ ለሱዳን ሲሰጥ)፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች በተለያየ ግዜ ሲወሰድ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ እኔ የምለው ግን የብሄር ግጭት በኢትየጵያ ውስጥ ሆነ ተብሎ የሚጫር ነው ወይስ የብሔሮች አንድ ላይ ተከባበብሮ መኖር አለመቻል? የብሄር ግጭት የሚነሳው ወያኔ የመብት ማስከበር ጥያቄ ሲነሳበት ብቻ ነው እንዴ? በነገራችን ላይ የትኛው ብሄር ነው የእከሌ ብሄር ከክልሌ ይውጣልኝ ብሎ ሰልፍ የወጣው? ወያኔ ግን ሖነ ተብሎ አንዱን ብሄር ከሌላው የሚያጋጩ ነገሮችን በመቆስቆስና የተባበረ አጀንዳ እንዳይኖር በማድረግ የተባበረ ህዝባዊ ተቃውሞን ማጨናገፊያ ሁነኛ መንገድ አድርጎ ቀጥሎበታል፡፡
ስለዚህ የተቃዋሚዎች የቤት ስራም ማተኮር ያለበት ይህንን የወያኔ ሰይጣናዊ አካሄድ ማክሸፍን ዋና አጀንዳ አድርጎ መሆን አለበት ባይ ነኝ ፡፡ የሁሉም ህዝባዊ ጥያቄዎች መነሻቸውም መድረሻቸውም የወያኔ ጨቋኝ ስርዐት መሆኑ በገሀድ እየታወቀ እውነታው እየተድበሰበሰ ሌላ ቅርጽና ይዘት ሲሰጠው በቸልታ መመልከት ለወያኔ አገዛዝ መራዘም ዋነኛ ስትራቴጂ ከመመቻቸት ባሻገር ለወያኔ ህዝብን የመከፋፈል አጀንዳ ስር እንዲሰድ መፍቀድም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በአንድነት ጨቋኙን የወያኔን መንገስት ማስወገድ ዋና ዐጀንዳ አድርገን እንንቀሳቀስ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚነሱት ሁሉም ተቃውሞዎች የጋራ አጀንዳ የጭቆናው ስርአት መወገድ ነው ስለዚህ አዚህ አጀነዳ ላይ አናተኩር ያኔ የሁሉም ጭቆና ማብቂያና መቀበሪያ ይሆናል ተባብረን ወያኔን ከነአስከፊ ጭቆናው ጋር እናስወግደው!!!!

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በድንጋይ ተፈነከተ
May 22nd, 2014
የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ትናንት ለምሳ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲያቀና ማንነታቸውን ባልለያቸው ሰዎች በድንጋይ መፈንከቱ ታውቋል፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8፡00 እንደደረሰ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ በመቅረብ ምንም ሳያነጋግሩት በድንጋይ ፈንክተውት መሰወራቸውን አቶ ስንታየሁ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ በድንጋይ ከተፈነከተ በኋላ ለደቂቃዎች ራሱን ስቶ የወደቀው አቶ ስንታየሁ በሰዎች እገዛ ህክምና አግኝቶ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ ‹‹የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት››የሚለውን ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩን ተከትሎ አቶ ስንታየሁ ታላቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ፓርቲው በመስከረም 19 እና ሚያዚያ 26/2006 አዲስ አበባ ላይ ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ስንታየሁ እጆቹን በካቴና አስሮ በእስር ቤት የሚገኙትን የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ትኩረት እንዲያገኙ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ በቅርቡ አንድነት ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ስንታየሁ ከሌሎች የፓርቲው አባላት ጋር ሲንቀሳቀስ በፖሊስ ተይዞ በህገ ወጥ መንገድ ታስሮ መለቀቁም አይዘነጋም፡፡

የአሜሪካ የሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና”
May 22, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

አሳድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሶሪያን ህዝብ አሳር ፍዳውን በማሳየት ላይ የሚገኙ እና በዘመኑ የሰውን ልጅ ከሚያሰቃዩ አምስት የመጀመሪያዎቹ ወሮበላ ወንጀለኞች ምድብ ውስጥ እንደሚካተቱ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2007 በተደረገው ምርጫ ባሽር 97.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለሰባት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ በዚያን ጊዜ የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት ማኮርማክ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “በሶሪያ ያለው ገዥ አካል ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንደልብ በህዝቡ ውስጥ ተንቀሳቅሰው ሀሳባቸውን በመግለጽ መመረጥ እንዳይችሉ ለማድረግ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ባለው ማስፈራራት እና በሰላማዊ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ የሚያራምዱት ግፍ የተሞላበት ጭቆና ላይ የቀረበው ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስባታል፡፡ የሶሪያ ህዝብ ተማዕኒነት ያለው ግልጽ እና በህዝቡ ሙሉ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ድባብን በመፍጠር ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ እና የሚወክሉትን ዕጩዎች መምረጥ እንዳይችል ባሽር አላሳድ መብቱን ቀምተውታል“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ስለአሳድ “አስቂኝ የምርጫዎች ትወና መድረክ” ማውሳት አዲስ ነገር አይደለም፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2011 የቀድሞ የየአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ደም ለተጠሙት ባሽር አላሳድ (በሺዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ ሰላማዊ ህዝቦችን ካለፈው ኦክቶበር ጀምሮ ቢያንስ 14 ጊዜ በኬሚካላዊ መሳሪያ ለጨፈጨፉት) መልካም ስብዕና ጥብቅና ቆመው ተስተውለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ለየት ያለ መሪ አለ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ወደ ሶሪያ በመሄድ ጉብኝት አድርገው የተመለሱት በርካታ የሁለቱም ፓርቲዎች (ዴሞክራቶች እና ሬፐብሊካኖች) የኮንግረስ አባላት አላሳድ የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ በመሆናቸው ላይ እምነት እንዳላቸው ገልጸው ነበር “ ብለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጊዜ ተቀይሮ ከሶስት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አሳድ “የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ” መሆናቸው ቀርቶ ወደለየለት “አሸባሪነት” እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተዋናይነት ተቀይረው ተገኙ፡፡ እንደ ሂላሪ አባባል የት ይደርስ የተባለ ወይፈን አጎንብሶ ሲጠባ ተገኘ መሆኑ ነውን?
