Friday, 28 February 2014

ESAT Yederegetse Dassesa February 28,2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Yederegetse Dassesa February 28,2014 Ethiopia | ESAT Tube

መታየት ያለበት- Sahara TV በ ተፈናቃይ አማሮች ላይ የዘገበው


ሀይለመድህን አበራ፦ የታፈነ ብሶተኛ ወይንስ የሚያደርገውን የማያውቅ የአእምሮ በሽተኛ?

February 27, 2014
አሰፋ (ከዳላስ)

መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው

የሰሞኑ ትኩስ ዜና በሆነው የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው:: በተለይ የኢትዮጵያው አገዛዝ እና እሱን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመደገፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚስጡዋቸው መላምቶች የሚያስገርሙና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከል ሁለቱን ልጥቀስ:: በአንድ  በኩል ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር አለበት ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም ያጎደፈ በማለት ለመውቀስ ይዳዳቸዋል::Ethiopian Airlines pilot Hailemeden Abera Tegegn
እንግዲህ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ሁለቱ ግምቶችና ወቀሳዎች በአንድ ግዜ እና በአንድ ላይ እውነት ሊሆኑ አይችሉም:: አንዱ እወነት ከሆነ ሌላው ሀሰት ይሆናል:: ይህም ማለት ሀይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ከሆነ የኢትዮጵያንም ሆነ የአየር መንገዱን መልካም ገፅታ በማቆሸሽ ሊወቀስ አይችልም:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአእምሮ ህመም አለበት ከተባለ በአእምሮ ህመም ውስጥ ሆኖ ለሚፈፅመው ድርጊት ሀላፊነት ሊወስድ አይጠበቅም:: አመዛዝኖና አስቦ ያደረገው ስላልሆነ:: ድርጊቱ በሰውየው እንደተፈፀመ ተደርጎ አይታሰብም:: ምክንያቱም ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሀይል ተፅእኖ ስር ሆኖ ያደረገው የተከናወነ በመሆኑ:: በዚህም የተነሳ መልካም ነገር ቢሰራም ሊመሰገንና ሊሸለም እንደማይችል ሁሉ ክፉ ነገር ቢያደርግም ሊወቀስ እና ሊፈረድበት አይገባም:: ይህ ካልሆነ ግን የአእምሮ በሽተኛ የሚለውን ማንሳቱ ብዙም ትርጉም ሊኖረው አይችልም:: ስለዚህ መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው::
ከላይ እንደገለፅኩት እውነት ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር ወይንም የመንፈስ ጭንቀት ነበረበት ከተባለ ሊታዘንለት ይገባል እንጂ ሊወቀስ አይችልም:: ምናልባት ሊወቀስና ሊጠየቅ የሚገባው የአእምሮ ችግር ውስጥ ያለን ሰው አውሮፕላን ማብረርን የመሰለ ከፍተኛ የመንፈስ መረጋጋትን የሚጠይቅ ከባድ ስራ ውስጥ እንዲሰማራ ያደረገው ክፍል ይመስለኛል:: ለነገሩ ሀይለመድህን የሰራው ስራ በአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ያለ ሰው ያደርገዋል ብሎ ማሰብ ፍፁም ይከብዳል:: አውሮፕላንን ያህል ነገር ከ200 በላይ ተሳፋሪ ጭኖ ያውም በሁለት የጦር ጄት አውሮፕላኖች እንደተከበበ አውቆ በተረጋጋ ሁኔታ በሰላም የሚፈልገው ቦታ ማሳረፍ መቻል አንድ የአእምሮ ችግር ካለበት ሰው የሚጠበቅ ድርጊት አይመስለኝም:: ይልቁንስ የሰከነ አስተሳሰብ ያለው እንዲሁም የሚያደርገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው የፈፀመው ተግባር እንጂ የአእምሮ መረበሽ ውስጥ ያለ ሰው ድርጊት ያለመሆኑን አእምሮ ያለው የሚረዳው ነው::
ሌላው ከዚሁ ከአእምሮ ህመም መላምት ጋር ተያይዞ መነሳት ያለበት ጥያቄ በርግጥ ልጁ የአእምሮ መታወክ ከነበረበት ለዚህ የአእምሮ ችግር ያበቃው ምክንያት ምንድነው የሚለው ነው:: እስካሁን ባለው መረጃ “የአእምሮ ህመም” የሚለው ጉዳይ በመጀመሪያ መነሳት የጀመረው እህቱ ሰጠችው ከተባለው “መግለጫ” በኋላ ነው:: እህቱ ተናገረች የተባለውን እንኳን ብንቀበል እሷ የተናገረችው ወንድሟ ከአጎቱ ሞት በኋላ መረጋጋት እንደማይታይበት፤ የሚከታተሉኝ “ሰዎች” አሉ ብሎ እንደሚያስብና በዚህም ምክንያት ጭንቀትና መረበሽ ይታይበት እንደነበር ገልፃለች:: ኮምፒውተሩን (ላፕቶፑን) ሲከፍት እንኳን ስለሚጠራጠር ካሜራውን ይሸፍን ነበር ብላለች:: ከቤተሰቡም ጋር የነበረው ግንኙነት እየቀነሰ መጥቶ ብቸኝነትን ማዘውተር እንደጀመረም አስረድታለች ነው የተባለው:: ይህ የሚያያሳየው በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ “የአእምሮ ህመሙ” ከአጎቱ ሞት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ነው::
በሌላ በኩል እስካሁን የታወቀውን በአጎቱ ሞት ዙሪያ ያሉትን እውነታ ስንመለከት “ሞተው ተገኙ” ከሚል በስተቀር ብዙም የታወቀ ነገር እንደሌለ እንረዳለን:: ስለዚህ የአጎቱ ሞት ለአዕመሮ ችግር በሚዳርግ መልኩ ያስጨንቀው ከነበረ ለምን ይህንን ያህል አስጨነቀው የሚለው መመለስ አለበት:: ለአጎቱ ካለው ቅርበት የተነሳ እሳቸውን በማጣቱ ጥልቅ ሀዘን ስለተሰማው አእምሮውን ረብሾት ይሆናል ብሎ ማሰብ ስህተት ላይሆን ይችላል:: በሌላ በኩል ደግሞ ስላሟሟታቸው የሚያውቀው ወይንም የሚጠረጥረው ነገር (ምስጢር) ስላለ በዚህም የተነሳ  ለራሱም ደህንነት ስጋት ውስጥ የከተተው ነገር በመኖሩ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ውስጥ ሊገባ እንደቻለ መገመትም ተገቢ ይመስለኛል::
በእኔ አስተያየት ከመጀመሪያው ይልቅ ሁለተኛው ግምት ለእውነቱ ይቀርባል እላለሁ:: በሁለት ምክንያቶች:: በመጀመሪያ የአጎቱ ሞት ምክንያት ባለመታወቁ:: በሁለተኛ ደረጃ ልጁ አውሮፕላኑን ከማሳረፉ በፊት ከበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች  (Air Traffic controllers) ጋር ባደረገው የመልክት ልውውጥ ወቅት እንዲፈፀምለት የጠየቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው:: እነዚህም የስዊዘርላንድ መንግስት ጥገኝነት እንዲሰጠውና ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ እንደማይሰጥ ማረጋገጫ እንዲሰጠው የሚጠይቁ ነበሩ:: እንግዲህ ይህ ልጅ የአእምሮ ችግር አለበት ከተባለ ይህም የአእምሮ ችግር  ከአጎቱ ሞት ጋር የተያያዘ ነው ከተባለ አውሮፕላን መጥለፍን ምን አመጣው? ጥገኝነት መጠየቅስ ለምን አስፈለገ? እርሱ በውስጡ የያዘው ምስጢርና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተያያዘ ስጋት ከሌለበት ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋችሁ እንዳትሰጡኝ ማለትን ለምን መረጠ? እርስ በርሱ የተምታታ አንድምታ የሚሰጡት ወገኖች እነዚህን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቅባቸዋል::
ለማንኛውም ወጣቱ ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ አውሮጵላን መጥለፍን ያህል ከባድ ድርጊት ውስጥ እንዲገባ ያስገደደውን ትክክለኛውንና የመጨረሻውን ምክንያት የምናረጋግጠው ከሱ ከራሱ አንደበት ስንሰማ ብቻ ነው:: አሁን ያለበት ሀገር ደግሞ ነፃ ሆኖ ሊናገር የሚያስችለው አጋጣሚ ስለሚፈጥርለት እውነታውን የምናውቅበት ግዜ እሩቅ አይሆንም::  እስከዚያ ድረስ ግን ስለልጁ አላማና ለዚህ ድርጊት ስለገፋፉት ምክንያቶች የሚሰነዘሩ ማናቸውም መላምቶች ተቀባይነታቸው ሊለካ የሚችለው ልጁ ራሱ ከፈፀመው ድርጊትና ከአንደበቱ ከተሰማው ቃል አንፃር እንጂ ከእኛ ፍላጎት ተነስተን መሆን የለበትም:: እንደኔ እንደኔ ግን ማንም የመሰለውን የማለት መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአእምሮ በሽተኛ ነው የሚለው ግምት እስካሁን ከታወቁት ጭብጦች ጋር ይጋጫል::

ESAT Daily News Amsterdam Feb 28 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Feb 28 2014 Ethiopia | ESAT Tube

Thursday, 27 February 2014

ESAT Daily News Amsterdam Feb 27 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Feb 27 2014 Ethiopia | ESAT Tube

በባህር ዳሩ ሰልፍ ከሰባ ሺህ በላይ ሕዝብ ነበር። በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደረጋል (መግለጫ ከአንድነት)

February 27th, 2014    
የአንድነት ፓርቲ ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚሆን ሕዝብ ድምጹን ለማሰማት መዉጣቱ ገልጾ፣ ለባህር ዳር ሕዝብ ያለዉን አክብሮኢትና አድናቆት የካቲት 20 ቀን 2006 ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ።
ፓርቲ የባህር ዳሩ አይነት እንቅስቅሴ በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎችን እንደሚደረጉ ያሳወቀ ሲሆን በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሰጡና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ከባዶ ጭንቅላት ይሻላል ባዶ እግር


 ከነጻነት አድማሱ
የካሀዲ መንጋ ቃሉ የሰበረ


የሀገር ደላላ ህዝቡን ያሳፈረ


ነፃነቱን ሽጦ ለጌታው ያደረ


በፍቅረ ንዋይ ዓይኑን የታወረ


ማንታ ምላሱ ምን ብሎ ተናገረ?



እሪ በሊ ጎንደር የፋሲል መኖሪያ


እሪ በሊ ጎጃም የጀግናው በላያ


ሰምቷል ወይ ወሎ ዴሴና ወልዲያ


ሁሉም ብሄረሰብ መላ ኢትዮጵያ።


አዎ!! እውነት ነው!!


ወገን ይደፈራል ባለቤቱ ሲተኛ


ከሽ ጦር ይብሳል አንድ ውሸተኛ


ህዝቡን የካደ የቁራ መልእክተኛ


ባህል የማይገዛው ባለጌ ነውረኛ


ሕግ የማያውቅ አፋኝ መተተኛ


ታሪክ አጉዳፊ አጉል እብሪተኛ


ምን አሉ ምን አሉ ስለኛ ስለኛ?

ገና ጉድ ይታያል ከተገኘ ሰሚ


ህልናው የሸጠ እናቱን አስማሚ


ህዝብን አዋራጅ ሀገር አውዳሚ


በኢትዮጰስያ ተፈጠረ ዛሬ


ከጫካ የመጣ የዱር አውሬ።

ከደንቆሮ መንጋ የብአዴን ካድር


ለሆዱ ያደረ የወያኔ አሽከር


ከባዶ ጭንቅላት የባንዳ ንግግር


ይሻላል አማራው በባዶ እግር።

አንተ ወጣቱ አደራ ተቀባይ


የወገን መከታ አንትንኩኝ ባይ


የለውጥ አርበኛ ሽቦ አቀጣጣይ


ኮርቻለሁ ባንተ ድምፅህ ስሰማ


ብርሃን ሲፈነጥቅ ከድቅድቅ


ከዚያው ከባህር ዳር ከጎጃም


ከበላይ ዘለቀ የወረስከው አርማ።


አዎ!!


