Monday, 30 December 2013

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

December 30, 2013
ሁኔ አቢሲኒያዊ



ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡

 በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡
 በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡:
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ '

በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡
 አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!

ደም ሰጥቶ ነፃነት የተከለከለ ህዝብ (ሽሬ) – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

(የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች - ፎቶ ከአብርሃ ደስታ)



ሽሬ ከመቀሌ በስተ ሰሜን ምዕራብ በ320(?) ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ከተማ ናት። በአውቶቡስ ጉዞ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት ይወስዳል (እኛ ስምንት ሰዓት ፈጅቶብናል)። ከመቀሌ ማይመኽደን፣ አጉላዕ፣ ዉቅሮ፣ ነጋሽ፣ እንዳተካ ተስፋይ፣ ፍረወይኒ (ስንቃጣ)፣ማይመገልታ፣ እዳጋሓሙስ፣ ዓዲግራት፣ አሕዘራ፣ ሴሮ፣ እንትጮ፣ ማርያም ሸዊቶ፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ዉቅሮማራይ፣ ሰለኽለኻ አቋርጠን ሽሬ እንዳስላሴ ገባን።

ሽሬ ለም መሬት ነው። ሰፊና ሜዳማ የእርሻ መሬት አለ። ህዝቡ እንግዳ አክባሪ ነው። ሽሬ የሆነ ደስ የሚል ነገር አለው። ግን ባከባቢው ብዙ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ። ይሄን ጉዳይ ሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። አሁን ግን ወደ የስብሰባው ጉዳይ እንግባ።
ዓረና መድረክ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ወሰነ። ስብሰባው የሚያዘጋጅ የዓረና ቡድን ወደ ከተማው ተላከ። በከተማው ስብሰባ ለማድረግ የሚያስችል ፍቃድና መሰብሰብያ አዳራሽ እንዲሰጠን ጠየቅን። ከአንድ ቀን በኋላ ስበሰባ ማድረግ እንደምንችል ፈቅደው አዳራሽ ግን እንደተያዘ ነገሩን። አዳራሽ መከራየት እንደምንችል ካልሆነ ደግሞ በሆነ ሜዳ ማካሄድ እንደምንፈልግ ነገርናቸው። ከአንድ ቀን በኋላ ተነጋግረው አዳራሽ ፈቀዱልን (ሜዳ ላይ ስብሰባ ከተደረገ ለነሱ ጥሩ አለመሆኑ ያውቁታል)።
አዳራሽ ካስፈቀድን በኋላ ሓሙስና ዓርብ ቀሰቀስን። ከአስር ሺ በላይ በራሪ ወረቀት ተበተነ። በማይክሮፎን ተጠቅመን መረጃው ለህዝብ አዳረስን። የከተማው ካድሬዎች በእግርና በመኪኖች እኛን እየተከታተሉና የሽሬ ህዝብ ለኛ ያለው ስሜት ይሰልዩ ነበር። ያኔ ካድሬዎቹና ሰላዮቹ በኛ ላይ ያደረሱት ምንም ተፅዕኖ አልነበረም። የተቀደደብን ወረቀትም ጭራሽ አልነበረም (በሌሎች አከባቢዎች ካድሬዎቹ ወረቀት ተቀብለው የሚቀዱ ነበሩ)። ዓርብ ቤት ለቤት ቀሰቀስን።

ካድሬዎቹና ሰላዮቹ የህዝቡን ጥሩ አቀባበል ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት አደረጉ። ዓርብ ከሰዓት የከተማው የካቢኔ አባላት ተሰብስበው በጉዳዩ ተወያዩ። ዓርብ ማታ (ከምሽቱ አንድ ሰዓት) የከተማው ከንቲባ አቶ መረሳ አታክልቲና ምክትል ከንቲባው መምህር ሃይለ አዳነ ወደ ማዘጋጃቤት ጠርተው ቅስቀሳ ማቆም እንዳለብን ነገሩን። ስላደረግነው ቅስቀሳ በቂ መረጃ መሰብሰባቸው፣ በጉዳዩ ካቢኔ መሰብሰቡና እስካሁን የተደረገ ቤት ለቤት ቅስቀሳ በቂ መሆኑ መግባባት ላይ መደረሱ ተነገረን።

