Thursday, 16 January 2014

የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃት ማጥፊያ መዳኒት

January 14, 2014
ከሮባ ጳዉሎስ
ROBA PAWLOS CONTENT WRITER
ሮባ ጳዉሎስ
ካለመታደል  ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።
ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ።  የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።
ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል።  ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።
ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ።  የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል። ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡  የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው። በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!

Angelina Jolie Joins Ethiopian Film \'Difret\' as Executive Producer

Thursday, 16 January 2014 7:22 |Tesfamichal Woldu


The actress called the Zeresenay Berhane Mehari-directed feature "a strong moment for art in Ethiopia."
Angelina Jolie has joined Zeresenay Berhane Mehari’s feature directorial debut Difret, which will have its world premiere in the World Cinema Dramatic Competition category at the Sundance Film Festival on Saturday.
Centering around a young Ethiopian girl who challenges the tradition of "telefax," the practice of abduction in marriage, usually of young girls, Jolie describes the film as "a strong moment for art in Ethiopia."

መረጃ ቅበላውን ለማኮላሸት ስንል አቅጣጫችን እንዳይስት …(ጋዜጠኝ ነብዩ ሲራክ)

January 16, 2014
በመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሃገራት እና በተለይም በሳውዲ አረቢያ በምንገኝ ስደተኞች ዙሪያ መረጃ ማቅረብ ከጀመርኩበት ከአስር አመታት በላይ ተቆጥረዋል። ዘመነኛው ፊስ ቡክ ቀልባችን ከሳበው ወዲህም በርካታ ወዳጆችን አፍርቸ መረጃ ከማቀበል አልፎ በማቀርባቸው መረጃዎች ዙሪያ ምክክት ውይይት ስናደርግ ከአምስት አመት በላይ ሆኖናል። ይህ ሒደት ብዙ አስተምሮናል!Nebiyu Sirak
በረጅሙ መረጃ ቅበላ ያለፍነው ዱላ ቀረሽ ሙግትና እሰጣ ገባ አንድ ሆነን አንድነትን ፣ ዜጎችን ከመከራ እንታደግ የሚል አንድ አላማ ይዘን በአደባባይ እየፎከርን ፣ በአንድ ቋንቋ ተግባብተን የተለያየ ቋንቋ እየተናገርን ከርመናል። በግል ጉዳዩ እንደሚያገባው ዜጋ ትናነትም ሆነ ዛሬ ወደፊትም ከተገፊው የሰማሁትን ብሶትና ምሬት ፍንትው ካለ የድምጽና የምስል መረጃ ጋር አቀርባለሁ ! ይህን ሳደርግ ታዲያ የሚታይ የሚሰማው እውነትነትን አረጋግጨው እንኳ ከሰብዕና ጋር በተቆራኘ ህሊናችን እንዳያቆስል በሚል መረጃውን በድፍን አስተላልፊ ለመሄድ የተገደድኩባቸው አጋጣሚዎች የሉም አልልም ፣ አሉ ! ዳሩ ግና መረጃውን ሳስተላልፈው የሚጠራጠሩኝን አመኔታ ለማግኘት አልፎ አልፎ ሳልወድ በግድ ምስሎችና የድምጽ መረጃዎችን ይፋ ለማድረግም የተገደድኩባቸው አጋጣሚዎች አሉ።
ከሁሉም በላይ የሚቀርበውን መረጃ ከሰብአዊነት እና ሰው ከመሆን ጋር ማገናዘብና የህሊና ፍርድ መስጠት የተሳናቸው ወገኖች በእውነት ውሸት ሙግት ውስጥ ሊከቱኝ ይሞክራሉ ። በስደተኛው ማህበራዊው ኑሮ ዙሪያ ያቀረብኩትን መረጃ ከሰብአዊነት ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት ፍቅር ፣ በስደተኛው ዙሪያ ባለ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገ ገሃድ በማይታይ ኢ ፍትሃው እሳቤ ጎራ ለይተን ስንሟገት ከርምናል ። የዚህ ሁሉ ድምር ደግሞ ዛሬ ላይ ለአደጋ ዳርጎን እዚህ ደርሰናል …
ዛሬም ካለፈው አንማርምና ከነዋሪው ተቀብየ ወደ እናንተ የማደርሳቸውን የግፉአን ዜጎች ሮሮና ጩኸት ከሰብአዊነት ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት ፍቅር ፣ በስደተኛው ዙሪያ ባለ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ባደረገ ገሃድ በማይታይ ኢ ፍትሃው እሳቤ ጎራ ለይተን የምንፏከት ሁሉ ወዮልን ! ሰሞኑን በግል በተከፈተብኝ ዘመቻ አሳዛኙ በውስጥ መስመር የሚላኩ ስድብነ ዛቻና ማስፈራሪያዎች አይደሉም። የማቀርበውን መረጃን ማደናቀፊያ መጠቀሚያ ሃይማኖትን ዘር ሆኖ ሲታይ ያማል። ለሰራው ያሳዝናል። እናንት ቦለቲከኞች ሆይ! ዝም ልታስብሉኝ አትችሉምና ስልቱ ቢቀያየርም ሳልበገርላችሁ እንደምጓዝ ላሳውቃችሁ ግድ ይለኛል። በምክክር የያዛችሁት ዘመቻ የረከሰ አካሔድ ነውና ከጥፋት ባጠትቆጠቡ ወዮልን ! መቆሚያ መቀመጫችሁ ፣ መነሻ መውደቂያችሁን አበክሮ የሚረዳ አምላክ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ህሊናችሁ ስሜታችሁ ያተገናኛችሁ እለት ታዝናችሁ ! ከራሳችሁ ጋር የታረቃችሁ ዘንድ በሰራችሁት ስራ ኑሯችሁ በጸጸት የተሞላ ይሆናልና ተጠንቀቁ ! መረጃ ቅበላውን ለማኮላሸት ስንል አቅጣጫችን እንዳንስት ! ከዚህ ውጭ የምለው የለም ….!

የመረጃ ነፃነት ? …. (

ይድነቃቸው ከበደ )


January 14, 2014
‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡Yidnekachew Kebede
መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡
በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡
ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡
ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡
በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን ማክበረ ነው፡፡
ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡
በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