የትግልህ ቋያ በሌላም ይቀጥላል


ከዳር እስከ ዳር በሁሉም


የኢትዮጵያ ጠላት እንደጨው


ታሪክ ምስክር ነው ህዝባችን


ጨለማ


ከተማ


ያስተጋባል


ይሟሟል


ያሸንፋል።





በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ለመሸፋፈን የሚደረገው ዘበት

February 26, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በማዕድኑ ዘርፍ የሚያካሂደውን ሙስና በማደብዘዝ እና በመሸፋፈን ንጹህ መስሎ ለመታየት እና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ለማግኘት በማሰብ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት(Extractive Industries Transparency Initiative (EITI)) ለተባለው ድርጅት ዕጩ አባል ለመሆን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ይፍጨረጨራል፡፡ የገቢ ምልከታ ተቋም/Revenue Observation Institute የቦርድ ሊቀመንበር እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የቦርድ አባል የሆኑት አንቶኒ ሪቸር እንደሚሉት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2010 ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ነበር፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ (Proclamation on Charities and Societies) የሲቪክ ህዝብ ማህበራት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው እና በሂደቱም ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚከለክል ደንቃራ በመሆኑ ነው የሚል ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡ ቦርዱ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ’ በስራ ላይ እንዳይውል ኢትዮጵያ ‘እስካልሰረዘች ድረስ የዓለም አቀፉ ድርጅት አባል እንድትሆን በተጨባጭ እንደማይፈቅድ ውሳኔ አስተላልፏል’፡፡ አንድ አገር ለአባልነት ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ሲደረግበትበአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነትተነሳሽነት/EITI ታሪክ የመጀመሪያው ብቸኛው ድርጊት መሆኑ እና እንዲሁም ደግሞ ለዚህእርምጃ መሰረት ሆኖ የቀረበው በግልጽከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዘ መሆኑ ነበር፡፡The regime in Ethiopia is seeking EITI membership
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI “የመንግስታት፣ የኩባንያዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እና የዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጥምረት“ ሲሆን ይህም “በጠንካራ ሆኖም ግን ለለውጥ ክፍት የሆኑ የኩባንያዎች ክፍያ እና ከተፈጥሮ ዘይት፣ ጋስ እና ከማዕድን የሚገኙ የመንግስት ገቢዎች በሰነድነት የሚታተሙበት እና የሚከሰቱ ውስንነቶች የሚቀነሱበት የአሰራር ሂደት“ የሚተገብር ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ነው፡፡ በግልጽ ለማስቀመጥ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን ለማሳደግ በአባል አገራት የሚገኙ ኩባንያዎች እና መንግስታት በአምራች ማአድን ኢንዱስትሪዎቻቸው የሚገኙትን ገቢዎች በግልጽ ለማሳወቅ ዓላማን ያደረገ ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው፡፡ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI “የገቢን ግልጸኝነት በአካባቢ ደረጃ መስፈርት በማውጣት “ እንዲተገበር በማደረግ በስፋት ይታወቃል፡፡
በአትዮጵያ ያለው ገዥው አካል፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት አባል መሆንን ይፈልጋል፡፡ አባል ለመሆን የሚፈልገው ግን በማዕድኑ ዘርፍ በእውነተኛነት ላይ የተመሰረተ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለማስፈን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው ዓላማው በሙስና የተዘፈቀውን የማዕድን ዘርፍ ለውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ገበያ ለማቅረብ እንዲመቸው የእውነተኛነት መታወቂያ እና ለመልካም አስተዳደር እና ለጥሩ ገበያ መለመድ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ፈቃድ እና በገዥው አካል የአባልነት ጥያቄውን ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ያቀረበው ከተቋሙ የእወቅና ድጋፍ በማግኘት የወደፊት ዓለም አቀፍ የመዋለ ንዋይ አፍሳሾችን እና የገንዘብ ተቋማትን በአገሪቱ መልካም አስተዳደር እንዳለ እና ደህንነት እንዲሰማቸው ለማስመሰል ታማኝነት በጎደለው መልክ የማታለል ዘዴ በመጠቀም ገዥው አካል ከፍተኛ ለሆነ ግልጽነት እና በእርግጥም ተጠያቂነት ለማስፈን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደረገ መሆኑን እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ለማታለል ድፍረት የተሞላበት ንቀት፣ ስልታዊ የድርጊት መርሀ ግብር እና በሀሰት ላይ በተመሰረተ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት እንዳለ በማስመሰል እና በማዕድኑ ዘርፍ አስተማማኝ የሆነ ደህንነት መኖሩን እንዲጠብቁ በማድረግ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ያልጠረጠሩትን ነገር በላያቸው ላይ ለመጫን ነው፡፡
እውነታው ግን ገዥው አካል ለእራሱ ዜጎች የግል ንብረት ወይም መዋዕለ ንዋያቸውን በአገር ውስጥ ለሚፈያስሱ ባለሀብቶች ንብረት ዋስትና የሌለው እና አጠቃላይ በሆነ መልኩ ሲታይ ግን በተቃራኒው ምቹ ያልሆነ ከባቢያዊ የንግድ ስርዓት ሁኔታ ዘርግቶ የሚገኝ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ኮፋክ/COFACE የተባለው ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ባቀረበው ዘገባ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአገሮች መካከል የሚሰጥ የኢንሹራንስ ብድር እና የብድር አገልግሎት አስተዳደር ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንዲህ በማለት ድምዳሜ ሰጥቷል፣ “አስቸጋሪ የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታ በተንሰራፋበት፣ የማህበራዊ ዘርፍ መረጃ እጥረት ባለበት ሁኔታ፣ ሙስና እና የግል ዘርፉን በማስገደድ ከውድድር ውጭ ማስወጣት“ እንደ መርህ በተያዘበት ሁኔታ ልማት እንደማይታሰብ ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ “ሙስናን ማዕከል“ ያደረገ ነው፣
በኢትዮጵያ ያለው የማዕድን ዘርፍ የሙስና ማዕከል እና የተግባር መገለጫ እንዲሁም የባለስልጣኖች የሙስና ድርጊት እና የማታለል ወንጀል ማሳያ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ባቀረበው መጠነ ሰፊ ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ በሙስና ተተብትበው ከተያዙ የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል የማዕድኑ ዘርፍ አንዱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ” ውስጥ “ሰባት ዓይነት የሙስና አደጋዎችን” ነቅሶ ያወጣ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ “ሶስቱ ዋነኛ አደጋዎች” ተብለው የቀረቡት “ፈቃድ በማውጣት፤ በፈቃድ አያያዝ ላይ በሚደረጉ ስምምነቶች እና በማዕድን ገቢዎች ላይ” የሚደረገው ሙስና ነው፡፡“ ሌላው አሳሳቢው የሙስና ዓይነት “ከካሳ ክፍያዎችና ከአካባቢ ነዋሪዎች ግዴታ፤ ኮንትራክተሮችና አምራቾች ከማዕድን ካምፓኒዎች ጋር ከሚያደርጓቸው የስምምነት ውሎች፤ ከካምፓኒዎች ምርቶች ጥራት መዝቀጥ እና የማዕድን ምርቶችንና መሳሪያዎችን ከመዝረፍ“ አንጻር የሚደረጉ የሙስና ዓይነቶች ናቸው፡፡
የዓለም ባንክ በግልጽ እንዳስቀመጠው “ፈቃድ በማውጣት ሂደት ጊዜ” “ባለስልጣኖች ፈቃድ ለማውጣትና ለመስጠት፤ ፈቃድ በቶሎ አውጥቶ ለመስጠት ወይም ደግሞ ብዙ ጉዳት የማያመጡ የፈቃድ ሁኔታዎችን ለመስጠት ከማዕድን ካምፓኒዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ይወስዳሉ ወይም ጉቦ ይቀበላሉ፡፡ ሌላው ተመሳሳይ አደጋ ባለስልጣኖች ፈቃድ በሚሰጡበት ወቅት ፈቃድ ከሚሰጡት ካምፓኒ ጋር በስውር ለእራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው ስምምነት ያደርጋሉ፤ ፈቃድ ለመስጠት የመሬት ባለቤትነትን ሊያገኙ ይችላሉ፤ የተወሰነ ድርሻ በአክሲዮን መልክ ወይም ከትርፍ የተወሰነ ድርሻን ይጠይቃሉ፤ ለእራሳቸው ወይም ለጓደኞቻቸው ቅድሚያ ምዝገባ እንዲያደርጉላቸው ከፈቃድ አውጭዎች ጋር ይሞዳሞዳሉ፡፡” በፈቃድ ስምምነት አያያዝ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ሆን ብለው የማዕድን ስምምነቶችን (ለምሳሌ ያህል የአካባቢ፤ የጤና እና የደህንነት ህጎችን እንዲሁም በአካባቢው የማዕድን ካምፓኒው በኃላፊነት የመጠየቅ ደረጃና ሁኔታን ያካትታል) በስራ እንዳይውሉ ያጨናግፋሉ፡፡
በማዕድን ገቢ አሰባሰብ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ለመሬት መጠቀሚያና ለታክስ የሚያደርጓቸውን ወጭዎች ለመቀነስ ሲባል ሆን ብለው ያመረቱትን ምርት መጠንና ትርፋቸውን በማሳነስ ወጭዎችን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ገዥው አሰተዳደር ከማዕድን ካምፓኒዎች የሚገኘውን ገቢ በትክክል ለማወቅ ነጻ የሆነ የማረጋገጫ አካል የለውም፡፡ ለመሬት መጠቀሚያና የገቢ ግብር መጠን በአጠቃላይ የሚወሰነው የማዕድን ካምፓኒዎች በአመኑት የምርት መጠንና ትርፍ ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ምክንያቱም በፌዴራል፤ በክልልና በከተሞች አስተዳደር ያሉ የፈቃድ ሰጭ ባለስልጣኖች በካምፓኒዎች ስላለው ሀብት የሚገልጽ ዝርዝርና ተጨባጭ መረጃ ስለማይገኝ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የማዕድን ካምፓኒዎች ካፒታላቸውንና የስራ ማስኬጃ ወጫቸውን ከፍ ሲያደርጉ ምርቶቻቸውንና የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥና የገቢ ማጭበርበር ክስተት መኖሩ ሲረጋገጥ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች በመንግስት አካላት እርምጃ እንዳይወሰድባቸውና የሚመለከታቸው አይተው እንዳላዩ እንዲያልፏቸው ኃላፊነቱ ላላቸው ባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
እ.ኤ.አ የ2012 የዓለም ባንክ ዘገባ በማዕድን ዘርፉ እስከ አሁን በተጨባጭ በተግባር የታዩና የተመዘገቡ የሙስና ዓይነቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ ጉቦ መቀበል፤ የሀሰት መረጃ መስጠት፤ በህገወጥ መንገድ ከማዕድን ካምፓኒዎች ገንዘብ መውሰድና ነጻነታቸውን ዝቅ አድርጎ ማየት፤ እና የውስጥ ህገወጥ መረጃዎችን በመጠቀምና ነጻነት የሌላቸወን ካምፓኒዎች በማጭበርበር ለአካባቢው ነዋሪዎች የተመደበውን ካሳ መስረቅ ሲሆኑ ሰፋ ባለ መልክ በማዕድን ዘርፉ የሚካሄዱ የሙስና ዓይነቶች ናቸው፡፡ በዓለም ባንክ ተመዝግበው የሚገኙ በመጥፎ ምሳሌነታቸው በግልጽ የሚታዩ ለህሊና የሚሰቀጥጡ የሙስና ዓይነቶች የሚከተሉትን ያካትታል፣
አንድ የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት ከፍ ያለ ገንዝብ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ታላላቅ ባለስልጣኖችና የካምፓኒ ባለቤቶች ይህንን ገንዝብ በሚስጥር ይይዙና ገንዘቡ በውጭ ባንክ አካውንት ለባለስልጣኖች እንዲደርስ ይደረጋል፡፡
አንድ ባለስልጣን የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቱን የስራ ፈቃዱ በቶሎ እንዲወጣለት ከፈለገ ለለጋሽ ድርጅት በርከት ያለ ገንዘብ መስጠት እንደሚጠበቅበት ይነግረዋል፡፡ ለጋሽ ድርጅቱ ሀቀኛ መስሎ ቢታይም ለባለስልጣኖች ለግል ወይም ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው ጥቅም ከመዋል ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ ክፍያ ሊውል ይችላል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት እንዲችል ካለው አሰራር አንጻር የጤናና የደህንነት ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ባለስልጣኑ ለካምፓኒ ባለቤቱ ጉቦ ካልከፈለ በስተቀር ተጨማሪና አላስፈላጊ የጤናና የደህንነት ግዴታዎች እንደሚጭንበት ይነግረዋል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት የአካባቢ ጥበቃ ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ይህም የሚያቀርበው ዕቅድ የአካባቢውን የውኃ አቅርቦት ከመርዛማ ኬሚካሎች በአስተማማኝ ሁኔታ ላያስወግድ ይችላል፡፡ አስተማማኝ የመርዛማ ኬሚካሎች ቁጥጥር ለማድረግ ወጭው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰለዚህ የተጓደለውን የቁጥጥር ስርዓት በመከተል ካምፓኒው ብዙ ወጭ ላለማውጣትና በተጓደለው ሁኔታ ለመስራት እንዲችል የስራ ፈቃዱን ለሚሰጠው ባለስልጣን ጉቦ ይሰጣል፡፡
ባለስልጣኖች ከማዕድን ካምፓኒው ትርፍ ድርሻ እንዲኖራቸው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ካምፓኒው ባለቤት የስራ ፈቃድ በባለስልጣኑ ውሳኔ መሰረት አገኛለሁ በሚል እምነት ለባለስልጣኑ ዘመድ ከማዕድን ፕሮጀክቱ ነጻ የትርፍ ድርሻ ሊሰጠው ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች በድብቅ በእራሳቸው ለተያዙ ካምፓኒዎች የስራ ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ ሊጠየቅበት የሚችል መሬት በድብቅ ያገኛሉ፡፡
አንድ ባለስልጣን የአንድ የማዕድን ቦታ የስራ ፈቃድ ይወጣበታል የሚል ግንዛቤ ካለው ባለስልጣኑ የስራ ፈቃዱ ከመውጣቱ በፊት መሬቱን ቅድሚያ ሊያከራየው ይችላል፡፡ የስራ ፈቃዱ ከተሰጠ በኋላ ግን የመሬቱ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ ወይም ባለስልጣኗ በመሬቱ ላይ ያለውን ወይም ያላትን የመሬት ባለቤትነት መብት በመጠቀም ለመሸጥ ወይም ለካምፓኒው የስራ ፈቃድ በመስጠት ለማከራየት ይችላሉ፡፡
ካምፓኒዎች የተሰጣቸውን የስራ ፈቃድ በህገወጥ መልክ ሊሸጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ የምዝገባ ስራን ማጭበርበር ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
አንድ በመንግስት መ/ቤት መምሪያ የማዕድን ስራ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችል ባለስልጣን አንድ ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ማውጣት እንደሚፈልግ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ካለው ግንኙነት አንጻር የቢዝነሱ ሰው በዚያ ቦታ ላይ በፍጥነት የስራ ፈቃድ ማውጣት እንዲችል ሊያሳስበው ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ለቢዝነሱ ሰው የስራ ፈቃዱን ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚያም የማዕድን ካምፓኒው ከቢዝነሱ ሰው ጋር የስራ ፈቃዱን ይገዛውና የቢዝነሱ ሰው ከባለስልጣኑ ጋር ትርፍ ሊጋራ ይችላል፡፡
አንድ አሳሽ ማዕድን ያለበትን ቦታ ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቦታውም ላይ ምልክት በማድረግ ጉዳዩ ወደሚመለከተው የስራ ፈቃድ ሰጭ አካል በመቅረብ የባለቤትነት ሰርቲፊኬት ማግኘት እንዲችል ሊያመለክት ይችላል፡፡ ሙሰኛ ባለስልጣን ግን ይህንን ግኝት ተቀብሎ አስሶ ባገኘው ስም አይመዘግብም፤ ይልቁንም የቢዝነስ ጓደኛ በመፈለግ በቢዝነስ ጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡ ይኸ ሙሰኛ ባለስልጣን በመጀመሪያ አስሶ ያገኘውን ሰው ሀሰት በመንገር የማዕድኑን ሀብት ከእርሱ በፊት ሌላ እንዳገኘው ይነግረዋል፡፡
ባለስልጣኖች ዘመዶቻቸው የኮንትራት ስምምነት በመፈራረም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ህገወጥ በሆነ መልኩ ከማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ጋር እንዲፈራረሙ ያደርጋሉ፡፡ ፈቃድ ሰጭው አካል ኮንትራቱን ከመስጠት አንጻር ወይም ማህበረሰባዊ የልማት ዕቅድን ከማምጣት አኳያ በካምፓኒው ሙሉ ወጭ ብዙ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ለካምፓኒው ይነግረዋል፡፡ ለምሳሌ ካምፓኒው መንገድ፤ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል እንዲገነባ ወይም አንዲጠግን ሊገደድ ይችላል፡፡ በዚህ መሰረት የመንግስት ባለስልጣኑ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን የመሰረተ ልማት ስራዎች ኮንትራት በድብቅ ለባለስልጣኑ ዘመድ በኮንተራት እንዲሰጥ ይነገረዋል፡፡
ባለስልጣኖችና የአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መድረስ ያለባቸውን ካሳዎች ይበላሉ፡፡ የማዕድን ስራ ካምፓኒዎች ለማህበረሰቡ የሚሰጡ ካሳዎች ዋጋ ከትክክለኛው ግምት በታች ዝቅ እንዲል ለባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
የአካባቢ ኗሪ ማህበረሰብ አባላት በመሬት የስራ ፈቃዱ መሰረት በሀሰት መሬቱን እንዳገኙ ይናገራሉ፡፡ ኮንትራክተሮችና አምራቾች በተጭበረበሩ የጨረታ፣ ይዞታዎችና ችግር ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅና በማጽደቅ ይሰማራሉ፡፡
የማዕድን ካምፓኒዎች ስለማዕድኖች ዓይነትና ጥራት ወይም ደግሞ ለአጽዳቂዎች ጉቦ በመስጠት የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሙስና ይሰራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዙ ይህ ዓይነቱን ሙስና በሚመለከት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ እንደማስመሳያነት?
በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል ከማዕድኑ ዘርፍ ከሚገኘው ገቢ ጋር በተያያዘ መልኩ በሀሰት ላይ የተመሰረተ የማስመሰያ ምናባዊ የማታለል ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡ የገዥውን አካል ዋቢ በማድረግ በወጡ መረጃዎች መሰረት “የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት ከማዕድኑ ዘርፍ በአገሪቱ ውስጥ በባህላዊ የአመራረት ዘይቤ በተሰማሩ አምራቾች አማካይነት ተመርቶ ወደ ውጭ ከተላከው ምርት 419 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ አግኝቷል፡፡ ከዚሁ ወደ ውጭ ከተላከው የማዕድን ምርት በመጠን የወርቅምርት ከፍተኛውን ደረጃ በመያዝ 409.1 ሚሊዮን ዶላር የውጭምንዛሬ ያስመዘገበ ሲሆን ለጌጣጌጥ የሚውል ድንጋይ እና ታንታለም እንደየቅደም ተከተላቸው 9.3 ሚሊዮን እና 1.6 ሚሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የሁለተኛ እና የሶስተኛነት ደረጃን ይዘዋል፡፡ ይህም ገቢ የተገኘው 7,878.3 ኪ/ግ ከሚመዝን ወርቅ፣ 20,126.3 ኪ/ግ ከጌጣጌጥ ከሚውል ድንጋይ እና 32.95 ቶን የሚመዝን ደግሞ ከታንታለም የተገኘ ነው… ከፍተኛ የሆነ የአመራረት ዘይቤን በመከተል በአገሪቱ ውስጥ ወርቅ በማምረት ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ሚድሮክ/MIDROC የተባለው ብቸኛ ኩባንያ ነው፡፡“ ሌሎች ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት “በአጠቃላይ ከአገሪቱ ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት ውስጥ የማዕድን ምርት 23 በመቶ ድርሻ በመያዝ ለኢትዮጵያ ሁለተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ለመሆን በቅቷል፡፡“ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ዋናው ጉዳይ ግን የሳጥኑን መክፈቻ ቁልፍ ከያዙት ሰዎች በስተቀር በማዕድን ዘርፉ የተመረተው ምርት በትክክል ምን ያህል ገቢ እንዳስገኘ በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ ገዥው አካል ከማዕድኑ ዘርፍ የተገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነ የሚያጣራ ነጻ የሆነ ምንም ዓይነት የአሰራር መንገድ ስለሌለ ከኩባንያዎች በሚገኙ ዘገባዎች ላይ ብቻ በመመስረት መገመት እንደሚኖርበት ይናገራል፡፡ እንዴት የሚመችነገር ነው እባካችሁ! እውነታው ግን ከማዕድኑ ዘርፍ ምርት ከሚገኘው ገቢ ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ሀብቱን በብቸኝነት የተቆጣጠሩ የገዥው አካል ቡድኖች፣ ለእነዚህ ቡድኖች አቀባባይ ሆነው በማዕድን ምርት ንግዱ ስራ ላይ በግንባር የተሰማሩ ሰዎች እና “በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ” ቁጥጥር ስር ያሉ ሌሎች ድርጅቶች ናቸው፡፡ ከማዕድን ፈቃድ ሽያጭ እና በህገወጥ መንገድ ከማዕድን ምርት ዘርፉ የተገኘው ገንዘብ በተያያዘ መልኩ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና ስፋት እና ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም፡፡ ሆኖም ግን ከወርቅ ማምረቻ ቦታዎች በቅርብ ርቀት ከሚገኙ ጥርጊያ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በመቶዎች ኪሎ የሚቆጠር የወርቅ ምርት ያለምንም ፍተሻ በአውሮፕላን እየተጫነ ከአገር እንደሚወጣ አስተማማኝነት ያላቸው የዓይን እማኞች ምስክርነታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት እና ዓይን ያወጣ የማዕድን ምርት ዘረፋ በተንሰራፋበት ሁኔታ ነው ገዥው አካል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዓለም አቀፋዊ ተቋም አባል ለመሆን በመፈለግ የአባልነት ጥጣቄ እያቀረበ ያለው፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ለምንድን ነው የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅያደረገው?
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI እ.ኤ.አ በ2011 ባረቀቃቸው ህጎቹ የሲቪል ማህበረሰቡ ነጻ ሆኖ መስራት እና ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ መቻል ለዕጩነት እና ለአባልነት የመምረጫ መስፈርት የመሰረት ድነጋይ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ለአባልነት ብቁ ሆኖ ለመገኘት በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል “የሲቪል ማህበረሰቡን ተሳትፎ ሊያዉኩ የሚችሉ እንቅፋቶችን ማስወገድ እና ገዥው አካል “የሲቪል ማህበረሰቡን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እና በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የሚሳተፉ ኩባንያዎች ተወካዮችን መብት ማክበር ይኖርበታል፣“ ገዥው አካል “ለሲቪል ማህበረሰቡ እና ለኩባንያዎች በስራ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ሂደት ጊዜ ምንም ዓይነት እንቅፋቶች እንደማይኖሩ ማረጋገጥ አለበት፡፡“ እንዲሁም “ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ኩባንያዎች አስፈላጊ የሆኑ ህጎችን፣ ደንቦችን እና አስተዳደራዊ ህጎችን እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ተግባራት በተጨባጭ ለመተግበር የሚያስችሉ ማዕቀፎችን ለማመቻቸት ዋስትና መስጠት አለበት፡፡“
ከዚህም በላይ ገዥው አካል “የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን የስራ ማዕቀፎችን ከሚያጠቡ ወይም ደግሞ የህብረተሰቡን በነጻነት የመወያየት ዕድል ከሚያደናቅፉ ተግባራት መታቀብ አለበት፣“ እንዲሁም “የሲቪል ማህበረሰቡ እና የኩባንያዎች ተወካዮች በግልጽነት እና በተፈጥሮ ሀብቶች አያያዝ ጉዳዮች ላይ ነጻ ሆነው መወያየት እንዲችሉ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡“ ገዥው አካል የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች የብዙ ባለድርሻ ቡድኖች አባላት ሆነው እንዲሰሩ ማረጋገጥ አለበት፡፡ እንዲሁም “በፖሊሲ ጉዳዮችም ከመንግስት እና/ወይም ከኩባንያዎች ነጻ ሆነው መስራት አለባቸው፣“ እናም “ያለምንም መሰናክል ወይም ጭቆና ከሚፈልጓቸው ቡድኖችም ጋር አብረው ነጻ ሆነው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI በግልጽ የሚፈልገው “የሲቪል ማህበረሰቡ ቡድኖች፣ ኩባንያዎች እና ወኪሎቻቸው ስለ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ሀሳቦቻቸውን ያለምንም ስጋት፣ ግዳጅ እና የበቀል ስሜት ሳይኖርበት በነጻነት ሀሳቦቻቸውን መግለጽ እንዲችሉ“ ለማድረግ እና “በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ላይ ተሳትፎ ያላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች በEITI በሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ግልጽ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሙሉ ነጻነት ማግኘት አለባቸው፡፡“ በማለት ህጉን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በኢትዮጵያ ባለው ገዥው አካል ከእንቅስቃሴ ውጭ ተደርገዋል፣
እ.ኤ.አ የወጣው የ2009 የገዥው አካል የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ህግ አዋጅ ቁጥር 621/2009/Charities and Societies Proclamation No. 621/2009 በኢትዮጵያ ያሉ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለማጥፋት አዋጁን መሳሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 ረቂቅ አዋጁን በጥሞና በማየት “የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ረቂቅ አዋጁን መመርመር“ በሚል ርዕስ ረዥም ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትንታኔዬ ላይ አዋጁ ጠቀሜታ የሌለው መሆኑን በማመን ይህ አዋጅ የማይጠቅም በመሆኑ ለምን መወገድ እንዳለበት 10 አሳማኝ ምክንያቶችን ዘርዝሬ አቅርቢያለሁ፡፡ እንዲህ በማለትም የክርክር ጭብጤን አቅርቢያለሁ፡፡ የአዋጁ ዋና ተልዕኮ ገዥው አካል የህግ ማፈኛ አድርጎ በማቅረብ ያነጣጠረው የሲቪል ማህበራት ተቋማትን በመገደብ እና ህልውናቸውን በማጥፋት ተቋማቱ የዴሞክራሲያዊ ተግባራትን በማሳለጥ ስጋት ይፈጥሩብኛል በሚል ልሳናቸውን አስቀድሞ ለመዝጋት እና ከሚጠብቀው ፍርሀት ለመገላገል የታለመ ነው ብዬ ነበር፡፡ አዋጁ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን በዘፈቀደ እና ምንም ዓይነት የህግ ምርመራ ሳያደርግ መቆጣጠር የሚያስችል የዘፈቀደ እና ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል የተለጠጠ እና ያልተገደበ ስልጣን እንደ ፍርድ ቤት ዳኛ መርምሮ ሳይሆን እንደፈለገው እንዲያደርግ ለበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት ኃላፊ ስጥቷል፡፡ አዋጁ ሳይፈለግ የመጣ በበጎ አድራጎት ደርጅቶች እና ማህበራት የውስጥ ጉዳዮች ላይ በኃይል የተጣለ፣ ለጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ትኩረት በመስጠት በተቋሞቹ የውስጥ ጣልቃገብነት ላይ እጁን ያስገባ እና ምክንያታዊ ያልሆኑ እና በጣም አስቸጋሪ የሆኑ እንዲሁም እራሱ ገዥው አካል የማይተገብራቸውን የገንዘብ ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ከሚታሰበው በላይ የተንዛዙ መስፈርቶችን በማቅረብ ድርጅቶቹ እንዳይሰሩ ሽባ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ አዋጁ ለመቅጣት የወጣ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አባል መሆን እና ተሳትፎ ማድረግም እንዳይቻል ለማስፈራሪያነት የወጣ ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ጭብጤም ላነሳው የምፈልገው ጉዳይ አዋጁ ህገመንግስታዊ ያልሆነ፣ የማይመች እና የሚቆጠቁጥ እንዲሁም አድሏዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch የአዋጁን መውጣት ተከትሎ አዋጁ የማያሰራ መሆኑን ለመግለጽ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፣ “የዚህ አዋጅ የታሰበው ውጤት እና በተግባር እየታየ ያለው ተጨባጩ እውነታ እንደሚያሳየው ማንኛውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መንግስት ሳያጸድቀው እና ሳይፈቅድ ምንም ዓይነት ስራ መስራት እንደማይችል በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡“ በተደጋጋሚ እንደምለው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላለው ገዥው አካል ስለህገመንግስት፣ የህግ የበላይነት እና ስለተጠያቂነት ማስተማር ማለት መስማት እና መናገር ለተሳናቸው ዱዳዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሱ እንደመስበክ ወይም ደግሞ በጥቁር የባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡
እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2010 የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት ጸሐፊ ማሪያ ኦቴሮ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅን አስመልክቶ ያላቸውን ስጋት በቅርቡ ላረፉት ለአቶ መለስ ዜናዊ እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር፣ “ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰቡን ሚና የሚጎዳ ነው“ ብለው ነበር፡፡ አቶ መለስ ግን የሴትዮዋን ስጋት ወደ ጎን ገሸሽ አደረጉት፡፡ ሆኖም ግን አዋጁ በኢትዮጵያ ያሉትን የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ተቋማትን ወዲያውኑ ማክሰም ጀመረ፡፡ እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ “እ.ኤ.አ በ2010 መጀመሪያ አካባቢ ብዛታቸው 4,600 የነበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብዙዎቹ እንዲከስሙ ተደርገው በመንገዳገድ ላይ የሚገኙ 1,400 ብቻ ሆነው ተገኙ፡፡ ከመክስም የተረፉት ወደ 30 በመቶ ብቻ መሆናቸው ሲታይ ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ያመላክታል፡፡ መረጃዎቼ እንደሚያስረዱት በህይወት ከተረፉት ድርጅቶች መካከልም የአብዛኞቹ ድርጅቶች የሰው ኃይል በ90 በመቶ ወይም በበለጠ ቅናሽ አሳዬ፡፡“ በግልጽ ለማስቀመጥ አዋጁ በኢትዮጵያ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ከስራ ውጭ አድርጓል! በተመሳሳይ ወር ገዥው አካል ቀደም ሲል የተቋቋሙትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን የእነዚህን ሁለት ጠንካራ ተቋማት አቅማቸውን ለማሽመድመድ በማሰብ ዓላማቸው እና የሚፈጽሟቸው ተግባራት ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ወንጅሎ የባንክ ሂሳቦቻቸውን በመዝጋት ንብረቶቻቸውን አገደ፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 ገዥው አካል አስር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን/NGOs ከአዋጁ በተጻራሪ መንገድ ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው በሚል ሰበብ መዝጋቱን እና ሌሎች በደርዝን የሚቆጠሩት ደግሞ የማይገባ ባህሪ በማሳየት ላይ ናቸው ያላቸውን ተቋማት እውቅና እንደሚሰርዝ በመዛት አወጀ፡፡ ገዥው አካል በተጨማሪም የሌሎች 17 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳይ በመጣራት ላይ ያለ መሆኑን ተናገረ፡፡ ገዥው አካል እርምጃውን 400 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከአዋጁ በተጻራሪ እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ሰበብ ከሰጠ በኋላ በቀጣይ አስፈላጊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በማስረገጥ ዝቷል፡፡ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2012 ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን/Heinrich Boll Foundation የተባለ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰራ የጀርመን አገር መንግሰታዊ ያልሆነ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ንብረቱን ሸክፎ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ የተጣሉትን እገዳዎች በመቃወም ከሀገር ለቅቆ ወጣ፡፡
እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2013 ገዥው አካል በሶስት መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ማለትም አንድ ኢውሮ/ One Euro፣ የእስላም ባህላዊ እና የምርምር ማዕከል/the Islmaic Cultural and Research Center፣ እና የጎሄ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ሴቶች የልማት ድርጅት/the Gohe Child, Youth and Women Development Organization የተባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን “ህገወጥ የኃይማኖት እንቅስቃሴ” ማድረግ የሚል ክስ በማቅረብ ስራቸውን በማቆም ከሀገር እንዲለቅቁ አድርጓል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2013 “በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/US Agency for International Development የገንዘብ ድጋፍ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት 29 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ 27ቱ ከአዋጁ ህግ በተጻራሪ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ብሎ ፈርጇቸዋል፡፡“ እ.ኤ አ. በ2013 ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አዋጁን በማስመልከት የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣ “የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በዓለም ላይ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ከወጡ ጨቋኝ ህጎች ውስጥ አንዱ ነው… እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰቡ የእንቅስቃሴ ምህዳር፣ የፕሬስ ነጻነት፣ እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የመግለጽ መብት እየጠበበ መጥቷል፣“ በማለት ዘገባውን ቋጭቷል፡፡
እ.ኤ.አ የ2014 የቤርቴልስማን የሽግግር አመላካች መለኪያ/Bertelsmann Transformation Index የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣ “በጨቋኝ ህጎች ምክንያት የብዙሀን መገናኛ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ተዘግቷል፣ የሠራተኛ እና የሙያ ማህበራት መንግስት ቀንብቦ ባስቀመጠው ማዕቀፍ ውስጥ መግባት ወይም ደግሞ እንደ ቀድሞው የመምህራን ማህበር መክሰም፣“ የሚል ሆኗል፡፡ የሚያስገርመው እውነታ ግን በአሁኑ ጊዜ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIየሚገኙት የሲቪል ማህበረሰብባለድርሻ አካላት ማለትም ግሎባል ዊትነስ/Global Witness፣ ኦፕን ሶሳይቲ ረቨኑ ዎችኢንስቲትዩት/Open Society Revenue Watch፣ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽል/Transparecny International፣ ከብዙጥቂቶቹ ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያእንዲንቀሳቀሱ ቢፈልጉ አይፈቀድላቸውም! እንዲህ ሆኖ እያለም ገዥው አካል በሚያስገርምቀልድ ነገር አቀራረብ እና እራሱን በሀሰት ጀቡኖየሞራል ስብዕና ያለው በማስመሰል ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር ለመገናኘት እና የሲቪልህብረተሰብ ተቋማት በነጻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉበተግባር ያለውን ቁርጠኝነት በአስመሳይነት ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅየሚያደርገው ሽርጉድ የማለቱ ጉዳይ ነው፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ስነስርዓቶች ላይ መቀለድ፣ በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካልየማጭበርበር ድርጊት መቆም አለበት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ላይ የጀመረው ማጭበርበር እና የዕጩ አባልነት ማመልከቻ ሰነድ ማቅረብ በተቋሙ ስነርዓት ላይ እያደረገ ያለውን ቀልድ ያመላክታል፡፡ ገዥው አካል የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዋና ዋና መርሆዎች እና ለሲቪል ማህበረሰብ መብቶች ጥበቃ በግልጽ የተቀመጡትን መስፈርቶች በሚገባ እያወቀ በዓይነ ደረቅነት የተቋሙ አባል ልሁን ብሎ የአባልነት ጥያቄ ማቅረቡ በእውነቱ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ የዕጩ አባልነት ማመልከቻው ለምን ጉዳይ እንደቀረበ በመጀመሪያ ሊመረመር ይገባል… የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን አባላት እና የእራሱን የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ክብር እና የድርጀቶቹን መርሆዎች የሚጥስ እና የሚያዋርድ ግልጽ ዘለፋ እና እንዲሁም ድርጅቶቹ ከአስርት ዓመታት ባላይ የሙስና ገመድ በሚገመድባቸው ሙሰኛ አገሮች ላይ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማምጣት አበርትተው ሲሰሩ በቆዩ ድርጅቶች ላይ ማፌዝ ነው፡:
የገዥው አካል የንቀት ዘለፋ መርሀግብር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ማህበረሰብ ለመታየት አለመቻል እና የተቋሙን የቦርድ አባላት ለማጭበርበር፣ ለማታለል እና በቦርዱ ዓይን ላይ አፍዝዝ አደንግዝ ለመጣል መሞከር የዱሮ አባባልን ስለተኩላ እና የበግ ለምድ ሁኔታ በተለይም ስለኢትዮጵያ ተኩላ መሰሪነት በበጎች መካከል ገብቶ ጸሎት ላድርስ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ገዥው አካል እውነተኛ ባህሪውን ማለትም ተኩላዊ፣ ገዳይ፣ ስግብግብ፣ ለሙስና ክፍት የሆነ፣ ሙሰኛ፣ ትርፍ አጋባሽ እና በማንኛውም ሞራላዊ ብቃቱ የበከተ መሆኑን ለዓለም ህዝብ በማሳወቅ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዕጩ አባል ለመሆን ማመልከቻ ለማስገባት ይፈልጋል፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ያሉት ሁሉም ሀሳቦች ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ማስፈን ናቸው፡፡ ገዥው አካል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያሉትን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ የማቋረጡን ኃላፊነት ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆነ ብቸኛ ዓላማው ግልጽነት እና ተጠያቂነት ከሆነ ድርጅት ጋር በእርግጠኝነት አባል ለመሆን ግምት ሊኖረው የሚችለው በምን ዓይነት መስፈርት ነው? የቀበሮ ባህታዊ በበጎቹ መንጋ መካከል ጸሎት ማድረስ ይችላልን? የትኛው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አገር ነው ከእንደዚህ ያለ የዘቀጠ ዕጩ አባል ጋር አብሮ መወያየት የሚሻው?
የገዥው አካል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዕጩ አባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት እራሱገዥው አካልበአሁኑ ጊዜ ያለውን አፋኝ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ በመሻር በምትኩ ሲቪል የሆነ የሲቪል ማህበረሰብህግ፣ ግብረገብነት ያለውእና የሰለጠነ ህግ በማውጣት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI- ኢትዮጵያ የተቋማዊግልጽነት እና እውነተኛ ጽኑአቋም/Ethiopia Institutional Transparency and Integrityንን ማስፈን ይጠበቅበታል ግዳጅም አለበት፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ክህደት በተሞላበት ስብዕና ለማታለል የመሞከር ጨዋታ እና ከዕውነተኛ ስብዕናው ውጭ በሆነ መልኩ ተገቢነት የሌለው ዓለም አቀፋዊ ክብር ለማግኘት የሚደረገው ሚስጥራዊ ሸፍጥ መጋለጥ እና መቆም አለበት!

