Friday, 31 January 2014

ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ::(አብርሃ ደስታ )

January 30, 2014                                          
በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ (እንደሚፈፀም) አስቡ። በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም። የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ። በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል። በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል። እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው። ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም። ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው። እናንተ ከስልጣን ወርዳቹ ስልጣን የህዝብ ሲሆን፣ ፍትሕ ሲነግስ፣ እኩልነት ሲሰፍን ለፈፀማችሁት ወንጀልና ላደረሳችሁት በደል በሕግ እንደምትጠየቁ አያጠራጥርም። በስልጣን የኖረ የለም። እንኳን አምባገነኖች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችም በስልጣን ኮረቻ ተቀምጠው ለዘላለም አይኖሩም።
ምናልባት እናንተ ምግባራችሁ አውቃቹ በህዝብ ስትተፉ ሀገር ለቃችሁ በመውጣት ለማምለጥ ትሞክሩ ይሆናል። ገንዘቡም አላቹ። ሁሉም ካድሬዎች (በሰዎች ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ እየታዘዙ ያሉ የህወሓት አባላት) ግን እንደናንተ (እንደ ህወሓት መሪዎች) ከሀገር ወጥተው ለማምለጥ ዓቅሙ የላቸውም። ደግሞ ዓቅሙ ቢኖራቸውስ ለምን በሰሩት ጥፋት ከሀገራቸው ለመሰደድ ይወሰንባቸባል? የህወሓት ባለስልጣንናት ከስልጣን ወርደው በሀገራቸው በሰላም የሚኖሩበት ሁኔታ ለምን አያመቻቹም? ለምን መርሃቸውን ከ «ስልጣን ወይ ሞት» ወደ «ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ በሀገር በሰላም መኖር» አይቀይሩም? ለካድሬዎቹስ አያስቡም እንዴ? የህወሓት ዕድሜኮ ትንሽ ነው። ህወሓት ሲሞት የህወሓት አባላትም ከህወሓት ድርጅት ጋር አብረው መሞት የለባቸውም። ህወሓትም ስልጣን ለህዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ ፓርቲ ሁኖ መቀጠል ይችል የለ?! ዕድምያችሁ ከህወሓት ድርጅት ዕድሜ በላይ እንዲሆን አድርጉ።
እኛ ሰለማዊ ታጋዮች ነን። ያላቹ ሃብትና ጠመንጃ በመጠቀም እኛን መደብደብ፣ ማሳሰር፣ ማሰቃየት፣ መግደል ትችላላቹ። አምባገነን ስርዓት የሚችለው ነገር ቢኖር ሰው ማሳሰርና መግደል ነው። የዓላም አምባገነን መሪዎች በማሳሰርና በመግደል የስልጣን ዕድምያቸው ዘለአለማዊ ማድረግ ከቶ አይቻላቸውም። ዛሬ እኛን ብትደበድቡና ብትገድሉ ዕድምያቹ እያሳጠራቹ እንጂ እያሸነፋቹ አይደላችሁም። እኛ ብንገደል ሌላ ሰው አለ። ሁሉም ሰው መግደል አይቻልም። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ከተገደለ ማንን ትጨቁናላቹ? የሚጨቆን ሰው ያስፈልጋችኋል። ሰው ጭቆና ሲበዛት በመሪዎቹ ላይ ያምፃል። እናም ትሸነፋላቹ። አምባገነን ተሸናፊ ነው። የማይሸነፍ ህዝብ ብቻ ነው። ምክንያቱም ህዝብ ለጭቆና አይነሳም። እኛን በማሰቃየት ሰለማዊ ትግሉ መግደል አይቻልም። ሰለማዊ ትግሉ በመግደል የሰዎች የነፃነት ጥያቄ መግደል አይቻልም። የሰዎች የነፃነት ጥያቄ በመግደል ሰዎችን ለዘላለም መጨቆን አይቻልም። ስለዚህ መሸነፋቹ አይቀርም።
የሰለማዊ ትግል በር ባትዘግቡን መልካም ነው። ምክንያቱም ደም መፋሰሱ፣ ጦርነቱ፣ መጠፋፋቱ አንፈልገውም። እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው። መንገዳችንም ሰለማዊ ነው። የሰላም በር ሲዘጋብን እጆቻችንና እግሮቻችን አጣጥፈን እንቀመጣለን ማለት ግን አይደለም። አንድ በር ሲዘጋ ሌላ በር ማንኳኳታችን ግድ ነው። ነፃነት እንፈልጋለንና። «መታፈን ይብቃን!» ብለን ተነስተናል። ስለዚህ ትግላችን በምንም ዓይነት ስትራተጂ ማስቆም አይቻልም። የሚቻለው ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ነው። ዴሞክራሲ ማስፈን ነው። ገዢዎች በሐሳብ መከራከር ሳይችሉ ሲቀሩ ወደ ሀይል እርምጃ እንደሚወርዱ እናውቃለን። ሐይል መጠቀም የሽንፈት ምልክት ነው። ህወሓት የፈሪዎችና የጨካኞች ስብሰብ መሆኑ አውቅ ነበረ፤ ወደ ድንጋይ ውርወራ ፖለቲካ ይወርዳል የሚል ግምት ግን ፈፅሞ አልነበረኝም። መንግስት ወንጀልን መከላከል ሲገባው ወንጀል ፈፃሚ ሆነ። ህወሓት ዉስጧ መበስበሱ እየሸተተን ነው። ምናለ ድንጋይ ባለመወርወር ገመናችሁ ባታጋልጡ? ለማንኛውም አደብ ግዙ የምትሰሩትን እወቁ። በሃይል የሚሆን ነገር እንደሌለ ተረዱ። ካለፉ ስርዓታት ታሪክ ተማሩ። ህዝብ እያያቹ ነው።

ESAT Daily News Amsterdam Jan 31 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 31 2014 Ethiopia | ESAT Tube

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ  የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ትናንት የዩኒቨርስቲ ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ በነበሩ  ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ  የአንዲት ተማሪ ጆሮ መቆረጡንና በርካታ ተማሪዎች እጆቻቸውና እግሮቻቸው መሰበሩን ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል።
ችግሩ የተፈጠረው የውሃ ኢንጂነሪንግር ተማሪዎች የትምህርት ዘርፍ ለውጥ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። ዩኒቨርስቲው የትምህርት-ዘርፍ  ለውጥ እንደማያደርግ እና መማር የማይፈልጉ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣት እንደሚችሉ ማስታወቂያ መለጠፉን ተከትሎ፣ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በሚወጡበት ጊዜ የፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ በመጠበቅ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ደብደባ ፈጽመዋል።
በአሁኑ ጊዜ የውሃ ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ በፖሊሶች እየተጠበቁ ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርስቲውን አስተዳደር ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የአማራው ክልል መሪ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቁ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል።
ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ፕሬዚዳንቱ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት ብለዋል።
አማራው “በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው” ያሉት ምክትል አስተዳዳሪውና የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊው፣ ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው  የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት ያሉት አቶ አለምነው፣ ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም ሲሉ ድምድመዋል።
ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው ብለዋል። ያንን ምግብ እየተመገበ እንደሚያቅራራም ገልጸዋል።
አንዳንድ የብአዴን አባላት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ንግግር እጅግ እንዳበሳጫቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
የብአዴን ካድሬዎች አንቀጽ 39 ለምን አይወጣም በማለት ላነሱት ጥያቄ፣ እኝሁ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ  ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር በማለት መልሰዋል ። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ መታየቱን ም/ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ ,,,,,,,,,

