Tuesday, 4 March 2014

ESAT Daily News Amsterdam Mar 04 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Mar 04 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Mar 04 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Mar 04 2014 Ethiopia | ESAT Tube

Obang Meto in Oslo, Norway on February 9, 2014 (+playlist)


የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ



አንዱ ዓለም ተፈራ


የእስከመቼ አዘጋጅ

የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓመተ ምህረት

የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ መሪዉን በማስተካከል ከመጨረሻው ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ "ሀቅ" ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ "ሀቅ" የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸ ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፈት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ ብለው ያሉበትን ለመመርመር ጊዜ አጠራቸው። ያጠራቸው ጊዜ ጥሏቸው ሄደ። እናም ባሉበት ቆመው ቀሩ።

መንግሥትን ለመምራት፤ ከፍተኛ ብስለትና ጥንቃቄ ታላቅ መሣሪያ ናቸው። "ጠላት" እና "ወዳጅ" ብሎ በመፈረጅ፤ ወዳጅን መጥቀምና ጠላትን መጉዳት በሚሉት ጋቢ ከተሸፈኑና በዛሬ ወንበር ከረጉ፤ ነገ የራሷን ወዳጅና ጠላት አበጅታ ከጎን ብቅ ስትል፤ የሚይዙትን ታሳጣለች። ለሁሉ ጥሩ ነገሮች ባለቤት ወዳጅ ብሎ የፈረጀውን ወገን ያቀሰሰና ለሁሉ ነገር መጥፎ ባለንብረት፤ ጠላት ብለው የፈረጀውን ሠፈር የወነጀለ ገዢ፤ መጨረሻው አያምርም። የኛ ገዢዎች እንዲያ ነበሩ፤ አሁንም እንዲያ ባይ በጀርባችን ተሸክመናል። ፍርሃትን በሕዝብ በመዝራት ለመግዛት የተነሱት ገዥዎቻችን፤ ራሳቸው በፍርሃት ተውጠው ከሕዝቡ ራቁ። ሕዝቡን ጠላት አድርገው ፈረጁት። መውደቃቸው የጊዜ ጉዳይ ሆነ።

ገዢዎች ከአመጣጣቸው ማንነታቸውን መገንዘብ ይቻላል። አንድ የተለዬ ወገን ቦድነው የመጡ ክፍሎች፤ ያንኑ ምርኩዝ ይዘው እስከመጨረሻው ሲሄዱ አየናቸው። ያ አመጣጣቸው ለተከተሉት ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያቸው መነፅራችን ነው። እናም እምነታቸውና ተግባራቸው ይኼንኑ አንፀባረቀልን። እብሪት የጉልበተኞች መመኪያ ሆነች። እብሪተኞች ዘለዓለማዊ ነን አሉ። በሥልጣን ላይ ሲሆኑ የረጋ አእምሮን መንገድ መጥረግ አቆሙ። በስሜትና በፍላጎት መብራት ጨለማውን ለማለፍ ተደናበሩ። የተፈጥሮ ሕግን ጠምዝዘው ሊዘውሩ ሞከሩ፤ ራቁታቸውን ተጋልጠው ቆማ። ንጉሡ ባሉበት ደነዘዙ፣ ደርጋማው መንግሥቱ ጭራውን ቆልፎ ሐራሬ ምሽግ ውስጥ ተደበቀ። ያሁኖቹ ደግሞ በተራቸው የት ይገቡ ይሆን?

