Thursday, 1 May 2014

ወያኔ የሚፈራው ምርጫ ወይስ ሕዝባዊ እምቢተኝነት (አመጽ)

May 1, 2014
ተስፋዬ ዘነበ
በዚች አለም በሕዝቦቻቸው ላይ የሚፈነጩ አምባገነኖችን ለማስወገድ የሚደረጉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወያኔ ዘረኛችን ለምን ሲያስደነብራቸውና በፍርሃት ሲያሸማቅቃቸው እንደሚኖር የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ የሚያደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወይም ውድመት በተለያየ መንገድ ሕዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም እራሱ ለፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ የሕዝቡን ብሶት ለማዳፈን ሀላፊነት የጎደለው ተግባራትን እየፈፀመ ሃገርን የመበተን ስራውን ቀጥሎበታል፡፡The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful.
በአዋጅ የተደነገጉ የሕዝብን አሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን እየሸረሸሩና አዋጅን በተራ መመሪያ እየሻሩ የስቃይ ቀንበሩን ያከብዱበታል ፡፡በየትኛውም ሁኔታ ማለትም የሰብአዊ መብቱ የተረገጠውን፣ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ስላለ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ የሚሰቃየውን የነፃነት ታጋይ፣ በስርዓቱ ብልሹና የተዝረከረከ አሰራር በኑሮ ውድነት እየማቀቀ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ወይ መፈትሄ ከመስጠት ይልቅ በተራ ካድሬያዊ ዲስኩር ከላይ ለዘረኛው ስርዓት ቃል አቀባይ ከሆነው ጠ/ሚ ተብዬው እስከ ልማታዊ ጋዜጠኛ ነን እስከሚሉት ድረስ በርሃብ ለጠወለገው ምስኪን ሕዝብ ጥጋብን፣ በገዛ ሃገሩ ፍትህ አጥቶ ለሚሰቃየው ፍትሃዊነትን እንዲሁም ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ነፃነቱን ለተነጠቀው ሕዝብ ዴሞክራሲን ነጋ ጠባ ይሰብኩታል፡፡
ይህው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ስለፈጠረው ሃገራዊ ቀውስ ብዙ ብዙ ቢባልም የዚህን መርዘኛ ስርዓት ሰንኮፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመጣል ከምርጫ ይልቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነት(አመጽ) ስለመሆኑ ስርዓቱ በሚያሳየውና ከሚሰጋባቸው ነገሮች ለመረዳት ይቻላል፡፡