January 31, 2014
መስፍን ወልደ ማርያም
ጥር 2006
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ቀላሉ ዘዴ መሰንከል ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
ለሰውም ቢሆን ዓላማውም ዘዴውም አንድ ነው፤ ልዩነቱ የሰው ልጅ እንቅስቃሴው አካላዊ ብቻ ሳይሆን አእምሮም መንፈስም ስላለው መሰንከሉ አካላዊ ብቻ አይሆንም፤ እንዳያስብ አእምሮውን ማፈን ግዴታ ይሆናል፤ ለአምባ ገነኖች ችግር የሚመጣው የሰዎች አእምሮ ሲያስብ ነው፤ ያሰበውንም መናገርና መጻፍ ሲጀምር ነው፤ ‹‹መጥፎ ሀሰብ››፣ ማለትም ለጨቋኞቹ የማይበጅ ጥሩ ሀሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ፣ በራድዮና በቴሌቪዥን ቢተላላፍና ብዙ ሰዎች ቢሰሙት አገር ይረበሻል፤ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ ይሆናል፤ አገዛዙ ሕዝቡን ለመሰንከል ብዙ ዘዴዎች አሉት፤ በስም ማጥፋት እንዳልከሰስ ዘዴዎቹን አልናገርም፤ ነገር ግነ ክፉ እንቅልፍ ይዞት የሄደ ካልሆነ በቀር የማያውቃቸው የለም፤ የማያውቅ ካለ በየቤቱ እየመጡ ይተዋወቁታል፡፡
ወያኔ የትግራይን ሕዝብ አንድ ለአሥር ጠርንፎ ከሃያ ዓመታት በኋላ ውሉ ጠፋበትና ጥርነፋው ላላ! የቂል ነገር ለትግራይ ያልተሳካውን ጥርነፋ በቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይም ለመዘርጋት አቅዷል ይባላል፤ የወያኔ መሪዎች በአዲስ አበባ ቤቶችን አፍርሰው መንገድ ከሠሩ በኋላ ባቡር ትዝ ሲላቸው መንገዱን አፍርሰው ሀዲድ ለመሥራት ይሞክራሉ፤ ጥርነፋ በትግራይ እንዳልሠራ እያዩ በቀሩት ክልሎች ያሉትን ሰዎች ለመጠርነፍ ይፈልጋሉ፤ ጭንቅላተቸው ውስጥ ያለው ምንድን ነው ያሰኛል፤ እንኳን እንዲህ መክሸፉ በተግባር እየታየ ይቅርና ማሰብ ለሚችል በሀሳብም ደረጃ የከሸፈ ነገር ነው፤ እንስሳትን መሰንከል ቀላል ነው፤ ጉልበትን በበለጠ ጉልበት ማሸነፍ ነው፤ መናገርን መሰንከል ግን አይቻልም፤ ምላሱ ቢቆረጥበትም ሰው ሌላ መንገድ ይፈልጋል፤ በደርግ ዘመን ከኤንሪኮ በር ላይ የማይጠፋ ወፍራም ድሪቶ የሚለብስ ዲዳ ሰው ነበር፤ አንዳንድ ቀን ያየውን ‹‹ሲያወራ›› አንዳንዶች ያስይዘናል በማለት ይሸሹት ነበር፤ ያያቸው ወታደሮች መሆናቸውን በራሱ ላይ መለዮ በእጁ ያሳይና ሹመታቸውን ደግሞ በትከሻው ወይም በክንዱ ላይ እያመለከተ ሰዎችን ጨረሷቸው ለማለት በእጁ አፉን ጥርግ ያደርጋል፤ እኛ እንደሰማነው ወታደሮቹም እየገባቸው በየጊዜው ይደበድቡት ነበር፡፡
ማሰብን መሰንከል ደግሞ ከመናገርን ወይም መጻፍን ከመሰንከል የበለጠ አስቸጋሪ ነው፤ ለኢጣልያ የገበረው ባንዳ ሁሉንም አየነው፤ አማኑኤል ደግ ነው፤ እያለ የኢጣልያኑን ቄሣር አሞገሰና በጊዜው በላበት፤ በኋላ የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ሲመለስና ሲቋቋም ባንዳው ተገልብጦ ኢየሱስ ክርስቶስን ማለቴ ነው አለ! ሰምና ወርቅ የሚባለው የተፈጠረው ሀሳብን የመግለጽ መሰንከልን ለማክሸፍ ነው፤ ማሰብን መሰንከል እስካልተቻለ ድረስ ሀሳብን መግለጽን መሰንከል አይቻልም፡፡
የሰንካዮችን ጭንቅላት አልፎ ሊሄድ የማይችል አንድ ታሪክ ደጋግሞ ያረጋገጠው ነገር አለ፤ ልፋ ያለው ዳውላ ይሸከማል፤ እንደሚባለው ጨቋኞችና አፋኞች እንደእንስሳ ለሆዳቸው ብቻ የሚገዙ ታማኝ አገልጋዮችን እየመለመሉ ዙሪያቸውን ያጥራሉ፤ ነገር ግን የሆዳሞቹ አገልጋዮች በሀሳብ ወረርሺኝ ሲመታና ሲነቃ አፋኞች ማሰብን ለመሰንከል ባለመቻላቸው የራሳቸው ታማኝ አገልጋዮች ይገለብጧቸዋል፤ ይህ የታሪክ እውነት ቢገባቸው ማሰብን መሰንከል መሞከሩ ቀርቶ ሀሳብን መግለጽንም ለመሰንከል አይሞክሩም ነበር፤ ምክንያቱም ማሰብ በሚቻልበትና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት አገር ሀሳብ አይፈነዳም፤ ሀሳብ እንደሚፈነዳ፣ ከፈነዳም በኋላ እንደወረርሺኝ መንደር ሳይመርጥ፣ ጎሣ ሳይመርጥ፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደው፣ ሀሳብ ብቻ ሊያግደው የሚፈልገውን ኃይል ሁሉ በዘዴ እያሽመደመደ ይንቀለቀላል፤ ይስፋፋል፡፡
አብርሃም ሊንከን አለ እንደሚባለው ‹ጥቂት ሰዎችን ሁልጊዜ ማታለል ይቻላል፤ ሁሉንም ሰው ለጥቂት ጊዜ ማታለል ያቻላል፤ ነገር ግን ሁሉንም ሰው ሁልጊዜ ማታለል አይቻልም፤› ለጥቂት ጊዜ የታለሉት ማታለልን ይማሩና ያታልላሉ! የተኙ መስለው ያሸልባሉ፤ የሚያለብሱ መስለው ያራቁታሉ፤ የሚያከብሩ መስለው ያዋርዳሉ፡፡
በመጨረሻም ተጠርናፊዎች ጠርናፊዎች ይሆኑና መክሸፍ ይቀጥላል! ጠርናፊም እስኪጠረነፍ ሌላ ነገር አላስተማረም፤ ተጠርናፊም ራሱን ከጥርነፋ እስኪያወጣ የተማረው ሌላ ነገር የለም፤ ማስረጃ ከተፈለገ ተቃዋሚ በሚባሉት ቡድኖች ውስጥ ሞልቶአል!!
መጨረሻም በኢጣልያ የአገዛዝ ዘመን አምስት ለአንድ ጥርነፋ ማለት አንድ ኢጣልያዊ ለአምስት አበሻ ማለት ይሆንና አንድ ጠርናፊና አምስት ተጠርናፊዎች በቋንቋና በባህል የማይግባቡ፣ በታሪክም ሆነ በማኅበረሰብ ኑሮ ዝምድና የሌላቸው፣ የወደፊቱም ሕይወታቸው በተረጋገጠ የበላይነትና የበታችነት ደረጃ የተወሰነ ስለሚሆን ጥርነፋው ትርጉም ያለው ሊመስል ይችላል፤ አምስት አበሻ ለአንድ አበሻ መጠርነፍ ግን በጠርናፊም ሆነ በተጠርናፊ በኩል ብርቱ የማሰብ ችግር (ከመንግሥተ ሰማያትም ቢሆን አመጣሃለሁ! ያለው ሰውዬ ዓይነት) ከሌለ በቀር ከንቱ ነው፤ በቀላሉ አንድ ለአምስት በማድረግ ዓላማውን መገልበጥ ይቻላል! አንድና አምስት ስድስት ነው፤ እንዲሁም አምስትና አንድ ስድስት ነው፤ ሁለትና አራት ስድስት ነው፤ ሦስትና ሦስትም ስድስት ነው፤ በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ሰው የምንለው ማንን ነው? ከብት የምንለው ማንን ነው? ሁሉም ሰዎች ከሆኑ ጠርናፊና ተጠርናፊ አይኖርም፡፡

በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ

January 30, 2014
ጥር 22/2006 (BlueParty Ethiopia)
እስካሁን 14 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር የታሰሩ ሲሆን ከታሰሩት ውስጥ አራት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ይገኙበታል፣
1. ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ)
2. ብርሃኑ ተ/ያሬድ (የሀዝብ ግንኙነት)
3. ዮናታል ተስፋዬ (የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
4. ይድነቃቸው ከበደ (የህግ አማካሪ)
A protest call in Gonder, Ethiopia


ሁለት ሹፌሮች እና አንድ ፊልም አንሺም (Cameraman) ከታሳሪዎቹ ውስጥ ናቸው፣ በአሁኑ ስዓት ታሳሪዎቹ በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣብያ ሲገኙ ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ) እና አግባው ሰጠኝ ወደ ጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወስደዋል።
ጥር 25 2006 ዓ.ም. የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለልን ህገወጥነት በተመለከተ በጎንደር መስቀል አደባባይ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሉኡካን ቡድን በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር የገባው ቡድን በጠቅላላ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ የቅስቀሳው አባላት በጎንደር ከተማ እና በተለያዩ ቦታዎች ቅስቀሳውን እንደጀመሩ የፓሊስ አባላት ፈቃድ ስለሌላችሁ መቀስቀስ አትችሉም ያሏቸው ሲሆን አባላቱም በህጉ መሰረት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ የሚጠበቅብን ስላልሆነ ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን በመሆናችን ህጋዊዎች ነን በማለታቸው ፓሊስ በማዋከብና በመደብደብ ጎንደር ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ መጉላላትና እንግልት እያደረሱባቸው ይገኛል፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችም ፖሊሶቹን ምን አደረጓችሁ በማለት እና ይህ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው በማለት አባላቱን ከፖሊስ ለማስለቀቅ የተቻላቸውን ያደረጉ ሲሆን ፖሊስም ሐይል በመጨመር ህዝቡን በዱላ በማባረር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድኑን እንዲሁም የጎንደር የፓርቲው መዋቅር አባላትን ጨምሮ አስረዋቸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ እየጠየቀ ሲሆን ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ለማድረግ ሌላኛው የሉኡካን ቡድን ከአዲስ አበባ በዛሬው እለት መንቀሳቀሱ ታውቆአል፡፡



















Thursday, 30 January 2014

ESAT Daily News Amsterdam Jan 30 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 30 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Yesamintu Engida with Engineer Yilikal Getinet Part I | ESAT Tube

ESAT Yesamintu Engida with Engineer Yilikal Getinet Part I | ESAT Tube

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

January 29, 2014


ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡
    “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።”
ይህ በግልጽ የሚታየው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች አንጸባራቂ ሥዕል ነው። ይህ ሁኔታ በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሀግሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለ የመንግሥት ሕገ ወጥነት ነው!


በኤኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ግዙፍ ነው። ድህነት ከመቀረፍ ይልቅ፡ ሥር እየስደደ መሆኑን ብዙዎች ያማርራሉ። ለጥቂቶች ግን ሀገሪቱ ምድራዊ ገነት ሆናለች። ሕዝቡ እየተደበደበም፡ በየቀኑ አልዋጥ ባይ ፕሮፓጋንዳ በግድ እየተጋተ ነው!
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ለብዙዎቹ የአዲስ አበባ መሽቀርቀር እንደአጠቃላይ የሃገሪቱ የልማትና ዕድገት መለኪያ ተደርጎ እንዲወሰድ የተቀነባበረ ጥረት የሚድረገው። የምርጫ ዘመን በመቃረቡ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስንዴ ለውጭ ገብያ ሻጭ ልትሆን ነው በማለት ጥር 18፣ 2014 አርሲ ሆነው ማስማታቸው ልብ ሊባል ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በልማት ገና ሀ ሁ … ላይ ናት – በምግብ 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን በቀን ሶስቴ ሳይሆን፡ አንዴም መመገብ ያልቻለች አገር ናት! ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የምዕራቡ ዓለም፡ በቋሚነት ከ10 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክዓመት ዓመት በዓለም አቀፍ እህል ዕርዳታ ሕይወት በመስጠት ላይ ያለው?


ከሁሉም ጎልቶ የሚነገርለትና የሕወሃት ስዎችም ቶሎ የሚስፈነጠሩበት የአገሪቱ ከትላልቅ ጦርነቶች መላቀቋ ነው። ስለዚህም የሕወሃት ስዎችና ደጋፊዎቻቸው በመመጻደቅ ሲናገሩ መስማቱ የተለመደ ሆኖአል። በዚህም መነሻነት፡ እንዲህ ይላሉ: ባለፉት 20 ዓመታት፡ ሕወሃት ለረዥም ዘመናት አገሪቱን ያደሙትን ጦርነቶች አቁሞ ልማት ላይ እንድታተኩር አደረገ የሚባለው በብዛት ይሰማል። የሕወሃት ስዎችም ይህ በተደጋጋሚ እንዲነገርላቸው ብዙ ጥረቶች አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። እራሳቸውም በተደጋጋሚ እራሳቸውን በዚህ ሲያሞካሹ ይሰማል፤ ለውጭ የፕሮፓጋንዳ ድርጅቶችም ይህንን እንዲያስተጋቡላቸው፡ ከፍተኛ ክፍያዎችን በየጊዜው ፈጽመዋል።


እስከዛሬ አጥግቢ ግንዛቤ ያላገኘው ግን፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የጦርነቶች አጋጋይ ሕወሃት መሆኑ ነው። የኤርትራንና የትግራይን መገንጠል ጉዞ በተግባር ሲተረጉም ኖረ። ቀኑ ደርሶ ጅብሃ ሲገነጠል፡ ሕወሃት ባዶ የሥልጣን ወንበር ስለታየው፡ ኢትዮጵያዊነትን መረጠ። በትግል አጋሩ ጅብሃ ዘንድ ይህ እንደክህደት እንዳይታበት – በስላም ሂዱ፡ ኢትዮጵያ ከእናነተ ስላም እንጂ ሌላው ቀርቶ የባህር በር እንኳ አያስፈልጋትም አለ። ይህንን አስመልከቶ፡ በየካቲት ወር 1994 ስብሃት ነጋ ለዓለምስገድ አባይ በስጡት ቃለ መጠይቅ የሕወሃት ቀደምት ፓሊሲ መገንጠል ሆኖ እስክ 1985 መቆየቱን ያረጋግጣሉ። ከቃለ መጠይቁ ውስጥ በጣም አሰገራሚው ነገር ግን፡ ብዙ የሕወሃት ተዋጊዎች ኢትዮጵያዊነትን ገና ድሮ አሽቀንጥርረው የጣሉ በምሆናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይ ከአማራ ጋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝትን በሙል ልብ አለመቀበላቸውን ነው ያመላከቱት [See Identity Jilted: Re-imagined Identity (1998)]።