በማተብዋ ልዳኝ – ወድቃ የተነሳችው

February 27, 2014
ከስንሻው ተገኘ
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።The Green, Yellow and Red Ethiopian National Fla
“ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ…
አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ (ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት ነበር። የሁሉም አገር – ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት።
ዓይናችሁን ጨፍኑና ጊዜን አጣጥፋችሁ ወደዚያ ዘመን (1952-53) ብረሩልኝ። መጀመርያ ስለዚህ ጉዳይ ዴቪድ ሜሬዲት The first dance of freedom ን መጽሐፍ አነበብሁና (በ1985) ወዲያው እጅግ ወዳጄ ለነበሩት ለልጅ ሚካኤል እምሩ አነሳሁባቸው። በወቅቱ በእንግሊዝ አገር ስለነበሩ በግል በትኩረት የሚያውቁት መሆናቸውን አረጋገጡልኝ። ከላይ ያቀረብሁት ዘገባም የማርቲን ሜሬዲትና የልጅ ሚካኤል እምሩ ጭምቅ ሪፖርት ነው። (ልጅ ሚካኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄዱ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።)
የወቅቱ ተራማጅ ሁሉ ይህንን በጽሞና ሲከታተል ኋይት ሖል (የእንግሊዝ መንግሥት) በዚያው ሰሞን (1953) በኢትዮጵያና አንድነትዋ ላይ ትልቅ ሴራ ሲያቀጣጥል ነበር። ሊቆራርጠን። አርነስት ቤቪን የተባለው የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶማሊያ ነፃ ስትሆን የኢትዮጵያን ኦጋዴን፣ ሪዘርቭድ ኤርያና – ሐውድ እንዲሁም ጅቡቲንና የኬንያን ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት አጠቃልላ ታላቅዋን ሶማሊያ ስትመሠርት በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ከአለውሀ ባሻገር ያለው መሬት በሙሉ (ማለትም ትግራይና ኤርትራ ተዋህደው ትግራይ ትግርኝ የሚባል አገር ለመፍጠር ሽርጉድ ይዘው ነበር።) lyndon larouche የተባለውና በመደበኛው አስተሳሰብ አክራሪና የተወናበደ የፖለቲካ ነውጠኛ የአገሩን ፖለቲካ ጨረሰና ዛሬ በመላው ዓለም እየደረሰ ያለው ችግር እንግሊዝ ዘርታ ያበቀለችው አድርጐ ነው የሚያቀርበው። ይኽ አይጠረጠርም። በበኩሌ እንደማውቀው እንግሊዙ አርነስት ቤቪን የጀመረውን አይኤም ሌዊስ ካልፈጸምሁት ብሎ እነ በረከት ሀብተ ሥላሴን፣ እነ መለስ ዜናዊን ይዞ ለዓመታት ተንደፋድፎአል። (መለስ በዜግነት ሶማሊያዊ ነበር)- በነገራችን ላይ እነ በረከት ሀብተሥላሴ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ ተወልደው ያደጉባት፣ ተምረው የተሾሙባት ኢትዮጵያ፥ ዓለማቸውን ያዩባት ውብ አዲስ አበባ- ወደ ኢምንትነት እንድትመለስ ሲፍጨረጨሩ እንደ ራስ ተፈሪ ያሉ ሕዝቦች “ቤታችን መግቢያችን (ራስታ የምንላቸው)” በማለት ወደዚያች አገር መጉረፍ ይዘው ነበር።
ተመስገን ደሳለኝ ወደ ጐንደር ሄዶ ነበር አሉ። ባዶ እጁን አልተመለሰም። ወያኔ ያነወራት፣ እንደ ተስፋዬ ሐቢሶ ያሉ (በተቆላበት የሚያፈሉ) ሰነፎች የተሳለቁባት፣ በመንፈሳዊና ሕዝባዊ ክብርዋ መለስ ያሾፈባት፣….ወያኔዎች በባዶ እግራቸው የረጋገጡአትና የኮሾሮ (የአምባሻ) መያዣ ያደረጉአት….በእኔ ዕድሜ ጅማሬ ላይ “ወድቃ የተነሳችው” እየተባለች ስትጠቀስ የቆየችው ሰንደቅ ዓላማ በጐንደር ምንኛ ታላቁን ክብርዋን ይዛ – እንዳለችና እንደምትኖር የምሥራቹን ነግሮናል። ብሥራት ነውና ምሥር ብላ! ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ይኸ ወጣት ጋዜጠኛ ነው።
ኢጣሊያ የኤርትራን ደጋማ አውራጃዎች ለመያዝ የቻለችው በ1889ዓ.ም እንደ አ.አ ነው። እዚህ ላይ የንጉሠ ነገሥቱን (አጤ ዮሐንስ) አጐት ራስ ደበብንና በኋላ ጊዜ የራስ ሥዩምን ሴት ልጅ ያገቡትን ደጃዝማች ገብረሥላሴን ማውገዝ ወይስ ማወደስ ይገባ እንደሆነ አላወቅንም እንጂ በእነሱ ድጋፍና መሪነት ነው ኤርትራ የተያዘችው። ዛሬ አኪሩ ዞሮ ባንዳ የሚወደስበትና የሚቀደስበት፣ ወደል ወደል መጽሐፍም በውዳሴ መልክ የሚቀርብበት በመሆኑ ነው ግራ የተጋባነው። አዎን ዓላማዬ በማንም ዜጋ ላይ የፍትሕ ድንጊያ ለመወርወር አይደለም። የእግዜሩን መንገድ ካወቅነው ጸሎታችን “ማረን” እንጂ “አፈራርደን” መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያን የሚታደጋት የራስዋ የኢትዮጵያ ልጅ መሆን እንደሚገባው ስንነጋገርና ስንስማማ ከቆየን በኋላ ሁሉም ነገር የተለዋወጠ ሆኖአል። ኢትዮጵያውያን አገራቸውንም ራሳቸውንም ማዳን አቅቶአቸው በአገሪቱ የሚጫወቱት ወገኖች የተነሱለትን አጥፊ ዓላማ ለመፈጸም አንዳች እንቅፋት አልገጠማቸውም። በተናጠል መስዋዕትነት የሚከፍሉ ግለሰብ የፖለቲካ ተዋናያውያንና ጋዜጠኞች ደግሞ የሚሞቱለትን ሕዝብ ሊቀሰቅሱ አልቻሉም። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያሉአት ልጆች እነዚህ ብቻ ናቸውን? እስከማለት የደረሱ አሉ። “የኢትዮጵያ ልጆች በደማቸውም በአጥንታቸውም ኢትዮጵያን ከእልቂት ለማዳን ካልቻሉ ወዴት ይኬዳል? ወደ ማን ይጮኻል?” ነቢዩ ዳዊት (ልበ አምላክ የሚባለው) ለዚህ አምላክ ራሱ በጆሮው የነገረው ቁም ነገር ነበር ይላሉ መጽሐፉን የሚተረጉሙ ሰዎች። “በልጆችዋ መተማመን ያቃታት፣ ልጆችዋ በግፈኞችና በጨቋኞች ያለቁባት ኢትዮጵያ ናት፤ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው” ይሉናል። ተስፋ ከመቁረጥ የመጣ አሳብ አይደለም። የአምላኩንም ሚና እንዳንረሳ ለማሳሰብ ነው። ውዳሴ ማርያምም ባይሆን ጥቂት እግዚኦታ!
እንደ ዛሬዋ ጐንደር ሁሉ ጣልያን ኤርትራን ከያዘ በኋላ ለስድሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ነፃነት ምልክትና የክብርዋ ዘላለማዊ መግለጫ የሆነችው አረንጓዴ፣ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ቢዘን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ ስትውለበለብ ቆይታለች። እግዚአብሔር በቤቱ (ቤተክርስቲያኑ) ላይ ያዋላት ለዚህ ሕዝብ መልእክት ኖሮት ይሆናል በማለት የገዳሙ አበምኔት በ1980 ገልጠውልኛል። በዚያን ዘመን ኤርትራ በጣልያን ሥር ብትወድቅም በየበዓላቱ ሕዝቡ ይዞት የሚወጣው ሰንደቅ- አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። አንድ ኤርትራዊ ሲሞት የአስክሬኑ ሳጥን በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃል። ሠርጐች ግርማማ የሚሆኑት በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ሲንቆጠቆጡ ነው። አብያተ ክርስቲያናት ይኽ ሰንደቅ ዓላማ ተለይቶአቸው አያውቅም። ለብዙ ዓመታት ወደ ኤርትራ ስመላለስ የኖርሁ፣ ሕዝቡን የማውቅና የማከብር ስለነበርሁ ዛሬ ይኽ ወገኔ ከዚያች ከታቦት እኩል ከሚያያትና የሕልውናው ተስፋ ከነበረችው ሰንደቅ ዓላማ ሲለይ ምን ተሰማው? እያልሁ ራሴን እጠይቃለሁ። ወይስ አዲሱ የኤርትራ ትውልድ ይኽንን ቁም ነገር አያውቀውም ነበር? እዚህ ባለሁበት አገር እንደኔው በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን አረጋውያን አውቃለሁ። ለሁሉም እንደ ቀልድ “አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ የሚለመድ ነው?” እላቸዋለሁ። በሻዕቢያ ውስጥ ከአሥርና ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ መቆየታቸውን የሚነግሩኝ ብዙ ጐበዞችን በየቀኑ አገኛቸዋለሁ። ሁለቱ በአንድ ቀን የአሜሪካ ዜግነት እንዳገኙ ሲነግሩኝ እንደ ቀልድ አድርጌ “አሜሪካዊ ለመሆን ነው ሰላሳ ዓመት የወጋችሁኝ?” እላቸዋለሁ።
ኤርትራውያኑ ራሳቸው በአጸፋው “እናንተስ ሰንደቅ ዓላማውን መቸ አስከበራችሁና ነው እኛን የምታሽሟጥጡን?” ሊሉን ይችላሉ። እግዜር ይመስገን የወያኔ ሕግ በማይሰራበት በዋሽንግተን፣ በለንደን፣ በጄኔቫ…በስዊድን…የምናምንባት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደ ልብ ትውለበለባለች። ስለዚህ ለኤርትራውያን ወገኖቻችንም “የተዋችኋትን ሰንደቅ ዓላማ በምትመለሱበት ጊዜም በዚያው ሞገስ ታገኝዋታላችሁ” ለማለት ይቻላል። (የኢትዮጵያ ሕግ በማይሰራባቸው በስዊድን ወዘተ ስል እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ ትዝ ትለኛለች። ለካንስ ስቶክሐልም ላይ የተናገሩት አዲስ አበባ ላይ ያስቀጣል?)
ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያከብር የኖረው የኤርትራ ሕዝብ ነበር ስል ሌላው ሕዝብ ደንታ እንዳልነበረው መግለጤ አይደለም። ግመሎቻችን፣ በጐቻችን፣ የጋማ ከብቶቻችን፣ የቤትና የዱር እንስሶቻችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የክብር ዓርማ ያውቁታል እያሉ የሚያወጉአችሁ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ብዙ ናቸው። የአውሳው ርእሰ መኳንንት ቢተወደድ አሊሚራሕ አንፍሬ በአንድ ወቅት “እንኳን አፋሩ ሕዝባችን ግመሎቻችንም ሰንደቅ ዓላማችንን ያውቁታል” ማለታቸው ይጠቀሳል። አጋጣሚ ነገር ላንሳና ኮማንደር ለማ ጉተማ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የመሥሪያ ቤቴን ቅርንጫፍ ሥራ ለማስተባበር ወደዚያ እመላለስ ነበር። ሁለት ጊዜ ያህል የኢሳውን ባላባትና ሱልጣን ደጃዝማች ዑጋዝ ሐሰንን ተዋውቄአቸው ነበር። “ትልቁ ልጄን ትመስለኛለህ” ሲሉኝ ልዩ ፍቅር አደረብኝ። ታዲያ በ1983 አካባቢ ቢትወደድ አሊ ሚራሕ የተናገሩትን ቃል በቃል ደጃዝማች (ዑጋዝ) ሐሰን ሲናገሩት ሰምቻቸዋለሁ። ማጋነን ባይመስል ግመሎቹ ቀጥ ብለው እንደሚቆሙ ይናገራሉ። ጐበዝ! “ግመሎቻችን ለኢትዮጵያ ከእኛ የበለጠ ታማኝ ናቸው” ብል በድፍረት ትወስዱብኝ ይሆን? ግመሎቻችን ጭምር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውቁታል! እነመለስ ከዚያች ቅርጽ የለሽ እንስሳ ማነሳቸው ከተሰማችሁ አብሬአችሁ ልከሰስ እችላለሁ።
ፋሺስቶች ባላደረጉት ድፍረትና ብልግና በቀለም እኛን ይመስል የነበረው መለስ የሕገ መንግሥት ጉባዔ ሲመራ ያቺን ሰንደቅ ዓላማ እንዴት እንዳብጠለጠለ ታስታውሳላችሁ። እዚያ ጉባዔ ውስጥ በጀግንነትና በታላቅ ወኔ ይቺን ሰንደቅ ዓላማ ያወድሱ፣ የቆሙላትና ስድቡን ሁሉ የተሸከሙላት ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ (ነፍሰ ሄር) ብቻ ነበሩ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ መንጋ ወሮበሎች ፋሺስቶች ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ በመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያሰሙ ያሰማሩባቸውን ሥራ ፈቶችና ማጅራት መችዎችን አስታውሶኝ ነበር። ይችም አገር ዛሬ (በ21ኛው ክፍለ ዘመን) በዋልጌዎች፣ በጫካ አደጐች፣ በቀማኞች…እጅ እንደገባች ሁላችንም ተከሰተልን። ያን ጊዜ ከመታኝ ብራቅ እስካሁን አላገገምኩም።
እኛ ኢትዮጵያውያን – ከእኛም በፊት የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ትውልዶች- በነፃነት ተጸንሰን፣ በነፃነት ተወልደን በነፃነትም ተጠልለን ኖረናል። የሰውን ልጆች እኩልነት የምትመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝባችንን የታሪክ ቅሬቶች፣ ሐውልቶችና የነፃነት ምልክቶች–የክብርና የማዕረግ ሀብቶቻችንን ስንንከባከብ ኖረናል። አገሪቱ ትኖር ዘንድ በሰንደቅ ዓላማቸው ሥር ተንበርክከው የፈጸሙትን መሐላ ያከበሩትን ጀግኖች በፈንታችን አክብረናቸዋል። በእስዋ ተመርተን ወደ ሞት አደባባዮች ነጉደናል። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ከሁለት መቶ ሺህ ከማያንስ ሠራዊትና መሪዎቻቸው ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አድዋ ዘምታ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ድል የሆነውን ግዳይ ተወጥታለች። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ እኛ ባለቤትዋ ሆንን እንጂ የዓላም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ አለኝታ ነበረች። ያስረዳሁ ይመስለኛል።
የዚያድ በሬ ወራሪዎች ያሳደዱአት አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የክብርና የአንድነት ምልክታችን በጐዴ፣ በካራማራ፣ በጅጅጋ በገላዲ…እንደገና ስትውለበለብ አይቻለሁ። በወረራው ወቅት የሶማሊያ እብሪተኛ ኅይል ባደረሰብን ጥቃት የተቃጠለና ያለቀሰ አንጀታችን ሰንደቅ ዓላማችን ዳግመኛ ስትውለበለብ እንደገና ማልቀሳችን ትዝ ይለኛል። አልፎ አልፎ እንደዚያ ያለ ጥቃት አይጠላም። ለነፃነትህና ለአንድነትህ ዘወትር እንደ ቆቅ ተጠንቅቀህ መቆምና መሞት ግዴታ መሆኑን እንዳትረሳ ያስገነዝብሃል።
የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ሲነሣ – አሁንም ተመስገን ደሳለኝ አነሳብኝና- ከውስጤ አንድ እሳተ ጐመራ መሳይ ነገር ሊፈነዳ ይደርሳል። ትዝታዎች አሉኝና። በኤርትራ በረሃዎች፣ ቅጥልጥል የሆኑ የመስሐሊት ሸንተረሮች፣ በሰሎሞና፣ በሸኢብ…ከኢትዮጵያ የአንድነት ሠራዊት ጋር የዘመቱት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰንደቅ ዓላማዎችን ዛሬ ዓይኔን ጨፍኜ አያቸዋለሁ። እዚያው ከሰንደቅ ዓላማው አጠገብ ክንዳቸውን እየተንተራሱ እየጣሉ የወደቁትን፣ በኋላም ነጭ የሰላም ዓርማ እያውለበለቡ እንኳ በፈሪዎች (ካወርድ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ጠንካራ መልእክት አለው) የተረሸኑት ኅልቁ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ። የብዘዎቹን አዛዦች አውቃቸዋለሁ። ለወረራ የተሰማራ ኅይል የለንም። ይልቁንም የኤርትራን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ፣ እያስጠበቀም ለመሞት በሰንደቅ ዓላማው “ምሎ” የተመመ ነበር። ተሳስተን ነበር ያለቅነው? ተሳስተን ነበር እንደወጣን የቀረነው – ሬሳችን የአራዊት ሲሣይ – የሆነው- ቀባሪ ያጣው….? የኤርትራ ሕዝብ ምነው አስቀድሞ ቢነግረን ኖሮ! በአርማጌዶን እንድንገናኝ ቀጠሮ መያዝ እንችላለን።
ከጥንት ጀምሮ- ለእኔ ጥንት ከሰባ ዓመት የማይበልጠው ነው- ከዚች ሰንደቅ ዓላማ ጋር የሚያስተሳስር ታሪክ አለኝ። የራሴ ትንሽ ታሪክ! ትንሽም ትዝታ። ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ውርስ-አረፍ ልዑልአየሁ የፋሺስቶችን እርግጫና ጡጫ ታስታውሳለች። በዚህ የተነሣ ዘወትር የአገር ልብስዋ ጥለት በሙሉ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። ይኸ ብቻ አይደለም። በአሥራ አራት ዓመቴ ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ከ17 ዓመት በፊት ወደ ስደቱ ዓለም እስክዛወር ድረስ በየዓመቱ ጋቢ ፈትላ ትልክልኛለች። ሌሎች ዘመዶቼ ጋቢ አስለምደውኛል። የወይዘሮ ውርሰአረፍ ጋቢ ግን ሁልጊዜ በአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ጥለት የደመቀ ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት (በሞት ያረፈችበት ዘመን) የመጨረሻውን ጋቢ ልካልኛለች። ታዲያ ይኽንን ልማዴን ታውቅ የነበረችው ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ይታይሽ ልዑልአየሁ “እቴቴን (ሟች እህታችንን) እንድታስባት ብዬ በእስዋ ምትክ ጋቢ ልኬልሃለሁ” ብላ ወደዚህ በመጣ ሰው አደራዋን ተወጣችው። አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ። ይቺኛይቱ እህቴም ወደ ታላቅዋ ዘንድ ሄደች። አላውቅም፥ ይገናኙ አይገናኙ። ለእኔ ግን ሰንደቅ ዓላማዬ ናፍቆቴ ሆኖአል። ተከናንቤው የምተኛው ጋቢ ባላጣም። (በነገራችን ላይ ውድ ወዳጄ ጐሹ ሞገስ በዚህ ረገድ ረስቶኝ አያውቅም።)
የኢትዮጵያ ድምፅ፣ በኋላ ደግሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ከበደ አኒሳ እንደ እናቴ ልጅ የምቆጥረው ነው። በንጉሡ ዘመን በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ አራት ሰዓት ላይ ይመጣና “ና ቡና ጠጥተን እንመለስ” ይልና ይዞኝ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በኩል ይነዳል። ልክ ቤተ መንግሥቱ አጠገብ ስንደርስ እኔም እሱም አንገታችንን አውጥተን ግቢውን እንቃኛለን። ሁለት የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ የብረት ምሰሶዎች አሉ። አንደኛው አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበት ነው። ሁለተኛው (አጠር ያለው) ደግሞ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ዓርማ መሐል አንበሳ አለው። ያ የጃንሆይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን እሳቸው በከተማው ከሌሉ አይውለበለብም። የንጉሠ ነገሥቱ በከተማው መኖር አለመኖር ምልክት ያ ነበር። ስለዚህ ትንታጉ ጋዜጠኛ ከበደ አኒሣ “ዛሬ ጀንሆይ በአዲስ አበባ ስለሌሉ መንግሥት በሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” ይልና ወደ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ሶደሬ ወዘተ እንከንፋለን። ብቻ በየሳምንቱ ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሰበብ የምናደርገው የጃንሆይን ሰንደቅ ዓላማ አለመውለብለብ ይሆንና “መንግስት ከሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” እያልን እብስ ማለት እንደ ባሕል ተያዘ። በእኛ ዘመን ቡድናችን (የእግር ኳሱ-አለዚያም ጊዮርጊስ) ቢያሸንፍም በደስታ፣ ቢሸነፍም በንዴት በቢራው ማዝገም የተለመደ ነበር። ስትናደድም ትጠጣለህ፣ ሲከፋህም ትጠጣለህ።
ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረች እነ ማርከስ ጋርቪ ሦስት ሺህ ጥቁር ወታደሮች መልምለው በክተት ተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። አጤ ኅይለሥላሴ የእንግሊዝን ጦር እየመሩ በመሄዳቸው ራስ ተፈሪያውያኑ ማርከስ ጋርቪና ራስ መኰንን (ራስታ) ጃንሆይን ተቀይመው እንደነበረ በወቅቱ ሲወራ ነበር። በጽሑፍም ቆይቶናል። ይቺን አገር- ይህን ሰንደቅ ዓላማዋን- ይህን ጐላ ያለ ታሪክዋን- ወደፊትም አውስተን የማንጨርሰውን- ትዝታዋን እነዚህ ሳንቀጣቸው ያደጉ፣ በማይምነታቸው የማያፍሩ ደፋሮች ይዘን መጓዙ ራሱ ሕመም ነው። ኅብረተሰብ ይጠይቀናል። ሰላምን በሰንሰለት፣ ዳቦን በባርነት የሚሸምቱ ሰዎች ዘመን ላይ መድረሳችን ይገርመኛል። ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ የሚያውቁአትና የሞቱላት ሰንደቅ ዓላማ መደፈር እንደ እብድ አድርጐአቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ። ወዲያው ጋዜጠኞች ሰብስበው ንግግር አድርገው አንድ ብዕር በሽልማት መልክ ሰጡኝ። እኔም ለዚች ሰንደቅ ዓላማ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንሁ- የሻለቃ አድማሴን ቃልም ምን ያህል እንደጠበቅሁ አላውቅም። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ያለ ጠባቂ መሆንዋ እውነት ነው። ያለ እስዋ ነፃነታችን ባዶ መሆኑ ይሰማኛል። ባለ አምባሻዋን የመለስን ድሪቶ አደራችሁን በምትክነት አናንሳው!
የነፃነት እጦት የሚመሰክረው የሰንደቅ ዓላማ መዋረድና የአገር መደፈር ምን ማለት እንደሆነ ዘላለማዊው ሐዲስ ዓለማየሁ “ትዝታ” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጠውታል። ራስ እምሩ፣ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ…በኢጣልያ ደሴት ታስረው በቆዩበት ጊዜ የቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ የባሕር ማዶ ቅኝ ግዛት ኅላፊ ራስ እምሩን እንዲያነጋግር ታዝዞ ይሄዳል። ቆፍጣናው መስፍን በመኝታ ቤታቸው ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ሰውየው ቆሞ ሲያናግራቸው ይሉኝታ የያዛቸው የእኛ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ወደየ ክፍላቸው ሊሄዱ ሲሉ ራስ እምሩ “ወንበር ልታመጡለት እንዳይሆን፤ እንዳታደርጉት” በማለት ቅኝ ገዥውንና የሀገሩ ባለቤት የሆነውን ባለሥልጣን አቁመው አነጋገሩት። በኢትዮጵያዊ ክብርና ኩራት እየተደበቡ “ ወዳጄ እኛ ዘንድ ምን አመጣህ?” ይሉታል። እሱም እንደ ባለስልጣን ሳይሆን እንደ አሽከር ቆሞ “ ግርማዊ የኢጣልያ ንጉሥ ኢማኑኤል ሳልሳዊና የመንግስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ያለዎትን ሀብት ንብረትዎን፣ ርስትዎንና ሌሎችንም እንደ ገንዘብ ያለውን ሀብትዎን ሊመልሱልዎ ወስነዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሊረከብልዎ የሚወክሉት ሰው ካለ ይነገረውና ይረከብልዎ!” ይላቸዋል።
የራስ እምሩ ቃል ለሰውየውም እዚያ ላሉትም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርኮኞች እስደንጋጭ ሆነባቸው። ባልተጠበቀው መልሳቸው ራስ እምሩ “የእኔ ሀብትና ንብረት የቀረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በተደፈረ- አገሬ በእናንተ በተረገጠች ጊዜ ነው። አሁን ሀብትና ንብረት የለኝም። ይህን የምትጠቅበውን ሀብትና ንብረት ለምትወድደው ሰው ልትሰጠው ትችላለህ።” ይሉታል። አጭር መልስ። ዲቦኖ፣ ባዶልዩ፣ ዱካ ዳውስታ፣ ግራዚያኒ፣ ፍራንካ..ወዘተ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መርገጣቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም። ይልቁን ቀደም እንዳልሁት ይቺው ሰንደቅ ዓላማ በኤርትራ ምድር እንዲያ ስትከበር በማንም ላይ በምንም ጊዜ ስላደረሱት ጥቃት ብዙም አልሰማንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን አምባገነን ሥርዓት አወረድሁ በሚል ግለሰብ ዓርማችን ስትናቅና ስትገፋ ለማየት ችለናል። የት? በጣይቱ ከተማ- በአዲስ አበባ! ባዕድና ጠላት፣ አስገባሪና ወራሪ የተባሉትም በዚህ ነው። የበላዔ ሰብን፣ የሒትለርንና የስታሊንን፣ የቀያፋን፣ የሔሮድስንና የጲላጦስን፣ የአስቀሮቱ ይሁዳን….ኅጢአት የደመሰሰ አምላክ ይሁነውና መለስ እንደ ገና ሲያላግጥብን ትልቅዋን ዓርማችንን ቡትቱ አስመስሎ ከማምጣቱም በላይ “የነፃነት ቻምፒዮን” ሆኖ ተከሰተ። ከቶውንም የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን እንደ ማካካሻ ሰጠን። ጥሩ ተጫውቶአል። እግዜር ይመስገነው በውጭ ያለነው ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር አልተለያየንም። እንደኔማ ቢሆን ሰው ሁሉ “ወፈፌ” ወይም የጀማመረው ካላለኝ በየቦታው ለብሼ ብሔድ ደስታዬ ነበር።
ለእኔ ሰንደቅ ዓላማዬ ሁሉንም ነች። የነፃነት ብሥራት፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ በክብር የመንጐራደድ ዋስትናዬ ናት። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካ ታጋይ ኅይሎች እየተመለከቱአት ቅኝ አገዛዝን ድባቅ የመቱባት ኅይል ናት። የአፍሪካ አገሮች ወደ ፍጹም አንድነት ይመጡ ዘንድ ታሪካዊ ጥሪ ያስተላለፈች ናት። ዛሬ ደግሞ ከወደቀችበት ትነሣለች። ሰው ሁሉ ኢትዮጵያን ቢክዳት “ኢየሩሳሌም ሆይ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ” ያለው አምላክዋ ወደ ክብርዋ ይመልሳታል። እንደ ተዋረድን አንቀርም። ወደ ታሪካዊ አንድነታችን በእርግጥ እንመለሳለን። አንዳንድ ደካማ “ነፍሳት” (አዎን “ነፍሳት”) የሚያናፍሱት መፍረክረክ ከንቱ ከንቱ…ሆኖ ያልፋል። አሜን አሜን!