እንደሚታወቀው በተደጋጋሚ የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ 97 ውጪ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለወያኔ መሳሪያ ከመሆን ወጪ የስርዓቱ የአፈና መዋቅር ተቃዋሚዎችን የሚያወላዳ አልነበረም፡፡ ይህ ማለት ይካሄዱ የነበሩ ምርጫዎች በህውሃት ዘረኛ ቡድን በተጠና የአፈና እንዲሁም በዋነኝነት ምርጫን ምርጫ ሊያሰኙ የሚችሉ ገለልተኛ ተቋማት በጠቅላላ በስርዓቱ መዋቅር የተዋጡና የተተበተቡ በመሆናቸው ለመገናኛ በዙሃን ሸፋንና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ መደለያ ካልሆነ በስተቀር ምርጫው ሳይጀመር ውጤቱ የታወቅ እንደ ነበር ከማንም የተሰወረ አደለም፡፡ ስለሆነም የህውሃት ቡድን አምስት አመት ጠብቆ የሚመጣ ምርጫ ከላይ እንደተጠቀሰው ለአንዳንድ ግብአት ይጠቀምበት እንደሆን እንጂ ምርጫ ስለተቃረበ እንቅልፍ የሚያጣ አይመስልም ምክንያቱም የምርጫ አስፈጻሚ አካላት እስከ ፍትህ ስርዓቱ በእጁ ናቸውና፡፡
የልቁንም ለዚህ እኩይ ስርዓት የራስ ምታት የሚሆንበትና ሰላም የሚነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት(አመጽ) ነው፡፡ በቃ የሚል ትውልድ ግፍና በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ለመሆኑ ማሳያ ይሆኑ ዘንድ አንዳንድ ነጥቦች እናንሳ፡፡
ከአመታት በፊት ቱኒዚያዊው ሙሃመድ ቡዋዚዝ የቢን አሊን አንባገነን መንግስት በሃገሩ በቱኒዚያና በሕዝቧ ላይ የሚያሳደረውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመቃወም እራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ካቃጠለ በሗላ ቱኒዝያን ጨምሮ ሊቢያ፣ ግብጽ፣ የመን፣ እስካሁንም በነወጥ ውስጥ ያለች ሶሪያ የደረሰውን ሕዝባዊ እምቢተኝንትና በየሃገሩ የተለኮሰው አመጽ የወያኔን ዘረኛ ቡድን ያስፈራውና ያሸማቀቀውን ያህል አምስት አመት ጠበቆ የሚካሄደው የየስሙላ ምርጫ አላሸበረውም፡፡
ይህንንም ለመገንዘብ በዛን ወቅት ሟቹ መለስ ዜናዊ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ማየት የበቃል፡፡ በመጀመሪያ የአረብን አለም አብዮት የሚዘገቡ አለም አቀፍ የመገናኛ ቡዙሃንን ማፈር ቀዳሚ ተግባሩ ነበር ሆኖም መረጃው በተለያየ መንገድ ሕዝብ ጋር መድረሱን የተረዳው ሟቹ ጠ/ሚንስትር የሕዝብን መንፈስ ለመሳብና ቤሔራዊ ስሜትን ሰቅጦ ይይዝልኛል ያለውን መላ ምቱ ዘየደ ባይሳካም ኤርትራን ለመውረር መዘጋጀቱን ማወጅ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው አብዮቱ የኢትዮጲያንም በር እንዳያንኳኳ ካለው ከልክ ያለፍ ፍርሃት ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ኖሮውን እንጂ የወረራ ዲስኩር ችላ እንዳልው ሲረዳ በኤኮኖሚም በፖለቲካ እንዲሁም ሃገራችን ያላትን መልካም የውጪ ገንኙነት የላገናዘበ በተጨማሪም በባለሞያዎች በቃ ጥናትና ምርምር ያልተደረገበትን እስካሁንም ዘርፈ ብዙ ችግር አዝሎ የሕዝብ ኪስ የራቆተውን የአባይ ግድብን እንካችሁ ብሎ ሻማ አለን፡፡ የሟቹን አላማ ይህኛው በተወሰነ መጠን አሳካለት ሆኖም አብዮት የፈራው ወይም ሕዝባዊ እምቢተኝነትን የፈራው የህውሃት ዘረኛ ቡድን የማይገፋ እዳ ለሃገርን ለሕዝብ ትቶ ችግሩን ፍርሃቱ ፈታበት፡፡