በእኔ የአዕምሮ ዕይታ ኬሪ በአላሳድ ላይ እያሰሟቸው ያሏቸው የውግዘት ቃላት ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳነሳ ያስገድዱኛል፡፡ የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “ለአስቂኝ የመድረክ ትወና” የዲፕሎማሲ አካሄድ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላልን? በዓለም ላይ “ሸፍጥ” ለመስራት የተቀነባበረ ተንኮል ነውን? ይህ ሁኔታ ሆን ተብሎ ህዝብን እና የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለመዘለፍ እና ለማዋረድ የሚደረግ ደባ ነውን? የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ዲፕሎማሲን በአስመሳይነት ወይም ደግሞ “በዲፕሎክራሲ” (የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲውን አስመሳይነት ለመግለጽ የተጠቀምኩበት ትርጉም ነው) ሰበብ ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ለይስሙላ እየተጠቀመበት ነውን? ማንም ቢሆን አመልካች ጣቱን በሌሎች ሰዎች ላይ ሲቀስር ሶስቱ ጣቶቹ ተቀስረው ወደ እራሱ እንደሚያመለክቱ በጥንቃቄ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2013 የመንግስት መምሪያ ቃል አቀባይ የነበሩት ኬሪ ኒኮላስ ማዱሮ በቤንዙዌላ በምርጫ አሸንፈው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን እውቅና እንደማይሰጡ እና እንደማይቀበሉ አሳወቁ፡፡ ማዱሮ ያንን ምርጫ በጣም በጠበበ ሁኔታ 50.66 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፈው ነበር፡፡ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ የነበሩት ሄንሪክ ካፕሪልስ ስለምርጫው ነጻ እና ፍትሀዊ አለመሆን ጉዳይ አስመልክቶ ዝርዝር ታሪኩን ከተናገሩ በኋላ ኬሪም የእርሳቸውን ሀሳብ በመቀበል የሀሳባቸው ተጋሪ በመሆን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ስለምርጫው ዝርዝር ማብራሪያ መሰጠት የነበረበት መሆኑን እናምናለን…በግልጽ ለመናገር ከፍተኛ የሆኑ የምርጫ ግድፈቶች ተከስተው ከሆነ ስለሚመሰረተው የማዱሮ መንግስት ቅቡልነት በርካታ ጠንካራ ጥያቄዎችን የምናነሳ ይሆናል“ ብለው ነበር፡፡ በተጨማሪም የኋይት ሀውስ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ጃይ ካርኔይ በተመሳሳይ መልኩ ስለምርጫው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ መቅረብ እንዳለበት በመግለጽ መግለጫ አወጡ፡፡
ዚምባብዌ እ.ኤ.አ ኦገስት 2013 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባካሄደችበት ወቅት ኬሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በግልጥ በማያሳስት መልክ እንየው፣ በአገር ውስጥ እና በአህጉራዊ የምርጫ ታዛቢዎች በቀረበው ዘገባ መሰረት በርካታ ግድፈቶች የተንጸባረቁበት ምርጫ መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነው የምርጫ ውጤት የዚምባብዌን ህዝብ ፍላጎት የሚያሟላ ነው የሚል እምነት የላትም…የቀረበው ማስረጃ እንደሚያረጋግጠው የዛሬው የምርጫ ውጤት የረቀቀ እና ጥልቅ የሆነ የምርጫ ማጭበርበር ሂደት ማክተሙን ያረጋገጠ ነው “ ብለው ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ሙጋቤ በዚያን ጊዜ በተካሄደው ምርጫ 61 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነገር ያሸነፉት፡፡
እ.ኤ.አ ሜይ 2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው ፓርላሜንታዊ ምርጫ በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ሲያውጁ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው “የሚያሳስበን እና በጉዳዩም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እንገልጻለን” በማለት የተለመዱ እና አሰልች የግዴታ አይነት የቃላት መግለጫዎችን ከመስጠት በዘለለ ስለምርጫ ዘረፋው ህገወጥነት በተጨባጭ በመሬት ላይ የሚታይ ያደረጉት አንድም ድርጊት አልነበረም፡፡ የኋይት ሀውስ ብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ የሆኑት ሚክ ሀመር እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ሂደቱን ከታዘበ በኋላ ባወጣው መግለጫ መሰረት ምርጫው ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን አያሟላም፣ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንን ስጋት እንገልጻለን፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባለስልጣኖች በምርጫው ዕለት ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና ወጣ በማለት በየአቅጣጫው ተዘዋውረው የምርጫውን ሂደት ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያልተሰጠው በመሆኑ የተሰማንን ቅሬታ እንገልጻለን፡፡ ነጻ የሆነ የምርጫ ታዛቢ ያለማግኘት እና ባሉት የነጻ ሜዲያ ተወካይ ታዛቢዎች ላይ የሚደረገው የማሸማቀቅ ስራ ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በጣም የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ዕለት በፊት እንኳ ነጻ እና ፍትሀዊ የምርጫ ከባቢ አልነበረም… ለነገሩ እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ የተካሄደው “ፓርላሜንታዊ ምርጫ” አስቂኝ የምርጫ ትወና መድረክ ነበርን? የዚህ ዓይነት መሰሪ እና ዕኩይ ተግባራት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በዓለም ላይ የሚካሄድ ዘለፋ እና በዴሞክራሲ ላይ የሚደረግ ሸፍጥ ነውን?“
በዝንጀሮ ቆንጆዎች መካከል የቀንጅና ውድድር አይካሄድም ሆኖም ግን ዩናይትድ ስቴትስ ባሽር አላሳድ 97.6 በመቶ ድምጽ በማምጣት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸንፈዋል በማለት ስታወግዝ በኢትዮጵያ በተደረገው ፓርላሜንታዊ “የብዙሀን ፓርቲ” ተብዬ ምርጫ አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፍኩ ብለው ድንፋታ ሲያሰሙ ዩናይትድ ስቴትስ አልሰማሁም፣ አላየሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብላለች፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ዕጩ ተመራጭ ኦባማ በማያቋርጥ ሁኔታ በየጊዜው በዋሽንግተን በሚወጡት “እምነት የማይጣልባቸው” “የውጭ ፖሊሲ መርሆዎች” ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸው ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልንታገላቸው ከሚገቡን ጠላቶች መካከል በእርግጠኝነት አንዱ አሸባሪነት ብቻ አይደለም… ይልቁንም እምነት የለሽ መሆንም አንዱ እና ዋናው ነው፡፡ “በስድስት ዓመታት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የኦባማ የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ ፖሊሲ ደጋፊዎቻቸው ኦባማን ወደ ታማኝ የለሽነት አውቶብስ ጎማ ስር ውስጥ ወርዉረዋቸዋል፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኬን ሮዝ በቅርቡ የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ፕሬዚዳንት ኦባማ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ቀዳሚ የትኩረት አጀንዳ አድርገው ባለመያዛቸው ምክንያት በርካቶችን አሳዝነዋል፡፡“ ወሳኝ በሆኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ ለመደራደር የሚያሳዩት ዝግጁነት ለሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት አናሳ መሆን የሚያመላክት አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ “በዓለም ላይ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ለነጻነታቸው እና ለመብቶቻቸው መጠበቅ የጋራ የሆነ ፍላጎት ያላቸው መሆናቸውን“ ኦባማ የረሱት ይመስላል፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ፕሬዚዳንት ኦባማ በጋና አክራን ሲጎበኙ ለአፍሪካ ወጣቶች ባደረጉት ንግግር ላይ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “ታሪክ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን/ት ጎን ነው“ በማለት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “መሪዎቻችሁ ለሚሰሯቸው ማናቸውም ስራዎች ሁሉ በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂዎች እንዲሆኑ የማድረግ ስልጣኑ አላችሁ፣ እናም ህዝቡን ሊያገለግሉ የሚችሉ ተቋማትን መገንባት እና ማጠናከር አለባችሁ፡፡“ በቅርቡ ኦባማ ከእነዚያ ወጣት እና ጀግና ኢትዮጵያዊውያን/ት አፍሪካውያን/ት ወጣቶች እርሳቸው “እምነት ማጣት” እያሉ በሚጠሩት ከፍተኛ ዋጋ ሰጥተውት በነበረው ጉዳይ ላይ በድንገት ትልቅ ፈተና ገጥሟቸው ተስተውለዋል፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት በሳን ጆሴ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አበበ ገላው በኋይት ሀውስ ድረገጽ ላይ እንደተለቀቀው ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር የሚከተሉትን የሃሳብ ልውውጦች አድርጓል፣
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ! ለኢትዮጵያ ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት ለኢትዮጵያ ጌታዬ!
ፕሬዚዳንት፡ ለትንሽ ጊዜ ቆይ፡፡ በምትለው ጉዳይ ላይ እስማማለሁ ሆኖም ግን ስጨርስ ኋላ ለምን አላነጋግርህም፣ ምክንያቱም ለመጨረስ እየተቃረብኩ ነው (የመሳቅ ዓይነት አዝማሚያ እያሳዩ)፡፡ እኔ እና አንተ ስለጉዳዩ እንነጋገራለን፡፡ ወደዚያው አካባቢ እየመጣሁ ነው፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)–
ፕሬዚዳንት፡ እዚያ ሂድ
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)–
ፕሬዚዳንት፡ በምትለው ጉዳይ ላይ አስማማለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም፡፡)
ፕሬዚዳንት፡ ከአንተ ለመስማት እፈልጋለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ እንወድዎታለን!