Wednesday, 26 February 2014

ሚሊየኖች ድምጽ – ትግሉን ይቀላቀሉ ኪሚሊዮኖች አንዱ ይሁኑ ! እንዴት ካሉ የሚከተለዉን ያንብቡ

February 26th, 2014                  
የባህር ዳር ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ሕዝቡ ከፍተኛ አፈናን ተቋቁሞ፣ ፍርሃትን አዉልቆ የነጻነትን ደዉል አውጇል። ሕዝብ በባህር ዳር ተናግሯል። በዚህ በባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠሩ ብቻ አይደለም ሕዝብ የተሰባሰበው። ዉስጥ ዉስጡን ከፍተኛ ድርጅታዊ ሥራ ስለተሰራ፣ ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ማንቀሳቀስ ስለተቻለ ነው። ድርጅቶች (መኢአድ፣ አድንነት እና ትብብር) በተናጥል ሳይሆን በትብብርና አብሮ በመስራት ስለመሩት ነዉ።
pic14
ይህ የባህር ዳር ሰልፍ በየቤታችን ትልቅ ደስታን እንደፈጠረ ይገባናል። ዜጎች በድፍረትና በነጻነት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ የመሰለ ደስታ የለም። ሁላችንም ተደስተናል፣ በባህር ዳር ሕዝብም ኮርተናል።
የባህር ዳሩ ሰልፍ ግን ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ መሆን የለበትም። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እየተደጋገሙ፣ በጥራትና በብቃት፣ በመቀሌ፣ በአዋሳ፣ በድሬደዋ፣ በጂማ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በመሳሰሉ ሌሎች ከተሞች መደረግ አለባቸው። የነጻነት፣ የሰላም፣ የኢትዮጵያዊነት እሳት መቀጣጠል አለበት።
አንድነት/መኢአድ በፊታቸው ከፍተኛ ሥራ አለባቸው። ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በባህር ዳር የታየዉን አይነት ሥራ ለመስራት ትልቅ ወጭ አለው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀበቶዉን እንዲታጠቅ፣ ትግሉን እንዲቀላቀል፣ የድርሻዉን እንዲወጣ ያስፈልጋል። ከአሁን በኋላ ወደ ኃላ መመለስ የለም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በባህር ዳር እንደተደረገዉ፣ በአገራችን ግዛቶች ሁሉ ሕዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፤ የግድ ነው። ይቻላልምም።
በባህር ዳር ሁኔታዎች ስለተመቻቹ አልነበረም። የፖለቲካ ምህዳሩ ስለተከፈተ አልነበረም። የመኢአድ እና አንድነት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ታስረዋል፣ ተዋክበዋል ከሥራ ተባረዋል፣ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ነዉ። ነገር ግን የተዘጋዉን በር በትግላቸው አስከፍተው ነዉ በባህር ዳር እንዳየነው ሕዝቡን ያንቀሳቀሱት።
በአገር ቤት ያለን ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች ፣ ወንዶች ፣ ወጣቶች አረጋዉያን፣ ክርስቲያኑ ፣ ሙስሊሙ፣ ትግሬው፣ አማራዉ፣ ኦሮሞዉ፣ ቅልቅሉ … ሁሉን ኢትዮጵያዊ ከአንድነት ጎን እንዲሰለፍ እንጠይቃለን። አንድነት እንደ ሌሎች ጠመንጃ የለውም። አንድነት የፈረንጆችን ጥቅም እንደሚያስጠብቁት እንደ ሌሎች የዉጭ መንግስታት ድጋፍ የለዉም። የአንድነት ኃይልና መተማመኛ ሕዝብ ብቻ ነው።
እንግዲህ
1. አገር ቤት ያለን በአካባቢያችን ወዳሉ የአንድነት ጽ/ቤቶች፣ በዉጭ ደግሞ ያለን የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች በመሄድ እንዴት መርዳትና መተባበር እንዳለብን እንጠይቅ።
2. http://www.andinet.org በመሄድ በክሬዲት ካርድ ወይንም ፔይ ፓል የገንዘብ ድጋፍ እናድርግ።
3. የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ እና የፍኖተ ነጻነት ገጽ ላይክ በማድረግ እየተሰሩ ያሉትን እንከታተል። መልእክቶችን በማስተላለፍ የቅስቀሳቅዎች አካል እንሁን::
https://www.facebook.com/FinoteNestanet https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj
4. አገር ዉስጥ ላለን በአካባቢያችን የአንድነት መዋቅር ከሌለ፣ በዉጭ ደግሞ የድጋፍ ድርጅት ከሌሉ፣ ሁለት ሶስት ፣ ሆነን እራሳችንን አደራጅተን፣ ፓርቲዉን ፓርቲዉን በማሳወቅ ትግሉን እንቀላቀል። የድጋፍ ድርጅቶች ከሌሉ፣ የአገር ቤቱን ትግሉ የሚደገፉ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በነርሱ በኩል ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።
5. በግለሰብ ደረጃም በጽሁፍ፣ በሃሳብ መርዳት ከፈለግን organizingethiopia@gmail.com በሚለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን።
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ወቅት እንዳለችዉ፣ ፀሐይ ለኢትዮጵያ ወጥቶላታል። ከአሁን በኋላ አይጨልምም::

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው

February 26, 2014
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)
(yiheyisaemro@gmail.com)