ያለፈው አልበቃ ብሎ፡ ዛሬም ሕወሃት ሀገሪቱ ውስጥ ሽብርና ፍርሃት በማንገስ የውስጥ ግጭቶችን በመተንኮስ: የተለያዩ ብሄረስቦችን አባሎች በማፈናቀልና ችግሮችን በማባባስ ተጠቃሚ ለመሆን ሲምክር ይታያል – ድ/ር ቴድሮስ ፍጹም “እኔ ያለሁበት ፓርቲ ውስጥ ይህ አይደረግም!” ብለው ዝናቸውን አጋልጠው ቢገዘቱም። ነገሩ ግን፡ ዛሬም በምሥራቅ በተለያያዩ የኦሮም ክፍሎችና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች መካከል፡ በደቡብም እንዲሁ በተለያዩ ጎሣዎች መካከል፡ አማራንና ኦርሞችን በማጋጭት፡ ጥላቻና መቃቃርን በዜጎች መካከል ለመፍጠር ብዙ ሲሞክር ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎችም፡ ለምሳሌ ቦረና፡ ተሳክቶለት ስሞኑን የብዙ ዜጎች ደም ፈሷል፤ ሕይወትም ተቀጥፏል። ቤት ንብረቶችም ተደምስሰዋል። ሌላው ቀርቶ፡ የሕክምና ባለሙያ የነበሩት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ – የዛሬው የሃይማኖትች ጉዳይና የጸረሽብር ኤክስፐርቱ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም – ኬንያ በሥጋቷ ምክንያት (2012ን በማስታወስ) ልተቀስቅሳቸው ብትሞክርም፡ ነገሩ አውቆ የተኛ ቢነቀንቁት አይሰማ ሆኖ እሳችውም እንደክረምት ድብ ክፉኛ አሸልበዋል።


ለማንኛውም፡ በዓለም ላይ እንደሕወሃት የተሳካለት የለም – ዕድሉን ሃገራችንን ለማሻሻል በሚገባ አልተጠቀመበትም እንጂ! ስለሆነም ክሥራ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ፡ ዕውነትን ተናግሮ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት ይልቅ፡ ሁሉንም ስው ማሞኘት እንችላለን በሚል ትዕቢት ብዙ የሚያሳፍሩ ተግባሮች ሲያከናወን ይታያል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በበጎነታችው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደጉን የሚመኙ የውጭዎቹ የፖለቲካ፡ የዲፕሎማሲና ኅብረተስባዊ መሻሻሎችን አራማጆች ይህንን የሕውሃትን የሰላም ማስፈን የዋህ መስል ቅጽል በአመኔታ የሚጋሩት በሁለት ተክፈለው ይታያሉ፡ –
(ሀ) በእውነትም ጦርነትና የንጹሃን ዕልቂት መቆሙን፡ ኢትዮጵያ ክድህነት ተላቅቃ ማየት የሚሹ ወገኖች፤
(ለ) ጊዘው የበለጸጉት ሃገሮች ወደታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ዘልቀው በመስፋፋትና በኢኮኖሚ ትብብር ስም የራሳቸውን ኤኮኖሚያዊ፡ የበላይነት ማቆየት የሚሹበት፡ ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያበራክቱበት በመሆኑ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተዳብረው፡ የሕወሃትን ገድል መተረኩ፡ ለሚሹት ዓላማ አንድ ጥቅም ትስስሮሽ መፍጠር የሚያስችል መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ወገኖችም እዚሀ ውስጥ ተስልፈዋል።

ከላይ የተመለከቱት ከተለያየ አግጣጫ ተነስተው ሁለቱም አንድ የሚገናኙበት መጋጠሚያ፡ ስለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንዲስተጋባ ማድረጋቸው ነው። በተለይም በሁለተኝው ክፍል የሚገኙት፡ በተቻለ መጠን ስለኢትዮጵያ በጎውን በማጋነን፡ የሕወሃትን የስብዓዊ መብቶች ጽልመት፡ ጎስኝነት፡ ሙሰኝነት የሚሸፋፍን አመለካከት በምዕራባውያንም ሆነ ምሥራቃዊ ሚዲያዎች ላይ በጊዜው ያስደስኮሩላቸዋል።


በተጨማሪም፡ እነዚህ ሀገሮች ለኢትዮጵያ ግዙፍ ዕርዳታ መፍሰሱን ይደግፋሉ። ነገር ግን ይህ ዕርዳታ በብዙ መስኮች – በተለይም በግብርናው – መስክ የሀገሪቱን ችግሮች፡ በምግብ ምርት እራስን ከማስቻል ይዘት ስሌለው፡ ትኩረታችውም ሆነ ጥረታቸው – በዘለቄታ ሀገሪቱን ከምግብ ዕርዳታ ተመጽዋች ነጻ ለማድረግ አላስቻለም። በመሆኑም፡ እየተደረገ ያለው፡ ትላንት እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ሶስተኛ መንግሥታዊ በጀቷን በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተመጽዋችነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውስጥና የውጭ ፖሊሲዋን በማክራየት እንድትቀጥል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮባታል።


በአሁኑ ወቅት፡ በተለያዩ ምክንያቶች (የስብዓዊ መብቶች አለመከበር ችግር፡ የየራሳቸው የሀገሮቹ የኢኮኖሚ ችግሮች) መንስኤነት፡ ከለጋሽ ሀገሮች በቀጥታ የሚገኝው ዕርዳታ በክፍተኛ ድረጃ ቀንሷል (ክአሜሪካና እንግሊዝ በስተቀር)። በዚህም ምክንያት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚስጠውን ብዙውን የዕርዳታና ብድር ጫና ድርሻ ተሸካሚ ሆኖአል።


ለምሳሌ፡ ሌላው ቀርቶ ስብዓዊ ዕርዳታን እንኳ በተመለከተ፡ 12 የአውሮፓ ኅብረት ሀገሮች (እንግሊዝን አይጭምርም) በ2012 ለኢትዮጵያ በባይላተራል መንገድ ለዕርዳታ ያዋጡት €24 ሚልዮን ሲሆን፡ በ2013 ይህ መዋጮ ወደ €12.4 ሚልዮን ወርዷል። ከነዚህም መካከል ትልቁን ቅናሽ ያደረገችው ጀርመን ናት – ከ€8.2 ሚልዮን ወ €4.2 ሚልዮን ዝቅ በማድረግ። በመሆኑም፡ከዚህም ከዚያም አስባስቦ የበጀት ምንጮች በማስባስብና ተጨማሪ ምክንያቶች በመፍጠር (ነፍስ ወክፈ መልሶ ማቋቋም) በ2013 እንዳደረገው፡ የአወሮፓ ኮሚሽን በ 2011-2013 12 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት እንዲቻል €130 ሚልዮን ለግሷል።
አሁን ለሁሉም ለጋሾች ከባድ የሆነው “የልማት” ዕርዳታውም እንዲሁ በበዙ ጥያቄዎች ላይ መውደቁ መሆኑ ይሰማል።


በዓለም ዙሪይ ያለፉው ሩብ ምዕተ ዓመት የልማት ጊዜ በመሆኑ፡ ብዙ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ይህ ዕድል ቢገጥማትም፡ መሣሪያ ያነገቡት የሕወሃት ሰዎችና አጫፍሪዎቻቸው ግንባር ቀድም ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፡ የትላንቱ ጦረኞችና የዛሬዎቹ የስላም ደጋፊ-መስል የአንድ ብኄረስብ ሰዎች፡ ሆን ብለው ዕኩልነትን የሚጻረር የፖለቲካ፡ የኤኮኖሚ፡ የደህንነትና ማኅበራዊ ፓሊስዎችን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።


ይህ ግን ዘላቂ መሠረት ስሌለው፡ ዛሬ የኤኮኖሚው የጥንድ ዕድገት ውደሳው ጋብ ብሎ፡ ሀገራችን የመንግሥት ብልግናና የሃስት ፕሮፓጋንዳ ከሚመገቡት መካክል ወድቃለች። በዚሁም ምክንያት (ሽፋኑ የውሃ ዕጥርረት፡ ድርቀት፡ የሃይማኖትና የብኄረቦች አለመቻቻልና ግጭቶች ላይ ቢመካኝም)፡ ተደጋጋሚ ዓለም አቅፍ ጥናቶች ኢትዮጵያ ከሚወድቁት የአፍሪቃአገሮች (Failed States) መካከል ተደምራ፡ የወደፊት ጽዋዋ አስፈሪ እንደሚሆን ቀንደኛ ደጋፊዎቿ ድምዳሜ ላይ መሆናቸውን በግልጽ የምንሰማበት ዘመን ላይ ደርስናል።


ድሮስ ቢሆን፡ የሕዝብ ዓመኔታ ያጣ መንግሥት፡ መሣሪያውን ደግኖ በኅይል ለመግዛት ከመሞከር ውጭ ምን አማራጭ አለው? ጊዜው የጥላቻ፡ የክፋትና የቂም በቀል በመሆኑ፡ በአንድ በኩል፡ የሕወሃት ስዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግሞ፡ የኢትዮጵያውያንን ስብዓዊ መብቶች በመግፈፍና መርገጣቸውን በማባባስ፡ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ጎዳን እየገፉ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕድገት ይኖራል?