ፕሬዚዳንት፡ እኔም እወዳችኋለሁ፡፡ ብቻ የንግግሬን መጨረሻ አበላሸህብኝ፡፡ ቢሆንም ምንም አይደለም፡፡ (ሳቅ እና የድጋፍ ጭብጨባ ከታዳሚው አስተጋባ፡፡) እሺ፡፡ ይህች አገር የመናገር ነጻነት የተከበረባት ናት– (የድጋፍ ጭብጨባ እንደገና አስተጋባ)– ይህም ታላቅ ነገር ነው፡፡
ለአምላክ/አላህ ምስጋና ይግባውና በአሜሪካ የመናገር ነጻነት አለን፡፡ አንድ ተራ ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰብ በቁጥጥር ስር እውላለሁ ብሎ ሳይፈራ፣ እታሰራለሁ ብሎ ሳይሰጋ፣ ድብደባ ወይም ደግሞ ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ ሳያስብ ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ቀጥ ብሎ ቆሞ በነጻነት መናገር ይችላል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እና አበበ በአንድ ዓይነት ስሜት ሆነው ነው የተነጋገሩት፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ጋዜጠኛ አበበ የንግግራቸውን መጨረሻ እንዳበላሸባቸው በቀልድ መልክ ተናግረዋል፡፡ አበበ ግን የኦባማ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ የትውልድ ሀገሩን እያበላሻት እንደሆነ በቁም ነገር ተናግሯል፡፡
ከዚህ ክስተት ልንማረው የምንችለው ታላቅ ቁም ነገር በዓለም ላይ ታላቅ ስልጣን እና ኃይል ያለው ሰው እና አንድ ተራ ዜጋ በዓለም መድረክ በአንድ ላይ መቆማቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በነጻነት ላይ በተለይም በመናገር ነጻነት ላይ እምነት አላቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አበበ ገላው በሳን ጆሴ ከተማ በመገኘት ድምጻቸውን ያሰማላቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የመናገር ነጻነት ወይም እምነትን በነጻ የማራመድ ነጻነት ወይም ደግሞ የመሰብሰብ ወይም ለሚፈጸሙባቸው በደሎች ቅሬታ የማቅረብ ነጻነት የላቸውም፡፡ ለዚህም ነው አበበ ገላው ድምጹን ከፍ አድርጎ ለኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቹ ነጻነት ሲል “ፕሬዚዳነት ኦባማ! ነጻነት ለኢትዮጵያ!“ እያለ የጮኸው፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የመናገር ነጻነት እና ሌሎች ነጻነቶች እንዲኖሩ እምነት ያላቸው በመሆኑ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ጥያቄው ተያያዥነት በሌላቸው ባዶ የተስፋ ቃላትን በማነብነብ የተግባር ኮስማና እና ድሁር የመሆናቸው እና የአፍሪካን ወሮበላ አምባገነኖች በጽናት የመደገፋቸው ጉዳይ ነው፡፡ ኦባማ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ በእርግጠኝነት እምነት ያላቸው ከሆነ ለምንድን ነው እርሳቸው ወይም (የእርሳቸው የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ፣ አምባሳደሮች እና ተወካዮቻቸው) የእርሳቸውን የመናገር ነጻነት እና በኢትዮጵያ በእስር ቤት የሚማቅቁትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪስቶች እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋቤላ፣ አጥናፍ ብርሀኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና በፈቃዱ ኃይሉ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርጉ የማይታዩት፡፡
ነጻነት በነጻ የማይገኝ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ በእርግጠኝነት ማወቅ አለባቸው፡፡ ተግባርን አግልሎ በረዥሙ ምላሳቸው ስለይስሙላ ነጻነት ብቻ ማውራት ርካሽ ንግግር ነው፡፡ በተደጋጋሚ እየተደረጉ ያሉት በጣም በርካታ ሆኖም ግን እርባናየለሽ ንግግሮች ናቸው፡፡ እናም በኢትዮጵያ ነጻነት እጅግ ውድ የሆነ ዋጋ ተከፍሎበት የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎቸም የእራሳቸውን ድሎት ሰውተው ለነጻነት የሚከፈለውን ክቡር ዋጋ በመክፈል ላያ ናቸው፡፡ ለሰው ልጆች የነጻነት ክብር ሲሉ በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ትንታንግ የነጻነት ታጋዮች የመኖር ሚስጥሩ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመታገል ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ወደ 200 አካባቢ የሚጠጉ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ የነጻነት ታጋዮች ለነጻነት ሲሉ ክቡር ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሩብ ምዕተ ዓመታትን ባስቆጠረው የአምባገነኖች የአገዛዝ ስርዓት ለነጻነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ገብረዋል፡፡ የእነዚህ ንጹሀን ዜጎች ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ በከፍተኛው የስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው እና ያለምንም ተጠያቂነት ደረታቸውን ነፍተው በአውራ መንገዶች እንደ ነጻ ሰው ሁሉ ሰው መስለው በወንጀል ባህር ውስጥ ሲዋኙ እንዳልቆዩ እና አሁንም እየዋኙ እያሉ መሆናቸው እየታወቀ ነጻ እና ከወንጀል የጸዱ በመምሰል ደረታቸውን ገልብጠው ሲንገዋለሉ እና ሲኮፈሱ ይታያሉ፣ የቁርጥ ቀን የማይመጣ መስሏቸው፡፡ ኦባማ አነዚህን ወሮበላ አምባገነኖች በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዶላሮች በመለገስ በስልጣኖቻቸው ላይ ተጣብቀው ህዝብን ሲያሰቃዩ እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ተዋቂዋ የአፍሪካ የኢኮኖሚክስ ምሁር የሆኑት እና “የበከተ እርዳታ/Dead Aid” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ዳምቢሳ ሞዮ እንደዘገቡት “በኢትዮጵያ በጣም ግዙፍ የሆነው በጀት 97 በመቶ የሚሆነው የመንግስት በጀት የሚመጣው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለዜጎች ይሁንታ በጉልበት በስልጣን ላይ ተፈናጥጦ ለሚገኘው ወሮበላ ገዥ አካል ሽማግሌ አናትም አባትም ናት! በአሁኑ ጊዜ 90 ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩን እያጣ እየተሰቃየ፣ ኢፍትሀዊነት ድርጊት እየተፈጸመበት እና መብቱ በወሮበላዎች እና በሙስና በበከቱ ደንቆሮ መሪዎች ነን ባዮች መዳፍ ስር ወድቆ አሳር ፍዳውን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡
የኦባማን የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲዎች እና መርሆዎች ከሚናገሯቸው ባዶ የሰብአዊ መብት ንግግሮች ለመለየት አይቻልም፡፡ ለአሳድ በምናባቸው “ቀይ መስመር” በማስመር የሶሪያን ህዝብ ሊጭርስ የሚችል ኬሚካላዊ መሳሪያ መጠቀም እንዳይችሉ የተሰመረውን ቀዩን መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ባለፉት በርካታ ወራት አሳድ ይህንን ኬሚካላዊ መሳሪያ በመጠቀም ቢያንስ 14 ጊዜ ተግብረውታል፡፡ ለአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች ኦባማ ቀጥሉ የሚል አረንጓዴ መብራት በማሳየት በቀዩ መብራት የሰብአዊ መብት ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
የአቦማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት መርሆዎች እንዲከበሩ ከልብ ተነሳሽነቱን የማያሳይ ከሆነ በተስፋ የሚያስሞሉ እና የዜጎችን ቀልቦች የሚገዙ ታላላቅ መግለጫዎችን እና ንግግሮችን በሚሊዮኞች ለሚቆጠሩ ለዓለም ዓቀፉ የማህበረሰብ አባላት በተደጋጋሚ ማሰማቱ ፋይዳው ምንድን ነው? የኦባማ አስተዳደር ይህን አሰልች እና አደንቋሪ የውሸት የሰብአዊ መብት አጠባበቅ መዝሙር ሲያሰማ ህዝቡ በሚደሰኮረው ዲስኩር እና በተጨባጭ ምንም የተደረገ ነገር ያለመኖሩን ሊያገናዝብ የሚችል አዕምሮ የሌለው ደደብ እና ደንቆሮ አድርገው ሊቆጥሩት ይሞክራሉን? ለምንድን ነው አቦማ በተደጋጋሚ በተግባር ሲያውሏቸው የማይታዩ የአስመሳይነት እና እምነተቢስነት ንግግሮችን እንደበቀቀን እየደጋገሙ ሲናገሩ የሚደመጡት? ፕሬዚዳንት ኦባማ! እስቲ ቆም ብለው ያስተውሉ፣ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በጊዜ ሂደት የሰብአዊ መብት ጥበቃን የሚያራምዱ እና መርሆዎቻቸው አድርገው ለመተግበር እንደገና ሊበራል ዴሞክራቶች ሆነው ይወለዳሉ ብለው ያስባሉን? የአረም አበባዎች አድገው ጽጌረዳ ይሆናሉን?