መግቢያ
“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፡- ‹በንቀት የሚመለከት ዐይን፤ ሐሰት የሚናገር ምላስ፤ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፤ ክፉ አሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፤ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኩሉ እግሮች፤ በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምሥክር፤ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው› ናቸው፡፡” ምሳሌ 6፣ 16 – 19
ከአፍ ከወጣ አፋፍ ነው
አለምነው መኮነን የተባለው የወያኔ እንደራሴ በአማሮቹ ሀገር እምብርት ዋና ከተማ ባሕር ዳር ላይ በዝግ ስብሰባ ተቀምጦ በወሻከተው ነገርና መዘዙ ሳቢያ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ሰውዬው ጅል መሆን አለበት – አለዚያም ወፈፌ፤ ከአፍ የወጣ ነገር የትም ሊደርስ እንደሚችል ካጣው እውነተኛ በሽተኛ ነው፤ ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ መባሉ ይህን ዓይነት ዕብሪት ለመግለጥ ነው፡፡ ወያኔዎች ሊታወሱም ሆነ ሊረሱ የማይፈልጉ ዕንቆቅልሾች መሆናቸውን በሰሞኑ ድርጊታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ኢትዮጵያዊ መቼት አማራን መሳደብ ትርጉም የሌለውና የደረቀ ወንዝን እንደመሻገር የሞተ ፈረስን እንደመጋለብ ያለ ዶንኪሾታዊ የጀብደኝነት ፉከራና ሽለላ  ነው፤ ስንትና ስንት ወቅታዊ ጠላት እያለ አርፎ የተቀመጠን ምሥኪን ወገን በጠላትነት ፈርጆ በተደጋጋሚ ኅሊናን ለማቁሰል መጣደፍ የዕድሜ ማራዘሚያ ክኒንን በከንቱ ውጦ እንደመጨረስ ያለ ሞኝነት ይመስለኛል፤ ወያኔዎች ሆይ! ያደርሳችኋል ግዴላችሁም – በኔ ይሁንባችሁ – እስከዚህን ቅጥ አምባራችሁ አይጥፋ፤ ጥጋባችሁን እንደምንም ቻል ለማድረግ ሞክሩ – የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ እንደሚያዘምት እናንተም ይህች በሸፍጠኝነትና በሁለገብ ዓለማቀፋዊ ሻጥር የያዛችኋት አዱኛና የመንግሥት ሥልጣን ናላችሁን አዙራችሁ የምትሆኑትን አጥታችኋልና ፈጣሪ የምትቋምጡለትን ዕብሪት አስተንፋሽ እስኪልክላችሁ ባልተቆጠበ ትግስት ተጠባበቁ፤ ፈጣሪ “የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ” ቸር አምላክ ነውና የምትፈልጉትን የጦር ድግስ ይነፍገናል ብላችሁ ሃሳብ አይግባችሁ፡፡ የዱሮ ጦር ሠራዊት እንደናንተ ጥጋብ ሲወጥረው  ጦር አምጪ እያለ መሬትን ይደበድብ ነበር አሉ፡፡ በምታምኑበት ይሁንባችሁና አማራውን ተውት – ብሶቱን በእህህኣዊ ዕንባው ወደላይና ወደሚመለከተው አካል ያስተላልፍ፡፡ ጓድ አለምነው መኮንን ስማኝ- ቴፕ ሪከርደር እንኳን  የሰጡትን ላለመቀበል አንዳንዴ ያንገራግራል – ችንጊያው ሲጎትት፣ አልማዙ ሲበላ ወይንም ባትሪው ሲያልቅ፡፡ አንተ ግን በአማራው መሀል ተቀምጠህ በጌታዋ እንደተማመነችዋ በግ ቀን በጣለው ሕዝብ ላይ እንዳንዳች የሚቀረና ቅርሻትህን ለቀቅኽው፡፡ ግዴለም፡፡ ግፍን ያላሳለፈ፣ ጡርን ያልሰማ ወደ ደህና ቀን አይወጣምና ይህም ለበጎ ነው፡፡ ለአንተ ግን “መጥኖ መደቆስ ቀድሞ ነበር” ማለትን እወዳለሁ፡፡ አሁን ማጣፊያው ሲያጥርብህና ንግግርህን በማሳመር ሰውን ለማስገልፈጥ እንደዋዛ በወረወርከው ስድብ ሕዝባዊ የተቃውሞ ውርጅብኝ ሲበራከትብህ “የአራት ቀናት ንግግር በኮምፒውተር ተቆርጦ ተቀጥሎ ነው እንጂ የወጣሁበትን ሕዝብ እንዴት ልሳደብ እችላለሁ?” ብለህ በዐይኔን ግምባር ያ’ርገው መሃላ ብትሸመጥጥ የእናቴ መቀነት አሰናከለኝ ዓይነት የተበላ ዕቁብ መሆኑን ልትዘነጋ አይገባም፡፡ አንተ አማራን የተሳደብከው የተማመንከውን ተማምነህ ምናልባትም በተማመከው ኃይል ታዝዘህ ነው ብንል አንሳሳትም፤ የወደፊቱን እንጃህ እንጂ ለአሁኑ ከሽልማት በስተቀር የሚገጥምህ ክፉ ነገር እንደሌለ በደኖንና ዐርባጉጉን በማስታወስ ብቻ በሚገባ እንረዳለን፡፡ ዱባ ካላበደ መቼም ቅል አይጥልም፡፡ አማራ ነኝ የምትለው አለምነውም ሆንክ የሌላ ብሔር አባል ወይም ነጭም ይሁን ጥቁር የማንኛውም የሌላ ሀገር ዜጋ  አንድን ሕዝብ ለመሳደብ ምንም ዓይነት አመክንዮ የለውም፡፡ ቅጽሎች የተፈጠሩት ይህን ዓይነት አወዛጋቢ ሁኔታ ለማስወገድ ነው፡፡ አንተ የትግራይን ብሔር በጅምላ ተሳድበህ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ወቅት ሥጋህ ለጅብ ነፍህን ለጀሃነብ ሰጥተው፤ህ በሣምንታት ውስጥ ተረስተህ ነበር – ምሳሌ ነው – የትግራይ ሕዝብ እንደሕዝብ ባለመሰደቡ የሚቆጨው ሰው ካለ የሸንጎ ፍርድ የሚገባው የመጨረሻ ወንጀለኛ ሰው መሆኑን አጥቼው አይደለም፤ ሕዝብ በደግ እንጂ በክፉ ሊነሣ የሚገባው ኑባሬ አይደለም፤ አልተለመደምም፡፡ ነገር ግን ዘረኛው የወያኔ መንግሥት አማራውን ራሱ ተሳድቦ ስላላረካው ራሱ በሾመውና በአማራነት በፈረጀው ‹ባለሥልጣን› አማራን ሊያሰድበው ወደደ፡፡ ይህ ደግሞ የግፍ ግፍ ነው፡፡ ፈረንጆቹ “adding an insult to injury” እንደሚሉት ነው፡፡ ስብሃት ነጋ፣ ሣሞራ(ሙሃመድ) የኑስና መለስ ዜናዊ አማራን በመሳደብ የሚወዳደራቸው የለም – እስኪሰለቻቸው እየሰደቡ አሰድበውታል፤ ግን ስድብ አይጣበቅ ሆኖ ተቸገሩ፡፡ እንግዲህ የነሱ ስድብና የነሱ የዘመናት ጭፍጨፋ ሊያረካቸው አልቻለም ማለት ነው፡፡ ያሳዝኑኛል፡፡ አንድን ጠላቴ ነው የምትለውን ሰው አንተው ራስህ በጥፍርህም፣ በጥርስህም፣ በጠበንጃህም፣ … በቻልከው ሁሉ ቦጫጭቀኸው እየተንጠራወዘ አልሞትልህ ሲል በከፊልም ይሁን በሙሉ በ“ደም” ይዛመደዋል የምትለውን ሰው ፈልገህ በእጅ አዙር ለማጥቃት መሞከር ከሰይጣናዊነት ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡
ስም ይቀድሞ ለነገር
ኃይለመድኅን አበራ ተገኝ ታሪካዊ ሥራ ሠራ፡፡ ወርቃማ ሥራ ሺህ ጊዜ በማንም ቢደጋገም ሊሰለች አይገባም፡፡ እናም እኔም እላለሁ – ይህ ወጣት ብዙ ክፍለ ጦሮች ሊሠሩት የሚከብዳቸውን ታላቅ ጀብድ ሠርቷል – ልክ እንዳገሩ ልጅ እንደአበበ ገላው (‹ሽጉጥ አልታጠቀ መትረየስ የለው፤ ባንደበቱ ገዳይ አበበ ገላው› ተብሎ የተገጠመውም እዚያችው ሥርፋ ለበቀለው ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡) የዚህ ረዳት አብራሪ ስም ራሱ ተናጋሪ ነው፡፡ “የመድሓኒት ኃይል የነጻነትን ቀንዲል ሊያበራልን ተገኘ” እንደማለት ነው – የት ተገኘ? ከዚያችው ጉደኛ ባህር ዳር ከተማ፡፡  ባህር ዳር መድሓኒትም መርዝም የሚበቅልባት ቦታ ሆነች፡፡ መርዝ ያልኩት አለምነውን የመሰለ ሰው እዚያችው ከተማ ውስጥ የተናገረውን ስለተናገረ ነው – እዚያው እከተማው መሀል ይሁን ዳር ላይ ተጎልቶ በማን አለብኝነት አማራን ዘለፈ፤ የምን መዝለፍ ብቻ በጋብቻ ከልክል ስድብ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ አስታጠቀው እንጂ! አሁን በሞቴ ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ እንዳትሉኝ እንጂ የ“ልጋጋምንና የለሃጫምን ልጅ ማን ያገባል? ከሰባቱ ልጆቼ አራቱ ጉድ ፈላባቸው! ሦስቱስ አለምነውን ቀድመው በማግባታቸው ተገልግለዋል፡፡ ለነገሩ አለምነው ብቻ አይደለም አማሮችን ለማዋረድ ወያዎች መቀመጫ ውስጥ ሄዶ የተወተፈ፤ እነገነት ዘውዴን፣ እነክፍሌ ወዳጆንና ሌሎች ሆዳሞችን በአለምነው ቅርጫት ልንከታቸው እንችላለን፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው፡፡ [“ትልቅ ነበርን ፤ ትልቅም እንሆናለን” - አሁን ከሬዲዮ ሰማኋት፤ ደስ የምትለኝ አባባል!]
ፆመ ኹዳዴ ተጀመረ!
ኹዳዴን የምትፆሙ በተለይ የኦርቶዶክስና የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እንኳን ለፆም መያዣው አደረሳችሁ (አብዛኞቹ ካቶሊካውያን የሚፆሙት ክርስቶስ የፆማቸውን ዐርባ ቀናት በመሆኑ የነሱ ፆም መያዣ ገና አልገባም፤ ብሎም ቢሆን እንደባህል ወስደው የኦርቶዶክስን የፆም ይትበሃል የሚከተሉም አሉ – 55 ቀናትን የሚፆሙ – ለቀድሞ የእሥራኤል ንጉሥ  ኃጢኣት ጭምር መሆኑ ነው)፡፡ ፆሙን በሰላም አጠናቅቃችሁ የጌታችንን የመድሓኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃነ ትንሣኤ ለማየት እንዲያበቃችሁ የኅያው እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ ፆምን መፆም ጥሩ ነው፡፡ ጸሎት መጸለይም ጥሩ ነው፡፡ መመጽወት ጥሩ ነው፡፡ መቀደስና እግዚአብሔርን በከበሮና በጸናጽል፣ በእምቢል፣ በበገናና በማሲንቆ ማወደስም ጥሩ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናትን ማነጽና ማሳነጽ ጥሩ ነው፤ እነዚህና መሰል ደጋግ ሃይማኖታዊ ተግባራት ከፈጣሪ ያገናኛሉ – የፋክስ መስመሮች ናቸው፤ እንዴት መከናወን እንደሚገባቸው መረዳት ግን ይገባል፡፡ አለበለዚያ ለቅጽፈት ይዳርጋሉ ብሎ ማስፈራራቱ ከዘመኑ ሃይማኖታዊ ዕውቀት አንጻር ተጠየቃዊ መከራከሪያ ባይሆንም በግንጥል ጌጥነታቸው ግን ነውረኝነታቸውን መጥቀስ ይቻላል፤ ግንጥል ጌጥ አሣፋሪ ነው፡፡ ለሁለት ጌቶች መገዛትም እንዲሁ፡፡ የሚታየኝን እናገራለሁና ለመቆጣት ያቆበቆባችሁ አደብ ግዙ፡፡ ደግሞም እውነትን ተጋፍታችሁ የትም አትደርሱም፡፡ ይህ ጉዳይ ሁለት አንቀጾች ሊሆንብኝ ነው መሰለኝ፡፡
ከገዳይና ዘራፊ መንግሥት ጋር መቀመጫዋን ገጥማ (ወንበር ለማለት አይደለም) አብራና ተባብራ ሕዝቧን የምታስፈጅ ቤተ ክርስቲያን ጸሎትና ምህላዋ ከዳመና በላይ ይቅርና ከዛፍና ከቤት ጣሪያ በላይም አልፎ አይሄድም – ይህን ለማለት ጉዝጓዜ መጽሐፍ ቅዱሱ ስለሆነ ማንም ያንብበውና ይረዳው፤ የጊዜውን መድረስም በእግረ መንገድ ይገንዘብ፡፡ ቀን ከእግዚአብሔር መንገድ ወጥቶ እንደልቡ ሲፏንንና በየእንትን ቤቱ ሲፋልል የሚውል ካህንና ደብተራ ሌሊት በቤተ መቅደስና በቅኔ ማኅሌት በያሬዳዊ ዜማና ወረብ ቃለ እግዚአብሔርን ማሽር ሲያቀልጥ ቢያድር የክርስቶስን አነጋገር ልዋስና – እውነት እውነት እላችኋለሁ አንድም ጽድቅ የለም፤ ልፋታቸው “የከንቱ ከንቱና ንፋስንም እንደመከተል ነው”፡፡ እንዲያውም ካህናትና ጳጳሳት በእግዚአብሔር ላይ እንደሚያሳዩት አመፃና የትዕቢት ጉዞ ቢሆን ኖሮ እስካሁንም ሁላችንም አልቀን ነበር፤ አንዳችንም ባልተረፍን፡፡ ነገር ግን የሚቀልዱበት እግዚአብሔር ትግስቱና የቸርነቱ ብዛት ገደብ የሌለው በመሆኑ ይሄውና “እስካሁን በአማርኛ በመቀደሴ ይጸጽተኛል፤ ከኢሕአዴግ ጋር መጪው ዘመን ብሩኅ ነው፤ ጭቃ ሕዝብ፤ “shoot him!”፣ የህዳሴውን ግድብ ያልደገፈ ኢትዮጵያዊነቱን በራሱ ገፍፎ ጥሏል፤ …” የሚሉ “ብፁኣን”  አባቶችና የነሱን ስም በየቅዳሤው እያወሱ የሚቀድሱ ደናቁርት ቀሣውስት እያሉን በመቻያው ችሎናል፤ አስችሎንማል፡፡ አንድም የበቃ ካህንና የሃይማኖት መሪ በሌለን ሁኔታ ወጉ አይቀርም “ፆም ሊፆም” በቀደም ለት ተያዘ፡፡ ሊያውም ከፋሲካው በበለጠ የሚፆመውም የማይፆመውም ለነፍሱ ሳይሆን ለሥጋው በሚንሰፈሰፍበት የገበያ ግርግር፡፡ ሃይማኖታችን ለሆድና ስለሆድ ወደተለወጠባት የልማድ እምነት ስትቀየር እንደማየት መጥፎ አጋጣሚ የለም፡፡ በኪነ ጥበቡ ይቅር ይበለን፡፡ አንድ አጭር ማሳሰቢያ አለኝ፡- ጆሮ ያላችሁ የማንኛውም ሃይማኖት አባቶች አዳምጡኝ፤  ይበልጡን ለገንዘብና ለተደላደለ ቅንጦተኛ ሕይወት ስትሉ ከእውነቱ መንገድ ወጥታችሁ ለሥጋችሁ ማደራችሁን በግልጥ የምታሳዩበትና የምታሾፉበት ፈጣሪ በራሱ ጊዜ የሚፈልገውን የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱ የሚጠበቅና የማይቀርም ሆኖ አሁን ለጊዜው ግን እንዲህ አድርጉ፡- አለሰዓት የምታስጮኹትን ዘመናዊ የድምፅ ማጉያ ነገ ዛሬ ሳትሉ ልጓም አብጁለት፡፡ የታመመ አለ፤ በሥራ የደከመ አለ፤ የአንድኛችሁን ጩኸት ሌላኛችሁ በማረፊያና መተኛ ሰዓት ይቅርና በመደነቋቆሪያው የቀኑ ጊዜም መስማት የማይፈልግ አለ፤ ልክ መሆን አለመሆኑ የራሱ ጉዳይ ሆኖ በምንም ነገር የማያምን ግን በቤቱ በሰላም ተኝቶ ማደር የሚገባው የአንዲት ሀገር እኩል ዜጋ አለ፤ በቤተ እምነቱ እንጂ ቤቱ ድረስ በሚመጣ ሰዓት ያልተገደበበት ረብሻና ሁከት በጸሎት ስም መታወክ የማይፈልግ አለ፡፡ ይህ ሁሉ ከጉዳይ መጣፍ አለበት፡፡ ሁሉም ነገር በሥርዓት መከናወን ይገባዋል፡፡ ባህልንና ሃይማኖትን ተመርኩዞ ዜጎችን ማስጨነቅ ተገቢ አይደለም፤ ፈጣሪም የሚወድላችሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ ለርሱ እንዲያውም የአእዋፋትና የዕፅዋት የተፈጥሮ ድምፅና ውዝዋዜ፣ የነፋሳትና የደመናት ዳንኪራና ንፅውፅውታ ከእናንተ በተሻለ የውዳሤና አምልኮት መባዎች ናቸው፤ የነሱ ደረቅና የለበጣ አይደለም – እውነት ነው፡፡ ደግሞም መጽሐፉ “የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜርን ለእግዜር” ስለሚል በደረቅ ሌሊት ከፍተኛ ድምፅ በሚያወጣ ማይክሮፎን ሀገርን ማናወጥ መብት አይደለም – እንደዚያ አስፈላጊ ከሆነ ከከተማዎች ውጪ በሚገኙ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያን ሕዝብን በጥቅል ሳያውኩ ማከናወን ይቻላል፡፡ በዱሮ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናት ሲሠሩ ከመኖሪያ አካባቢዎች ራቅ ይሉ ነበር፤ እንዲያም ሆኖ ኤሌክትሪካዊ ማጉሊያዎች ስላልነበሩ እንደዛሬው ሁከት አልነበረም፡፡ ስለጸሎት ምንነትና ርዝማኔም የክርስቶስን አስተምህሮዎች ደግማችሁ አጢኑ፡፡ እውነቴን ነው የምለው – አሁን አሁን በፉክክርና በደራ በየሽርንቁላው እንደጠላ ቤት በሚቀለሱ የእምነት ቤቶች ሕዝብ እየተረበሸ ነው፤ ብሶቱን ስለማይናገርና ስለሚያፍርም እንጂ ሕዝቡ በዚህም እየተማረረ ከመጣ ሰነባብቷል፤ ለስንቱስ ቀን ጠብቀንለት ይዘለቃል? ከቤተክርስቲያን ግድግዳ በጥቂት ሣንቲ ሜትሮች ወይም በጣት የሚቆጠሩ ሜትሮች ርቀት ላይ የወንደላጤዎች መኝታ ቤት ወይም የተከራይ ሴተኛ አዳሪዎች ክፍል ወይም የጭፈራ ቤት መኖሩን ታውቃላችሁ? ብርሃንና ጨለማ ምን ኅብረት አላቸው? ችግር አለ ምዕመናን፡፡ ብዙ ችግር አለ፡፡ የቋራው መይሳው ካሣ በዳግም ልደታዊ የሂንዱይዝም እምነት መሠረት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ተብሎ እስኪመጣ አንጠብቅ፡፡ ተግባራችን መስታውታችን ይሁነንና ራሳችንን በመመርመር  እንደእግዚአብሔር ትዕዛዛት እንጂ እንደሰይጣን ደባ አንጓዝ፡፡ ልበ ወኩልያትን የሚመረምር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ አንድ ካህን በሥውርም ይሁን በግልጥ ምን እየሠራ የእምነቱ ትውፊታዊ መገለጫ የሆነውን ጽላት ወይም ታቦት እንደሚሸከምና ቃለ ምዕዳን እንደሚሰጥ ፈጣሪ ሳያውቅ ይቀራል ብሎ የሚያስብ ጅላጅል ቄስ ካለ ከሕዝቡ ንቃተ ኅሊና በእጅጉ የወረደ የንቃት ደረጃ ላይ ይገኛል ማለት ነውና ሣይረፍድበት ራሱን ይፈትሽ – አብረን ስለምንኖር ሙሉ በሙሉ እንተዋወቃለንና … ፡፡ (“ውርድ ከራሴ፤ እኔ የለሁበትም…” እያለች የምትዘፍን ሴት አቀንቃኝ ከአንዱ ኤፍኤም በአሁኒቷ ቅጽበት ትሰማኛለች፡፡) ሕዝቡን አደንቁራ ያስቀረች ሃይማኖታችን መሠረቷን ሳትለቅ ልትታደስ ይገባታል፤ ይህ የሚሆነው ከትንሽ ጀምሮ ነውና እዚህ ላይ የጠቀስኩትን ሃሳብ ልብ የሚል ልብ ይበል፡፡ የተለመደ ቅጥልጣይ ሰው ላይ መለጠፍ የማይሠራባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውንም ልብ እንበል፡፡ እውነት ብትመር ብትጎመዝዝም እንደምንም ማወራረድ ነው፡፡ አካሄዳችን የተበለሻሸ ነው፡፡ ይታረም፡፡ በዚያ ላይ “ባለቤቱን  ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” እንዲሉ ሆኖ ከቄሶቹ ባልተናነሰ በፈጣሪ ላይ የሚዘብቱት ወያኔዎች የማይፈርድባቸው መስሏቸው ከመነሻቸው ጀምረው ሃይማኖትን ለማጥፋት ምን ምን እያደረጉ እንደመጡ የምናውቀው ነው፡፡ ይሄውና በነሱና በተባባሪ የሃይማኖት አባቶቻቸውና ጭፍሮቻቸው የበከተ ዲያብሎሣዊ አመራር የተነሣ ዛሬ ዛሬ በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ግራ እየገባቸውና መዳን በሃይኖማኖት መለዋወጥ እየመሰላቸው ወደሌሎች የሃይማኖት ዘርፎች እየነጎዱ ነው፡፡ ይንጎዱ፡፡ ሥራቸው ያወጣቸዋል፡፡ እዚያም ቤት እሳት መኖሩን ያላወቁ ማለትም ከሸሹበት ቤት የጠሉት እንከን ወይንም ገመና በሚሸሹበት ቤት የሌለ የሚመስላቸው የዋሃን በሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊና አእምሯዊ እንግልት ለጊዜው ማዘናችን ባይቀርም ሁሉም የሥራውን ማግኘቱ የነበረና ያለ ነውና በዚያ እንጽናናለን፡፡ የሃይማኖተኞች ጠርዝ የለቀቀ ውስልትናና ሃሳዊነት ከዓለማውያን ሶዶም ወገሞራዊ ብልግና ጋር ሲጋጠሙ ለሚፈጠረው አርማጌዴዎናዊ ትዕይንት ዝግጁ ሆነን እንድንጠብቅ  በዚህ አጋጣሚ የጋራ ግብዣ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ ግን ዛሬ ምን ነካኝ? የጤና ነው ብላችሁ ነው? አሃ፣ በቃ! እስከመቼ?
በሦስት ዓመታት ውስጥ ከ20 እስከ 38 ሚሊዮን ብር ወጪ
እውነተኞቹም ይሁኑ የተጋቦት ወያኔዎች ራሳቸው መርጠው፣ ራሳቸው ሾመውና ራሳቸው መርዘው ለህመም የዳረጉትን የአንድ ክልል ‹ፕሬዚዳንት› ለማሳከም ብዙ ሚሊዮን ብር ከዚህ ምስኪን ሕዝብ ደረቁቻ ካዝና መመዝበራቸውን ሰማን – በአነስተኛ ግምት 20 ሚሊዮን ብር – በከፍተኛ ግምት 38 ሚሊዮን ብር፡፡ የኢትዮጵያ ካዝና መቼም ለዜጎቹ አይሆንም እንጂ ለባለሥልጣናትና ባለሥልጣናት ለሚመሳጠሯቸው የውጭና የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የወርቅ ጎተራ ነው፡፡ የሀገሬ ባላገር በባዶ እግሩ እየሄደ፣ ጨርቁ አልቆ ራቁቱን በብርድ ቸነፈር እየተሰቃዬ አፍንጫውን ተይዞ ከሚከፍለው ግብር ሰባት ሚሊዮን ብር የሚገዛ መኪና ለባለሥልጣን የሚሰጥባት ሀገር ሆናለች አሉ – ኢትዮጵያ፤ በየመሥሪያ ቤቱ አላግባብ የሚባክነው ገንዘብ፣ ሥራው ከመጠናቀቁና ርክክብ ከመፈጸሙ በፊት የሚፍረከረከው የፈረደበት የመንግሥት መንገድና ሕንጻና በቀላል ብልሽት የሚጣለው ተሸከርካሪና ሌላ ንብረትማ አይነሣ፡፡ እንደመጥፎ ዕድል ሆኖ ሀገራችን ብዙ ታማሚ ባለሥልጣናትን በውድ ወጪ ሊያውም በውጪ ሀገራት በማስታመምም ትታወቃለች፡፡ ጥቂት አብነቶችን ለመጥቀስ ያህል- መለስ ዜናዊ፣ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ መሀመድ የኑስ፣ አለማየሁ አቶምሳ፣ ሙላቱ ተሸመ፣ ሥዩም መስፍን እና ሌሎችም ሙትና ቁስለኞች ሁሉ ሞሰብ ገልባጮች ናቸው፡፡ ባለሥልጣኖቻችን ኢትዮጵያቸውን በዕድገትና ሥልጣኔ ወደላይ ስላስፈነጠሯት ለራስ ምታትና ለጉንፋንም ሳይቀር አውሮፕላናቸውን እያስነሱ ከቅርብ ጎረቤት ኬንያ ጀምረው ደቡብ አፍርሪካ፣ ሳዑዲና ታይላንድ እንዲሁም አውሮፓና አሜሪከ ለህክምና ይሄዳሉ፤ ሲፈልጉም ለመዝናናትና ከበሽታቸው ለማገገምም ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ እኛ ደግሞ በወባና በርሀብ፣ በስደትና በሙስና እናልቃለን – ሲያስተውሉት ግን በርግጥም ጉደኛ ዘመን ነው እባካችሁን! በነገራችን ላይ ያቺ ዮዲት ጉዲት አዜብ የሚሏት መበለት መቼ ነው የ“ሀዘን” ልብሷን የምታወልቀው? ሀዘኑ ጎዳት አይደል? ቅድም በአንድ ስብሰባ ላይ እኮ ሃሳብ ልትሰጥ ግራ እጇን ስታንከረፍፍ አይቻት ነው – ሳያት ብቻ እንዴት ደሜ እንደሚንተከተክ አትጠይቁኝ፡፡ ባለራዕዩ ሰውዬ በአጽሙ ሀገር መግዛቱን እስኪያቆም ድረስ የምትቀጥል ይመስለኛል፡፡ ሌላውማ ዱሮውንስ ምኑ ቀረባትና! ወይ የሀፍረታችን ምንጭ ብዛት!