እኔ ራሴ ባየኋቸው ሶስት የተከታተሉ ገዢዎቻችን፤ ይህ ሀቅ በጣም ጎልቶ ታይቷል።

በመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥቱ፣ ራሳቸው በፈጠሩትና ባመኑበት "ከአምላክ የተቀባሁ ነኝ!" ባይ እብሪት፤ ሕዝቡን ለሳቸው የተሠጠ አገልጋይ በማድረግ፤ ጊዜ ሲለውጥና የዓለም ፖለቲካ መልኩን ሲቀያይር፣ ከኋላችን የነበሩትና አዲስ ነፃ የወጡ የአፍሪቃ ሀገሮች ቀድመውን ሲሄዱ፣ በሀገራችን በሚሠጠው ትምህርት የዓለምን ግስጋሴ የተገነዘበው የተማረው ክፍል የስልጣኔ ናፍቆቱ ሲያድግ፣ የዓለም ህዝብ የኑሮ ደረጃ ከፍ እያለ ሲወጣና የኛ ኑሮ ባለበት ከመዘፍዘፉ የተነሳ የኋሊት ጉዞ ሲጀምር፤ ያመኑበት መለኮታዊ ገዢነታቸው ዓይናቸውን አውሮ ማየት ተሳናቸው። እናም የግል ጠባቂ ብለው ያደራጁት የጦር ኃይል ያለበት የኑሮ ሁኔታ አላስጨነቃቸውም። ሁሉም በተዓምርና በሳቸው ምኞት ብቻ የሚመራ አድርገው ሲያዩት፤ ታሪክ ያልተገናኙ አድርጎ ከሥራቸው መሬት ካዳቸው። እናም ሲነቁ በጨለማ ተውጠው የሚጨብጡትን አጡ። ተነድተው የታሪካቸው የመጨረሻ ምሽት፤ ባልታወቀበት ቦታ ሆነ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየካቲት ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረት ባንድነት ተነስቶ የራሱን መንግሥት ለመመሥረት ሲዘጋጅ፤ ባቋራጭ የገባው የወታደሮች ቡድን አብዮቱን አኮላሸው። በሂደቱም አንድ አምበገነን ወጥቶ፤ የፈራቸውን፣ የጠላቸውን፣ በሕልሙ የሚያስበረግጉትን፣ ለሱ ሠጥ ለጥ ብለው፣ አሜን ጌታዬ ብለው ያልተገዙለትን በማሰር፣ በመግደልና በተለያዬ መንገድ በማጥፋት ሊገዛ ተነሣ። ሰዎችን እንደ ጠጠር በፈለገበት ማስቀመጥና ማዞር፣ ማሽከርከርና መጣል የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሆነ። ራሱን ኢትዮጵያ፣ የሱን ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ፣ እሱን ያልተቀበለ ኢትዮጵያን ያልተቀበለ በማድረግ ሊገዛን ፈለገ። በመሐል ቤት ራሱ በሚያልመው መነፅር ሀገሪቱንና የሀገሪቱን የፖለቲካ ሀቅ እየተመለከተ ከህዝቡ ተለዬ። ሕዝቡ ለማያባራ ጦርነት ልጆቹን መገበር እምቢ አለ። ሕዝቡም መጥፎ ነገር እንደነካ እንጨት ራቀው። እናም ብቻውን ቀረ። ዙሪያውን ሲከበበ፤ ጅራቱን ቆልፎ እንደሚሮጥ ፈሪ ውሻ፤ እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ሐራሬ ፈረጠጠ።

በቦታው የተተካው ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ደግሞ፤ ራሱን ልዩና ብቸኛ ሆኖ የተፈጠረ አዳኝ በማድረግ፤ ለሁሉም ነገር እሱ ብቻ መፍትሔ አዋቂና ራሱ ብቻ ትክክለኛ ሆኖ በመቅረብ፤ እሱም እንደቀደሙት ሁሉ፤ ሕዝቡ ገዢው የሚለውን የሚሰማ፤ ገዢው የሚያዘውን የሚፈፅም አድርጎ እየገዛ ነው። በዚህ ተግባሩ ከሕዝቡ ተነጥሎ ተንሣፏል። ቀደም ያሉ ገዢዎቻችንን ያስቆጧቸው ወገኖች በሥራቸው እንዳቆጠቆጡት ሁሉ፤ በአዲሱ ገዥዎቻችን ላይም የሕዝብ ወገን የሆኑ ተቃዋሚዎች በየቦታው ተኮልኩለዋል። አሁንም ያለበትን ሀቅ ሳይሆን፤ የሚያልመውን እየተቀበለ እውነቱን ማየት አቃተው።

ጊዜያዊ የመሰለያ አምስት ለአንድ ጥፋሮውንና ወታደራዊ ጥንካሬውን የማይበገር ምሽግ አድርጎ ወስዶታል። የሚታየውን በሀገሪቱ የሠፈነ የኅብረተሰብ ችግርና የኑሮ ሁኔታ እንዳያይ የራሱ ቅንጦትና ምቾት አውሮታል። እንደቀድሞዎቹ ራሱን ዘለዓለማዊ አድርጎ ወስዷል። እንደቀደሙትም ተራውን እየጠበቀ ነው።

