Wednesday, 16 July 2014

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

July 16th, 2014                   
ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-
መኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤ የባንክ አካውንት ቁጥር፡- AEUP – SP 235
አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የባንክ አካውንት፡- UDJ – A/C 47
በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስንተባባር እናሸንፈላን!!
ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባudJAEUP

በደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ አወጣ

July 16th, 2014
ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የአቋም መግለጫን ስለማሳወቅ፡
ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ 06/11/06 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት በመሰብሰብ የፓርቲውን የስራ እንቅስቃሴና በቅርቡ በታሰሩ የፓርቲው የበላይ አመራሮች በአቶ ሀብታሙ አያሌው እና በአቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በሰበብ አስባቡ በሚታሰሩ ሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ህገ ወጥ ድርጊት አባላቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. የዜጎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና ከፈለጉት ፓርቲ ጋር የመወገን መብታቸውን መንግስት እንዲያከብርና እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡
2. በህገ መንግስቱ የተፈቀዱት የዜጎች መብቶች ሳይሸራረፉ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ እንዲያከብርና እንዲያስከብርእንጠይቃለን፡፡
3. ዜጎች ለመብታቸው መከበር ፍላጎታቸው እየሰፋና እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን በማወቅ ገዢው ፓርቲ ከድርጊቱ እንዲታቀብና የዜጎች መብት እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡
4. ለዲሞክራሲ እውን መሆንና መዳበር ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን ገዢው ፓርቲ ጠንቅቆ በማወቅ ለሰላማዊ ትግሉ መዳበር መንግስት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን በማለት ያቋ ም መግለጫ ያወጣን ሲሆን
በመጨረሻም የፓርቲያችን የላእላይ ምክር ቤት ያለአግባብ የታሰሩ ወንድሞቻችን ሁኔታ ያሳዘነው ቢሆንም ነገር ግን የነሱ መታሰር የትግሉን ምእራፍ ከማስፋትና የበለጠ ከማቀጣጠል ባሻገር አንድም እርምጃ ወደ ኋላ የማይመልሰውና ሁሉንም አባል የበለጠ ለትግሉ ያነሳሳ መሆኑን አምኖ ከእስካሁኑ በበለጠ የትግል ስልቱን በማስፋት በዜጎች መብት ላይ እየዘመተ ያለውን የገዢው ፓርቲ በአደባባይ እና በአዳራሽ በህዝብ የምናወግዝበትን የሰላማዊ ትግል ስልት ፓርቲው እንዲያመቻችልን በማለት የዞኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የአቋም መግለጫ ያወጣ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!10462481_668385689913035_7014532587449142359_n

Monday, 7 July 2014

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ESAT special program on ATO ANDARGACHEW TSIGE EXTRADITION from Yemen at transit | ESATTUBE

ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና የመጀመሪያ እርከን ተግባሪዊ የትግል ጥሪ

July 6th, 2014
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
በየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።
አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።
ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶች ጋር ንቅናቄዓችን ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ የቻለ መሪ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ለወያኔ የጉሮሮ ቁስል የሆነበት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ጋር ግንቦት 7 የፈጠረው ጠንካራ ትብብር ነው። በትህዴን ጋር በመሆን አቶ አንዳርጋቸው ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ጀርባ መንጠልጠል እንዳይችል አድርጎታል። እናም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ከዘረኝነት ፀድቶ መገኘት ማለትም ጭምር ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት በኢትዮጵያዊያን እኩልነት እና እኩል ባለመብትነት ከልብ ማመን እና ለእኩልነት በጽናት መታገል ማለት ነው።
አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን የግድ የግንቦት 7 አባል መሆንን አይጠየቅም። አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን ለመልካም ዓላማዎች መሳካት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀትን እንጂ የግድ ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር መወገንን አይሻም። ያም ሆኖ ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የሆነ ሰው በጠንካራ ድርጅት የታገዘ ትግል አስፈላጊነት ይረዳል።
በመጨረሻም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ኦኪሎ ኦኴኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እዚህ ዘርዝረን ልንጨርሳቸው የማንችላቸው ጀግኖቻችንን ሁሉ መሆን ማለት ነው።
የ“ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ዘመቻ ትኩረቶችን በየጊዜው የምንገልጽ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል ያለበት የዓለም ዓቀፍ ዘመቻው የመጀመሪያ እርከን ትኩረቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
የዘመቻው የመጀመሪያው እርከን ትኩረቶች
ይህ የመጀመሪያ እርከን ሶስት ቦታዎች ላይ ያተኩራል፡- የመን፣ ብርታኒያ እና ወያኔ
የመንን በተመለከተ
የየመን መንግሥት የዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ የየመን የራሷን ህግ በመተላለፍ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለየመን መንግሥት የተደረገው ተማጽኖ ሰሚ ጆሮ አላገኘም። እስካሁንም ድረስ የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውን ማሠሩንና ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን በይፋ አላመነም። እኛ ባለን መረጃ መሠረት በአይሮፕላን ማረፊያው ከማገት ጀምሮ በልዩ በረራ ወደ ኢትዮጵያ እስከ መላክ ድረስ ያለውን የውንብድና ሥራ በየመን በኩል ሆኖ የሠራው ቀጥታ ተጠሪነቱ ለየመን ፕሬዚዳንት የሆነው የስለላ ድርጅት ነው። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ሊቀለበስ የማይችል እና በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የየመን መንግሥትና ሕዝብ ይህን እንዲያውቁት ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው የተግባር እንቅስቃሴ አካል ነው።
የመንን በተመለከተ የሚቀጥለው ሳምንት ዘመቻችን ግብ ቁጣችንን የየመን ፕሬዚዳንት እና የየመን መንግሥት ብቻ ሳይሆን የየመን ሕዝብም እንዲያውቅ ማድረግ ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ያህል ተጠቅሰዋል።
1.ለየመን ፕሬዚዳንት አዲስ መረር ያለ ደብዳቤ ተጽፎ በፋክስና በኢሜል በየመን መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶችና ኤምባሲዎች አድራሻዎች መላክ። በመልዕክት መጨናነቅ ከሚገባቸው የየመን ተቋማት አንዱ አዲስ አበባ የሚገኘው የየመን ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ በዘመቻው የምትሳተፉ ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ እናሳስባለን፤ የኢንተርኔትና የፋክስ መልክቶችን ስትልኩ ራስን ለጉዳት በማያጋልጥ መንገድ መደረግ ይኖርበታል።
2.የየመን ኤምባሲዎችን ሥራ ማወክ በሚችሉ ሰልፎችና ተቃውሞዎች ማጨናነቅ። የፕሬዚዳንቱን ፎቶና የአገሪቱን ባንዲራ ማቃጠል። ይህ በውጭ አገራት ብቻ መደረግ ያለበት ነው።
3.በውጭ አገራት በየከተሞች ለሚገኙ የየመን ኮሚኒቲዎች ደብዳቤ መፃፍና መንግሥታቸውን እንዲቃወሙ መገፋፋት፤ ይህንን ካላደረጉ ግን ከመንግሥታቸው ጎን ተሰልፈው በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዳወጁ የምንቆጥረው መሆኑን በማያሻማ መንገድ መንገር፤
4.በየመን አየር መንገድና በማናቸው የየመን የንግድ ድርጅቶችና ቢዝነሶች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በቢዝነሶቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ ተግባር በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጭም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መተግበር የሚኖርበት አቢይ ተግባር ነው።
5.በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የየመን ቢዝነሶችን መርጦ ምርቶቻቸው እና አገልግሎቶቻቸው እንዲጠሉ ማድረግ። ከእንግዲህ በየመን ገንዘብ የተሠራ ወይም ከየመን የመጣ ብስኩትም ይሁን ሲጃራ የወገናች ደም የነካው እቃ ነው።

