Friday, 21 February 2014

“ከአሜሪካ በላይ ራሳችን ተጽዕኖ መፍጠር አለብን” ታማኝ በየነ

February 20, 2014Photo
ፋክት መጽሄት
የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ከፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ESAT Kignit Drama 21 February 2014 | ESAT Tube

ESAT Kignit Drama 21 February 2014 | ESAT Tube