እኛም ተቃወምን። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ደግሞ ‘ስለ ቅስቀሳው በቂነት የምናውቀውና የምንወሰነው እኛ ራሳችን እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ ቅስቀሳችን እንቀጥላለን’ አለ። ምክትል ከንቲባው በጣም ተናዶ ‘አንደኛ ስትቀሰቅሱ መሳደብ አቁሙ’ አለ።

 ‘መቼ ነው የተሳደብነው’ ስለው ‘ግዕዙይ ምምሕዳር’ ብላችኋል አለኝ። ለካ በማይክሮፎን ስንቀሰቅስ የስብሰባው አጀንዳዎች እንዘረዝር ነበር። ከአጀንዳዎቹ አንድ ስለ ‘መልካም አስተዳደር እጦትና መፍትሔው’ የተመለከተ ነበር። በትግርኛ ‘ግዕዙይ ምምሕዳርን መፍትሒኡን’ ይላል። አስገደም አስከትሎ ‘ግዕዝይናኮ ሙስና ነው።

ስለ ሙስና እንነጋገራለን’ አለ (ሙስና በትግርኛ ግዕዝይና ነው)። ምክትል ከንቲባውም ‘ታድያ ሙስናኮ መንግስታችን ህወሓት እየተታገለው ነው ያለው፤ እናንተ ምን አገባቹ’ አለ።
ርእሱ ለመቀየር ሞከርኩ። ‘እስከ ስብሰባው ቀን ድረስ ብንቀሰቅስ ችግሩ ምንድነው’ ብዬ ጠየቅኩ። ከንቲባው ‘አንደኛ ህዝቡ በቅስቀሳው ደስተኛ አይደለም፤ ሊረብሽ ይችላል። ሁለተኛ ነገ ቅዳሜ ነው፤ የገበያ ቀን ነው። ሦስተኛ እስካሁን በቂ ቅስቀሳ ተደርጓል’ የሚሉ ሦስት ምክንያቶች አቀረበ። እኛም ለሦስቱ ምክንያቶች መልስ ሰጠን። ‘አንደኛ ህዝቡ አይረብሽም፤ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል። ሁለተኛ በሕጉ መሰረት ከገበያ ቦታ አምስት መቶ ሜትር ርቀን ነው የምንቀሰቅሰው። ሦስተኛ እኛ በፈለግነው ግዜ ቅስቀሳው እንጀምራለን፣ እናቆማለን’ አልን።

ቅስቀሳው ማቆም እንዳለብን፣ የካቢኔ ዉሳኔና ትእዛዝ መሆኑ ነገሩን። ትእዛዝ ከሆነ በፅሑፍ እንዲያሳውቁን ጠየቅን። በፅሑፍም አሳወቁን። ፅሑፉ ለሚደርስብን ችግር የከተማው አስተዳደር ሐላፊነት እንደማይወስድ ይጠቁማል። ፀጥታ የማስከበር ሐላፊነት የመንግስት ተግባር ነው፤ የኛ ስራ አይደለም ብለን ቅዳሜም ቅስቀሳችን ቀጠልን። ምንም ችግር አልደረሰብንም።

እሁድ ጠዋት በተፈቀደልን አዳራሽ አከባቢ በማይክሮፎን ህዝቡን ስለ ስብሰባ ማስታወስ ጀመርን። መቀስቀስ እንደሌለብን ፖሊስ ነገረን (ፖሊስ ቅስቀሳው ለማስቆም መታዘዙ ነግሮናል)። መቀስቀሱ አቁመን ወደ አደራሹ ሄድን። ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ሰዎች ተሰባስበዋል። አደራሹ ግን ዝግ ነው። ዘበኛው እንዲከፍትልን ጠየቅን። ‘አልታዘዝኩም’ አለ። ከድር ወደተባለ አለቃው ደወልኩ። አዳራሹ መክፈት እንዳለበት ነገረው። ባደራሹ በር ሁለት ሰዎች አሉ። ‘ጥብቃ ነን’ አሉ። ግን የህወሓት ካድሬዎች ናቸው።