በተጨማሪ ይህው ዘርኛ ቡድን በአለም ዙሪያ የተደረጉ የተሳካላቸው ምርጫዎችን እያነሳ የሰጋበት ግዜ አይታወስም፡፡ በአንጻሩ ምርጫ ያጭበረበሩ አምባገነኖችን ሕዝብ ሲቃወምና ድምጹን ለማስመለስ የሚያደርገውን የነፃነት ትግል አሉታዊ መልክ ሰጥቶ ባዘጋጃቸው የፖለቲካ ተንታኝ ተብዬዎች ውግዝ ከማርዮሰ ሲያስብላቸው ይውላል፡፡ በየትኛውም መልኩ የሚካሄዱ ሕዝባዊ እቢተኝነት(አመጽ) ከማውገዝ ወደ ሗላ ብሎ የማያቀው ይህ ስርዓት ሰሞኑን ዘጋቢ ፊልም መስራት በማይሰለቻቸው ልማታዊ ጋዜጠኞቹ ይቀርብ የነበረው የዚሁ የፍርሀትና እራሱን እየከፈነ ያለው ያበቃለት የህውሃት ዘረኛ ቡድን ቅዠት ነው፡፡
ቅዠቱ የቀለም አብዮት ይልና ከብርቱካናማው የዩክሬን አብዮት ጀምሮ ቬንዙዌላ የድርሳል አጠቃላይ ምልከታው አብዮት ወይም ሕዝባዊ እምቢተኝነት የሚከናወነው ሕዝብ ፈልጎት ሳይሆን ከምዕራባዊያን እዲሁም በምዕራባዊያን ሃገራት ከሚኖሩ ዜጎች ፈላጊነት የሚመነጭ ነው ይለናል ኸረ እንደውም እነዚሁ ምዕባዊያን የማይፈልጓቸውን መንግስታት የሚያሶግዱበት አንዱ መሳሪያ ሕዝባዊ አመፅ ነው በማለት ይቀጥላል፡፡ ሌላው የሚገርመው የ 97 ምርጫን ተከትሎ ሕዝብ የተቀማ ድምጹን ለማሰመለስ ያደረገውን እንቅስቃሴና ንጹሃን ወገኖቻችንን በዚሁ ዘረኛ ቡድን የተነጠቅንበት ትእይንትም እንደ ዘጋቢ ፊልሙ አገላለጽ በሌሎች ሃገራት እንደተደረገው ሁሉ በምህራባዊያንና በነዚሁ ሃገራት በሚኖሩ ዜጎች የተቀነባበረ እንደሆነ ያትታል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ወያኔን ይህንን ያህል ዘመን በሕዝብ ጫንቃ ላይ ያስቀመጡት እነሱ ምዕራባዊያን ሆነው ሳለ ስጋቱን ምን እንዳመጣው ነው፡፡
ሕዝብ ለሚያቀርበው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ፣ የፍትህ ጥያቄ እንዲሁም የዴሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ጀርባ ሰጥቶ በትምክህት መኮፈስ በቃኝ ለሚል ለውጥ ፍላጊ ትውልድ እሳት ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን አሁን የተያያዘው መንገድ ይህው ነው፡፡
ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚባለው የትም ይሁን የት መሰል የአመባገነኖችን ዙፋን የሚያነቃንቅ ሕዝባዊ አመጽ የሕውሃት ቡድን እራስ ምታት ነው፡፡ ሕዝብንም በመከፋፈልና በመለያየት የተጋው ፍርሃቱን ለማብረድ ነው፡፡ በተረፈ አምስት አመት ቆጥሮ የሚመጣን ምርጫ ያውም 99.6% ሊሰርቅበት የሚችል ለእርሱ በእርሱ የተከፈተ የምርጫ ስርዓት ያሰጋዋል ተብሎ አይገመትም፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በፍርህት የሚያርደውም የሚያሶግደውም ሕዝባዊ እምቡተኝነት(ሕዝባዊ አመጽ) ነው፡፡ በተለይ አሁን ስርዓቱ በስብሶ እራሱን በገነዘበት ሰዓት ሊቀብረው የሚችል በኢትዮጲያዊነት ጥላ ስር በአንድነት የተደራጀ በቃ በሎ ነፃነቱ የሚያውጅ ተውልድ ነው!!!