እንደ ትክክለኛው አካሄድ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስን “የተሳሳተ የኢሰብአዊ ፖሊሲ” ቢያንስ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በመርህ ደረጃ በመመስረት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአፍሪካ ሲፈጸሙ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልክታ ጆሮ አልባ መሆኗን ማሳወቅ አለባት፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የኢሰብአዊ ፖሊሲ መብት መርሆዎች በሚከተሉት ቀላል ሀሳቦች ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ፡
አፍሪካ በምዕራቡ ዓለም እንደሚታሰበው ወይም ደግሞ በተግባር እንደሚስተዋለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ አስፈላጊዋ አይደለም፡፡ “ሰላም እና መረጋጋት” ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ የምታራምደው ትልቁ እና ጠቃሚዋ የፖሊሲ አካሄድ መሳሪዋ ነው፡፡ በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች የሚፈጸሙ ሰብአዊ ወንጀሎች ሌሎች አለመረጋጋቶችን እና ግጭቶችን ይወልዳሉ ከሚል የተሳሳተ እምነት አንጻር ዩናይትድ ስቴትስ አይታ እንዳላየ፣ ሰምታ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ታልፈዋለች፡፡ (ለምሳሌ ያህል በደቡብ ሱዳን ሳልቫኪር እና ሬክ ማቻር በሚያደርጉት ሰይጣናዊ ድርጊት ሰበብ ለፈጸሙት ግድያ፣ እልቂት፣ ዘር ማጥፋት፣ ህዝብን በኃይል ከሚኖርበት ቀየ ማፈናቀል፣ እስራት፣ ስቃይ አስገድዶ መድፈር እና የጎሳ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ከተጣያቂነት ነጻ ነው የሚሆኑት፡፡)
የዩናይትድ ስቴትስን ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጥቅሞች እስካከበሩ እና ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት ላይ የከፈተችውን ጦርነት እስካልተቃወሙ ድረስ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በአፍሪካ አህጉር ላይ በጠራራ ጸሐይ ኮሮጆ ገልብጠው ምርጫ ሲዘርፉ እና ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀሙ በአፍሪካውያን/ት ዜጎች ላይ የቁማር ጨዋታ ሲጫወቱ አሜሪካ ጸጥ በማለት በትዕግስት የምትመለከተው ደንታም የማይሰጣት የዕለት ከዕለት ጉዳዩዋ ሆኗል፡፡
የፍራንክሊን ዲ.ሩዝቬልት “በየትኛውም የዓለም ክፍል” እንዲተገበሩ የሚገባቸው አራቱ አስፈላጊ የሰው ልጆች ነጻነቶች በአፍሪካ ላይ ግን ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ጨለማ የተንሰራፋበትን የአምባገነኖች አገዛዝ በማንኮታኮት እራሷን ከጀግና የነጻ የዓለም ህዝቦች ጋር ለማስተሳሰር የሩዝቬልትን ራዕይ አትከተልም፡፡ “አራት አስፈላጊ የሆኑ የሰው ልጅ ነጻነቶች የሚገለጹባት ዓለምን ዕውን ሆና ማየት እንፈልጋለን፡፡” በማለት ሩዝቬልት የተናገሩትን ወደ ተግባር ለአፍሪቃ አያስፈለግም፡፡የመጀመሪያው የመናገር እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት – (ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር በዓለም ላይ ሁሉ)፡፡ ሁለተኛው ማንም ሰው በራሱ መንገድ አምላኩን የማምለክ እና የፈለገውን እምነት በመያዝ የእራሱን እምነት የማራመድ መብት – (ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር)፡፡ ሶስተኛው የፍላጎት ነጻነት መብት – ከዓለም አቀፍ ሁኔታ አንጻር ሲተረጎም ይህ ማለት የእያንዳንዱን አገር ጤናማ የሰላም ጊዜ የማስፈን እና የእያንዳንዱን ዜጋ ፍላጎት – በየትኛውም የዓለም ክፍል ማሟላት (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡ አራተኛው ከፍርሀት ነጻ የመሆን መብት… ከዚህ አንጻር ማንም ጠብ አጫሪ አገር ተነስቶ በጎረቤቱ ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጥቃት አይፈጽምም፡፡ እንደዚሁም በዓለም ላይ ጥቃት ለመፈጸም አይቻለውም (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡ የሩዝቬልት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድንጋጌ እና ሌሎችም በድንጋጌው እየተፈተሉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ትክክለኛ እና “በተግባር ተኮር ፖለቲካ” ፖሊሲ ላይ እራሱን ብቁ ያደረገ በሚከተሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ የሰብአዊ መብት ፖሊሲ ግድፈቶችን ግልጽ በሆነ መልኩ ያካትታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በአፍሪካ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ስላሏት እሴቶች፣ መርሆዎች እና ፖሊሲዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ ስላሏት ዝንባሌዎች እና ዓላማዎች እንዲሁም አለመግባባቶች እና ግንዛቤ ያለመኖር ችግሮች አይኖሩም፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዩናይትድ ስቴትስ ስለሚኖራት የሰብአዊ መብት ስህተቶች የሚናገሩት በጣም ጥቂት ነገር ብቻ ይሆናል፡፡ ከንፈሮቻቸውን ይነክሳሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ አምባገነኖች ለሰሩት ታማኘነት ላለው እና መልካም ስራ ትክክለኛ ምስጋና ያገኛሉ፡፡ ዩናይትድ ሰቴትስ ወዲያውኑ እነዚህን አምባገነኖች እንዳላየች አድርጋ የመሄድ አስመሳይነቷን ታቆማለች፡፡
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና ነውን”?
የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ፕሬዚዳንት ባሽር አላሳድን “አሸባሪ” ወንጀለኛ ናቸው ብለው ከፈረጁ በኋላ የአላሳድ የቀጣዩ ዓመት የምርጫ ዕቅድም “አስቂኝ የመድረክ ትወና” ነው ብለው ተችተው ነበር፡፡ ኬሪ በመቀጠልም እንዲህ በማለት ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “አሳድ ከአሸባሪ ኃይሎች ጋር ህብረትን ፈጥረዋል፣ አሸባሪዎችንም እያቀረቡ እና እየረዱ ነው፣ እናም በእራሳቸው ህዝብ ላይ አሸባሪነትን በመፈጸም ዕኩይ ተግባራት ላይ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡“ እንዲሁም ኬሪ የሚከተለውን ነገር አጽንኦ በመስጠት ተናግረዋል፣ “የአሳድ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዕቅዶች ለታዕይታ የተዘጋጁ አስቂኝ የመድረክ ትወናዎች ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ለመተግበር የሚደረጉ ምርጫዎችም በህዝብ ላይ የሚካሄዱ ዘለፋዎች ናቸው፣ እንደዚህ ዓይነቶቹ ዕኩይ የምርጫ ዕቅዶች በሶሪያ እና በዓለም ህዝቦች ዴሞክራሲ ላይ የሚቃጡ ሸፍጦች ናቸው፣“ ብለው ነበር፡፡
አሳድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሶሪያን ህዝብ አሳር ፍዳውን በማሳየት ላይ የሚገኙ እና በዘመኑ የሰውን ልጅ ከሚያሰቃዩ አምስት የመጀመሪያዎቹ ወሮበላ ወንጀለኞች ምድብ ውስጥ እንደሚካተቱ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2007 በተደረገው ምርጫ ባሽር 97.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለሰባት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ በዚያን ጊዜ የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት ማኮርማክ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “በሶሪያ ያለው ገዥ አካል ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንደልብ በህዝቡ ውስጥ ተንቀሳቅሰው ሀሳባቸውን በመግለጽ መመረጥ እንዳይችሉ ለማድረግ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ባለው ማስፈራራት እና በሰላማዊ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ የሚያራምዱት ግፍ የተሞላበት ጭቆና ላይ የቀረበው ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስን ያሳስባታል፡፡ የሶሪያ ህዝብ ተማዕኒነት ያለው ግልጽ እና በህዝቡ ሙሉ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ድባብን በመፍጠር ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ እና የሚወክሉትን ዕጩዎች መምረጥ እንዳይችል ባሽር አላሳድ መብቱን ቀምተውታል“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ስለአሳድ “አስቂኝ የምርጫዎች ትወና መድረክ” ማውሳት አዲስ ነገር አይደለም፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2011 የቀድሞ የየአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ደም ለተጠሙት ባሽር አላሳድ (በሺዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ ሰላማዊ ህዝቦችን ካለፈው ኦክቶበር ጀምሮ ቢያንስ 14 ጊዜ በኬሚካላዊ መሳሪያ ለጨፈጨፉት) መልካም ስብዕና ጥብቅና ቆመው ተስተውለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ሀሳባቸውን አጠናክረው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ለየት ያለ መሪ አለ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ወደ ሶሪያ በመሄድ ጉብኝት አድርገው የተመለሱት በርካታ የሁለቱም ፓርቲዎች (ዴሞክራቶች እና ሬፐብሊካኖች) የኮንግረስ አባላት አላሳድ የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ በመሆናቸው ላይ እምነት እንዳላቸው ገልጸው ነበር “ ብለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንድ ጊዜ ተቀይሮ ከሶስት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አሳድ “የለውጥ አራማጅ ሀዋርያ” መሆናቸው ቀርቶ ወደለየለት “አሸባሪነት” እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተዋናይነት ተቀይረው ተገኙ፡፡ እንደ ሂላሪ አባባል የት ይደርስ የተባለ ወይፈን አጎንብሶ ሲጠባ ተገኘ መሆኑ ነውን?
በእኔ የአዕምሮ ዕይታ ኬሪ በአላሳድ ላይ እያሰሟቸው ያሏቸው የውግዘት ቃላት ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳነሳ ያስገድዱኛል፡፡ የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ “ለአስቂኝ የመድረክ ትወና” የዲፕሎማሲ አካሄድ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላልን? በዓለም ላይ “ሸፍጥ” ለመስራት የተቀነባበረ ተንኮል ነውን? ይህ ሁኔታ ሆን ተብሎ ህዝብን እና የሰብአዊ መብት ጥበቃን ለመዘለፍ እና ለማዋረድ የሚደረግ ደባ ነውን? የኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት አያያዝ ዲፕሎማሲን በአስመሳይነት ወይም ደግሞ “በዲፕሎክራሲ” (የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲውን አስመሳይነት ለመግለጽ የተጠቀምኩበት ትርጉም ነው) ሰበብ ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ለይስሙላ እየተጠቀመበት ነውን? ማንም ቢሆን አመልካች ጣቱን በሌሎች ሰዎች ላይ ሲቀስር ሶስቱ ጣቶቹ ተቀስረው ወደ እራሱ እንደሚያመለክቱ በጥንቃቄ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2013 የመንግስት መምሪያ ቃል አቀባይ የነበሩት ኬሪ ኒኮላስ ማዱሮ በቤንዙዌላ በምርጫ አሸንፈው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን እውቅና እንደማይሰጡ እና እንደማይቀበሉ አሳወቁ፡፡ ማዱሮ ያንን ምርጫ በጣም በጠበበ ሁኔታ 50.66 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፈው ነበር፡፡ የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ የነበሩት ሄንሪክ ካፕሪልስ ስለምርጫው ነጻ እና ፍትሀዊ አለመሆን ጉዳይ አስመልክቶ ዝርዝር ታሪኩን ከተናገሩ በኋላ ኬሪም የእርሳቸውን ሀሳብ በመቀበል የሀሳባቸው ተጋሪ በመሆን እንዲህ ብለው ነበር፣ “ስለምርጫው ዝርዝር ማብራሪያ መሰጠት የነበረበት መሆኑን እናምናለን…በግልጽ ለመናገር ከፍተኛ የሆኑ የምርጫ ግድፈቶች ተከስተው ከሆነ ስለሚመሰረተው የማዱሮ መንግስት ቅቡልነት በርካታ ጠንካራ ጥያቄዎችን የምናነሳ ይሆናል“ ብለው ነበር፡፡ በተጨማሪም የኋይት ሀውስ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ጃይ ካርኔይ በተመሳሳይ መልኩ ስለምርጫው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ መቅረብ እንዳለበት በመግለጽ መግለጫ አወጡ፡፡
ዚምባብዌ እ.ኤ.አ ኦገስት 2013 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባካሄደችበት ወቅት ኬሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በግልጥ በማያሳስት መልክ እንየው፣ በአገር ውስጥ እና በአህጉራዊ የምርጫ ታዛቢዎች በቀረበው ዘገባ መሰረት በርካታ ግድፈቶች የተንጸባረቁበት ምርጫ መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆነው የምርጫ ውጤት የዚምባብዌን ህዝብ ፍላጎት የሚያሟላ ነው የሚል እምነት የላትም…የቀረበው ማስረጃ እንደሚያረጋግጠው የዛሬው የምርጫ ውጤት የረቀቀ እና ጥልቅ የሆነ የምርጫ ማጭበርበር ሂደት ማክተሙን ያረጋገጠ ነው “ ብለው ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ሙጋቤ በዚያን ጊዜ በተካሄደው ምርጫ 61 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነገር ያሸነፉት፡፡