በሩ ተከፈተ። ህዝብ ለመግባት በር ላይ ሲደርስ ሁለቱ ካድሬዎች ወደ አደራሹ የሚገባ ሰው የቀበሌ መታወቅያ በእጁ የያዘ ብቻ መሆኑ አወጁ። ህዝቡም ‘መታወቅያ አናሳይም’ አለ። ‘መታወቅያ ካላሳያቹ አትገቡም’ ተባለ። ጭቅጭቅ ተጀመረ። ‘በህዝብ ስብሰባ ለመሳተፍ መታወቅያ አያስፈልግም’ ብዬ ለሁለቱም ካድሬዎች ነገርኳቸው። ‘መታወቅያ ያስፈልጋል ተብሏል’ አሉኝ። ‘ህዝቡ መፈተሽ ያለበትኮ ፖሊስ እንጂ እናንተ አይደላችሁም’ አልኳቸው። ካድሬዎቹ የአዳራሹ በር ዘጉት።

ወደ ከንቲባው ደውዬ ህዝብ በፖሊስ ብቻ እየተፈተሸ፣ የቀበሌ መታወቅያ ሳይጠየቅ እንዲገባ ለማድረግ ሕጋዊ ፖሊስ እንዲመደብልን ጠየቅኩት። እሱም ፖሊስ እንደማይመድብ፣ የቀበሌ መታወቅያ ያለው ብቻ መግባት እንዳለበትም ነገረኝ። እኔም እንደዛ ከሆነ ስብሰባው ከአዳራሹ ዉጭ እንደምናደርገው ነገርኩት። ‘አይሆንም’ አለኝ።

‘መታወቅያ ያልያዘ አይገባም’ ስለተባለ ስብሰባው ባደራሹ በር ለማድረግ ተስማማን (ልብ በሉ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ እንደማይመድብና ለሚፈጠረው ችግር ሐላፊነት እንደማይወስድ ነግሮናል)። አደራሽ ዉስጥ ገብቶ የነበረ ሰው እንዲወጣ አደረግንና ስብሰባው ባደራሹ በር አከባቢ ባለው ሜዳ ጀመርን። በጣም ብዙ ህዝብ ነበር (በሺዎች የሚቆጠር)።

የከተማው አስተዳዳሪዎች መጡ (ከንቲባው፣ ምክትል ከንቲባው፣ የፕሮፓጋንዳ ሐላፊው … እስከ ቀበሌ ተጠሪዎች ተሰባስበው መጡ። ስብሰባው ማቋረጥ እንዳለብን ነገሩን። ከፈለጋቹ እሰሩን እንጂ ህዝብ ጠርተንማ ስብሰባ አናቋርጥም አለን። እኛ ከከተማው አስተዳዳሪዎች ጋር እንጨቃጨቃለን። የዓረና ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ ግን ንግግር ማድረግ ጀመረ። አለመግባባቱ ግን እየከረረ መጣ። ባከባቢው ደንብ የለበሰ ፖሊስ አልነበረም። የደህንነት ሰዎች ግን መዓት ነበሩ።

አንድ የፖሊስ አዛዥ መጣ። ‘ስርዓት ያዙ’ አለን። ‘ስብሰባ እያካሄድን ነን’ አልን። ‘እዚህ ስብሰባ እንድታደርጉ አልተፈቀደላችሁም’ አለ (ትክክል ነበር፤ በሜዳ ስብሰባ ለማድረግ አልተፈቀደልንም)። ‘ግን ህዝቡ በካድሬዎች ወደ አዳራሽ እንዳይገባ እየተከለከለ ነው’ ብለን ለፖሊሱ ነገርነው። ፖሊሱ ‘አሁን ወደ ተፈቀደላቹ አዳራሽ ግቡ’ ሲለን ህዝቡ ለመግባት ሰልፍ ያዘ።