ሰበር ዜና፣ በጎንደር ተኩሱ ቀጥሏል፣ በግጭቱ 6 ሰው ሞቷል

May 1, 2014
ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ከጎንደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል (ነገር-ኢትዮጵያ)

——————————
ነገረ-ኢትዮጵያ – ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታ አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ቤቶችን ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን ወቅት (ከቀኑ 6፡ 43) ተኩስ እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎቹ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ በተላለፈበት ወቅት ህገ ወጥ አለመሆናቸውን፣ ካልሆነም መንግስት ቅያሬ ቦታና ጊዜ መስጠት እንዳለበት በመግለጽ አንለቅም ብለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዛሬው ቀን ግጭቱ የተነሳውም አፍራሾቹ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸውን ቤቶች ቀለም በመቀባታቸውና ህዝቡም እንዳይቀቡ በመከልከሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በግጭቱ ፖሊስ፣ ፌደራልና ልዩ ኃይል የተሳተፈበት ሲሆን ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የአካባቢው ወጣቶች ላይ ድብደባና እስራት እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ‹‹ወጣቶችን እንደ እንሰሳ በአንድ ገመድ አስረው እየደበደቧቸው ነው፡፡ ህዝብ በጅምላ እየታሰረ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ቢያቆምም በአሁኑ ወቅት በሶስቱም ሰፈሮች ጥይት እየተተኮሰ ነው›› ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የተወሰደው እርምጃ የጎንደርን ህዝብ በማስቆጣቱ ከዚህ የባሰ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል ሲሉም ገልጸውልናል፡፡ በግጭቱ ወቅት የመጀመሪያዋ የሞት ሰለባ የሆነችው ልዩ ኃይል ቤቷ እንዲፈርስ ቀለም ሲቀባ የተቃወመች የልጆች እናት እንደሆነችም ታውቋ፡፡

ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

May 1, 2014
ሐራ ተዋህዶ

ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት አያያዝና አጠባበቅ ላይ ለዛሬ የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጥናታዊ ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

  • ዛሬ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 – 11፡00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም አዲሱ አዳራሽ ‹‹ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲሁም አያያያዝና አጠባበቅ›› በሚል ርእስ የተጠራው የጥናት ጉባኤ ክልከላ መንሥኤ ‹‹የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለትን ባልተከተለ መልኩ በቀጥታ የአድባራትንና የገዳማትን አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ስብሰባ መጥራት›› የሚል ነው፡፡

  • ለጥናታዊ ጉባኤው የተጠሩት የገዳማትና አድባራት አለቆች ቤተ መዘክር ያላቸው ሦስት አብያተ ክርስቲያን ብቻ መኾናቸውን የገለጹት የጉባኤው አስተባባሪዎች በበኩላቸው÷ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች፣ ምሁራንና እንግዶች ጥሪ ያደረገው ዕቅዱና አስፈላጊነቱ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ቀርቦ ከተመከረበትና ከተፈቀደ በኋላ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡

  • ፓትርያርኩ ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነበትን አሠራር በመሻር ማንኛውንም ስብሰባዎቹንና ጉባኤዎቹን ኹሉ ያለልዩ ጽ/ቤታቸው ፈቃድ እንዳያካሒድ ከሕጉ ውጭ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በላኩት የልዩ ጽ/ቤታቸው ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡

  • የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የጥናታዊ ጉባኤውን መከልከል በተመለከተ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደደው፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ስለጉባኤው እንደሚያውቁና ዝግጅቱም የአሠራር ክፍተት እንደሌለበት ለልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ በማሳወቅ ሊታገድ እንደማይገባው በመከራከራቸው ነው፡፡

  • ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የዋናውን መሥሪያ ቤት ማለትም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን መምሪያዎችና ድርጅቶች ጨምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎች ኹሉ በበላይነት የማስተዳደር ሥልጣንና ተግባር የሚሰጠው ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ነው፡፡ በዚኽ ረገድ የፓትርያርኩ ሓላፊነት በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጡ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በፊርማቸው የማስተላለፍ፣ በተግባር ላይ መዋላቸውንም መከታተልና መቆጣጠር ነው፤ ፓትርያርኩ የሚፈጽሟቸው ተግባራት ካሉም ዓበይትና የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ ያረፈባቸው መኾን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡

  • በፓትርያርኩና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሥራ አለመግባባቶች እየተባባሱ የመጡ ሲኾን መንሥኤውም÷ በአማሳኞችና ጎሰኞች የሚመከሩት ፓትርያርኩ የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ጨምሮ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የሥራ ዘርፎች በቀጥታ የመምራትና የማስተዳደር ሓላፊነት ያለባቸውን ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በመጋፋት የጀመሩት አካሔድ ነው፡፡