እንዲያውም፡ የራሱን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ሲል፡ የኢትዪጵያ ሕዝብ ፍላጎትና አመለካከት ሳይጠየቅ ኤርትራን በፊርማው እንድትገነጥል ያደረገ፡ አገሪቱን የባሀር በር ለማሳጣት የደፈረ የመንግሥታዊ ባህልና ኃላፊነትና ግንዛቤ የሌለው ሕወሃት፡ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ቆርጦ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሕዝቡን በቃ! የሚል ድምዳሜ ላይ ማድረሱ አያጠራጥርም!
በዓለም ታሪክ ውስጥም ሕወሃት “ታዋቂ” የሚሆነው፡ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፡ የሀገርን ልኡላዊነትና መሬት ቆርሶ ለጎረቤት ሀገርና ለከፍተኛ ብድር ስጭና ገንዘብ ለዋጭ አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።


ዛሬም ሆነ ነገ፡ ለሀገራችን ዘላቂው መፍትሄ ግን መንግሥት የሕዝብን ፍላጎት ለማክበር መቻሉና ለዚህም ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው። ይህንን ለማድረግ፡ አሁንም ትንሽ የተስፋ መስኮት አለ – የሕውውሃት ስዎች ኃላፊነት የሚስማቸው ቢሁን። ይህ ለሕወሃትና ግብረአበሮቹ ተቀባይ ሳይሆን ቢቀር፡ ቀሪው ምርጫ ሕዝቡ እየተረገጠ መቀጠል፡ ወይንም እነርሱ ከመድረኩ መወገድ ነው።

Tuesday, 28 January 2014

2014 Golden Pen of Freedom awarded to jailed Ethiopian journalist


eskinder_nega
Serkalem Fasil, the wife of Eskinder Nega
eskinder_nega
Eskinder with son Nafkot
Mr Nega was arrested on September 14, 2011 after publishing an article criticising his government’s use of the 2009 Anti-Terror Proclamation to jail and silence critics, including Ethiopian actor and activist Debebe Eshetu.  He was sentenced on 23 January 2012 and denounced as belonging to a terrorist organisation.

In making the award, the WAN-IFRA Board sent a message to the Ethiopian government that misusing anti-terror legislation to jail journalists and those critical of his government is unwarranted and against international protocols, including the Vienna Declaration on Terrorism, Media and the Law.
“This award recognises the courage of Eskinder Nega to speak out despite the risks that saw him jailed under his country’s draconian and overly broad anti-terror laws,” said WAN-IFRA President Tomas Brunegård, speaking on behalf of the Board.

“We call on the Ethiopian government to release Eskinder Nega and all journalists convicted under the sedition provisions, including Solomon Kebede, Wubset Taye, Reyot Alemu, and Yusuf Getachew”, said Mr Brunegård, who recently visited Ethiopia as part of an international mission that found that the country’s publishers and journalists practice journalism in a climate of fear.

The Golden Pen of Freedom is an annual award made by WAN-IFRA since 1961 to recognise the outstanding action, in writing or deed, of an individual, a group or an institution in the cause of press freedom. More on the Golden Pen can be found at
http://www.wan-ifra.org/node/31099

The award will be presented on 9 June during the opening ceremonies of the World Newspaper Congress, World Editors Forum and World Advertising Forum, the global summit meetings of the world’s press, to be held in Torino, Italy.

In an opinion piece published in the New York Times, Mr Nega said of his imprisonment: “I’ve never conspired to overthrow the government; all I did was report on the Arab Spring and suggest that something similar might happen in Ethiopia if the authoritarian regime didn’t reform... I also dared to question the government’s ludicrous claim that jailed journalists were terrorists.”

WAN-IFRA has been vocal in their opposition to Ethiopia’s misuse of anti-terror legislation, writing to late Prime Minister H.E. Meles Zenawi in 2012 requesting the immediate release of Mr Nega and most recently demanding his release, along with four other imprisoned journalists, in a joint international press freedom mission to Ethiopia, conducted with the International Press Institute. The full report from the international press freedom mission can be found at
http://www.wan-ifra.org/node/97172

Mr Nega opened his first newspaper, Ethiopis, in 1993, which was soon shut down by authorities due to its critical reporting. He then, along with his wife Serkalem Fasil, managed Serkalem Publishing House, responsible for newspapers such as Asqual, Satenaw and Menelik, all of which are currently banned in Ethiopia.  He has also had his journalist’s licence revoked since 2005, but continued to publish articles despite the ban.

Mr Nega is no stranger to being imprisoned due to his writings. He was detained at least seven times under Prime Minister Meles Zenawi.  This included a 17-month jail sentence, along with his wife, on treason charges for their critical reporting on the Meles government's violent response to peaceful protests that followed the disputed 2005 elections.

WAN-IFRA, based in Paris, France, and Darmstadt, Germany, with subsidiaries in Singapore and India, is the global organisation of the world’s newspapers and news publishers. It represents more than 18,000 publications, 15,000 online sites and over 3,000 companies in more than 120 countries. Its core mission is to defend and promote press freedom, quality journalism and editorial integrity and the development of prosperous businesses.?

ESAT Daily News Amsterdam Jan 27 2014 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Daily News Amsterdam Jan 27 2014 Ethiopia | ESAT Tube

Monday, 27 January 2014

ስኬታማ ውድቀት (Successful Failure!)



January 27th, 2014
ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል፡፡ ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!


ሰሞኑን ለራሴ የጥሞና ጊዜ እንዲኖረኝ ፈለግሁና በንባባዊ አርምሞ ሰነበትኩ፡፡ በግሌ እንደብዙዎች ሰዎች ብዙ ጉድለት አለብኝ፡፡ ከነዚህ አንድኛው በመሸታ ቤቶችና በግል ግንኙነቶች ከጨዋታዎች ከምሰማው፣ ከመገናኛ ብዙኃን ከምከታተለው፣ በትምህርት ምክንያት ካገኘኋቸው አነስተኛ ግንዛቤዎችና ከጥቂት ንባቦች በስተቀር ስለሀገሬ ታሪክ ብዙም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡ ይህን ትልቅ ክፍተት በተቻለ መጠን ለማጠጋጋት አንድ ሃሳብ መጣልኝ – ማንበብ፡፡


 እርግጥ ነው የጥንታዊቷን ኢትዮጵያን ቀርቶ የትናንቷን አሜሪካን ታሪክም ቢሆን በንባብ ለመረዳት መሞከር አባይን በጭልፋ እንደማለት በመሆኑ ይህን መሰሉን ታላቅ ተግባር በአንድ ሰው ዕድሜ ማከናወን ከባድ ብቻም ሣይሆን ከነአካቴው የሚቻል አይደለም፡፡ ግን ከለዬለት ድንቁርና በተወሰነ ደረጃ መውጣት የሚቻለው ራስን በንባብ ማበልጸግ ሲቻል በመሆኑ ጊዜየ በፈቀደልኝ ጥቂት መጻሕፍትን – ከፊተኞችም ከአሁነኞችም – ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ወደ አሥር ይጠጋሉ፡፡ ከነዚህ ግንዛቤ አስገኚ መጻሕፍት ውስጥ የርዕዮት ዓለሙ “የኢሕአዴግ ቀይ እስክርቢቶ” የሚለው አንዱ ነው፡፡ እመለስበታለሁ፡
የአለቃ ተክለኢየሱስ “የኢትዮጵያ ታሪክ” መጽሐፍ ሌላው ነው፡፡