‘ህዝቡ መታወቅያ እየተጠየቀ ነው’ ብለን ለፖሊሱ አሳወቅን። (ከከንቲባውና ጓደኞቹ ጋር የምናደርገው ንትርክ ግን እየከረረ ነው)። ፖሊስ ‘መታወቅያ አያስፈልግም። እየፈተሻቹ አስገቡት’ አለ። ከንቲባው ‘ያለ መታወቅያማ ሰው አይገባም’ አለ።

 ፖሊሱና ከንቲባው ተጨቃጨቁ። ከንቲባው ተቆጣው። ከዛ ፖሊሱ እኛንና የህወሓት አባላትን መሸምገል ጀመረ። አስገደ ገብረስላሴ ‘አትረብሹን’ አለ (አስገደ ተናዶ ነበር)። መታወቅያ የያዘ ብቻ ሰልፍ ስይዝ መታወቅያ ያልያዘ ጥግ ያዘ። አንድ የደህንነት ሐላፊ ነው የተባለው ሰው መጥቶ ለሚፈት ሹ ካድሬዎች ‘የቀበሌ መታወቅያ ያለው ሳይሆን የዓረና መታወቅያ ያለው ብቻ ነው የምታስገቡ’ የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ።
‘ስብሰባው’ኮ የህዝብ እንጂ የዓረና አባላት ብቻ አይደለም’ አልኩና ሁኔታው በፌስቡክ ለመዘገብ ወደ ኢንተርኔት ካፌ ገባሁ። በአደራሹ በር አከባቢ የተሰበሰው የሽሬ ከተማ ህዝብ ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነበር እነ አቶ ከንቲባ። ግን በጣም ብዙ ስለነበር በቀላሉ መበተን አልተቻለም። እንዳውም ጭቅጭቁ ለምስማት ይጠጋ ነበር።

ከደቂቃዎች በኋላ ተመለስኩ። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ወጥቶ በማይክሮፎን መናገር ጀመረ። ‘የሽሬ ህዝብ ታፍነሃል…’ ምናምን ይላል። ከዞኑ ፅሕፈት ቤት ሦስት ሰዎች በፍጥነት ጮክ ብለው እየተናገሩ ወደ ተሰበሰው ህዝብ ተቀላቀሉ። የከተማው አስተዳዳሪዎችና ተጠሪዎች እንዲሁም የደህንነት ሰዎች አሰባስበው አስር ዓመት የማይሞላቸው ህፃናት አስከትለው ‘ሆ’ አሉ። እየጮሁ ዓረናና የዓረና አባላትን መሳደብ ጀመሩ። ‘ዓረና ሻዕቢያ ነው! ዓረና ኪራይ ሰብሳቢ ነው! ዓረና አሸባሪ ነው! እያሉ ይጮኃሉ።
አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ሁኖ ይናገራል። የሚናገረውን ነገር ህዝቡ እንዳይሰማው ለማድረግ ድምፅ እየጨመሩ ‘አስገደ ሌባ’ እያሉ መጮህ ተያያዙት። ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ተበተነ (ጥጉ ጥጉ ያዘ)። አከባቢው እነሱ ብቻ ተቆጣጠሩት። ፎቅ ላይ ሁነን ቪድዮ ለማንሳት ሞከርን። መጨረሻ እየጮሁ ወደ ዞን አስተዳደር ህንፃ ገቡ። ስብሰባው ተስተጓጎለ።

ረብሻው ይመሩት የነበሩ ሦስት ሰዎች ሲሆኑ ሁለቱ ተፈናቃይ ኤርትራውያን (ግን በማዘጋጃቤት የተቀጠሩ)ና አንድ የደህንነት ሐላፊ ናቸው። ግን ለምንድነው ኤርትራውያን ለህወሓት የሚደግፉ? የሽሬ ህዝብ ህወሓትን ያልደገፈ አርትራውያን ለምን? የሽሬ ህዝብ ግን በሁኔታው እጅግ መገረሙ ከሠዓት በኋላ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