ኡክሬን በ3 ወር የሕዝብ አመፅ ድል በድል ሆነች
የምሥራች! ሕዝብ ማለት እንዲህ ነው፡፡ ኡክሬናውያን በሦስት ወር አመፅ በአሥር ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለድል መብቃታቸውን እየሰማን ነው፡፡ እልኸኞችና በጣም ጀግኖች ናቸው፡፡ ካለመስዋዕትነት ድል ባለመኖሩ ወደ መቶ የሚጠጉ ዜጎች(88) በዚህ በሰሞኑ አመፅ ተሰውተዋል፡፡ ጽናት ማለት እንዲህ ነው፡፡ የኛ ግን እንደተጀመረ ሳያልቅ ቁጭ ብሎ አለ፡፡ ግን እሱ ባለው ጊዜ ማለቁ አይቀርም፡፡ ያም ማለቂያ ጊዜ የቀረበ ይመስለኛል፡፡ ግን ግን … በዚህስ ላይ ለብቻው ትንሽ እናውራበት …
አንድ ሕዝብ ለተራዘመ ጭቆና የሚጋለጠው ለምንድን ነው?
በእኔ ዕይታ ሀገር በቀል አምባገነን ገዢዎች በሁለት ይከፈላሉ፡- በመጠኑ ማሰብ የሚችሉ ሀገር ወዳድ አምባገነኖችና ከከርሳቸው ውጪ ጭራሽ ማሰብ የማይችሉ ድፍን ቅል አምባገነኖች፤ (እነዚህኞቹ ከድፍን ቅልነታቸውና ከሆዳምነታቸው በተጨማሪ የውጪ ጠላትን ተልእኮ አንግበው ሀገርን ለማፍረስ የሚጥሩ መሠሪዎች ናቸው)፡፡ ሁለቱን በደርግና በወያኔ ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ በጭካኔ ረገድ እምብዝም አይለያዩም፡፡ አንዳቸውን የሌላኛቸው ግልባጭ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በአገዛዝ ሥልት ግን ሰማይና መሬት ናቸው፡፡ ስለደርግ ማውራቱ ለአሁኑ አይጠቅመንም – በወደቀ ላይ ምሣር ማብዛት ለአሁኑ ችግር መፍትሔ አይሆንም፡፡ ወያኔ ክፉ ሽንት ነው፡፡ ወያኔ የክፉ ሽንት ውላጅ ነው፡፡ ቀደምት ጠላቶቻችን በሃይማኖታችን ሠርገው ገብተው ወሩን ሙሉ በዓል፣ ዓመቱን ሙሉ ፆም አፅዋም አድርገው ለ“ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ” ተረት እንደዳረጉንና በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ጀቡነው ለማስቀረት እንደሞከሩት ሁሉ ወያኔም በትውልድ ገዳይነቱ የሚታወቀውን የትምህርት ሥርዓት ከዘረጋ ወዲህ እንደከብት ለሆዱ የሚጨነቅ ትውልድ እንጂ ለሀገሩና ለኅሊናዊ ዕድገቱ የሚተጋ ዜጋ ሊፈጠር አልቻለም – በአብዛኛው፡፡ አንድ ሕዝብ ደግሞ በመንፈሣዊ ሕይወቱ ማለትም በአእምሯዊ ዕውቀትና በንቃተ ኅሊና የግንዛቤ ምጥቀቱ ወደፊት ካልተራመደ በስተቀር ከዚህም ባለፈ ቢያንስ የነበረውን እንኳን ጠብቆ መቆየት ካልቻለ ለገዢዎች ምቹ ነው፤ ይህ ዓይነቱ ማኅበረሰባዊ መደላድል እንዲፈጠር ደግሞ ጨቋኞች አጥብቀው ይሠራሉ፤ ከጓደኞቿ ተለይታ የምትወጣ ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ሲሳይ እንደመሆኗ ሀገራቸውን የሚወዱና በትምህርት የላቁ ጥቂት ዜጎች ቢኖሩም አንድም ለሞት አንድም ለእሥራት አንድም ለስደት አንድም ለዕብደትና አሊያም ለአንገት መድፋት እየተጋለጡ ሀገር እንደግመል ሽንት የኋሊት ቀረች፡፡ አምባገነኖች ለኅልውናቸው የሚጠቅሙ ሁሉም የክፋት ሰበዞች እንዲለመልሙ ይጥራሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ ዘረኝነት ነው፡፡ ዘረኝነት የማይምነት ውጤት ነው፤ ጦጣ ከጦጣ ጋር፣ ነብር ከነብር ጋር፣ ፍየል ከፍየል ጋር … መስተጋብር መፍጠራቸው ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በዚህ ስሌት ሰው ከሰው ጋር ኅብረት መፍጠሩ የሚጠበቅ ነው – አንድ ዘር በመሆኑ፡፡ ነገር ግን ሰው ከሰው ጋር መተባበሩና መፈቃቀዱ ቢከብድ ቢያንስ በጥቁርና በነጭ ወይም በቢጫ፣ በሀገርና በክልል ወይም በአህጉር ደረጃ በሚታዩ ቅርበቶች መተባበር ቢኖር የሚታገሱት መለያየት ነው – ከእንስሳት እንደወረስነው ደመነፍሳዊ መለያየት ቆጥረን ማለት ነው፡፡ ከዚህ አልፎ ግን በኢትዮጵያ እንደምናየው የአንድን ዘር የበላይነት በሌሎች ላይ በግልጥ በሚታይ ተግባራዊነት ዐውጆ መንቀሳቀስ ምን ሊባል እንደሚችል ማሰቡ ራሱ ለራስ ምታት ይዳርጋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር ታዲያ የፍጹማዊ ማይምነት ውጤት መሆኑ ሊዘነጋ አይገባውም፡፡ በአንድ ሕዝብ መሀል ጤናማና ተፈጥሯዊ የሚባሉ ልዩነቶች አሉ፤ እነዚያ ጠብና ጭቅጭቅ አያመጡም፡፡ ከመንገድ የወጡ ልዩነቶች መረን በለቀቀ ሁኔታ ከተንሠራፉ ግን የአሁኑን የመሰለ ማኅበራዊ ቀውስ በማስከተል የሕዝብንና የሀገርን ኅልውና ይፈታተናነሉ፡፡ ይቅርታ ሁለተኛ አንቀጽ መድገሜ ነው፡፡
ወያኔ ዘመናዊና ጥራት ያለው ትምህርት በኢትዮጵያ እንዳይኖር የሚጥረው ለምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በተማረና በሠለጠነ ማኅበረሰብ ውስጥ የወያኔን የመሰሉ ማስጠሎ የመንግሥት ሥርዓቶች ለ23 ዓመታት አይደለም ለአንድ ዓመትም ሊቆዩ አይችሉም፡፡ ጉዳዩ የሕዝብ ብዛት አይደለም፡፡ በአንድ ሰው ወይም በአንድ ቡድን ፍላጎት ለመመራት(ለመገዛት) ምቹ ሆኖ የሚገኝ 85 ሚሊዮን ሕዝብ በአንዲት ቀጭን ለበቅ ወይም በቁጣ ድምፅ ብቻ እንደሚነዳ የሃምሳና ስልሳ ከብቶች መንጋን ያህል አያስቸግርም፤ ይህን ዘግኛኝ ሀገራዊ ገጽታ እውን ለማድረግ ደግሞ የአሁኑ ብቻ ሣይሆን የቀደሙት መንግሥታትም የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል፡፡ ወያኔ በተመቻቸለት ጥርጊያ ዘው ብሎ ድንገት ገባና በማን አባት ገደል ገባ የእረኞች ጥንታዊ የማጣያ ዘዴ በትምህርት ያልገፋውን ሕዝብ በማናቆር መርዘኛ ሥርዓቱን ዘረጋ፡፡ ጨካኝ አምባገነናዊ ሥርዓት በመዘርጋት ረገድ 1.3 ቢሊዮን የሚገመተው የቻይና ሕዝብ ዕጣም ከኛው ተመሳሳይ ነው – በኑሮ ተሽሎ መገኘቱ የነፃነትን ጣዕም እንደሚያጣጥም ሊያስቆጥር አይችልም፤ እርግጥ ነው ቻይናውያን በአምባገነን ቻይናውን እንጂ እንደኛ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በካዱ አጭበርባሪና ህግአልባ ማፊያዎች አይገዙም፡፡ የገዢዎች ዋና የሚጨነቁበት ነገር የአገዛዝ ዘዴን ማወቁ ላይ ነው፡፡ በተለይ ዴሞክራሲ በሌለባቸው ሀገራት መንግሥትና ሕዝብ ማለት ዐይጥና ድመት ማለት ናቸው፡፡ ዐይጦች ከድመት ጥቃት ለማምለጥ ሁልጊዜ ብልህና አስተዋይ መሆን አለባቸው፡፡ ድመት ለዐይጥ ምንም ዓይነት ምሕረት አታደርግም፡፡ ዐይጦች ችሮታና ምሕረትን ከድመት ከጠበቁ የዋህነት ነው፤ የብዛት ጉዳይ ከቁብ ሳይጣፍ፡፡ ድመት በሕይወት የያዘቻትን ዐይጥ ዐይኗን አጥፍታ እንዴት እንደምትጫወትባት አስታውሱ፤ ወያኔም ተቃዋሚዎችን በአጠገቡ አስቀምጦ በቅርብ እየተቆጣጠረ እንዴት እንደሚጫወትባቸውና በሀገሪቱ ዴሞክራሲ ያለ ለማስመሰልም እንዴት እንደሚጠቀምባቸው ልብ በሉ፡፡ በውጪ ያሉትንም ሰው እያሠረገ ሲቻል ለማጥፋት ሳይቻል ለመከፋፈልና ለማዳከም፣ የሕዝብ አለኝታና የብሶት መተንፈሻ የሆነውን ኢሳትንም ለማዘጋት የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ አትርሱ፤ እንዳሻው ከሚፈነጭበት የሕዝብ ጫንቃ ላይ ሊያወርደው የሚሞክርን ኃይል ሁሉ ባለ በሌለ ዘዴና ጉልበት ማጥፋት የወያኔ ትልቁ ሥራ ነው – ሌላው ሁሉ ሁለተኛና ሦስተኛ ከፈለገም መቶኛ ነው፡፡ ከጭቆና ለመውጣት ሆ ብሎ የሚነሣ በአግባቡ የተማረና የሠለጠነ፣ ከአጉል ባህልና ከጎጂ ልማድ ነጻ የወጣ፣ ቀናነትን መከባበርንና ትህትናን የተላበሰ፣ በእውነተኛ የሃይማኖት አባቶች የሚመራ፣ ዘረኝነትንና አድልዖዊነትን የሚጠየፍ ማኅበረሰብ መፍጠር ከተቻለ ነጻነትና ዴሞክራሲ ለነዚህ ነገሮች እንደምርቃት ያህል በተፈጥሯቸው ወደሕዝባችን የኅሊናና የፖለቲካዎች ጓዳ የሚገቡ እንጂ ብዙ ትግልን የሚጠይቁ አይሆኑም፡፡ መማርና መሰልጠን ሲባል ደግሞ ለአንድ ወገን ብቻ የሚተው ሣይሆን ለሁሉም ነው፡፡ ሕዝቡ ዘመናዊ ከሆነ አመራሩም ዘመናዊ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው – ያልዘሩት አይበቅልምና አሁን ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል አብዛኞቻችንን እንደሚመስል ወይም እንደማይመስል ለማወቅ ትንሽ ራሳችንን የመፈተሸ ሥራ ማካሄድ ሳይኖርብን የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አንድ ሕዝብ ከሚገባው በላይ ወይም በታች መሪ አያገኝም የሚባለውን ነባር አባባል መመርመርና ራሳችንን ከዚህ ነጥብ አኳያ ማስተካከል ይኖርብናል፡፡ እኛ ጥሩ ስንሆን ጥሩ መሪ ይኖረናል፤ እኛ መጥፎ ስንሆን ደግሞ መጥፎ መሪ ይገጥመናል፡፡ ፈረንጆቹ “what goes around comes around” የሚሉት “ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል” ወይንም “አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ” ለማለት ፈልገው ይመስለኛል፡፡ አዎ፣ እኛን እላይ ለማየት ከፈለግን የላዩን ወደኛው አምጥተን ከታችኛው ጋር ማስተያየትና ልዩነታችንን መገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡ የላይኛው ከታች እንጂ ከላየ-ላይኛው ጽርሃ አርያም እንደማይወርድ ማወቅ አለብን፤ አራት ኪሎ የምትገቡት በሁኔታዎች አስገዳጅነትም በሉት በሌላ አንተና እርሷ ወይም እገሌና እንቶኔ እንጂ ከጨረቃ ወይም ከማርስ አዲስ ትውልድ ተፈጥሮ አይደለም…፡፡ ባልተማረ ሕዝብ ውስጥ አጋጣሚን እየተጠቀመ ወደሥልጣን የሚወጣው በአብዛኛው ብዙም ያልተማረው ቀጣፊና መልቲው ነው – ይህን ለብዙ ጊዜ አይተን በተግባር አረጋግጠናል፡፡ የቅርቦቹ ተፈሪ መኮንን፣ መንግሥቱ ኃ/ማርያምና ለገሠ ዜናዊ ዲ ኤን ኤያቸው ቢጠና ከሌላው ሕዝብ የሚለዩት የሚቃወሟቸውን ቀድመው በማጥፋት ድፍረትና ጭካኔ የተሞላበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰዳቸው እንዲሁም በሥልጣን ሽሚያ የሚጠረጥሯቸውን ጓደኞቻቸውንና የቤተሰባቸውን አባላት ሳይቀር ከጉያቸው እያወጡ እንደሰውነት ተባይ በጣቶቻቸው በመጨፍለቅ ምንም ዓይነት ሥጋት እንዳይኖርባቸው በማድረጋቸው እንጂ የክሮሞዞማቸው ቁጥር ከእኔና ከአንተ በልጦ ወይም በኢትዮጵያዊነታቸው እነሱ ተሽለው አይደለም፡፡ ይህን የአጭበርባሪዎች መንገድ እስከወዲያኛው የምንዘጋው ታዲያ ብዙው ዜጋ ሲማርና ሲሰለጥን በዚያም ምክንያት እውነተኛ ዴሞክራሲን ለይምሰልና ለታይታ ሳይሆን በማወቅና በሃቅ ስናሰፍን ነው፡፡ መንገድና ሕንጻ ደግሞ የጥቂቶችን ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እንጂ የብዙኃንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ልማት የሚያንጸባርቅ ሊሆን እንደማይችል ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ ስለዚህ ራስን በትምህርትና በዕውቀት እንዲሁም በቀና አመለካከትና አስተሳሰብ ለመገንባት ዘወትር መጣር ይኖርብናል ማለት ነው፤ ከልጆች አስተዳደግና ከቤተሰብ አያያዝ ጀምሮ ብዙ ይጠበቅብናል፡፡ ሕዝቡ ጠሊቅ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ በ“አንተ ታውቃለህ” ብቻ፣ በ“ከዚህ ይብስ አታምጣ” ብቻ፣ በ“ሺም ታለበ መቶ ያው በገሌ” ብቻ … ተወስኖ የሚኖር ከሆነ የጥቂቶች መፍጨርጨር ብቻውን የትም አያደርስም፡፡ ሊያውም ከጥቂቶቹም ውስጥ ብዙዎቹ ድብቅ አጀንዳቸው ለግል ጥቅምና ፍላጎት መሆኑን መገመት አስቸጋሪ ባልሆነበት ሁኔታ፡፡ አንድ ጠብሰቅ ያለ አንቀጽ መሰለሴ ነው፡፡
ማኅበረሰባችን አሁን የሚገኝበትን ቅርጽ ማሰቡ ሊያደክም ይችላል፡፡ አእምሮን ያናውዛል፡፡ ቲቪም ተመልከት፤ ሬዲዮም አዳምጥ፤ ከሰው ጋርም አውራ – ከማንም ጋር ተነጋገር ደርዝ ያለው ነገርና የትምህርትን ውለታ የሚያስታውስ አንድም ነገር ማግኘት እየከበደ ነው፤ አብዛኛው ወሬ ስፖርት፣ ተራ አሉቧልታና ወሲብ ነው፡፡ ጭንቅላትን በሚያፈነዱ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮች በተወጠረች ሀገር ውስጥ እንደደላው ሰው ሚዲያውና የሰዎች ትኩረት ሁሉ ይበልጡን በትርኪ ምርኪ ነገሮች ተጣብቦ ስታይ የት ነው ያለሁት ትላለህ – እርግጥ ነው ብዙ የጊዜው ሰዎች ጠግበዋልና ለነሱ ዘመኑ ሠርግና ምላሽ ነው፤ ከተሞችንና መዝናኛ ሥፍራዎችን በሞላ ተቆጣጥረዋል፡፡ የብዙዎች መዘናጋት የሚያሳየው ግን አንድም አፈናው በማያፈናፍን ሁኔታ ተባብሶ አፋችንን ሙሉ በሙሉ አዘግቶናል ወይም ሰው ችግሩን ትቶ በዋዛ በፈዛዛ ጊዜውን ለማሳለፍ ወስኗል ማለት ነው፤ ብቻ ሁኔታው በእጅጉ አሳሳቢ ነው፡፡ በዚህ መሀል ኃይለመድኅንን የመሰሉ ጀግኖችን በድንገት ማግኘቱ አጥንትን ዘልቆ የሚያለመልም ተስፋን ማጫሩ በጄ እንጂ ሁኔታዎች አስከፊ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሀብት ክፍፍሉን ስናይ፣ በቃላት ለመግለጽ የሚከብደውን የኑሮ ውድነት ስንታዘብ፣ በዘረኝነት ላይ የተመሠረተውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወታደራዊና ሃይማኖታዊ መዋቅር ስንመለከት፣ የሕዝቡን የንቃተ ኅሊና ደረጃ ስንቃኝ፣ የምሁራንንና የልሂቃንን ዝምታና እረጭታ ስናስብ፣ የወያኔ ፖለቲከኞችን የልብ ድንዳኔና ጭካኔ ስንመለከት፣ የሙስናውን መስፋፋትና የንግዱን መረን ማጣት ስናይ፣ የባለሥልጣናትን ማይምነትና የአስተዳደር ችሎታ ማነስ ስንታዘብ፣ የድህነትን መክፋት ስናስብ፣ የርሀብተኛውን ቁጥር ስናይ፣ በኑሮ ጣጣ ምክንያት በሀሽሽ፣ በመጠጥና በነገር ሰክሮና አብዶ ብቻውን እያወራ የሚሄደውን ዜጋ ስናስብ፣  … እኛንም ዕበዱ ዕበዱ የሚል መጥፎ መንፈስ ሊወርረን ይችላል፡፡ … በነጋዴዎችና ባለሥልጣናት የሙስና ትስስር ከቆዳችን አልፎ ዐፅማችን እንዴት እንደሚገሸለጥ አንድ ምሳሌ ልናገርና ላብቃ፡፡ በነገራችን ላይ የኔ የ4 ሺህ ብር የተጣራ ደሞዝ ቤተሰቤን ማስተዳደር ካቆመ ቆይቷል – ታዲያ እንዴት ትኖራለህ ካላችሁ መልሴ፣ ዘፋኙ “እኔስ እንደምንም … ሰው አልችል አይልም…” እያለ እንዳቀነቀነው እንደሰው ‹ባጀት በማጠፍ›ና ብዙ ነገሮችን አስቦ በመተው ብቻ ነው (ለምሳሌ ሥጋን፣ ወተትን፣ ቅቤን፣ ነጭ ጤፍን፣ ህክምናን፣ መዝናናትን …. ከዝርዝርህ ታወጣና ወይም እንደመስቀል ወፍ በተወሰነ ጊዜ ‹ታያቸውና› መኖር ተብሎ ትኖራለህ – ከዚያም እንደሰው ተፈጥረህ ስታበቃ እንደበግ ኖረህ ትሞታለህ፤ ሞትህም ተብሎ ወግ አይቀርም ዘመድ አዝማድና ጓደኛ እንደነገሩ ያለቅስልሃል ወንድሜ – እንጂ የሉካንዳ ቤት መስኮት ላይ መቆም አይደለም በዚያ በኩል ማለፍም የሞራል ብቃት ላይኖርህ ይችላል – ሕዝቡ እኮ በቁሙ ሞቷል ማለት ይቻላል፤ አብዛኛው ዜጋ የሚኖረው በተዓምርና በምትሃት ይመስላል፡፡ ምናለ በሉኝ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥጋ ቤቶች ሥጋቸውን በነጭ ሱቲ ይሸፍኑና ለማየት ብቻ ሳያስከፍሉን የሚቀሩ አይመስለኝም፤ ለዚያስ አያድርሰኝ)፡፡ የኔ ደሞዝ እኔንና ቤተሰቤን በቅጡ ማኖር ካቆመ ከኔ አምስትና ስድስት እጅ ወደታች የሚገኙ ዜጎች አሁን በሚከፈላቸው በዱሮው ገንዘብ ሥሌት በሣንቲም ደረጃ የሚገመት ደሞዝ እንዴት እንደሚያኖራቸው ይታሰባችሁ፡፡ ማሰብ ደግሞ “እኔ እንትናን ብሆን” ብሎ እንጂ ለራስና ስለራስ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የአርባ ብር የዱሮ ደሞዝ ምን የመሰለ ቪላ ቤት ያሠራ ነበር – ሊያውም ፉሪና ሱሉልታ ሳይሆን አዲስ አበባ መሀል ከተማ፡፡ አርባ ብር አሁን በአንድ ተራ ቡና ቤት ልሙጥ ሽሮ ቢያበላ ነው፡፡ ለአንድ ተራ የሀብታም ነጋዴ ቤት ሊቀረጽ የማይችል የበር ቁልፍ ለመግዛት የኔን ደሞዝ እንደሚፈጅ ሰምቻለሁ – አራት ሺ ብር! ምሳሌ ሆቴል በሚባለው አንዱን ቤቱን ለግርማ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ በመቶ ሺዎች ብር ለመንግሥት ያከራየው ወያኔ ሰውዬ ሁቴል ቤት ብትገቡ አንድ ክትፎ ብር አራት መቶ ብር ነው አሉ፡፡ እኔ በዚያ ቤት ውስጥ የወር ደሞዜን እንዳለ ባወጣት አሥር ጊዜ ክትፎ መብላት እችላለሁ ማለት ነው፡፡ … ወደምሳሌየ ልሂድ መሰለኝ፡- አንድ የአምስተኛ ክፍል ምሩቅ ነጋዴ ነው፡፡ ዕድሜው ወደሃያዎቹ እኩሌታ ነው፡፡ የሠራው ቤትና ያገባት ምሽት ሌላ ናቸው፡፡ መኪናውን አታንሱት፤ ግራ እጁ ላይ ያለው የውሻ ሰንሰለት እሚያህል የወርቅ ካቴናም እንዲሁ አይነሳ፡፡ በአንድ ጉዳይ ተገናኘንና ሊጋብዘኝ ሆነ – አፈኛ ሰው አንዳንዴ ጋባዥ አያጣም መቼም፡፡ “የሆድ ምቀኛው አፍ ነው” እንደሚባለው ግብዣን ከልክዬ ሆዴ እንዳይቀየመኝ የማላደርገው ጥረት የለምና በደስታ እሺ አልኩ፡፡ አምስት ሰዎች ሆነን ወደርሱ ምርጫ ምግብ ቤት አመራን፡፡ ምን አለፋችሁ – ለኔ ብቻ የወጣውን ሳሰላው ብር 350 ነው – አንድ ኪሎ የፍየል ጥብስና አንድ ጠርሙስ ከግማሽ ጠጅ፡፡ ጠጁ ደግሞ አሁን በብጥሌ ብርሌ ስድስት ብር የሚሸጠው ነፍሱን ይማርና የቤተ መንግሥቱ የጋሽ ድጋፌ ጠጅ እንዳይመስላችሁ – በሊትር መቶ ብር ነው፤ አለፈልኝ ነው እምልሽ የኔ እህት፡፡ የገረመኝ ለግብዣው ያን ያህል ገንዘብ መውጣቱ ወይም እኔ ሠርቼ እየገባሁ የበይ ተመልካች መሆኔ አይደለም፡፡ ያ ወጣት ልጅ ሀሁን ሳያውቅ በሸውራራ የንግድ አሠራር በሚያገኘው ገቢ በወር ከ75 ሺህ ብር በላይ ዕቁብ ይጥላል፡፡ ምቀኝነት የተጠናወተኝ እንዳይመስላችሁ – በፍጹም፡፡ ግን የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ አካሄድ ወደገደል እየወሰደን መሆኑን ለማሰገንዘብ ያህል ነው፡፡ ለነገሩ ሚስቱ ሦስተኛውን ልጅ ስለወለደችለት ከአልማዝ ጌጥ በተጓዳኝ የ2.5 ሚሊዮን ብር መኪና ገዝቶ በጦፈ ግብዣ ላይ የሸለመ ወያኔ መኖሩንስ ከፋክት መጽሔት አንብቤ የለምን? እንዲህ ዓይነት ነጋዴዎችን አንቀባርሮ የሚያኖረው ደሞዜ ለኔ ባይተርፈኝ ታዲያ ይፈረድበታል ምዕመናን? የሰው ልጅ ግብዝነት ግን ይገርመኛል – በዚህ ዓይነት የውሻቸውን ልደት የሚያከብሩ ከውሻቸው የማይሻል ጭንቅላት ያላቸው ሀብታሞችም እኮ ይኖሩ ይሆናል፡፡ ወይ ሰው ሆኖ የመፈጠር አበሳ! ግን ግን ይህች ሀገር የማን ናት? መንግሥትን ደጀን ያደረጉ ሌባ ነጋዴዎችና ሙሰኛ ባለሥልጣናት እየተመሳጠሩ እስከመቼ ነው በተለይ የተቀጣሪ ሠራተኛውን ኑሮ መቀመቅ እንዳወረዱት የሚቆዩት? እኛስ ወግ ደርሶን ከአኗኗሪነት ወጥተን ማለፊያ ሕይወት የምንመራው መቼ ነው?  እነሱ አንገት ካጡ መብታችንን ማስከበር የምንችልበት መንገድ የለም ወይ? (በነገራችን ላይ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች ከፊሉ ምሣ እንደማይዙ፣ ከነዚሁ ከፊሎች ውስጥ ግማሾቹ በቀን አንዴ እንኳን የረባ ነገር እንደማይመገቡና ከነዚህ ግማሾች ውስጥ ብዙዎቹ ከምግብ ዕጥረት የተነሣ በየክፍላቸው ‹ፌንት› እያደረጉ እንደሚወድቁ የሰማችሁ ይመስለኛል፡፡ ሌላ ሌላውን ቅንጦት እርሱትና በልብስ ረገድ እንኳን በውድ ዋጋ ከስንት አንዴ የምትገዛ ሞተ ከዳ (ልባሽ ጨርቅ) እየተጣጣፈችና መልኳን ከአንዴም ሁለት ሦስቴ እየቀየረች ለበርካታ ዓመታት ትለበሳለች፡፡ ባይገርማችሁ ስገዛት ቢጫ የነበረች አንዲት ጃኬቴ መጀመሪያ ወደቀይነት ከዚያም ወደ አረንጓዴነት አሁን በማብቂያው ደግሞ ወደአመዳምነት ተለውጣለች፤ ሁሉንም ቀለሞች ታዳርስ እንደሆነ ጉዷን አያለሁ በሚል ከመኝታ ሰዓት ውጪ አዘውትሬ በመልበስ  መጨረሻዋን በጉጉት እየተጠባበቅሁ ነው – በእግረ መንገዱም ጓደኞቼ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ፣ ከፊት ለፊትም ሆነ ከበስተጀርባ እኔን በአሻጋሪ አይተው በጃኬቴ ለመለየት አይቸገሩም፡፡) ነገ ሩቅ ይመስላል፤ መምጣቱ ግን አይቀርም፡፡ ትንሽ ዕውቀት መጥፎ መሆኑን ከልብ እረዳለሁ፤ ስለዚህም ለእኔ እውነት በመሰለኝና ባመንኩበት ነገር ብዙም ባልተለመደ ግልጽነት “በዘባረቅኋቸው” የግል አስተያየቶቼ የተነሣ ያስቀየምኳችሁ ብትኖሩ በኅያው እግዚአብሔር ስም ይቅር እንድትሉኝ እለምናለሁ፡፡ ሚዲያዎች ጥናቱን ይስጣችሁ – እኔስ ተወረድኩት፡፡