ለኔ፤ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ቡድን ነገ፤ ጉዳዬ አይደለም። ጉዳዬ፤ የኛ የኢትዮጵያዊያንና የሀገራችን የኢትዮጵያ ነገ ነው። እንደትናንቶቹና ዛሬ በዙፋኑ ላይ ቁጢጥ እንዳለው፤ ሌላ አምባገነን ገዢ እንዲተካ አልፈልግም። የእስከዛሬው አንገፍግፎኛል። ይህ ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ግፉ እንዲቀጥል በምንም ሁኔታ መንገድ አሠልጢዎች መሆን የለብንም። ታዲያ እኛ ምን ማድረግ አለብን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። መልሱን ደግሞ ነገ ሳይሆን ዛሬ መሥጠት አለብን። እጆቻችን አጣጥፈን መጪውን መጠበቁ፤ በተዓምር ኢትዮጵያዊያን የምንፈልገውን ሀቅ እንዲከተል አያደርግልንም። እናም እኔ ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ። ብቻዬን የምጥረው የትም እንደማያደርስኝ አውቃለሁ። ችግሩ የሁላችን የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው። መፍትሔውም በሁላችን በኢትዮጵያዊያን ጥረት የሚገኝ ነው። እናም ለርስዎና ለመሰሎችዎ ጥያቄ አለኝ።

ያሁኑ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ሲወገድ ምን እንዲተካ ነው የሚፈልጉት?

ይህ እንዴት ሊመጣ ይችላል?

የኔና የርስዎ፤ የያንዳንዳችን አስተዋፅዖ ምንድን ነው ይላሉ?
የኔን ላጋራዎ፤
አሁን በሀገራችን ያለው ወራሪ ዓይነት ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ነው። ሀገራችንን ወደ ከፍተኛ አደጋ እየመራት ነው። የነገው የሀገራችን ዕጣ አደገኛ ሁኔታ ላይ ወድቋል። እኛ የዚህን ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተላችን፤ ኢትዮጵያዊያን የምንፈልገውን ሕዝባዊ አስተዳደር አያመጣልንም። የራሳችንን ተግባር ነው መወሰን ያለብን። ሀገር አቀፍ የሆነ ሁሉን ኢትዮጵያዊያንን ያጠቃለለ የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞ፤ የዴሞክራሲያዊ አሠራር መሠረቱ ሲጣል ብቻ ነው አስተማማኝ የሆነ የወደፊት የሚኖረን። ለዚህ ደግሞ ሁላችንን የሚካትት ራዕይና ተልዕኮ ሊኖረን ይገባል። ይህ መንግሥት በሕዝቡ ግፊም ሆነ ራሱ በውስጡ በመንቀዙ መውደቁ አሌ አይባልም። ጥያቄው መቼ? ብቻ ነው።

በኔ እምነት፤ ኢትዮያዊነታችንን የተቀበልንና የሕዝቡን ትግል የምንደግፍ ሁሉ፤ በመጀመሪያ ማመን ያለብን፤ የምንፈልገው ተከታይ ሥርዓት፤ ለምናደርገው ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ነው። ምን እንፈልጋለን? በአንድነት ሆነን ተሰባስበን በምናደርገው የአደረጃጀት ተሳትፎ፤ በግል ወንም በቡድን ሥልጣን መያዝ ወይንም አንድን ርዕዩተ ዓለም የማራመድ ጉዳይ ቦታ የለውም። ቦታ ያለው፤ በአንድነት ሁላችን፤ ሀገራችን ከዚህ ወራሪ ከመሰለ አስተዳደር ነፃ ወጥታ፤ ሕዝቡ የወደደውን መንግሥት ለማቋቋም መሸጋገሪያ መንገድ ማዘጋጀቱ ነው። ሕዝቡ የወደደውን ከመምረጡ በፊት የመሸጋገሪያ ወቅት አለ። እናም የኛ የትግሉ ተሳታፊነት በትግል ዕሲውቶቻችን ይመራል። እናም የትግል ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤

ሀ) ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ ተከብሮለት፣

ለ) የሀገራችን አንድነት ተጠብቆ፣

ሐ) የሕግ የበላይነት ሠፍኖና፤

መ) የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው፤

የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን የሚያመቻች የሽግግር መንግሥት መቋቋሙ ነው። እኒህ አራት የትግል ዕሴቶች ሁላችንም በታጋይ ክፍል የተሠማራነው የምንጋራው ስለሆነ፤ በነዚህ ዙርያ መሰባሰቡ ወደ አንድ ያመጣናል። እናም እነኚህን አራት የትግል ዕሴቶች የተቀበልን ኢትዮጵያዊያን፤ በኢትዮጵያዊነታችን መሰባሰባችን ግዴታ ነው።።

ታሪክ ጥሏቸው ሲጓዝ ባሉበት ቆመው የተያዙትን ገዢዎቻችንን እናጢን። ኃላፊነቱ የኛ ነው ብለን እስካልጨበጥንና ግዴታችንን እስካልተወጣን ድረስ፤ ሌሎች በሚያመጡት ለውጥ የኛን ፍላጎት እንዲሟላ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ፤ በቀላሉ ጅልነት ነው። ከአፄው የከፋና የከረፋ ደርግ ተከተለ። ከደርግ የገማና የተግማማ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ ተከተለ። የከፋ አይመጣም እያልን የተሻለ ባጠገባችን አላልፍም አለ። የሚቀጥለውስ የመዓት ነው። እኛ ካላወቅንበት! ምን ይላሉ?

ESAT Menalesh Meti with Activist Asayesh Tamiru from Mannheim Germany Part ii March 04 2014 | ESAT Tube

ESAT Menalesh Meti with Activist Asayesh Tamiru from Mannheim Germany Part ii March 04 2014 | ESAT Tube

የታመቀው ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሷል !

March 3, 2014
* የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለወገኖቻችሁ ድረሱላቸው!
* ተጸወእኖ ፈጣሪዎችም እታድክሙን ፣ ሂዱና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ!
ሰሞኑን ከጅዳው የሽሜሲ ጊዜያዊ የእስር ማቆያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወራት በእስር ተንገላታን ሲሉ የመረረ ሮሯቸውን ገለጹልኝ ። ሮሯቸወ ሰሚ ማጣቱን አምርረው የገለጹልኝ ወገኖች ከእኔ አልፎ ተርፎ ለጀርመን ራዲዮ የዝግጅት ክፍል ሳይቀር ምሬት ሮሯቸውን ማስተላለፋቸውን ገልጸውልኛል።Nebiyu Sirak
ዛሬ ረፋድ ላይም በተንቀሳቃሽ ስልኬ ደውለው እጃችሁን ስጡ ተብለው በሰጡ እየደረሰባቸው ያለው መጉላላት በመክበዱ ወደ የሞት ሽረት አድርገው ቁርጡን ለማወቅ እንደሚገደዱና ይህንንም ” ለጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ለአለም ድምጻችን አሰማልን !” ሲሉ እያለቀሱ ሃሳባቸውን ሲያስረዱኝ መጭውን ለመገመት አዳጋች አልነበረም!
የግፉአኑ የአደራ ቃል አለብኝና ስልኬን እንደዘጋሁ ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ወደ ተጠባባቂው ቆንስል ጀኔራል ሸሪፍ ከይሩ ደወልኩ ። ስልካቸው ይጠራል ግን አያነሱትም! ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም … ተስፋ ሰንቄ ወደ ሌላኛዋ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩበ። እርሳቸውም አያነሱም! ደጋገምኩት ፣ መልስ ግን የለም ! የሚያዝ የሚጨበጥ ማጣት እንዴት ያማል?
ከሰአታት በኋላ እኩለ ቀን ከዚያው ከሽሜሲ ተደውሎለወኝ ስልኩን ሳነሳው የሰው ጫጫታ ፣ እሪታ ፣ አኡኡታና የጥይት ድምጽ ሰማሁ … ደዋዩን ወንድም ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? አልኩት “መረረን ፣ ድረሱልን አልን ፣ የሚሰማን አጣን ፣ እስር ቤቱን ሰብረን ወጣን !” አለኝ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰልኝ … ከዚያን ሰአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከሽሜሲ የሚደርሰኝ መረጃ ደስ አይልም ! የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአካባቢው የተገኙ ቢሆንም መፍትሄ ማምጣት ግን የቻሉ አይመስልም !
የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለመረጃ ቅርብ ሁኑ ! ወገንን ለመደገፍ ትጉ ! የወገኔን የወገናችሁን ክፉ ደግ መረጃ እንዳላቀብል ፣ አታስተላልፍ ከፖለቲካው ጋር እያገናኛችሁ ከመወንጀል እስከ ተራ አሉባልታ የምትሞጅሩኝ የምትሞግቱኝ ተሰሚነት ያላችሁ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሆይ ! አታድክሙን ! ስሙኝ ? እነሆ እየሆነ ያለውን ሂዱና ተመልከቱ ! የምትቆረቆረቆሩት ለወገኖቻችሁ ከሆነ እነሆ ድረሱላቸው !
በቃ ! ሌላ ምን ይባላል