 ይህ መጽሐፍ ዶክተር ሥርግው በሚባሉ ምሁር የአርትዖት ሥራ እንደተካሄደበት ተገልጾኣል፡፡ ግሩም እሳት ነው፤ ሲያነብቡት እያቃጠለ፣ እየለበለበና ኢትዮጵያዊነትንም እያስረገመ ተነብቦ ማለቁ አይቀርም ያልቃል፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ሥልጣን የማይወዱ መሆናቸውን በማስረዳት የሕይወት ዘመናቸውን እያገባደዱ የሚገኙት ፕሮፌሰር መስፍን የጻፉት “አገቱኒ”ም በስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አንብቤዋለሁ፡፡ “ካረጁ አይበጁ ነው”ና ደግሜ እያነበብኩት መሆኔን እስክረዳ ብዙ ገፆችን ብጓዝም ጊዜና የማንበብ ፍላጎት ሞልቶ እንደተረፈው ሰው ጨረስኩት (በዚች መጽሐፍ ላይም በጨረፍታ ብመለስ ደስ ይለኛል)፡፡ ኢትዮጵያ የማያውቋት ሁሉ ዝናዋን ከሩቅ በመስማት ውዱን ሕይወታቸውን ሣይቀር ሊገብሩላት የፈቀዱ የዓለም ዜጎች እንደነበሩ “ጥቁር አንበሣ” በሚል መጽሐፍ ተጋድሎውን ካነበብኩለት ኩባዊ ሻምበል ልረዳ ችያለሁ፡፡ ይህን “ጉራ” የምቸረችርላችሁ ስለሁለት ምክንያት ነው፤ አንዱ ጉድለትን ለማስተካከል በግድ ወደንባብ መዞር እንደሚገባን በተለይ ለወጣቱ ትውልድ ለመጠቆም ነው፡፡ ሁለተኛውን ረሳሁት፡፡


የተሣካ ውድቀት ውስጥ መግባት እኛ ኢትዮጵያውያን ብርቃችን እንዳልሆነ ያነበብኳቸው መጻሕፍት ሁሉ በኩራት ይመሰክራሉ፡፡ እነዚህም ሆኑ ሌሎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የማውቃቸው ታሪኮቻችን የሚነግሩኝ አንድ ነገር ቢኖር እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ የሚጎድለን የተፈጥሮ ቅመም መኖሩን ነው፡፡ ይህ የጎደለን ቅመም እጅግ መሠረታዊ ከመሆኑ የተነሣ ፈልገን ካላገኘነውና ካላስተካከልነው ከአሁን በኋላ አምስት ሚሊዮን ዓመታትም በሀገርነትና በሕዝብነት ብንኖር በዬጊዜው ከምንገባባቸው የተሣኩ ውድቀቶች መውጣት ፈጽሞውን አይቻለንም፡፡ ብዙዎቻችን አዘውትረን እንደውዳሤ ማርያም እንደምንደጋግመው ምቀኝነትና የሥልጣን ጥም በደማችንና በመቅኒያችን የመሸጉብን ስለመሆናቸው የቀድሞና የአሁን ታሪካችን ነጸብራቅ የሆኑ እነዚህን መጻሕፍት በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡

 አልጋ ለመቀማት ወይም አልጋውን ላለመቀማት ሲል ንጉሥ አባት ልዑል ልጅን በጦርና በጎራዴና ምግብን በመመረዝ ሣይቀር የሚገድልበት፣ ነገሥታት ከሀገራዊ ልማት ይልቅ ለሥልጣናቸው ሲሉ ለብዙ አሠርት ዓመታት በማያቋርጡ ጦርነቶች ራሳቸውንና ሕዝባቸውን የሚማግዱበት፣ ለሥልጣንና ለሹመት ሲባል አንዱ ሌላውን በመርዝና በሰይጣናዊ መተትና ድግምት የሚጨራረሱበት፣ የሥልጣን አራራን ለማስታገስ ሲባል የገዛ ሚስትን ሳይቀር ለከፍተኛ መሪዎች እያቀረቡ በትዳርና በ“ፍቅር” ጡር የሚሠራበት፣ ሃይማኖትን መሣሪያ በማድረግ ሕዝብ ከእውነተኛ የፈጣሪ መንገድ እንዲወጣና የነገሥታት ባሪያ እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎችና ነገሥታት የሚመሣጠሩበት፣ በዕብድና ወፈፌ ነገሥታት የደንቆሮ አገዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በረባ ባልረባው ሚዛን የማይደፋ ምክንያት እጅ እግራቸው እንዲቆረጥና በ“እኔን ያዬህ ተቀጣ” ለመቀጣጫነት የሚዳረጉበት፣… አሣፋሪ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ውጪ በሌላ ሀገር ስለመኖሩ በበኩሌ አላውቅም፡፡ የትናንቱ ድንቁርናችን ተባብሶ ዛሬም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምናስተውላቸው የውድቀታችን መንስኤዎች ከጥንቱ የተወረሱ እንደሆኑ መገንዘብ አይከብድም፡፡
ውድቀት ምንድነው? እንዴትስ ይታወቃል?

ብዙ መፈላሰፍ አያስፈልግም፡፡ በአጭሩ ውድቀት ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያና ውድቀት በፍቺ ይመሳሰሉ፤ አንዱ ቃል ሲጠራ ሌላው ይታወሳል፡፡ ይህን ለመገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትና እየተዟዟሩ መጎብኘት ነው፤ በሁሉም ዘርፍ የተዘፈቅንበትን ኪሣራና ድቀት (Decadence) በአጭር ጊዜ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡ ልብ ማለት ያለብን ነገር ደግሞ ሕንጻና መንገድ የዕድገት ምልክት አለመሆናቸውን ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ ዘመን በተሣካ ውድቀት ውስጥ የገባችበት ዘመን የለም ማለት ይቻላል፡፡ የጥንት አባትና እናቶቻችን የጀመሩት ውድቀት ግዘፍ ነስቶ በአካል የታየው አሁን ባለንበት ዘመን ላይ ነው፡፡ ከታክ የማንማር፣ ጥፋትን እያሻሻልንና እያዘመንን ለሌላ ጥፋት ዝግጁ የምንሆን ዜጎች ብንኖር እኛ ኢትዮጵያውን ብቻ ነን፡፡ አሁን ያለንበት የውድመት ደረጃም ሲያንሰን ነው፡፡
የማንተዛዘን፣ አንዳችን በአንዳችን መከራ የምንደሰት፣ በአንዳችን መቃብር ላይ ሌላኛችን የሠርግ ዳስ የምንትል እጅግ ክፉዎች ነን፡፡ እውነት ቢነገር ምን ያመጣል? ምንም!!