እ.ኤ.አ ሜይ 2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው ፓርላሜንታዊ ምርጫ በቅርቡ ያረፉት አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ሲያውጁ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው “የሚያሳስበን እና በጉዳዩም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እንገልጻለን” በማለት የተለመዱ እና አሰልች የግዴታ አይነት የቃላት መግለጫዎችን ከመስጠት በዘለለ ስለምርጫ ዘረፋው ህገወጥነት በተጨባጭ በመሬት ላይ የሚታይ ያደረጉት አንድም ድርጊት አልነበረም፡፡ የኋይት ሀውስ ብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ የሆኑት ሚክ ሀመር እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ሂደቱን ከታዘበ በኋላ ባወጣው መግለጫ መሰረት ምርጫው ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን አያሟላም፣ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንን ስጋት እንገልጻለን፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባለስልጣኖች በምርጫው ዕለት ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና ወጣ በማለት በየአቅጣጫው ተዘዋውረው የምርጫውን ሂደት ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያልተሰጠው በመሆኑ የተሰማንን ቅሬታ እንገልጻለን፡፡ ነጻ የሆነ የምርጫ ታዛቢ ያለማግኘት እና ባሉት የነጻ ሜዲያ ተወካይ ታዛቢዎች ላይ የሚደረገው የማሸማቀቅ ስራ ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በጣም የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ከምርጫው ዕለት በፊት እንኳ ነጻ እና ፍትሀዊ የምርጫ ከባቢ አልነበረም… ለነገሩ እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ የተካሄደው “ፓርላሜንታዊ ምርጫ” አስቂኝ የምርጫ ትወና መድረክ ነበርን? የዚህ ዓይነት መሰሪ እና ዕኩይ ተግባራት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በዓለም ላይ የሚካሄድ ዘለፋ እና በዴሞክራሲ ላይ የሚደረግ ሸፍጥ ነውን?“
በዝንጀሮ ቆንጆዎች መካከል የቀንጅና ውድድር አይካሄድም ሆኖም ግን ዩናይትድ ስቴትስ ባሽር አላሳድ 97.6 በመቶ ድምጽ በማምጣት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸንፈዋል በማለት ስታወግዝ በኢትዮጵያ በተደረገው ፓርላሜንታዊ “የብዙሀን ፓርቲ” ተብዬ ምርጫ አቶ መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፍኩ ብለው ድንፋታ ሲያሰሙ ዩናይትድ ስቴትስ አልሰማሁም፣ አላየሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብላለች፡፡
የኦባማን የሰብአዊ መብት መርህ መገንዘብ፣
የኦባማ የሰብአዊ መብት አያያዝ መርህ ግልጽ እና ቀጥተኛ ይመስላል፡፡ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ የማውጣት ስራ በዋናነት ከሁለት ሰይጣኖች መካከል የትኛው የተሻለ ምርጫ ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው፡፡ ዓለም እንደ እነ አሳድ፣ ሙጋቤ እና ማዱሮ ባሉ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የሚፈጽሙ የተጠሉ “ሰው በላ ጭራቆች” የተሞላች ናት፡፡ እንዲሁም እንደ የግብጹ ኢል ሲሲ ፣ የኡጋንዳው ሙሴቤኒ፣ የሩዋንዳው ካጋሜ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የኢትዮጵያው አቶ መለስ ዜናዊ በሰው ልጆች ላይ ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶችን የፈጸሙ እና አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ የተሻሉ ““ሰው በላ ጭራቆች” ናቸው፡፡ በሁለቱ ጭራቆች መካከል ያለው ልዩነት የኋለኞቹ የእኛው “ሰው በላ ጭራቆች” መሆናቸው ነው፡፡ የእራሳችንን ስራ ይሰሩልናል፡፡ ትዛዛችን ይቀበላሉ:: ለዚህ ውለታቸው ደግሞ ነጻ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል፡፡ በየዓመቱ በምጽዋት ስም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዶላሮች እንሰጣቸዋለን፡፡” በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ሀሳቧን አጠቃላለች፡፡እ.ኤ.አ በ2008 ዕጩ ተመራጭ ኦባማ በማያቋርጥ ሁኔታ በየጊዜው በዋሽንግተን በሚወጡት “እምነት የማይጣልባቸው” “የውጭ ፖሊሲ መርሆዎች” ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸው ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልንታገላቸው ከሚገቡን ጠላቶች መካከል በእርግጠኝነት አንዱ አሸባሪነት ብቻ አይደለም… ይልቁንም እምነት የለሽ መሆንም አንዱ እና ዋናው ነው፡፡ “በስድስት ዓመታት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የኦባማ የሰብአዊ መብት ጥበቃ አያያዝ ፖሊሲ ደጋፊዎቻቸው ኦባማን ወደ ታማኝ የለሽነት አውቶብስ ጎማ ስር ውስጥ ወርዉረዋቸዋል፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኬን ሮዝ በቅርቡ የሚከተለውን ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ፕሬዚዳንት ኦባማ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ቀዳሚ የትኩረት አጀንዳ አድርገው ባለመያዛቸው ምክንያት በርካቶችን አሳዝነዋል፡፡“ ወሳኝ በሆኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ ለመደራደር የሚያሳዩት ዝግጁነት ለሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት አናሳ መሆን የሚያመላክት አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ “በዓለም ላይ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ለነጻነታቸው እና ለመብቶቻቸው መጠበቅ የጋራ የሆነ ፍላጎት ያላቸው መሆናቸውን“ ኦባማ የረሱት ይመስላል፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ፕሬዚዳንት ኦባማ በጋና አክራን ሲጎበኙ ለአፍሪካ ወጣቶች ባደረጉት ንግግር ላይ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈው ነበር፣ “ታሪክ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን/ት ጎን ነው“ በማለት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “መሪዎቻችሁ ለሚሰሯቸው ማናቸውም ስራዎች ሁሉ በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂዎች እንዲሆኑ የማድረግ ስልጣኑ አላችሁ፣ እናም ህዝቡን ሊያገለግሉ የሚችሉ ተቋማትን መገንባት እና ማጠናከር አለባችሁ፡፡“ በቅርቡ ኦባማ ከእነዚያ ወጣት እና ጀግና ኢትዮጵያዊውያን/ት አፍሪካውያን/ት ወጣቶች እርሳቸው “እምነት ማጣት” እያሉ በሚጠሩት ከፍተኛ ዋጋ ሰጥተውት በነበረው ጉዳይ ላይ በድንገት ትልቅ ፈተና ገጥሟቸው ተስተውለዋል፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት በሳን ጆሴ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አበበ ገላው በኋይት ሀውስ ድረገጽ ላይ እንደተለቀቀው ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር የሚከተሉትን የሃሳብ ልውውጦች አድርጓል፣
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ! ለኢትዮጵያ ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት ለኢትዮጵያ ጌታዬ!
ፕሬዚዳንት፡ ለትንሽ ጊዜ ቆይ፡፡ በምትለው ጉዳይ ላይ እስማማለሁ ሆኖም ግን ስጨርስ ኋላ ለምን አላነጋግርህም፣ ምክንያቱም ለመጨረስ እየተቃረብኩ ነው (የመሳቅ ዓይነት አዝማሚያ እያሳዩ)፡፡ እኔ እና አንተ ስለጉዳዩ እንነጋገራለን፡፡ ወደዚያው አካባቢ እየመጣሁ ነው፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)–
ፕሬዚዳንት፡ እዚያ ሂድ
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም)–
ፕሬዚዳንት፡ በምትለው ጉዳይ ላይ አስማማለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ (አይሰማም፡፡)
ፕሬዚዳንት፡ ከአንተ ለመስማት እፈልጋለሁ፡፡
አበበ ገላው (የስብሰባው ታዳሚ አባል)፡ እንወድዎታለን!