የዋሽንግተንና የአዲስ አበባ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየተተቸ ነዉ

March 3, 2014
በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለንያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱአንባገነናዉያን ጋር  እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ!
ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 24/2006 (ቢቢኤን) የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ገደብየለሽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማመላከት ያደረጋቸዉን ጥናቶች ዋቢ በማድረግ በየካቲት 20/2006 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።መሰረቱን አርሊንግተን ቨርጂኒያ ያደረገዉ ፖለቲኮ የሚባለዉ ጋዜጣ/መጽሔት የኦባማ አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስትን ከመሰሉ ለነጻነት ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ያለዉ ምጸታዊ የዲፕሎማሲ ቁርኝትንም ይተቻል።
ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የዩናይትድ እስቴትስ መንግስታት ዜጎቻቸዉን ከሚጨቁኑ አገራት ጋር ግንኙነት ለመመስረት እምብዛም እንደማይጥሩ ፖለቲኮ እየገለጸ፤ለሚዛናዊነቱ ተስፋ የተጣለበት የኦባማ ካቢኔ ከሌሎቹ የዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዝዳንቶች  በባሰ መልኩ ለዜጎቻቸዉ ደህነነት ምቹ ካልሆኑ 25 አገራት ጋር ግንኙነት አለዉ ሲል የኦባማን የብሐራዊ ደህነነትና ጥበቃ አማካሪ የሆኑትን ሱዛን ራይስ ንግግርን በዋቢነት ያቀርባል። ራይስ “ግልፅ እንሁን አንዳንዴ እኛ አጥብቀን የምንይዛቸዉን ዉድ የሆኑ መብቶችን ከማያከብሩ መንግስታት ጋር የስራ ግንኙነት አለን” በማለት በባለፈዉ የነሐሴ ወር መናገራቸዉን ፖለቲኮ ይገልጻል።
ፖለቲኮ ለነጻነት የማይመቹ ብሎ ከጠራቸዉ 25 አገራት ዉስጥ ኢትዮጵያን በቁጥር 11 ላይ ያስቀመጠ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ይመሯታል የምትባለዋ ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጓን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣መንግስትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አካላትን ለማሰር እንደ ማህተም ትጠቀምበታለች ሲል ተጠያቂ ያደርጋል።ፖለቲኮ አክሎም የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በ1999 ሶማሊያን በመዉረር እራሱን ለዩናይትድ እስቴትስ ግልጋሎት ማቅረቡንያስረዳል። ይህንንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በአሜሪካ የሰለጠኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከብሔር ብሔረሰቦች የተነሱ አማጺያንን ለማስቆም የጦርነት ወንጀል መፈጸማቸዉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ክስ ቢቀርብበትም  ዋሽንግተን አዲስ አበባን በዲፕሎማሲ “እቅፍ-እቅፍቅፍ” እያደረገች መቀጠሏን ገልጿል።
ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ይጥሳሉ ከሚባሉት ጭቋኝ አገራት ጎራ ብትመደብም ፤እንደ አዉሮፒኣይኑ ቀመር በ2008 ብቻ ከዩናይትድ እስቴትስ 969 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ ተቀብላለች!
በኢትዮጵያ ዉስጥ ቀጣይ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ግድያ፣እስር፣የሐይማኖትነጻነትን መነፈግ፣የፕሬስ ነጻነት መመንመን፣የመማርና ማስተማር ሒደት ነጻነት በመንግስት መዳፍ ዉስጥ መግባት፣የመደራጀት-የመሰባሰብ-ሐሳብን በነጻ የመግለጽ ሁለንተናዊ መብት፣ የፍርድ ቤት አሰራር መበላሽትና በስልጣን መባለግን በመተንተን የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየካቲት 20/2006 አመታዊ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። የኦባማ አስተዳደር አካል የሆነዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳቃቂ የሆነ የመብት ረገጣ ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖሩን እያወጀ የኦባማዉ ቤተ-መንግስት ኢትዮጵያን ከመሰሉ በአንባገነናዉያን ከሚመሩ አገራት ጋር “መለስ-ቀለስ” ማለቱ እያስተቸዉ ነው። የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን የሚመሩት ጃን ኬሪ አገራቸዉ ከስህተት የጠራች አለመሆኗን ያስረዳሉ።
“ዛሬ ስለ ሌሎች አገራት ያለዉ ሪፖርት ይፋ ለማድረግ ብንመጣም፤ እዚሁ አገራችን ላይ እራሳችንን በከፍተኛ መልኩ ተጠያቂ እናደርጋለን! እንከን የለሽ አለመሆናችንን እናዉቃለን” ጃን ኬሪ።
ጃን ኬሪ መስሪያቤታቸዉ ይፋ ያደረገዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ዋሽንግተን ዲሲ ባሉ የመስሪያ ቤቱ አባላት ጥናት ብቻ የተዘጋጀ  ሳይሆን በእያንዱ አገራት ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ሲያስረዱ “በመላዉ አለም ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በጥናት እንደዚሁም እነዚህን ጽሁፎችን በመጻፍ አክቲቪስቶችን በመቅረብ መንግስታትን በማናገር የኤንጂኦና የሚዲያ ሪፖርቶችን በመተንተን አያሌ ሰአታትን አባክነዋል”ሲሉም ገልጸዋል።
ኬሪ ለነጻነትና ለመብት በሚደረግ ጥረት ዉስጥ ግለሰባዊ ሚና የጎላ መሆኑን መሆኑንም ይገልፃሉ።ከተለያዩ አገራት የለዉጥ ተምሳሊት የሚሏቸዉን ግለሰቦችን ስም በማንሳት የኢትዮጲያዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሚናን አድንቀዋል  “እስክንድር ነጋ ሐሳብን በነጻ ስለመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚጽፍ ነው” ብለዋል።
በሚያዚያ 4/2004 የፔን አሜሪካን ሽልማትን ያገኘዉ እስክንድር ነጋ አለም አቀፋዊ ትኩረትን ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት በሽብር ፈጠራ ወንጅሎት ከመስከረም 3/2003 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል።
የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነጻነትን ከሚነጥቁ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ነጻነትን ከተነፈጉ ብዙሗን አጋር በመሆን አብሮ እንደሚቆም ኬሪ ቃላቸዉን እያደሱ ይናገራሉ “ዛሬ ቃላችንን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን! ክብርን ከሚነፍጉ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ክብርን ከሚሹ ብዙሗን ጋር አብረን ለመቆም ዝግጁ መሆናችንንም ለመግለጽ እንወዳለን!”በማለት ቢያስረዱም መንግስታቸዉ ከጨቋኝ አንባገነናዊያን ጋር በሚያደርገዉ ዲፕሎማሲያዊ ቅርርብ ተጠያቂ እየሆነ ነው።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ብዙ ቃልኪዳን የገቡት በራክ ኦባማ ቃሊኪዳናቸዉ አለተፈጸመም። በተመሳሳይ መልኩ ያሁኑ የዉጭ ጉዳይ መስራያ ቤት ሐላፊ ጃን ኬሪም ሆኑ የቀድሞዋ ሒላሪ ክሊንተን ከአንባገነናዊያን ጋር ያለዉን ግንኙነት ሲያደረጁ እንጂ ሲያመነምኑ አልተስተዋለም በማለት  በርካታ ምሁራን፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ተንታኞች ወቀሳ ያቀርቡባቸዋል።
በጥር 12/2001 ቃለመሃላ የፈጸሙት ፕሬዝዳንት ኦባማ ሰላምና ክብርን ለሚሹ የአለማችን ዜጎች የርሳቸዉ መመረጥ ብስራት እንደሆነ አመላክተዉ ነበር። ከትላላቅ የአለማችን መዲናዎች ጀምሮ ወላጅ አባታቸዉ እስከመጡበት የኬኒያ መንደር የተስፋ ቃል ነበራቸዉ! እንዲም በማለት  ስሜትን በሚነካ መልኩ ተናግረዉ ነበር…
“ከትላልቆቹ መዲናዎች እስከ አባቴ የተወለደባት መንደር ዛሬ ለሚመለከቱን ህዝቦችና መንግስታት፤ አሁን አሜሪካ የእያንዳንዱ አገር የእያንዳንዱ ግለሰብ ወዳጅ ናት! ሰላምና ክብርን ለሚፈልጉ ሴቶችና ህጻናት ዳግም ለመምራት ዝግጁ ነን” ፕሬዝዳንት በራክ ኦባማ።
ኦባማ ምንጫቸዉ ለሆነችዋ አፍሪካ ፕሬዝዳንታዊ ሐይላቸዉን በመጠቅም ያበረከቱት አስተዋፅኦ አናሳ ነዉ።ፕሬዝዳንቱ ቃለመሃላቸዉን ሲፈጽሙ ስልጣንን በማጭበርበር-በሙስናና የሐሳብ ልዩነትን በማፈን በሚቆናጠጡ አንባገነናዉያን ላይ ጣታቸዉን ቢቀስሩም ከነዚህ ምቹ ያልሆኑ አሳፍሪ መንግስታት ጋር እርሳቸዉም ይሁን ካቢኔአቸዉ ዲፕሎማሲያዊ ገደብን አለማበጀቱ አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።
በአሜሪካዋ መዲና በዋሽንግተን ዲሲ ጥር 12/ 2001 ቀዝቃዉ አየር በጭብጨባ እየሞቀ ብዙዎች እያለቀሱ ኦባማ ለአንባገነናዊያን መልእክት አስተላልፈዋል።
“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ አንባገነናዉያን ጋር  እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ።
ብዙ የተገቡ ቃልኪዳስኖች ተግባራዊ ሳይሆኑ በየካቲት 20/2006 ከዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአመቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲታወጅ “ከነጻነት ፈላጊዎች ጋር እንቆማለን!” የሚል ቃልኪዳን ተገብቷል።የዩናይትድ እስቴትስ መንግስት ባወጣዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት “ጨቋኝ-አፋኝ-አሳሪ-ገዳይ-ኢዲሞክራሲያዊ” መሆኑን ይፋ አድርጓል። ፖለቲኮ ጋዜጣ/መጽሔት ይህ ሪፖርት በወጣበት ማግስት የኦባማ አስተዳደር ኢትዮጵያን ከመሰሉ ለዜጎቻቸዉ ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ይወዳጃል ሲል ይተቻል።
የዲሞክራሲ ተምሳሊት ነን የሚሉ የምእራቡ አገራት ለአንባገነናዊያን ዲፖሎማሲያዊ ከለላ መስጠታቸው የጥቅም ትስስር ወይስ ምጸታዊ የሆነ የዲፕሎማሲ ጨወታ? የሚለዉ ጥያቄ ቢነሳም …ትችቱእንደቀጠለ ነዉ።