ብዙ የውድቀት መከሰቻዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዱ የውድቀት ምልክት የአርአያሰብዕ (Iconic Figure(s)) መንጠፍ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ ወጣቱ ትውልድ “ወደፊት እንደ እገሌ ነው የምሆነው!” ብሎ ከፊት ለፊቱ የሚያስቀምጠው ሰው እየጠፋ ነው፡፡ ዙሪያ ገባውን ብንቃኝ አርአያ የሚሆን ሰው ማግኘት እንቸገራለን፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርቀት ዋና ሀገራዊ ኪሣራ ነው፡፡ የነበሩን መልካም ሰዎችና በሥራቸው አንቱ የተባሉ ዜጎች ብዙዎቹ ከመሬት ሥር ውለው ጥርኝ አፈር ሆነዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ቢኖሩም ዘመኑ ለነሱ አርአያነት ምቹ ባለመሆኑና በወቅቱ የወያኔ መንግሥት በጠላትነት ስለሚፈረጁ በሀገር ውስጥና በውጪው ዓለም ተደብቀዋል፡፡


 በወቅቱ መንግሥት ትልቅ ዜጋ ማለት የወያኔን ዘረኛ መንግሥት ፖሊሲዎች ተቀብሎ በወንጀልና በኃጢኣት መመላለስን የመረጠ፣ በሰይጣናዊ ተግባራት ተጠምዶና በባዕድ አምልኮት ተጠምቆ ለሥጋው ድሎት ብቻ የቆመ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በአንጻራዊ አነጋገር የተሻለ በሚባል ኢትዮጵያዊ የአንድነት ዘመን ውስጥ በምርጥ ዜግነት የሚያሳውቁ ማኅበራዊና ምሁራዊ ተግባራትን በአሁኑ የወያኔ ዘመን ማከናወን ለእሥርና ለእንግልት እንዲሁም ለስደት ይዳርጋል፡፡ ሆዳምነትና ዋልጌነት በነገሠበትና የመንግሥት መታወቂያ በሆነበት ዘመን የሀገርና የሕዝብ አለኝታ ሆኖ ብቅ ማለት ሌላው ቀርቶ ባልተፈጸመ ወንጀል – የወያኔ የወንጀል መፈብረኪያ የደኅንነት መሥሪያ ቤት በሚሸርበው የፈጠራ ክስ – ወህኒ ሊያስወርድ ይችላል፡፡ የቴዎድሮስ ካሣሁንን መስዋዕትነት ያስታውሷል፡፡ ወሩ በገባ በ22ኛው ቀን የሞተን ዜጋ ወሩ በገባ በ23ኛው ቀን ከውጪ ሀገር በመጣው ቴዲ ላይ መላከኩ የገጪውና የተገጪው ግንኙነት ምናባዊ እንጂ እውናዊ መሆኑን እንኳንስ ‹ፍርድ ቤቱ›ና ከሳሾቹ እኛም እናውቅ ነበር – ማወቅ በራሱና ብቻውን ዋጋ የለውም እንጂ፡፡


 ወያኔ መርዘኛ በቀለኛ ነው፡፡ ወያኔ ከመረዘ ሳያንፈራፍር በቀላሉ አይለቅም፡፡
በአሁኑ ወቅት ምሁር አለን ማለት ያስቸግራል፡፡ አድርባይና እበላ ባይ አስመሳይ ወይም በዘመኑ ቋንቋ ‹ፎርጅድ› ምሁር እንጂ ትክክለኛው ምሁር በመብራት ተፈልጎም አይገኝ፤ አሉ ከሚባሉት ጥቂት ወጣትና አንጋፋ ምሁራንም መካከል በትዕቢትና በትምክህት የማይወጣጠሩ ልሂቅነታቸው ያላሳወራቸው ትሁት የሕዝብ አገልጋዮችን ለማግኘት መቸገራችን አልቀረም – ከወደቁ አይቀር ውድቀቱ ሁለንተናዊ መሆን አለበትና ይህ የኢትዮጵያ ምሁራን መኮፈስ የማይጠበቅ አይደለም፡፡


 ሁሉንም ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ዘርፎች ብናይ አርአያ ሊሆኑን የሚችሉ ድንቅ ዜጎችን ሣይሆን ለሆዳቸው ያደሩ አጋሰስና ግልብ ዜጎችን ነው የምናገኝ – በአብዛኛው፡፡ ሆድ ሰውነትን ሲገዛው ጭንቅላት ይጫጫና ከርስ/ቦርጭ ውስጥ ወርዶ ይወተፋል፡፡ ያኔ ኅሊና ትጠፋና ሆድአደርነት የማያፍሩባት ይልቁንም የሚኮሩባት የወቅቱ ፋሽን ትሆናለች፡፡ ሀቀኝነት እያሳፈረ ቅጥፈትና ዕብለት ያሾማል፤ ያሸልማል፡፡ በከንቱ ካልታበይንና ባለፈ የደግ ዘመን ጥቂት ታሪክ ተጀቡነን በተረት ተረት መኖርን ካልመረጥን በስተቀር ሀገራችን በዚህ አሣፋሪ ሂደት ውስጥ ትገኛለች – በችኮላ የ‹ደርግ ዘመን› ብላችሁ እንዳታነቡብኝ አደራችሁን፡፡


 የሚብለጨለጨውን የቻይና ቴክኖሎጂና ሕንጻና መንገድ በዚህ ስሌት አናስገባውም፡፡ መጥፎ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ እነዚህ የሚታዩ ኳሻርኳራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ውጤቶች በተወሰነ ደረጃ በሀገር ምስል ላይ አወንታዊ ሚና ስለሚጫወቱ መልካም ነገሮች ናቸው፡፡ ውድቀታችንን ግን ሊታደጉ ወይም ሊሸፍኑና እንዳልወደቅን ሊመሰክሩ ግን አይችሉም፡፡
ለእውነት ሲል የወያኔን ግፈኛ አገዛዝ በጥናታዊ ጽሑፉ አጋልጦ ሲመረቅ የለበሳትን ጥቁር ገዋን ያስመሰገነ ምሁር እንፈልግ – ካገኘን እሰዬው፡፡ በሚያገኘው ደሞዝ ብቻ እየኖረ ሕዝብን የሚያገለግል ባለሥልጣን እንፈልግ – ካገኘን እሰዬው፡፡ (እዚህ ላይ የአቶ ገብሩ አሥራትን ከሙስና የጸዳ ስብዕና ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡ አንድ ሰው የተለዬ ቆንጆ ምግብ ያምረውና ወደገብሩ ቤት በእንግድነት ይሄዳል – ቀደም ሲል ገብሩ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት በነበረበት ወቅት ነው፡፡


 የቀረበለት ምግብ ግን የጠበቀው ሥጋና በአትክልትና ፍራፍሬ የታጀበ የሀብታም ብፌ ሣይሆን ተራ ቀይና አልጫ የሰላሱት ምግብ ይሆናል፡፡ ሰውዬው በግልጽነት “እዚህ ቤት እንዲህ ያለ ምግብ ነው እንዴ እሚዘጋጀው?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ ያገኘው መልስ “የምንኖረው መንግሥት በሚከፍለን ደሞዝ ብቻ በመሆኑ ከዚህ የተለዬ ምግብ ማዘጋጀት አንችልም፡፡” የሚል ነበር፡፡ ይህችን እውነት ለመተንፈስ አጋጣሚ እፈልግ ነበር – ዛሬ ተሳካልኝ፡፡) በሚያገኘው ደሞዝ ብቻ እየኖረ የሀገርን ዳር ድንበር የሚያስከብር አንድም ቢሆን የመከላከያ ወይም የፖሊስ ሠራዊት መኮንን ብናገኝ ዕድለኞች ነን፡፡ የፈጣሪና የመንግሥት ሕጎች በሚያዙት መሠረት ነግዶ የሚከብር ቢያንስ አንድ ነጋዴ እንኳን ቢኖረን አሁንም ዕድለኞች በሆን፡፡


 የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በቤተ መቅደስ እንደሚያንበለብለው ሁሉ በሕይወቱም ፈጣሪን የሚታዘዝ ቢያንስ አንድ ጳጳስ ቢኖረን ሎጥን ያገኘን ያህል በቆጠርነው ነበር፡፡ ቴዎድሮስ ካሣሁንንና ሻምበል በላይነህን ከመሳሰሉ በጣት የሚቆጠሩ የኪነ ጥበብ ሰዎች በስተቀር ከምንትስ ምንትስ በዘለለ የሕዝብን ብሶትና ችግር በፈጠራ ሥራዎቻቸው የሚያካትቱ የሥነ ጥበብና የኪነ ጥበብ ሰዎች ቢኖሩን መታደል ነበር፡፡ በተሠሩ በጥቂት ቀናት ወይም ወራት ውስጥ የሚፍረከረኩ የመንግሥት ቤቶችንና መንገዶችን የሚገነቡ በሙስና የተበከሉና በዕኩይ ሥነ ምግባር የተዘፈቁ ሀሳዊ መሃንዲሶች ሀገር ምድሩን ባይሞሉት ኖሮ ትምህርት ዋጋውን እንዳላጣ እንረዳ ነበር፡፡