Monday, 24 February 2014

ESAT Daily News Amsterdam Feb 24 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Feb 24 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ልጇን በጀርባ አዝላ ድምጿን ለማሰማት የወጣች ሴት

February 23rd, 2014      
ልጇን በጀርባ አዝላ ድምጿን ለማሰማት የወጣች ሴትudj_lady
አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር የጠሩት ሰልፍ፣ በሶሻል ሜዶያዎች ዋን መነጋገሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን የሰማቸውን ደስታ እየገልጹ ሲሆን ፣ በባህር ዳር ሕዝብ ኩራት እንደተሰማቸው እየጻፉ ነዉ። ኢሳትን ጨመሮ በርካታ ሜዲያዎች፣ ፓልቶክ ክፍሎች፣ ድህር ገጾች ትኩረታቸው ጎጃም ሆኖ የባህር ዳሩን ታሪካዊ እንቅስቅሴ እየዘገቡም ነዉ።
አንዲት ኢትዮጵያዊት ልጇን በጨርባዋ አዝላ ፣ ለመብቷ፣ ለነጻነቷ፣ ድምጿን ለማሰማት ሰልፉን ተቀላቅላ ትታያለች። በሶሻል ሜዲያዎችም ብዙዎች ለዚች እህት አድናቆታቸውን እየገለጹ ነዉ።
እኛም ለዚች እህታችን ያለንን አክብሮትና አድናቆት እንገልጻለን። በአሥር ሚሊዮኖች ለምንቆጠር፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ለተበተንን፣ ዝምታን ለመረጥን፣ ትግል፣ አገርን መዉደድ፣ ለነጻነት መቆም ምን ማለት እንደሆነ ያስተማረችን፣ ጀግና ሴት ናት።

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ

ልማታዊ ግስጋሴ እስከ ግድበ ህዳሴ በደረሰበት ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የእድገት መስፈርት ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛ ነች እየተባለ በመሪዎቿ በሚነገርላት ጊዜ። አሸባሪዎችን ከመነሻቸው ለማምከን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት የሰዎችን ድርጊት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብን ጭምር የሚመረምር ምትሃታዊ ሃይል ተደራጅቶ ባለበት ሁኔታ የዴርቶጋዳን ልብወለድ መሰል ነገር መታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ለመሆኑ የዛሬ ልጆች ጀግና አይደሉም የሚል ማን ነው?
በውጭ ሃገር የዜና ማሰራጫዎች ወሬው እንደተሰማ አስተያየት ለመክተብ ጣታቸው እንደ ክላሺኒኮቭ ፊደል የሚያንጣጣ ሁሉ ፓይለቱ ጥገኝነት ለማግኘት ብሎ እንዲህ ማድረጉ አሳፋሪ ነው፣ አላዋቂ አፍሪካዊ መሆን አለበት፣ ይቀጣ! ይቀጣ! የሚሉ ሃረጎች በርክተው ነበር። እነዚህ በአብዛኛው አፍሪካ ማለት አንድ ሃገር የሚመስላቸው የእውቀት ብርሃን የጨለመባቸው ናቸውና ምንም ማድረግ አይቻልም።Ethiopian Airlines plane Co-Pilot Hailemedehin Abera Tagegn.
ሁለተኛው ሰሞኑን ነገረ ስራው አያምርም ነበር የሚልና አእምሮው ለየት ያለ ነገር የሚያሳየው ‘ሺዞፍሬንያ’ እሚሉት ነገር እየጀማመረው ነበር የሚለው ነው። እህት ሁሉም ይስማልኝ በማለት በመረጃ መረቦች በተነች የሚባለውን ያነበበ ሰው ለበረራ ብቁ ነው የሚለውን ፈቃድ ሰጪም ወፈፍ ያደረገው መሆን አለበት ቢል አላጋነነም። ይሄ እብድ እየመሰለ ሲሰልል የኖረ ወያኔ ወፈፌነትን በጣም ስለተለማመደው አማኑኤል ሆስፒታልን የደህንነት ማሰልጠኛ ኮሌጅ አድርጎ ቢመለከት አይፈረድበትም ብለን መሳቅም መብታችን ነው። ቁም ነገሩ ግን የበረራውን ደህንነት ለማስጠበቅ የአብራሪዎችንምጤናና ደህንነት መከታተል ስለሚገባው ያንንም ማድረግ ባለመቻሉ ወደ ትልቅ ስህተት ራሱን እየጨመረ ነው። በዚህ ሁኔታ ምን  ያህል ወፈፌ ፓይለቶች ይኖሩ ይሆን ብሎ መጠየቅም ያስፈልጋል። ከሆነም ምን አይነት አስተዳደር ቢኖር ነው ጨርቅ ጥሎ የሚያሳብደው፣ ሃገር ጥሎ የሚያስኮበልለው ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው በአንድ-ለአምስት ተጋግዞ መዋሸት ይቻል ይሆናል ከዚያ መረብ ውጪ ላለነው ግን አስቂኝ ትዕይንት ነው።
እኔ አውሮፕላኑን ጠለፈ የሚለው አገላለጽ እጅግም አልተመቸኝም።  ረዳት አብራሪው ድምጼ ይሰማልኝ በማለት ማቆም የማይገባው ስፍራ ላይ አውሮፕላኑን አቆመ ለዚያውም ያለ ፍርሃትና ሽብር መደናገጥና መርበትበት ተሳፋሪውም ኮሽታ ሳይሰማ። አቅጣጫ በቀየረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ለተሳፋሪዎቻቸው ቡና ሻይ እያቀረቡ ምቾታቸውን እየጠበቁ ዋናው አብራሪ ጋዜጣቸውን እያነበቡ ምቾታቸው ሳይጓደል አረፉ። ተሳፋሪዎች የሆነውን ሁሉ ሳያዩ ረዳቱ አብራሪ በገመድ ወርደው ለፖሊሶች እጃቸውን ሰጡ። እንግዲህ የአእምሮ በሽተኛ እንደዚህ ከሆነ ተጋግዘን ብንታመምስ ምን ነበረበት?
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ስለመኖሩ መጠራጠር አውቆ መጨፈን ይሆናል። በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የሀገሪቱ አስተዳደርን ገጽታ የሚያበላሽ ድርጊት ተከናውኗል። ስለምን የሃገሪቱን ገጽታ የሚያጎድፍ እንደሚባል አይገባኝም። የሀገሪቱን ገጽታ የሚያጠለሹት ጎጠኞችና አምባገነኖች ናቸው። የነርሱ አስተዳደር መበስበሱን፣ ሁሉንም ዘርፍ ማለትም ብዙሃኑን የሀገሪቱ ሕዝብ ማሳዘኑን በዚህም ምክንያት ምሬት መኖሩን ነው ይህ ወንድማችን አደባባይ ያወጣው። አዎ የአስተዳደሩን ብልሹነትና እንዳይድን ሆኖ መታመም ነው አደባባይ ያወጣው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ገጽታ ሳይሆን ዓለም የተመለከተው የአስተዳደሩን መጥፎነት ነው።
ቤተሰቦቹ ተገድደው የሚያወጧቸው መግለጫዎች ይበልጥ የሚያጋልጡት ይህ ማፍያ ቡድን እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችልና በቤተሰብ ችግርና ሃዘን ውስጥ እንኳን በመግባት ሊፈጽም የሚችለውን አረመኔያዊ ድርጊት ነው። ቤን የሚሉት ለማጅ ጋዜጠኛ ወሎ ሄዶ ባላቸውን አለቆቹ ገድለው እርሱ ደግሞ በሙስሊም አክራሪዎች እንደተገደሉ ለማስመሰል ሃዘንተኛዋን ባለቤት ሌላ ፖለቲካ ሲያሰራ እንደነበረው ያለ ዜናን ማስታወስ ተገቢ ነው። ያለንበት ዘመን የራሽያ አብዮት የፈነዳበት ጊዜ አይደለም በአይነቱ በተለይም በመረጃ ቅብብሎሹ ረገድ እጅግ በጣም የተለየ ዘመን ነው። የዚያን ጊዜ ታክቲክ በመጠቀም አሁን የሚታየውን አመጽ ማፈን አይቻልም። ይልቁኑ እብዶቹ መንግስት ነኝ ባዮችና ወፈፌዎቹ ጋዜጠኛና ካድሬዎች ከአሳፋሪ ተግባር ቢታቀቡ ነው የሚሻላቸው።
ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራ ቃል ሳይተነፍስ ማለት የሚፈልገውን የተናገረ ይመስለኛል። የምቾት ህይወትን ትቶ ሙያውን ተሰናብቶ መሄዱ ጀግንነት ነው። የብዙዎችን ሰቆቃና ቁጣ ያለውን የአስተዳደር በደልና ዘረኛነት ማጋለጡ ጀግንነት ነው። ራሱን ከዚህ ጨቋኝ ስርዓት ነጻ ማውጣት ለርሱ ቀላል እጅግ በጣም ቀላል ነገር ሆኖ ሳለ በሙያው በክህሎቱ የአለምን ትኩረት የሚስብን ነገር የአንድ ሰው ሕይወት ሳያጠፋ ማስተላለፍ መቻሉ ጀግንነት ነው። ይልቁንም ደግሞ የታወከ አእምሮ ኖሮ(አዋኪውና አስቀዋሹ ምክንያት ምን እንደሆነ ይታወቃልና) በዚህ አይነት የተረጋጋ መንፈስ እንዲህ ያለ መልዕክት ማስተላለፍ መቻሉ ይበልጥ አስደናቂ ያደርገዋል። ምናልባትም በሽታ መሆኑ ቀርቶ ልዩ ስም የሚሰጠው የመንፈስ ጥንካሬ ተብሎ የሚታወስ ይሆናል።  ለወንድማችን ሃይለመድህን አበራ መልካም ጤንነትና ፍትህን እመኛለሁ። ቤተሰቡና ወዳጆቹ ተመሳሳይ የመንፈስ ጥንካሬ ያድርባቸው ዘንድም አሳስባለሁ።

ወያኔን ተሸክሞ መኖር ይብቃን!

February 23, 2014
በዳዊት መላኩ ( ከጀርመን)
የሰው ልጅ ካመረረ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ማሰብ አይችልም፡፡ ለነፍሱም ፈጽሞ አይሳሳም፡፡ ወቅቱ 1998 ዓ.ም ነው፡፡ የ97 ሰባቱን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ ስሙን  ለጊዜው የማላስታውሰውን ወጣት ሁኔታ ላካፍላችሁ፡፡ በእለቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ረባሻ ነበር፡፡ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብጥብጡ ተዛምቱዋል፡፡ ቀደም ብሎ ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዳይገቡ ስጋት ተፈጥሩዋል፡፡ ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቡዋል፡፡ የከተማው ወጣቶች  ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ተማሪዎችን ይዘው መውጣት ያፈልጋሉ፡፡ ተማሪዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ድምጻቸውን ማስማት እና ተቃዉሞአቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡ በመሀል ዙሪያውን የከበበው የፌዴራል ፖሊስ በታጠቀው መሳሪያ በማስፈራራት እየተከላከለ ያገኛል፡፡ ከውጪ ወደውስጥ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ከውስጥያ ያለው ደግሞ ወደ ውጪ እንዳይወጣ በመሀል ሆነው  ይከላከላሉ፡፡ ማሪዎች ያሳደባሉ፤ ይጮሀሉ፡፡ በዚህ መሀል በአዲሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ በኩል አንድ ረዘም ያለ  መልካማ ወጣት መሳሪያ ደግነው ለግዳይ የሚጠባበቁትን ወታደሮች ከምንም ሳይቆጥር ከወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ መጣ፡፡ ወታደሮች ተመለስ! ተመለስ! ትሞታለህ እያሉ ይጮሀሉ፡፡ በለው! በለው! ያባባላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ነፍሱ ፍትህ የተጠማች ወጣት ግቡ ወደ ግቢው በመምጣት ድምጹን ማስማት  በመሆኑ  የወታደሮችንም ጩኸት ሆነ የተደቀነውን መሳሪያ ከምንም አልቆጠረውም፡፡
የወጣቱን ድፍረት ላየ ሰው ሞት የሚባል ነገር ከምድር  እንደሌለው የተረዳው ይመስል ነበር፡፡ ሩጫውን ቀጠለ፡፡ መግደል የተካኑት ወታደሮችም በሁለት ጥይት አከታትለው መቱት፡፡ እንደኛው ጥይት ትክሻውን የመታው ሲሆን ሁለተኛው ጥይት ኩላሊቱን አካባቢ ነው የመታው፡፡ እንደዚህም ሁኖ ወጣቱ አሁንም እየሮጠ በሸቦ ከታጠረው የዩኒቨርሲቱው አጥር ሲደርስ አጥሩን አልፎ መግባት አልቻለም፡፡ ሽቦው እጥር ስር ወደቅ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች የወደቀውን ወጣት ለማንሳት ከያሉበት  ሮሩዋጡ፡፡ የሽቦውን አጥርም ፈልቅቀው ወደ ውስጥ ይዘውት ገቡ፡፡ወደያው ወደተማሪዎች ክሊኒክ ይዘውት ሄዱ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ  የሚሰሩት ዶ/ር ታጀበ አለሙ እና ነርስ በላይነሽ እርዳታ ቢያደርጉለትም ማትረፍ አልቻሉም፡፡ ወጣቱ ህይወቱ አልፋለች፡፡ ግቢው ታመሰ፡፡ ለቂሶ ዋይታ እየዩ ሆነ፡፡ በመሀል የምሳ ሰሀት ስለደረሰ  የተወሰኑ ተማሪዎች ምግብ እንብላ ሲሉ ሌሎች ደግሞ እሬሳ አጋድመን መብላት የለብንም ሲሉ እንብላ የሚሉት ከላይ ትእዛዝ ተላለፎላቸው ኑሮዋል እናንተ ምን ትሰራላችሁ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ስለተባሉ ጉዳዩ ወደ ብሄር ጠብ ተቀይሮ  ተማሪዎች ጎራ ለይተው ድብድብ ተጀመረ፡፡ ከዚያም ግቢው ሙሉ በሙሉ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ሽንት ቤት እንኩዋን ለመውጣት የወታደሮችን ፈቃድ ተጠይቆ ነው፡፡ ከዶርም እንዳይወጣ ተከለከለ፡፡ ትምህርትም ተቁዋረጠ፡፡ ከሳምንት በላይ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ቀስ በቀስ ተረጋጋ፡፡
እንግዲህ እንድትረዱልኝ የፈለግሁት የሰው ልጅ ትግስቱ ገበድ እንዳለው ነው፡፡ ከዚያ ገደብ በላይ ማለፍ እንደማይቻል በዚህ ወጣት ታሪክ ይነግረናል፡፡ ማናኛውም ነገር ገደብ (tolerance limit) አለው፡፡ ለምሳሌ አንድ ላስቲክ ስንስበው እስከተወሰነ ደረጃ ይለጠጣል፡፡ ከዚያ ደረጃ በኃላ ይበጠሳል፡፡ ውኃ በፈሳሽነት ደረጃ የተወሰነ ሙቀትን ወይም ቅዝቃዜን ተቁቁም ይቆያል፡፡ ከዚያ ደረጃ ሲያልፍ ወይ  ይተናል ወይ ወደ በረዶነት ይለወጣል፡፡ የአንድ ብረት ጥንካሬው የተወሰነ ሀይልን ለመቁዋቋም ነው፡፡ የሀይል መጠኑ ሲበዛ ይጣመማል ወይም ይሰበራል፡፡ የወያኔ አፈና እስከተወሰነ ደረጃ ህዝቡን ለማስጊንበስ ረድቶታል፡፡ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ያለፉትን ጊዜያት በስልጣን ተደላድሎ የሀገርን ሀብት እየዘረፈ እንዲቆያ አግዞታል፡፡ ነገር ግን ዘላልም ስልጣን ላይ እንዲቆይ አያደርገውም፡፡ ማናኛውም ነገር ከገደቡ ማለፍ ስለማይችል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን መሸከም የሚችለውን  ያክል ታክሻው እስኪጎብጥ ግፍ እና በደሉን ችሎ ተሸክሞትል፡፡ ላለፉት 23 አመታት ሲያነቋሽሹት፤ ሲገድሉት፤ ሲዘርፉት፤ ከመኖሪያው፣ ከቤቱ ፣ከስራው ሲያፈናቅሉት፤ ከሀገር ሲያስወጡት፤ በእምነት በጎሳ እየከፋፈሉ ሲያጫርሱት ብዙ ብዙ ታግሷቸዋል፡፡ አሁን  ህዝቡ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነበት ከራሱ አሽቀንጥሮ መጣል ያፈልጋል፡፡ ዛሬ አንድነት እና መኢአድ  በጠሩት ሰልፍ የታየው የህዘብ ስሜት ምን ያክል እየገነፈለ እንደሆነ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የሚነግረን ህዝቡ ምን ያልክ ለውጥ እንደሚፈልግ ነው፡፡ እንግዲህ አወዳደቁ እንዳይከፋ ቀስ ብሎ ትንሸራቶ መውረድ ከቻሉ ለወያኔ እና ለደጋፊዎች እሰየው ነው፡፡ ካለሆነ ግን ህዝቡ በግድም ቢሆን አንኮታኩቶ ጥሎ መሰባባሩ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ ስለዚህ ወያኔ ወይ በራሳቸው ጊዜ ቀስ ብለው ይውረዱ ወይ  በግድ ይወገዱ፡፡

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

February 22, 2014
Ginbot 7 weekly editorialየአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]

February 23, 2014

Update: Watch Video

የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

የሲድኒ ኢትዮጵያዊያን የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ፣ አዲሱ አምባሳደር ሀፍረት ገጠማቸው