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል! (ግንቦት7)

March 4, 2014
Ginbot 7 weekly editorialየባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ሺህ ጊዜ እንደሚሻል አካሉን ብቻ ሳይሆን ህሊናውንም ለትግራዩ ነፃ አውጪ ህወሓት ባርነት ላስገዛው “የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)” እያለ እራሱን ለሚጠራው ድርጅት መሪዎች ተናገረ።
ባርነት ክፉ ነው። በባርነት ላይ የጭንቅላት ባዶነት ሲታከልበት ደግሞ አለምነው መኮንንን የመሰሉ የብአዴን መሪዎችን ይፈጥራል። የብአዴን መሪዎች ለጌታቸው ህወሓት ያላቸውን ታማኝነት ለማሳየት ራሳቸውን ማዋረዳቸው ሳያንስ እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በጅምላ መስደባቸው ብአዴን እንደ ድርጅት የሚገኝበት የተዋረደ ደረጃ ያሳያል።
ህሊና ያለው ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። ዛሬ በጉልበተኛ የባርያ አሳዳሪ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። እንደ ብአዴን መሪዎች በታማኝ ባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።
የአማራ ሕዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በፋሽስት ጣልያን ወረራ ጊዜ ለጠላት ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። እነሱም ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። በገዢዎቹ ለመወደድ የራሱን ሕዝብ የሚዘልፍ፣ የሚሰድብና የሚያዋርድ እንደ ብአዴን ያለ አዋራጅ ድርጅት በአማራ ምድር አልታየም።
ለዚህም ነው የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ የብአዴንና የወያኔን አፈናዎችን በጣጥሶ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቁጣውን በባዶ እግሩ አደባባይ በመውጣት የገለፀው። እግር ባዶ መሆኑ ጭንቅላት ባዶ የመሆኑ ያህል የሚያሳፍር አይደለም። ድህነት ወንጀል አይደለም። ነፃ አዕምሮና የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ አስተዳደር ካለ ድህነትን ማሸነፍ ይቻላል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት የማደግ እድል አላቸው። ስለሆነም ግንቦት 7 ለባህርዳሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ አደራጆችና ተሳታፉዎች “እንኳን ደስ ያላችሁ” በማለት የትግል አጋርነቱን መግለጽ ይሻል።
ግንቦት 7፣ ብአዴንን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ከዚህም በተጨማሪ የብአዴንን ከፍተኛ አመራር ከሌላው ለይቶ ይመለከታል። ብአዴን ነፍሳቸውን ሳይቀር ለወያኔ በሸጡ ሰዎች የሚመራ፤ ነፃ የመውጣት ተስፋ የሌለው ራሱ ባርያ የሆነ ድርጅት ነው። አባላቱ ግን ከዚህ የተለዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግንቦት 7 ያውቃል።
ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህም በፊትም ደጋግሞ እንደገለጸው፤ በተለያዩ ጊዜያት ራሳቸውን ከወያኔ ባርነት ነፃ ለማውጣት በወሰዱት እርምጃ መስዋእትነት የከፈሉ የብአዴን አባላት መኖራቸውን ያውቃል። ግንቦት 7 ለእነዚህ ቆራጦች ትልቅ አክብሮት አለው። ዛሬም ህሊናቸውን ሙሉ በሙሉ ያልሸጡ የብአዴን አባላት አሉ ብሎ ያምናል። እነዚህ ወገኖቻችን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የግል፣ የወገንና የአገር ግዴታ አለባቸው ብሎ ያምናል።
ስለሆነም ዛሬም ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን ጥሪዓችንን እናድሳለን።
የብአዴን አባላት ሆይ!!! የገዛ ራሳችሁን፣ የአማራን ሕዝብ እና ኢትዮጵያን እያዋረደ ካለው ብአዴን ተላቀቁ፤ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን ግደሉት። የብአዴን መኖር ለወያኔ ካልሆነ በስተቀር ለማንም አይበጅም። ነፃነት ካለ ድህነትን በሥራ ማሸነፍ ይቻላል። ሰው ባርያ ሆኖ በሀብት ቢንበሸበሽ ምን ይፈይድለታል?
የብአዴን አባላት ሆይ!!! ወደ ህሊችሁ ተመለሱ። ራሳችሁንም የበደላችሁትን ሕዝብ የመካስ እድል አድል አላችሁ ተጠቀሙበት። ይህንን ባታደርጉ ግን ለገዛ ራሳችሁ ፀፀት፤ ለልጆቻችሁ ሀፍረትን የምታወርሱ መሆኑን አትዘንጉ። ወያኔ መሸነፉ በጭራሽ የማይቀር መሆኑን እያወቃቸው በድህረ ጣልያን ወረራ ባንዶች ያገኙትን ምህረት እናገኛለን ብላችሁ አታስቡ።