ፕሬዚዳንት፡ እኔም እወዳችኋለሁ፡፡ ብቻ የንግግሬን መጨረሻ አበላሸህብኝ፡፡ ቢሆንም ምንም አይደለም፡፡ (ሳቅ እና የድጋፍ ጭብጨባ ከታዳሚው አስተጋባ፡፡) እሺ፡፡ ይህች አገር የመናገር ነጻነት የተከበረባት ናት– (የድጋፍ ጭብጨባ እንደገና አስተጋባ)– ይህም ታላቅ ነገር ነው፡፡
ለአምላክ/አላህ ምስጋና ይግባውና በአሜሪካ የመናገር ነጻነት አለን፡፡ አንድ ተራ ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ግለሰብ በቁጥጥር ስር እውላለሁ ብሎ ሳይፈራ፣ እታሰራለሁ ብሎ ሳይሰጋ፣ ድብደባ ወይም ደግሞ ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ ሳያስብ ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ቀጥ ብሎ ቆሞ በነጻነት መናገር ይችላል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እና አበበ በአንድ ዓይነት ስሜት ሆነው ነው የተነጋገሩት፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ጋዜጠኛ አበበ የንግግራቸውን መጨረሻ እንዳበላሸባቸው በቀልድ መልክ ተናግረዋል፡፡ አበበ ግን የኦባማ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲ የትውልድ ሀገሩን እያበላሻት እንደሆነ በቁም ነገር ተናግሯል፡፡
ከዚህ ክስተት ልንማረው የምንችለው ታላቅ ቁም ነገር በዓለም ላይ ታላቅ ስልጣን እና ኃይል ያለው ሰው እና አንድ ተራ ዜጋ በዓለም መድረክ በአንድ ላይ መቆማቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በነጻነት ላይ በተለይም በመናገር ነጻነት ላይ እምነት አላቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አበበ ገላው በሳን ጆሴ ከተማ በመገኘት ድምጻቸውን ያሰማላቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የመናገር ነጻነት ወይም እምነትን በነጻ የማራመድ ነጻነት ወይም ደግሞ የመሰብሰብ ወይም ለሚፈጸሙባቸው በደሎች ቅሬታ የማቅረብ ነጻነት የላቸውም፡፡ ለዚህም ነው አበበ ገላው ድምጹን ከፍ አድርጎ ለኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቹ ነጻነት ሲል “ፕሬዚዳነት ኦባማ! ነጻነት ለኢትዮጵያ!“ እያለ የጮኸው፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች የመናገር ነጻነት እና ሌሎች ነጻነቶች እንዲኖሩ እምነት ያላቸው በመሆኑ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ጥያቄው ተያያዥነት በሌላቸው ባዶ የተስፋ ቃላትን በማነብነብ የተግባር ኮስማና እና ድሁር የመሆናቸው እና የአፍሪካን ወሮበላ አምባገነኖች በጽናት የመደገፋቸው ጉዳይ ነው፡፡ ኦባማ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ በእርግጠኝነት እምነት ያላቸው ከሆነ ለምንድን ነው እርሳቸው ወይም (የእርሳቸው የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ፣ አምባሳደሮች እና ተወካዮቻቸው) የእርሳቸውን የመናገር ነጻነት እና በኢትዮጵያ በእስር ቤት የሚማቅቁትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪስቶች እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አቤል ዋቤላ፣ አጥናፍ ብርሀኔ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና በፈቃዱ ኃይሉ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርጉ የማይታዩት፡፡
ነጻነት በነጻ የማይገኝ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ በእርግጠኝነት ማወቅ አለባቸው፡፡ ተግባርን አግልሎ በረዥሙ ምላሳቸው ስለይስሙላ ነጻነት ብቻ ማውራት ርካሽ ንግግር ነው፡፡ በተደጋጋሚ እየተደረጉ ያሉት በጣም በርካታ ሆኖም ግን እርባናየለሽ ንግግሮች ናቸው፡፡ እናም በኢትዮጵያ ነጻነት እጅግ ውድ የሆነ ዋጋ ተከፍሎበት የሚመጣ ጉዳይ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎቸም የእራሳቸውን ድሎት ሰውተው ለነጻነት የሚከፈለውን ክቡር ዋጋ በመክፈል ላያ ናቸው፡፡ ለሰው ልጆች የነጻነት ክብር ሲሉ በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ትንታንግ የነጻነት ታጋዮች የመኖር ሚስጥሩ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመታገል ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ወደ 200 አካባቢ የሚጠጉ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ የነጻነት ታጋዮች ለነጻነት ሲሉ ክቡር ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሩብ ምዕተ ዓመታትን ባስቆጠረው የአምባገነኖች የአገዛዝ ስርዓት ለነጻነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ገብረዋል፡፡ የእነዚህ ንጹሀን ዜጎች ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ በከፍተኛው የስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው እና ያለምንም ተጠያቂነት ደረታቸውን ነፍተው በአውራ መንገዶች እንደ ነጻ ሰው ሁሉ ሰው መስለው በወንጀል ባህር ውስጥ ሲዋኙ እንዳልቆዩ እና አሁንም እየዋኙ እያሉ መሆናቸው እየታወቀ ነጻ እና ከወንጀል የጸዱ በመምሰል ደረታቸውን ገልብጠው ሲንገዋለሉ እና ሲኮፈሱ ይታያሉ፣ የቁርጥ ቀን የማይመጣ መስሏቸው፡፡ ኦባማ አነዚህን ወሮበላ አምባገነኖች በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዶላሮች በመለገስ በስልጣኖቻቸው ላይ ተጣብቀው ህዝብን ሲያሰቃዩ እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል ብሎ መናገር ማጋነን አይሆንም፡፡ ተዋቂዋ የአፍሪካ የኢኮኖሚክስ ምሁር የሆኑት እና “የበከተ እርዳታ/Dead Aid” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ዳምቢሳ ሞዮ እንደዘገቡት “በኢትዮጵያ በጣም ግዙፍ የሆነው በጀት 97 በመቶ የሚሆነው የመንግስት በጀት የሚመጣው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለዜጎች ይሁንታ በጉልበት በስልጣን ላይ ተፈናጥጦ ለሚገኘው ወሮበላ ገዥ አካል ሽማግሌ አናትም አባትም ናት! በአሁኑ ጊዜ 90 ሚሊዮን የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩን እያጣ እየተሰቃየ፣ ኢፍትሀዊነት ድርጊት እየተፈጸመበት እና መብቱ በወሮበላዎች እና በሙስና በበከቱ ደንቆሮ መሪዎች ነን ባዮች መዳፍ ስር ወድቆ አሳር ፍዳውን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡
የኦባማን የሰብአዊ መብት አያያዝ ፖሊሲዎች እና መርሆዎች ከሚናገሯቸው ባዶ የሰብአዊ መብት ንግግሮች ለመለየት አይቻልም፡፡ ለአሳድ በምናባቸው “ቀይ መስመር” በማስመር የሶሪያን ህዝብ ሊጭርስ የሚችል ኬሚካላዊ መሳሪያ መጠቀም እንዳይችሉ የተሰመረውን ቀዩን መስመር እንዳያልፉ ያስጠነቅቋቸዋል፡፡ ባለፉት በርካታ ወራት አሳድ ይህንን ኬሚካላዊ መሳሪያ በመጠቀም ቢያንስ 14 ጊዜ ተግብረውታል፡፡ ለአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች ኦባማ ቀጥሉ የሚል አረንጓዴ መብራት በማሳየት በቀዩ መብራት የሰብአዊ መብት ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
የአቦማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት መርሆዎች እንዲከበሩ ከልብ ተነሳሽነቱን የማያሳይ ከሆነ በተስፋ የሚያስሞሉ እና የዜጎችን ቀልቦች የሚገዙ ታላላቅ መግለጫዎችን እና ንግግሮችን በሚሊዮኞች ለሚቆጠሩ ለዓለም ዓቀፉ የማህበረሰብ አባላት በተደጋጋሚ ማሰማቱ ፋይዳው ምንድን ነው? የኦባማ አስተዳደር ይህን አሰልች እና አደንቋሪ የውሸት የሰብአዊ መብት አጠባበቅ መዝሙር ሲያሰማ ህዝቡ በሚደሰኮረው ዲስኩር እና በተጨባጭ ምንም የተደረገ ነገር ያለመኖሩን ሊያገናዝብ የሚችል አዕምሮ የሌለው ደደብ እና ደንቆሮ አድርገው ሊቆጥሩት ይሞክራሉን? ለምንድን ነው አቦማ በተደጋጋሚ በተግባር ሲያውሏቸው የማይታዩ የአስመሳይነት እና እምነተቢስነት ንግግሮችን እንደበቀቀን እየደጋገሙ ሲናገሩ የሚደመጡት? ፕሬዚዳንት ኦባማ! እስቲ ቆም ብለው ያስተውሉ፣ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በጊዜ ሂደት የሰብአዊ መብት ጥበቃን የሚያራምዱ እና መርሆዎቻቸው አድርገው ለመተግበር እንደገና ሊበራል ዴሞክራቶች ሆነው ይወለዳሉ ብለው ያስባሉን? የአረም አበባዎች አድገው ጽጌረዳ ይሆናሉን?