  • ፓትርያርኩ የሚመለከታቸውንና የማይመለከታቸውን ዐውቀውና ለይተው በብቃት የመምራት አቅም ያጡትን ያኽል በዙሪያቸው የከተሙ አማሳኞችንና ጎጠኞችን መሸጋገርያ ያደረገውን ውጫዊ ተጽዕኖ በቀጥታ ተቀብሎ ለማስፈጸም የሚታይባቸው ፍጥነትና ታዛዥነት በእጅጉ እንዲናቁና እንዲጠሉ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡

*           *           *

  • ጥናታዊ ጉባኤው÷ ማኅበረ ቅዱሳን በመተዳደርያ ደንቡ መሠረት ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማት፣ ዕድገት፣ ታሪክ፣ ቅርስና መሰል አርእስተ ጉዳዮች ጥናት የሚያደርጉ ሰዎችን በተለይም ወጣት ምሁራንን ለማበረታታትና በተቻለው ኹሉ ለመርዳት፤ ሃይማኖታቸውን የሚጠብቁ፣ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚከባከቡና ሀገራቸውን የሚወዱ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት በተጣለበት ሓላፊነት መሠረት ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ተያያዥነት ባላቸው ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ለማከናወን ባቋቋመው የጥናትና ምርምር ማእከል በየኹለት ወሩ የሚካሔድ መደበኛ መርሐ ግብር ነው፡፡

  • የማኅበሩ የጥናትና ምርምር ማዕከል በየኹለት ወሩ የሚያካሒደው መደበኛ ጥናታዊ መድረክ አካል የኾነውና የሚመለከተው የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ዝርዝር ይዘቱን ከአንድ ወር በፊት በጋራ ውይይት ጭምር እንዲያውቀው ተደርጎ የተጠራው ጥናታዊ ጉባኤ፣ በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲኹም ጥበቃ ላይ ያተኮረ መኾኑ የመርሐ ግብሩ መግለጫ ያመለክታል፡፡

  • ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ ‹‹ዜና መጻሕፍተ ብራና›› በተሰኘውና ለሦስተኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጥናት ጉባኤ ባቀረቡት ጽሑፋቸው እንደገለጹት÷ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ገበታቸው የወርቅ የኾነ፣ የብርዓቸው አጣጣልና የብራናቸው ንጽሕና፣ የቅርፃቸው ማማርና ውበት ሲመለከቱት በእውነት የእነርሱን መልክና ቅርፅ የኑሮ ቤት አድርጎ መኖር እንጂ በዚኽ ዓለም በሥጋዊ ኑሮ ታስሮ መኖርን አያስመኙም፡፡

  • ከቅዱሳን ገድላትና ድርሳት ባሻገር አያሌ ‹የቴዎሎጊያ እና ፊሎሶፊያ› ሀብት ያካበቱት ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በይዘታቸው ‹‹እግረ ኅሊና ያልደረሰበት፣ የአእምሮ ክንፍ ያልበረረበት የተሸሸገ ጥበብና ያልተሞከረ ስውር ፍልስፍና›› የተካበተባቸው ናቸው ያሉት ሊቁ÷ ያልተከፈተውን የዕውቀት ጎዳና፣ ዓይን ያላየውን ዦሮ ያልሰማውን በጥበበኞች ያልታሰበውን ብልሃትና ሥነ ጥበብ መፈለግና መሻት ፈልጎም ማግኘትና አግኝቶም በፍሬውና በመልኩ መጠቀም ከአኹኑ ትውልድ የሚጠበቅ አዲስ አለኝታ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ የምሥራች መኾኑን አመልክተዋል፡፡