ስብሰባው ተጀምሮ ተስተጓጎለና ወደ ቢሮአችን አመራን። ህዝቡ ‘አይዟቹ’ ይለን ነበር። ከዛ እኔ ወደ ዓድዋ አመራሁ። የማገኛቸው የዓረና አባላት ለማደራጀት ነበር። ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓድዋ ነበርኩ። ዓድዋ ሁኜ ስለ የሽሬ ስብሰባ ለመፃፍ ፈለግኩ። ግን ደክሞኝ ነበር። የተወሰነ መረጃ ለመስጠትና ዓድዋ ከተማ እንደምገኝ ለማሳወቅ ትንሽ ፃፍኩኝ። ግን እንተርኔት ደካማ ስለነበር ፖስት ማድረግ አልቻልኩም። ፅሑፉ ግን በፍላሽ ይዠው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ ወደ መቀሌ ጉዞ ጀመርኩ። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መቀሌ ገባሁ። ዓድዋ ሁኜ የፃፍኩት በመቀሌ ከተማ ለጠፍኩት። ለካ ፅሕፉ ‘ዓድዋ ነኝ ያለሁት’ የሚል አለው።

 (ልብ አላልኩትም ነበር። ያስታወስኩት አሸናፊ የተባለ ጓደኛዬ ሲነግረኝ ነው። ደክሞኝ ነበር። ድካሙ አሁንም አልወጣልኝም)።
‘የምጥሰጠን መረጃ ታማኝ ከሆነ ለምን በፎቶ ወይም ቪድዮ አታስደግፈውም’ የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ።

 ግን ፎቶ ወይም ቪድዮ የማልለጥፍበት ወይ የማላነሳበት ምክንያት አለኝ። በውቅሮ ከተማ ስብሰባ ስናደርግ ካድሬዎች ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍ ይመልሱ ነበር። ካድሬዎቹ ህዝብ ሲመልሱ በካሜራ እንቀርፃቸው ነበር።

 ባጋጣሚ ግን የከተማው ፖሊስ ኮማንደር ሰው ሲመልስ ቀረፅነው (ከሌሎች ካድሬዎች ጋር)። የፖሊስ ኮማንደሩ ‘ያለ ፍላጎቴ ቀርፀውኛል’ ብሎ ፖሊስ ጣብያ ወሰደን። ካሜራው በፖሊስ ተያዘ። አባሎቻችን ተንገላቱ፣ የተቀረፀ ቪድዮ አጠፉት፣ በዛ ሂደት የዉቅሮ ስብሰባችን ሳንቀርፀው ቀረን።

ከዉቅሮ ትምህርት ወስደን ቀረፃ የምናካሂድ በስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ብቻ ነው። በማይጨው ከአደራሽ ዉጭ አልቀረፅንም። በተምቤን ካድሬዎቹ በአደራሹ በር አከባቢ ተሰፍስፈው ሲያስቸግሩን በሞባይል የምቀርፃቸው መስዬ ባከባቢው አለፍኩ። የተቀረፁ የመሰላቸው የዓብይ ዓዲ ከተማ ፖሊስ ኮማንደር (ክብሮም)ና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ። ‘ያለ ፍቃዳችን ቀረፅከን’ አለኝ። ‘አልቀረፅኩም’ ብዬ ሞባይሌን በባለሙያ ተፈተሸ። ምንም አልቀረፅኩም። ተለቀቅኩ።


ከዚህ በመነሳት በሽሬም እንዳያስተጓጉልን በመስጋት ከአዳራሽ ዉጭ ቪድዮ ለመቅረፅ ይሁን ፎቶ ለማንሳት አልፈለግንም ነበር። ግን ስብሰባው መስተጓጎሉ ከተረዳን በኋላ ግን ሁኔታው በቪድዮ ቀርፀነዋል፣ ፎቶም አንስተናል። የነበረን ሐሳብ ግን ስብሰባው ተጀምሮ የሚካሄደው ዉይይት ለመቅረፅ ያለመ ነበር። የተሳታፊዎች ፍቃድ ከሆነ ማቅረብ እችላለሁ። በሚቀጥለው መታወቅያ ያልያዙ ሰዎች ጥግ ይዘው ሲጠባበቁ የሚያሳይ ነው።

