Sunday, 9 March 2014

አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር የሚሊኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ አደረገ

March 9, 2014
ፍኖተ ነጻነት
አንድነትለዲሞክራሰና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃግብር በተከታታይ ሊካሂዳቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ በየሆነውን የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊተ ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት ነው፡፡ ህዝባዊ ንቅናቄው ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ አንድነት የመሬትን ጉዳይ በአጀንዳነት በመምረጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግ የመረጠባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡UDJ party to launch 2nd millions march for democracy
በአዲስ አበባ በሚደረግ ትዕይንተ ህዝብ እንደሚጀመር የሚጠበቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” ህዝባዊ ንቅናቅ 14 ከተሞች ላይ ሰላማዊ ሰል እንደሚደረግና ሶስት ከተሞችም በተጓዳኝ ለህዝባዊ ንቅናቄው መመረጣቸው ታውቋል፡፡ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባ ፣ደሴ ፣ሐዋሳ ፣አዳማ/ናዝሬት ፣መቀሌ ፣ደብረታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ነቀምት፣ለገጣፎ፣አዲስ አበባ ሲሆኑ ተጓዳኝ ከተሞቹ ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ) እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንድነት ፓርቲ ባለፈው ዓመት(2005ዓ.ም) ለሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ስክታማ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል፡፡