ብርታኒያን በተመለከተ

የእንግሊዝ መንግሥት ማድረግ የነበረበትን እና ማድረግ ይችል የነበረውን ሁሉ አድርጓል ብለን አናምንም። እርምጃው ፈጣን አልነበረም፤ አሁንም አይደለም።
ስለሆነም እንግሊዝን በተመለከተ የዘመቻችን ግብ የእንግሊዝ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመንፈጉ መክሰስ እና ከአሁን በኋላም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና መሪያችን እንዲያስፈታ መወትወት ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ተዘርዝረዋል።
1.የእንግሊዝ መንግሥትን በህግ መክሰስ (ይህ በንቅናቄው ጽ/ቤት የሚሠራ ሲሆን ዝርዝሩ ወደፊት ይገለፃል)፤
2.ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ደብዳቤ ጽፎ በፋክስና በኢሜል ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለኤምባሲዎች በብዛት መላክ። አንዱ ትኩረት የሚደረግበት ኤምባሲ አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመቻው የሚሳተፉ ወገኖች አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
3.በለንደን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደጃፍ፤ በሌሎች አገሮች ደግሞ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቁጣ የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄድ።
ወያኔን በተመለከተ
ወያኔን በተመለከተ የሚደረጉ ትግሎች በሙሉ ወያኔን ከስልጣን በማስወገድ ላይ ያነጣጠሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ወያኔን ለመጣል ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ፡ ከቁም ውርደትና ባርነት ለነጻነትና ለፍትህ ከወያኔ ጋር ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁ እየጣሉ ለመውደቅ ፤ መስዋእት ለመሆን በወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንና የህዝብ ሃይሎች የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቅሴ ነው ፤ እንቀላቀላቸው።
በተለያዩ ምክንያቶች ወሳኙን ትግል መቀላቀል የማይችሉ ወገኖቻችን በያሉበት ሆነው ከወያኔ የስለላ መረብ ተጠነቅቀው ራሳቸውን በቡድን ያደራጁ፤ ይህንኑ የሚያግዙ ተግባራት ለመፈጸም ራሳቸውን ያዘጋጁ። እነዚህ ተግባራት ወያኔን በገቡበት እየገቡ በማሳፈር ፤እረፍት በመንሳት፤ የፈፀሟቸውን ወንጀሎች በአደባባይ በመናገር እንዲሸማቀቁ በማድረግ፤ ማንነታቸው ለሸሪኮቻቸው ወይም ለሥራ ባልደረቦቻቸው በመንገር ወዳጅ በማሳጣት፣ ንግዶቻቸውን ኩባንያዎቻቸው እንዲከስሩ በማድረግ የፋናንስ አቅማቸው በማዳከም ረገድ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ከዚህ አኳያ ሊደረጉ ከሚገቡ ተግባራት የሚከተሉት በምሳሌነት ተዘርዝረዋል።
1.በምዕራቡ ዓለም በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያሉት እና የሚመላለሱ ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ መደራጀትና እንደየሀገሩ ሁኔታ አግባብ ያላቸውን የህግ መሳሪያዎች መጠቀም፤
2.በመላው ዓለም የወያኔ ኤምባሲዎችና የኮንሱላር ጽ/ቤቶች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤
3.በመላው ዓለም የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (ከሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣ ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ፡ የሥራ ፤ የማኅበራዊ ትብብርና ግንኙነት አለማድረግ፤ ፊት መንሳት ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን ማካሄድ። የወያኔ አባላትንና ደጋፊዎችን በሁሉም ዓይነት ግንኙት ማግለል፡ አለመተባበር በኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።
4.በማናቸውም የዓለም ክፍል ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ሲቪል፣ የወታደራዊና የደህነት ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣ ማስነወር፣ መውጫ መግቢያ ማሳጣት፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀባይነት እንደሌላቸው በሕዝብ ላይ ለፈጸሙት ወንጀሎች ሁሉ የሕዝብ ቁጣ ዒላማ እንዲሆኑ እንደልባቸው መፏላል እንዳይችሉ ማድረግ። በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ራሱ በቡድን አደራጅቶ ለወያኔ ታጣቂዎች ጥቃት ሳያጋልጡ አድብቶና አስልቶ ተመሳሳይ ድርጊቶች መፈፀም
5.የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ አገዛዝ የሚመሩ እንዲሁም በወያኔ ኤፈርት ስር ያሉ ኩባንያዎች፤ቢዝነሶች ላይ እቅባ ማድረግ፤ የሸቀጥና የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ አለመሆን፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ሥራቸውን ማጨናገፍ ማደናቀፍ፤ አሻጥሮችን በተደራጀ መልክ፣ በጥናትና በብልሃት ተግባራዊ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተግባሪዊ መደረግ ይኖርበታል።
6.በዌስተር ዩኒየን፣ በመኒ ግራም እንዲሁም በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በወያኔ ደጋፊዎች በመሠርቷቸው ልዩ ልዩ የገንዘብ ላኪ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ የገንዘብ መላኪያ መንገዶችን መፈለግ፤ እነዚህ በሌሉባቸው አካባቢዎች የፈጠራ ችሎታን በመጠቀም ገንዘብ ለዘመድ አዝማድ በወያኔ በኩል ሳይላክ የሚደርስበትን ሁኔታ መፍጠር፤ የወያኔን የፋሽታዊ አገዛዝ አንዱና ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ የማድረቂያ ዘዴዎችን ሁሉ በመፈለግ ተግባሪዊ በማድርግ የወያኔን በዘረኝነትና በዘረፋ የተገነባ የገንዘብና የኢኮኖሚ አቅም ማዳከም፤ መቦርቦር፤ መናድ።
7.ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያ ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ። (የእነዚህን ዝርዝሮች በተከታታይ ይገልጻሉ)
8.የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በተለይ ደግሞ ሳያስተምሩ ለወያኔ ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር (ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣ እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)
9.ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጆሮችና ከወያኔ ጋር የተያያዙ የንግድ ቤቶችና ኩባንያዎች የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ። (ዝርዝራቸውን በተከታታይ እናወጣለን)
በመጨረሻም የወጣቱ የማያልቅ የፈጠራ ችሎታ ከላይ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተቱ ሆኖም ግን ውጤታማ የሆኑ የተቃውሞ መግለጫ ዘዴዎች ያፈልቃል ብለን እናምናለን። ስለሆነም ዘመቻውን በየአካባቢው በሚገኝ ሀሳብና ፈጠራ ማዳበር ይቻላል። ይህ ዘመቻ ወያኔ ከስልጣን እስኪባረር ድረስ በየጊዜ እየከረረ መሄድ እንዳለበት ታሳቢ አድርጎ መነሳት ይኖርበታል። ስለሆነም በየጊዜው አዳዲስ ነጥቦችን ተግባሪዊ የትግል ስልቶችን እንጨምራለን።
ለመላው የአትዮጵያ ሕዝብ፣ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሁሉ፣ ለሁሉም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሁሉ በኅብረት በጋራ ሆነን፤ ትከሻ ገጥመን ለተግባሪዊ ትግል በቁርጠኝነት እንድንነሳ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።
ይህ ዘመቻ ወያኔን ከስልጣን ለማባረር ምድር ላይ ከምናደርገው የመረረ ትግል ጋር ሲቀናጅ የሚፈለገውን ውጤት ስለሚያስገኝ ለነፃነቱ ግድ ያለው ዜጋ ሁሉ በሙሉ ኃይሉና አቅሙ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ ጥሪ ያቀርባል።