ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የአቋም መግለጫን ስለማሳወቅ፡
ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ 06/11/06 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት በመሰብሰብ የፓርቲውን የስራ እንቅስቃሴና በቅርቡ በታሰሩ የፓርቲው የበላይ አመራሮች በአቶ ሀብታሙ አያሌው እና በአቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በሰበብ አስባቡ በሚታሰሩ ሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ህገ ወጥ ድርጊት አባላቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. የዜጎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና ከፈለጉት ፓርቲ ጋር የመወገን መብታቸውን መንግስት እንዲያከብርና እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡
2. በህገ መንግስቱ የተፈቀዱት የዜጎች መብቶች ሳይሸራረፉ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ እንዲያከብርና እንዲያስከብርእንጠይቃለን፡፡
3. ዜጎች ለመብታቸው መከበር ፍላጎታቸው እየሰፋና እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን በማወቅ ገዢው ፓርቲ ከድርጊቱ እንዲታቀብና የዜጎች መብት እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡
4. ለዲሞክራሲ እውን መሆንና መዳበር ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን ገዢው ፓርቲ ጠንቅቆ በማወቅ ለሰላማዊ ትግሉ መዳበር መንግስት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን በማለት ያቋ ም መግለጫ ያወጣን ሲሆን

በመጨረሻም የፓርቲያችን የላእላይ ምክር ቤት ያለአግባብ የታሰሩ ወንድሞቻችን ሁኔታ ያሳዘነው ቢሆንም ነገር ግን የነሱ መታሰር የትግሉን ምእራፍ ከማስፋትና የበለጠ ከማቀጣጠል ባሻገር አንድም እርምጃ ወደ ኋላ የማይመልሰውና ሁሉንም አባል የበለጠ ለትግሉ ያነሳሳ መሆኑን አምኖ ከእስካሁኑ በበለጠ የትግል ስልቱን በማስፋት በዜጎች መብት ላይ እየዘመተ ያለውን የገዢው ፓርቲ በአደባባይ እና በአዳራሽ በህዝብ የምናወግዝበትን የሰላማዊ ትግል ስልት ፓርቲው እንዲያመቻችልን በማለት የዞኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የአቋም መግለጫ ያወጣ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡
No comments:
Post a Comment