February 23, 2014
አቢይ አፈወርቅ (ሲድኒ, አውስትራልያ)
በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አረጋ ሀይሉ ትላንት (ቅዳሜ ፌብሯሪ 22 ቀን) የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንን በልማት ዙሪያ ለማነጋገር የያዙት ፕሮግራም በአሳፋሪ ሁኔታ ተደመደመ።
ይህ በሜሪላንድ ሲቲ ካውንስል የተካሄደው ስብሰባ አምባሳደሩንና የስብሰባውን አስተባባሪዎች ጨምሮ በድምሩ 20 ሰዎች እንኳ ያልተገኙበት ሲሆን በርካታ ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ለሰዓታት በአዳራሹ በር ላይ ቆመው ደማቅ የተቃውሞ ድምጽ ሲያሰሙ ውለዋል።  ቪዲዮ ክሊፑን ለመመልከት
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲያስፖራውን ለመከፋፈል ከዓመታት በፊት ያወጣውና በሲድኒም የአገዛዙ ወኪሎች ለረጅም ጊዜ የደከሙበት ዕቅድ ‹ውጤት አስገኝቷል› በሚል ያለአግባብ የተመኩት አምባሳደር አረጋ መላው የሲድኒ ነዋሪ እንዲገኝላቸው መወትወት የጀመሩት ከ2 ሳምንታት አስቀድሞ ነበር። ይሁንና የወገኖቻቸው ሰቆቃ እንደ የእግር እሳት የሚያንገበግባቸው የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ግን ሳምንቱን ሙሉ ‹የስብሰባው አጀንዳ የዲሞክራሲ መታፈንና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ መሆን ይገባዋል› በሚል እርስ በርስ በስልክ የጸሁፍ መልዕክቶችና በሶሺያል ሚዲያዎች ኃሳብ ሲለዋወጡ ነበር የቆዩት። በዚህም የነዋሪው የቁጣ ልክ ከፍተኛ መሆኑ ድንጋጤ ውስጥ የከተታቸው አምባሳደር አረጋ ከስብሰባው አንድ ቀን አስቀድመው ለፖሊስ በመደወል ሀሳባቸውን መቀየራቸውንና በግል አዘጋጆቹ ከሚመርጧቸው ሰዎች በቀር ማንም ወደ አዳራሹ እንዳይገባባቸው ለመጠየቅ ተገደዋል።
Ethiopians in Sydney, Australia protest
ገና በመጀመሪያ ጉዟቸው በፈጸሙት የስሌት ስህተት ለሀፍረት የተዳረጉት አዲሱ አምባሳደር በይፋ የጋበዟቸውን ሰዎች ለማየት እንኳን ባለመድፈራቸው ከስብሰባው አንድ ሰዓት ዘግይተው ወደአዳራሹ በጓሮ በር ገብተዋል። ሰልፈኛውም በሳቅና በወረፋ ተሳልቆባቸዋል።
በስሜት ንዳድ የጋሉት ኢትዮጵያዊያን ከአዳራሹ በር ላይ ቆመው በከፍተኛ ድምጽ መፈክሮችና አገራዊ መዝሙሮችን ያሰሙ ነበር። ባኳያው ደግሞ እየተንጠባጠቡ ወደ ስብሰባው በማምራት ላይ ከነበሩ አናሳ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎች መሀል አንዳንዶቹ የተቃውሞውን ጥንካሬ በመመልከት ከቅርብ ርቀት ፊታቸውን እያዞሩ ሲመለሱ ታይተዋል።
Ethiopians in Sydney, Australia protest against Ethiopian government
የአገዛዙ ወኪሎች ‹ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ይሸነፋሉ› በሚል የገመቷቸውን ኢትዮጵያዊያን በማባበልና በመደለል ለረጅም ጊዚያት የደከሙበት ይህ ዝግጅት፤ ነባር የህወሀት ደጋፊዎችን፣ አምባሳደሩንና የዝግጅቱን አስተናባሪዎች ጨምሮ 20 የሚሞሉ ሰዎችን እንኳ ማሰባሰብ ያለመቻሉ ለኤምባሲው ሀፍረትን፣ ለተቃዋሚዎች ደግሞ እርካታን ሊያጎናጽፍ በቅቷል።
በሚያስተዛዝብ ደረጃ አብዛኞቹ ታዳሚዎች ከተመሳሳይ ብሄር የፈለቁ ቢሆኑም ተቃዋሚዎቹ ግን እየደጋገሙ “እናንተ የትግራይን ብሄር አትወክሉም!” “የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን የአገር ፍቅርን የሚያውቁ ኩሩዎች ናቸው። እናንተ ግን ሆዳሞች ናችሁ።” ሲሏቸው ተደምጠዋል። አስገራሚ የአቋም ለውጥ አድርጋ ‹ዓይንሽ ለዓፈር› የተባለችውን አርቲስት አይናለም ተስፋዬን ጨምሮ አራት ያህል የሌላ ብሄር ተወላጆችም ወደ አዳራሹ ሲገቡ ታይተዋል።
ከስብሰባው ታዳሚዎች በቁጥር ከአራት እጥፍ በላይ የሚልቀውና አንገቱን ቀና አድርጎ በከፍተኛ የስሜት ንዳድ ድምጹን ሲያሰማ የቆየው ተቃዋሚ ከያዛቸው መፈክሮች መሀል ፦”ያለ ዲሞክራሲ ልማት የለም” “የጸረ ሽብር አዋጁ ሽብር ማራመጃ ነው።” “የመሬት መቀራመቱ ይቁም!” “በኢህአዲግ ፖሊሲ ሙሰኞች እንጂ አገር አይለማም” የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል። በግፍ እስር ላይ የሚገኙት ንጹሀን የህዝብ ልጆች እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም በጋለ ስሜት ሲጠቀሱ ውለዋል።
ባስመዘገቡት ውጤት እርካታ የተሰማቸው የአገዛዙ ተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን የዕለቱን ተልዕኳቸውን አጠናቀው ወደ የቤታቸው ከመመላሳቸው በፊት በአገራቸው ጉዳይ ከመቼውም በላይ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባቸው ተወያይተዋል። መልካም ትብብርና ወንድማዊ ስሜት ያልተለያቸው የአውስትራሊያ ፖሊሶችም ልባዊ ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን እነሱም በአጸፋው ሰልፈኛው ሰልፉን በፍጹም ጨዋነት በማካሄዱ ምስጋና አቅርበውለታል። ይህን የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሚያኮራ ቅንጅት ያስተናበሩት የሰልፉ አዘጋጆችም ተገቢው አክብሮት ተችሯቸዋል።

Saturday, 22 February 2014

በአውስትራሉያ ሲድኒ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አምባሰዯሩ የጠራውን ስብሰባ በመቃወም ሊይ ይገኛለ!



በዚሁ በቋጠሮ ገጽ ሊይ የወጣው የወያኔ መንግስት ዲያስፖራውን የመቆጣጠር ተልዕኮ አካል የሆነውና በአዲሱ አምባሳዯር የተጠራውን ስብሰባ ሇመቃወም በሲድኒ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰአት በአዳራሹ በር ሊይ ሆነው ጩህታቸውን እያሰሙ ይገኛለ።


በነገራችን ሊይ በታዋቂ አርቲስቶች የመጠቀም እቅዳቸው በአንጋፋዋ አርቲስት አይናሇም ተስፋዬ የተሳካሊቸው ይመስሊል። አይናሇም በተቃዋሚው ኢትዮጵያዊ እየተሰዯበች ወዯ ስብሰባው ገብታሇች።

ተወዳጇ ያልናት አርቲስት ተወዳጅነቷ በህዝብ ሳይሆን የዯም እዳ ባሇባቸው የወያኔ ባሇስልጣናት መሆኑን ይፋ አድርጋሇች፡፤

ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው ክንፉ አሰፋ

February 22nd, 2014
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ “ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?” ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሳምንት ዘ ሄግ ላይ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲነግሩን ጣል ያደረጓት ቀልድ ናት። የዚህች ቀልድ የፖለቲካ እንድምታ ቀላል አይደለም። መልእክትዋ ሲጠቃለል የኢትዮጵያን ህዝብ እየለቀቀ መሆኑን ትነግረናለች። እየከፋ የመጣው የኑሮውና የፖለቲካ ሁኔታ የህዝቡን አእምሮ ብቻ አይደለም እየነካው ያለው። ህዝቡ እየተገፋ ሃገርሩን ለቆ እንዲሰደድ እየተገደደም ይገኛል። በተለይ ደግሞ ሃገሪቱ በድህነት ያስተማረቻቸው ምሁሮችዋንና ባለሞያዎችዋን እንደዋዛ እያጣች ከመጣች እነሆ ሁለት አስርተ-ዓመታት ተቆጠሩ።
እለተ ሰኞ የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም.።

የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት የጣለው በኢትዮጵያዊው ፓይለት ጉዳይ ላይ ነበር። እንደዚህ አይነት ክስተት ሲፈጸም አዲስ አይደለም። ግን ይኽኛው ልዩ ነው። ይዘቱ ለየት ይበል እንጂ በ 1998 (እ.ኤ.አ.) ዩዋን ቢን በተባለ ቻይናዊ ፓይለት ከተፈጸመው ድርጊት ጋር ይመሳሰላል። የ30 አመቱ ወጣት የበረራ ቁጥር CA905 የሆነውን የቻይና አውሮፕላን በመያዝ የታይላንድን የአየር ጠረፍ ሰብሮ ገባ። የ27 አመት እድሜ ያላት ሚስቱን ይዞ ታይዋን ላይ ያረፈው ፓይለት ለዚያ አደገኛ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት የኢኮኖሚ ችግር ነበር። የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ጭማሪ፣ የመሳሰሉ ከራስ ወዳድነት ያላለፉ ጥያቄዎች በማንሳት የፓይለቱ የራሱን ክብር ዝቅ አደረገው።
በ 1995 (እ.ኤ.አ.) ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ በግዳጅ ከአውስትራልያ ወደሃገሩ እንዲመለስ ተደረገ። ኢትዮጵያዊ ግን የኦሎምፒክ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ጀት ግሪክ ላይ ለመጥለፍ በመሞከሩ የአለምን ዜና ርእስ ሆኖ ነበር። ጋዜጠኛው የፕላስቲክ ቢላዋ የበረራ አስተናጋጅዋ አንገት ላይ በመደገን ወደ ሀገሩ እንዳይላክ ጥያቄ አቀረበ። በመጨረሻም ኢትዮጵያዊ ወገን ባደረገው ርብርብ የዚህ ወጣት አላማ ተሳካለት።
የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለየት የሚያደርገው ለዚህ ከባድ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት ነው። የግል ሳይሆን የሃገር፣ የራስ ሳይሆን የወገን ጉዳይ። ረዳት ፓይለቱን እብድ ያሰኘውም ይኸው ነገር ይመስለኛል። ሃይለመድህን የ40 ሺህ ብር ደሞዝተኛ ነው። በኑሮው ምንም የጎደለበት ነገር የለም። ከመካከለኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በላይ ይኖራል። የስደት ጥማት እንኳን ቢኖርበት ለመሰደድ በዚህ ሁኔታ አውሮፕላን ማገት እንደማይኖርበት ጠንቅቆ ያውቃል። ለዓለም ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልገው አንድ መልእክት ነበር። "ሜይዴይ... ሜይዴይ... የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ላይ ነው!"
ተልእኮው በሚገባ ተሳክቷል።
ሰኞ ማለዳ የመስርያቤታችን የውይይት ርእስ የነበረው ጄኔቭ ላይ ሳይታሰብ ያረፈው ቦይንግ 767 ጉዳይ ነበር። የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ታሪካዊ ውሳኔ የስራ ባልደረቦቼን ከሁለት ጫፍ ከፍሎ ለረጅም ውይይት ጋብዟቸውዋል። አንደኛው ወገን ፓይለቱ ያደረገው ጠለፋ ነው ብሎ ሲከራከር፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ድርጊቱ እንደጠለፋ መታየት የለበትም ይላል። የሁለቱን ወገን ክርክር እየሰማሁ ምንም ሳልተነፍስ ለረጅም ግዜ ቆየሁ። አእምሮዬ ግን አንድ ነገር ላይ ተጠምዶ ነበር። ክስተቱ ለፖለቲካ ደንታ የሌላቸውን እነዚህ ነጮች ማነጋገር መቻሉ እጅግ ደንቆኛል። "ወጣቱ ፓይለት ምን ያህል በደል ቢበዛበት ይሆን ለዚህ ካባድ ውሳኔ የበቃው?" የሚለው ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ይመላለስ የነበረ ጉዳይ ነው። አብዛኞቹ ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታ በደንብ እንዲረዱ ማድረጉም አልቀረም። ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል' ነውና ሁሉንም ነገር ለማስረዳት አሁን በጣም ቀላል ሆነ።
ሃይለመድህን አበራ 'እብድ ነው' የሚሉም አልጠፉም፤ ልክ እንደ አፈቀላጤው ሬድዋን። ለነጮቹ ነገሩ እንግዳ መሆኑ አልቀረም። ፓይለት ሆኖ፣ ጥሩ ኑሮ እየኖረ፣ ቤት- ንብረቱን፤ የሚወዳት ሃገሩንና ቤተሰቡን ትቶ ለእስራት፣ ለስደትና ለእንግልት ራስን ማዘጋጀት እብደት ነው ሊባል ይችላል።
በኢትዮጵያ ተመክሮም የፓይለት ሞያ ያስከብራል። በሃገራችን የፓይለቶች የኑሮ ደረጃ አንደኛውን ረድፍ ይይዛል። ይህንን የመሰለ ህይወት ጥሎ የስደትን ኑሮ መምረጥ የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረስ ደግሞ እብድ ቢያስብል የሚደንቅ አይደለም። የሚገርመው የስርዓቱ ካድሬዎች ይህንን አባባል መደጋገማቸው ነው። ከራሳቸውም አልፈው የፓይለቱ ቤተሰቦችን በማስፈራራት ይህንን እንዲመሰክሩ ሲያደርጉ ይታያል። ወትሮውን በእብዶች መሃል አንድ ጤነኛ ሰው ካለ፣ እሱ እብድ ነው። እነሱ በሰብአዊ መብት ላይ ሲቀልዱ በዚያ የማይተባበራቸው ሁሉ እብድ ነው። ለህሊናው ሳይሆን ለመኖር ሲል ሰበአዊ መብቱ ላይ የማደራደር ሁሉ ሽብርተኛ - አልያም የአእምሮ በሽተኛ ነው።
እብድ ሰው ያንን ግዙፍ አውሮፕላን በስርዓት አብርሮ፤ በስርዓት ካሳረፈ፤ በኢትዮጵያ ፓይለት ለመሆን የቅጥር መስፈርቱ እብድ መሆን ነው። ግና በአውሮፕላኑ የነበሩ 202 ተሳፋሪዎችን ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳያውቁት ጄኔቭ ላይ ማረፋቸው ብቻ እነሱ የሚሉት ይጻረራል። ሃይለመድህን ዋናውን ፓይለት በሃይል አላስገደደውም። ተሳፋሪዎች እንዳይረበሹም ስለድርጊቱ አንዳች ነገር አልተነፈሰም።
ለባለስልጣናቱ ጥያቄ አለኝ። የሃይለመድህን እብድ መሆኑን እያወቁ ለምን ፓይለት አድርገው ቀጠሩት? የእሱ እብድ መሆኑ ለባለስልጣኖቹ እንዴት አሁን ታያቸው?
ያም ታባለ ይህ - የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. በስዊስ ላይ የተፈጠረው ነገር "ከሺ ቃላት... " እንደሚሉት አይነት ነው። አንዲት ትንሽ ድርጊት የአለምን ህዝብ ከጫፍ እስከጫፍ አነጋገረች። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት እና በአንዲት ቃል ብቻ ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ ሁሉ ለአለም አሳወቀ። ይህንን ለማድረግ ግን ራሱን መስዋዕት ማድረግ ነበረበት። ወጣቱ ሊደርስ የሚችልበትን ነገር ሁሉ አስቀድሞ ያውቀዋል። ከሃገር አመራረጥ ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች በሙሉ የተጠኑ እና በጥንቃቄ የተደረጉ መሆናቸውን ሂደቱ ራሱ ይመሰክራል።
ወጣቱ ፓይለት ሃገሩን ይወዳል። የልጅነት ህልሙን እውን ያደረገበትን የፓይለትነት ሙያም ያከብራል። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው። ራስ ወዳድ ቢሆን ኖሮ ፓይለት ሁሉ እንደሚኖረው በሃገሩ እየሰራ መኖር ይችላል። እንደ እብደት ያስቆጠረበት የዚህ ውሳኔ ምክንያቱ ግን ለህሊናው ብቻ ተገዥ መሆኑ ነው። ለሱ ቅርብ የሆኑትም ይህንኑ መስክረዋል።
በሃገራችን ሰርቶ የመኖር ዋስትና በአንባገነኖች እጅ ላይ ወድቋል። በነጻነት የመስራት፣ በነጻነት የመናገር፣ በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ...ወዘተ ዋስትና ሳይኖር የመኖር ትርጉሙ ምንድነው? ሰው ያለ ነጻነት ምንድነው? ለመኖርማ እንስሳትም እየበሉ ይተኛሉ እየተነሱም ይበላሉ - ከዛ ይተኛሉ። ከእንስሳ የሚለየን ነጻነታችን መሰለኝ። ያለ ነጻነት ህይወት ትርጉም የለውም።
በኢትዮጵያ 80 ሚሊየን ህዝብ ያለነጻነት ይኖራል። ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት የዚህ ሁሉ ህዝብ ድምጽ ሆነ። የ80 ሚሊየን ህዝብ ድምጽ ሆኖ በራሱ ላይ መፍረድ መቻል ደግሞ እብደት ሳይሆን ጀግንነት ነው። አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለበት፣ ምን መናገር እንዳለበት...ወዘተ ሲወሰንት ለአንባገነኖች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ህሊናም ባርያ ይሆናል። በተለይ የራስ መተማመን እና የሙያው የተካነ ሰው ተገዥ የሚሆነው ለህሊናው ብቻ ነው። እንዲህ አይነቱ ሰው መብቱን ለድርድር አቅርቦ ራሱን በባርነት አያስገዛም። በመብቱ ላይ የሚደራደር ካለ ህሊናውን የሸጠ ሰው ብቻ ነው። ነጻነት የሚገዛ ውይንም የሚሸጥ ነገር አይደለም። ነጻነትን ሊገዛው የሚችለው ህሊናችን ብቻ ነው። ያለ እራሳችን መልካም ፈቃድ ደግሞ ማንም ሃይል ነጻነታችንን ሊደፍር አይቻለውም። ሰዎች በአካል ሊታሰሩ ይችሉ ይሆናል። የሰውን ህሊና ግን ማንም ሃይል ሊያስረው አይችልም። ኔልሰን ማንዴላ ለ27 አመታት ሲታሰር ህሊናው ነጻ ነበር። በአንጻሩ አሳሪዎቹ ነጮች የአካል ሳይሆን የህሊናቸው እስረኞች ነበሩ።
ሃይለመድህን የህዝብ ድምጽ በመሆን ከህሊናው ጋር የገጠመውን ሙግት ያሸነፈ ጀግና ነው። አላማው በውስጡ የቆሰለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ለአለም ለማሳወቅ ነበር። ይህ ባይሆን ኖሮ ችግር ውስጥ ያማያስገቡት ሌሎች ብዙ አማራጮች እና እድሎች ነበሩት። "ዘ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር" የተባለው ጋዜጣ የሃይለመድህንን ስደት መጠየቅ አስመልክቶ ባሰፈረው ዘገባ የኢህ አዴግ ስርአት ብልሹነትና የሰብአዊ መብት ረገጣው መባባሱን በስፋት ዘግቧል። ሌሎች መገናኛ ብዙሃንም የሃገሪቱን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው እንዲመረምሩት አድርጓቸዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ሲነግሩን የኢአዴግ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ሃገሪቱን ወደ ጥርነፋ ፖለቲካ እና ቁምራ ኢኮኖሚ አሸጋግሯታል። ጥርነፋ እና ቁምራ አዲሶቹ ኢህአዲግኛ ቋንቋዎች ናቸው። ጥርነፋ ማለት አንድ ሰው አምስት ሰዎችን እየሰለለ በማገት ከገዥውፓርቲ አሰራር እንዳያፈነግጥ የማሰርያ ዘዴ ነው። ማንነትን የሚፈታተነው ይህ አሰራር አየር መንገድን ጨምሮ በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት ተግባራዊ እየሆነ መጥቷል።
ቁምራ ደግሞ ቁርስ፣ ምሳና ራት በአንድ ግዜ ማለት ነው። ነብሳቸውን ይመርና አቶ መለስ በአንድ ወቅት ሲጠየቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቴ በልቶ እንዲኖር ነበር ህልማቸው። እነሆ ዛሬ 70 በመቶው የኢትዮጵያ ህዝብ ሶስቱንም የእለት ምግብ አንድ ግዜ በቁምራ እንዲያጠቃልል አበቁት። 10ሺህ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚተዳደረው ከቦሌ አየር መንገድ እና ከሆቴሎች የሚጣል ቆሼ እየበላ ነው። በአንጻሩ ደግሞ እነ ስብሃት ነጋ ለአንዲት ጠርሙስ ሉዊስ ኮኛክ 260፣ 000 (ሁለት ሞቶ ስልሳ ሺህ ብር) ያወጣሉ። የ100 ሺህ ብር መጋረጃ ያለው፤ የ60 ሚሊየን ብር መኖርያ ቤት ውስት በሚዋኙ እጅግ ጥቂቶች እና ቆሻሻ እየተመገቡ በሚኖሩ ብዙሃን ወገኖች መሃል ያለው ክፍተት ይህ ነው አይባልም። ይህንን የኑሮ ሚዛን መዛባት የሚቃወመውን ስም ያወጡለታል። ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን ይህንን የሃብት ድልድል ለመቀበል ህሊናው የማይፈቅደውን ሁሉ "እብድ" የሚል ስም ይሰጡታል።
የ"እብዱ" ፓይለት ጉዳይ በህግ አይን ሲታይ ጠለፋ ሳይሆን እገታ ነው - የስዊዘርላንድ አቃቢ ሕግ እንደገለፀው። እገታ እና ጠለፋ እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ድርጊቱ ጠለፋ ቢባል ኖሮ ቅጣቱም የከፋ ይሆናል። እገታም ቢሆን በስዊስ ህግ ከ3 እስክ 20 አመት ሊያስቀጣ ይችላል። የዳኝነት ስልጣኑም ያለው አውሮፕላኑ በግዛቷ ያረፈበት የስዊዘርላንድ ፌዴራል መንግስት ላይ ነው። ለግዜው ሃይለመድህን አበራን አግኝቶ ማነጋገር ስለማይቻል ወጣቱን ያቆሰለው ጉዳይ ላይ ከዚህ የበለጠ ማለት አይቻልም። የአቃቤ-ህጉ ምርመራውን እንዳበቃ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ያን ግዜ የበለጠ መረጃ ይኖራል።
ኢትዮጵያዊ ወገን በሙሉ፣ ራሱን አሳልፎ ለሰጠው ለዚህ ፓይለት ባገኘው መንገድ ሁሉ ድጋፉን መግለጽ ይጠበቅበታል።