  • የተማረው ትውልድ የጠፋባትን የወርቅ ቀለበት ለማግኘት ባጡ፣ ቆጡ፣ ማዘንቱ፣ ማቶቱ ሳይቀር ኹሉንም በጥንቃቄ እያገላበጠች የምትፈልገውን ሴት መምሰል እንዳለበት ሊቁ በጽሑፋቸው መክረዋል፡፡ የበሬ ቆዳው በገዛ ሞራው እንዲለፋና እንዲለሰልስ የሀገራችን መልክና ቅርፅ በገዛ ሥነ ጽሑፋችንና ቅርፃችን ማሣመር እንድንችልና በዝግ ቤት ከየቤተ መቅደሱ ምህዋርና ከዋሻ ውስጥ ወይም ከመንደርና ደንበኛ ካልኾነ ዕቃ ቤት ተደብቆ ትውውቁ ከሌሊት ወፍና ከአይጥ መንጋ ጋራ የኾነውን የአባቶቻችንን ሥነ ጽሑፍ እያሠሥንና እየመረመርን ለተከታዩ ትውልድ እንድናቆይም በጥናታቸው አደራ ብለው ነበር፡፡

  • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች የበጀት እጥረትንና የሰው ኃይል ውሱንነትን በመጥቀስ ተግባራቸውን ማከናወንና የታሰበውን ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደተሳናቸው ከሰሞኑ የስድስት ወር ዕቅድ ክንውን ሪፖርት በተረዳንበት ኹኔታ ያልነበሩና የሌሉ ለመኾን የተቃረቡትን ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ላይ ያተኮረው ጥናታዊ ጉባኤ የተከለከለበት ዋነኛ ምክንያት ታድያ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ እንደተመለከተው ዝግጅቱን ካለማወቅ አልያም የዝግጅት ሒደቱ የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለት አልተከተለም ከሚለው የተለመደ የማሰናከያ ስልት ጋራ በርግጥም የተያያዘ እንዳልኾነ ግልጽ ነው፡፡

  • የልዩ ጽ/ቤቱ የክልከላ ውሳኔ ከታወቀበት ከትላንት ቀትር ጀምሮ ደብዳቤውን እያሰራጩ የሚገኙት በፓትርያርኩ ዙሪያ በአማካሪነትና ረዳትነት ስም ከተጠጉት እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ የዓላማና የጥቅም ግንኙነት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነኃይሌ ኣብርሃ መኾናቸው ሲታይ የክልከላ ውሳኔው ምንጭ፣ የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ከታገደበት የካቲት ወር ጀምሮ የተጠናከረውና ማኅበሩን ብሎም ቤተ ክርስቲያኒቱን የማዳከም ልዩ ተልእኮ ባላቸው ባለሥልጣናት ጭምር ተደግፎ የቀጠለው ጫና ስለመኾኑ ግልጽ ያደርገዋል፡፡

  • የማኅበሩ አመራር ስለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የክልከላ ደብዳቤ ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ መምከሩ የተገለጸ ሲኾን በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት የጽሑፍ ምላሽ እንደሚሰጥ ተመልክቷል፤ የጎሰኝነት ሰለባ በመኾንና ለአማሳኞች ሽፋን በመስጠት በበታች ሠራተኞች ዘንድ ሳይቀር ክፉኛ እየተናቁና እየተጠሉ በመጡት ፓትርያርክ ዙሪያ የተኮለኮሉትን ጥቅመኞች የማጋለጥ እንቅስቃሴም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እየተገለጸ ይገኛል፡፡

Ethiopian Orthodox Church, Mahibere Kidusan

ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!

May 1, 2014
Ginbot 7 Ethiopian opposition partyግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል።
የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።
ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋል። ኦህዴድ በወያኔ ቅጥረኛነት የኦሮሚያ ወጣቶችን በማስጨፍጨፍ ላይ ያለ እኩይ የአድርባዮች ስብስብ ነው።  ወጣቶች የተቃወሙት ይህንን ነው።እነዚህ ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባቸዋል። ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል። የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል ያገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ ያገባናል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድ ጥሪ ያደርጋል።  በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ  የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።
የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይን ያነሱ ወጣቶች ብቻ  አይደሉም። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ናቸው። ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ  ካለቀ በኋላም አልተፈቱም።  ይህ ሰቆቃ ማብቃት አለበት።
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ESAT Kignit Darge Meshesha 01 May 2014 | ESAT Tube

ESAT Kignit Darge Meshesha 01 May 2014 | ESAT Tube