ላሜሪካ የሰብአዊ መብትን የሚተካ የኢሰብአዊ ፖሊሲ የቀረበ ሀሳብ፣
ኦባማ በውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሰብአዊ መብትን በኢሰብአዊ ፖሊሲ መቀየሩ ይበጃል፡፡ የእርሳቸው ስልታዊ የሆኑ ብሄራዊ የሀገር ጥቅሞችን ብቻ በሚያስገኙ ተግባራዊ የፖለቲካ ተግባራት ላይ ብቻ ማተኮራቸው የሞራል ሰብዕናን እና ትክክል ያልሆኑ የፖለቲካ እሴቶችን እንዲያሽቆለቁሉ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ አባባል ስለሰብአዊ መብት ጥሩ እና ጥሩ ያልሆኑ ንግግሮችን ይናገራሉ፡፡ አምባገነናዊ ስርዓት ስለሚያከትምበት እና ዴሞክራሲ በዓለም ላይ ስለሚያብበት ሁኔታ ይናገራሉ ሆኖም ግን የአሜሪካንን የአጭር ጊዜም እንኳ ቢሆን ብሄራዊ ጥቅሟን ከሚነካ አካሄድ ጋር ለሰከንድ እንኳ በፍጹም የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም፡፡እንደ ትክክለኛው አካሄድ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስን “የተሳሳተ የኢሰብአዊ ፖሊሲ” ቢያንስ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በመርህ ደረጃ በመመስረት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአፍሪካ ሲፈጸሙ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልክታ ጆሮ አልባ መሆኗን ማሳወቅ አለባት፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የኢሰብአዊ ፖሊሲ መብት መርሆዎች በሚከተሉት ቀላል ሀሳቦች ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ፡
አፍሪካ በምዕራቡ ዓለም እንደሚታሰበው ወይም ደግሞ በተግባር እንደሚስተዋለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ አስፈላጊዋ አይደለም፡፡ “ሰላም እና መረጋጋት” ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ የምታራምደው ትልቁ እና ጠቃሚዋ የፖሊሲ አካሄድ መሳሪዋ ነው፡፡ በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች የሚፈጸሙ ሰብአዊ ወንጀሎች ሌሎች አለመረጋጋቶችን እና ግጭቶችን ይወልዳሉ ከሚል የተሳሳተ እምነት አንጻር ዩናይትድ ስቴትስ አይታ እንዳላየ፣ ሰምታ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ታልፈዋለች፡፡ (ለምሳሌ ያህል በደቡብ ሱዳን ሳልቫኪር እና ሬክ ማቻር በሚያደርጉት ሰይጣናዊ ድርጊት ሰበብ ለፈጸሙት ግድያ፣ እልቂት፣ ዘር ማጥፋት፣ ህዝብን በኃይል ከሚኖርበት ቀየ ማፈናቀል፣ እስራት፣ ስቃይ አስገድዶ መድፈር እና የጎሳ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ከተጣያቂነት ነጻ ነው የሚሆኑት፡፡)
የዩናይትድ ስቴትስን ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ጥቅሞች እስካከበሩ እና ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት ላይ የከፈተችውን ጦርነት እስካልተቃወሙ ድረስ የአፍሪካ ወሮበላ አምባገነኖች በአፍሪካ አህጉር ላይ በጠራራ ጸሐይ ኮሮጆ ገልብጠው ምርጫ ሲዘርፉ እና ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ እየተጠቀሙ በአፍሪካውያን/ት ዜጎች ላይ የቁማር ጨዋታ ሲጫወቱ አሜሪካ ጸጥ በማለት በትዕግስት የምትመለከተው ደንታም የማይሰጣት የዕለት ከዕለት ጉዳዩዋ ሆኗል፡፡
የፍራንክሊን ዲ.ሩዝቬልት “በየትኛውም የዓለም ክፍል” እንዲተገበሩ የሚገባቸው አራቱ አስፈላጊ የሰው ልጆች ነጻነቶች በአፍሪካ ላይ ግን ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ጨለማ የተንሰራፋበትን የአምባገነኖች አገዛዝ በማንኮታኮት እራሷን ከጀግና የነጻ የዓለም ህዝቦች ጋር ለማስተሳሰር የሩዝቬልትን ራዕይ አትከተልም፡፡ “አራት አስፈላጊ የሆኑ የሰው ልጅ ነጻነቶች የሚገለጹባት ዓለምን ዕውን ሆና ማየት እንፈልጋለን፡፡” በማለት ሩዝቬልት የተናገሩትን ወደ ተግባር ለአፍሪቃ አያስፈለግም፡፡የመጀመሪያው የመናገር እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት – (ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር በዓለም ላይ ሁሉ)፡፡ ሁለተኛው ማንም ሰው በራሱ መንገድ አምላኩን የማምለክ እና የፈለገውን እምነት በመያዝ የእራሱን እምነት የማራመድ መብት – (ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር)፡፡ ሶስተኛው የፍላጎት ነጻነት መብት – ከዓለም አቀፍ ሁኔታ አንጻር ሲተረጎም ይህ ማለት የእያንዳንዱን አገር ጤናማ የሰላም ጊዜ የማስፈን እና የእያንዳንዱን ዜጋ ፍላጎት – በየትኛውም የዓለም ክፍል ማሟላት (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡ አራተኛው ከፍርሀት ነጻ የመሆን መብት… ከዚህ አንጻር ማንም ጠብ አጫሪ አገር ተነስቶ በጎረቤቱ ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጥቃት አይፈጽምም፡፡ እንደዚሁም በዓለም ላይ ጥቃት ለመፈጸም አይቻለውም (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡ የሩዝቬልት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድንጋጌ እና ሌሎችም በድንጋጌው እየተፈተሉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ (ከአፍሪካ በስተቀር)፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ትክክለኛ እና “በተግባር ተኮር ፖለቲካ” ፖሊሲ ላይ እራሱን ብቁ ያደረገ በሚከተሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ የሰብአዊ መብት ፖሊሲ ግድፈቶችን ግልጽ በሆነ መልኩ ያካትታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በአፍሪካ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ስላሏት እሴቶች፣ መርሆዎች እና ፖሊሲዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ ስላሏት ዝንባሌዎች እና ዓላማዎች እንዲሁም አለመግባባቶች እና ግንዛቤ ያለመኖር ችግሮች አይኖሩም፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዩናይትድ ስቴትስ ስለሚኖራት የሰብአዊ መብት ስህተቶች የሚናገሩት በጣም ጥቂት ነገር ብቻ ይሆናል፡፡ ከንፈሮቻቸውን ይነክሳሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ አምባገነኖች ለሰሩት ታማኘነት ላለው እና መልካም ስራ ትክክለኛ ምስጋና ያገኛሉ፡፡ ዩናይትድ ሰቴትስ ወዲያውኑ እነዚህን አምባገነኖች እንዳላየች አድርጋ የመሄድ አስመሳይነቷን ታቆማለች፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)