ባጠቃላይ በሽሬ ያደረግነው ቅስቀሳ ዉጤታማ ነበር። ስብሰባው (ተጀምሮ ሳያልቅ) በድል ተጠናቋል ማለት ይቻላል። ህወሓቶች ግን የህዝቡ የተቃውሞ መንፈስ በጣም አስደንግጧቸዋል። ሁሉም በስብሰባው እንዲሳተፍ ቢፈቀድለት ኑሮ ወደ ሁለት ሺ ሰው ይሳተፍ ነበር የሚል ግምት አለን። ግን ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ ተነፈገ።

የፈለገውን ሐሳብ በነፃነት እንዳያራምድ ተደረገ። ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ መከልከል ህዝብን ማፈን ነው። ታድያ ህዝብ እንዲህ ከታፈነ ለምን ነበር ይህን ሁሉ መስዋእትነት የከፈለው? የሽሬ ህዝብ ደሙ የሰጠ ለነፃነቱ አልነበረም እንዴ? ደም የሰጠ ህዝብ ነፃነት ይከለከላል?

ለማንኛውም የሽሬ ህዝብ የካድሬዎችን ማስፈራርያ ሳይበግረው በስብሰባው ለመሳተፍ መጥቷል። ህዝቡ በስብሰባው እንዳይሳተፍ የተደረገው በማስፈራራት ሳይሆን የአደራሹን በር በመዝጋትና ስብሰባው እንዳይካሄድ በመረበሽ ነበር። ህዝቡ ግን ለውጥ ይፈልጋል። በቅስቀሳው ወቅት ብዙ አባላት አፍርተናል። ስብሰባው ቢካሄድ ኑሮ ደግሞ የበለጠ ይሆን ነበር። በሐሳብ መከራከር የሰለጠነ መንገድ ነው። ህወሓቶች ዓቅም ካላቸው በህዝብ ፊት ቀርበው ከኛ ጋር ይከራከሩ። ስብሰባ መረበሽ ጀግንነት አይደለም። ጀግንነት ተከራክሮ ማሸነፍ ነው።

በትግራይ ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ የሚል መንግስት እንዴት በዓረና ስብሰባ ይደነግጣል? ህወሓት የህዝብ ድጋፍ ካለው ለምን ዓረና ከህዝብ እንዳይገናኝ እንቅፋት ይፈጥራል? ህወሓት ዓቅም እንደሌላቸው አረጋግጠዋል። በሽሬ ከተማ ህወሓት ምንም ድጋፍ እንደሌለውም አረጋግጠናል። የሽሬ ህዝብ በጣም የተበደለ ነው።

ይህን ሁሉ መስዋእትነት በነፃነት የመሰብሰብ መብት ካላስገኘ ታድያ ፋይዳው ምንድነው? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚያምን ቢሆን ኑሮ ይህን ያህን አይፈራም ነበር።

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው













ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።

በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።

ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል

በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።

የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል።

 መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

Ethiopians in South Sudan seek help

Ethiopian emigrants that reside in the Unity State of South Sudan are stating that they are found in war zone and are at risk.

Six Ethiopians working in the State’s main road construction said they have been hiding inside heavy machineries for the past two days. They said two Ethiopians have been killed while three were wounded.

Although the total number of Ethiopians that have been killed so far is unknown, according to the Voice of America (VoA) Amharic service, 30 Ethiopians have been killed until the December 26, 2013.

The Ethiopian migrants have told ESAT that their government has not reached out to them so far. They said they are puzzled that when the government of Kenya and Uganda have evacuated their citizens from South Sudan, the Ethiopian government did not do.

Four Ethiopian women who have been raped in the Jonglei State of South Sudan have received medical treatment in the United Nations Hospital in Juba.

Meanwhile, According to the Inter-Governmental Authority on Development (IGAD), spearheaded by leaders of seven East African countries, South Sudanese President SalvaKiir expressed hiscommitment to cease fire in the recently war-ravaged country.

 Uhuru Kenyatta, the Kenyan President, said, “Let it be known we in IGAD will not accept the unconstitutional overthrow of a duly and democratically elected government in South Sudan.”
More than 1,000 people have been killed in fighting between the government and rebels since 15 December when violent clashes began in the capital, Juba.