 ዘርዝረን በማንጨርሳቸው አጠቃላይ ችግሮች ውስጥ ተነክረናል፡፡ የትምህርት ጥራት አይነሳ፤ ሁሉም ዜሮ እየሆነ ነው፡፡ ለኅሊናቸው የሚታዘዙ ሠራተኞች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወታደሮች፣ ባለሥልጣኖች፣ ነጋዴዎች፣ ዘፋኞች፣ ደራሲዎች፣ የሃይማኖት አገልጋዮች፣ዳኞች፣ ጠበቆች፣ ግምበኞች፣ ወዛደሮች፣ …. ጥቂት እንኳን ቢኖሩን ድቀታችን መልክ በኖረው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን የተሣካ ውድቀት ውስጥ የመገኘታችንን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ይህችን ሀገር እንደገና ገምብቶ ሀገር ለማድረግ ምን ዓይነት ጥረትና ስንትና ስንት ልፋት እንደሚጠይቀን ፈጣ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ብዙ ነገሮች ብቻ ሣይሆኑ ከሞላ ጎደል ሁሉም ነገሮች ከደንቡና ከሥርዓቱ ወጥተው በቀላሉ የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ገብተናል፡፡


አንዳንዶቻችንን ሊያስከፋን ይችል ይሆናል፡፡ ግን እውነት ስለሆነ እዚህ ላይ ሳንጠቅስ ልንዘለው አንችልም፡፡ ወያኔ በሀገራችን ያነገሠው ዘረኝነት ከቃላት የመግለጽ አቅም በላይ ነው፡፡ትግሬን ተጠቃሚ ለማስመሰልና ከሌላው ሕዝብ ጋር ለማቃረን በእግረ መንገድም በእርግጥም የዘረኛውን ሥርዓት የጎሣ ተዋፅዖ በማጉላት በሥርዓቱ እምነት የሚጣልባቸውን ዜጎች ይበልጥ ለመጥቀም ሲባል እየታዬ ባለ የተንሻዋረረ ጎጠኛ አሠራር የማንታዘበው ጉድ የለም፡፡ ይህ እግዚኦ የሚያሰኝ ጉድ በማንም ሀገር በመቼም ዘመን አልታየም፡፡


 የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድም ይህን ያህል ግፍና በደል በጥቁሮች ላይ የፈጸመ አይመስለኝም፡፡ የኛ ዋና ችግርና ለአሣራችንም ቀጣይነት አስተዋፅዖ እያደረገ ያለው ክስተት የኛ ጨቋኞች በመልክና በቀለምም በባህልና በቋንቋም ከኛው ከተጨቋኞቹ ጋር በመመሳሰላቸው ጠላትን ከወዳጅ በቀላሉ መለየትና ዘረኛውን ከጤናማው ለይተን መተማመንን በመፍጠር ለነጻነት ትግሉ መትጋት አለመቻላችን ነው፡፡


 አስቸጋሪ ነው ጓዶች፡፡ አንተን ከመሰለ ሰው ጋር ታግለህ ወደምትፈልገው ድል ለመብቃት ከባድና ጊዜንና ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው፡፡ አንዱና ትልቁ ችግር ይህ ስለሆነ እንጂ እነዚህን አረሞች ለመንቀል የማይቻል ሆኖ አይደለም፡፡ ግን ደግነቱ ይህም ያልፋል፡፡ ቆሞ ያለ የሚመስለው ግን ይጠንቀቅ!
ለአሁኑ ግን የዘረኝነቱ ዳፋ በሀገርህ ላይ ተቀምጠህ ሀገርህ እስኪናፍቅህ ድረስ፣ በወገንህ መካከል እየኖርክ ወገን እንደሌለህ እስኪሰማህ ድረስ፣ የጋራ እናት ሀገር እያለህ ምንም ዓይነት ዜግነት የሌለህና ባለቤት የሌለለው የመንገድ ላይ ውሻ የሆንክ ያህል እስኪሰማህ ድረስ ውስጥህን ዘልቆ በሚበረብር የሀገርና የወገን ርሀብ ትሰቃያለህ፡፡


 ይህም ማለፉ ባይቀርም ለጊዜው ጭንቅላትህን ሊያፈነዳ በሚችል ሥነ ልቦናዊና እንደዬሁኔታውም ኢኮኖሚያዊ ችግር ልትወጠር ትችላለህ – በዚህ ያበዱና ለማበድም የተዘጋጁ እጅግ ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ በ“ሰው ሀገር” እየኖርክ መብትህን መጠየቅ እንደማትችል፣ ብትሞክር ደግሞ ቢያንስ እንደሚሳቅብህና እንደሚፌዝብህ ስትረዳ ሀዘንህ ዕጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡ ኬንያ ወይም ሆኖሉሉና ፊጂ ብትኖር የማይጓደልብህ ሰብኣዊ መብት የገዛ ሀገሬ በምትላት ኢትዮጵያህ ውስጥ ወደህና ፈቅደህ ባልሆንከው የዘርህ ማንነት ምክንያት ሲዳላብህ ስታይ አለመፈጠርህን ትመርጣለህ፡፡


 ይህች ሀገር፣ ሀገር ተብላ ነው እንግዲህ እነሌንጮ ገብተው በ‹ሰላማዊ መንገድ ሊታገሉና ሕዝብን ነጻ ሊያወጡ› እንደሆነ እየተወራ ያለው፡፡ ተስፋ ስትቆርጥ አንድም ትወጣለህ አንድም ትገባለህ ማለት ነው፡፡ እኔ ተስፋ ቆርጬ መውጣት ፈልጌ መውጫ አጥቼ ቀረሁ፡፡ እነሌንጮ ተስፋ ቆርጠው ወጥተው ተስፋ ቆርጠው ሊመለሱ ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ተስፋ ቆርጦ ይወጣና ተስፋን ሰንቆ ይገባል – እንደአውራምባው ዳዊት ከበደ ያለው፡፡ ይሄ ‹ተስፋ› እሚሉት ግን መልኩ ምን ይመስል ይሆን?
ገባ ብለን በተጨባጭ እንየው፡፡ ትግሬዎች አትቀየሙኝ፡፡ እኔም ዋናው ትግሬ ነኝ፡፡ ዘመኑ ሲያልፍ ትግሬያዊ ማንነቴን እገልጣለሁ – ሊያውም አስፈላጊ ከሆነ፡፡ ያ ግን በመሠረቱ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ቀዳሚው ሰውነት ነው፤ እናሳንሰው ካልን ደግሞ ኢትዮጵያዊነት፡፡ እነዚህ ሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎችም – በነገራችን ላይ – ወደው አይደለም እንዲህ የሆኑት(አማራጭ አጥተው በገቡበት የወንጀል ዓለም የሚደሰቱበት አይመስለኝም)፡፡


 ወደ እውነት ቢመጡ ሥልጣኑን እንደሚያጡት ለአእምሯቸው ነግረው ስላሳመኑት ነው – በዚያም ላይ ከጥንት ጀምረው የሠሯቸው ብዙ መጥፎ ተግባራት ስላሉባቸው በነዚያ ላለመጠየቅ ዋናው አብነት ሥልጣንን አጠናክሮ እስከሕይወት ፍጻሜ ወንበርን የፊጥኝ ማለት መሆኑን ያውቃሉ – በዚህ ረገድ እነሱ ስህተት የለባቸውም፤ ችግሩ የኛ የተጨቋኞች ነው – እነሱን በጋራ ትግል ላለመጣል የተዋዋልነው ፊርማ የለሽ ስምምነት ነው እየጠቀማቸው የሚገኘው፡፡ ጥቂቶች(minorities) “ተወዳድረን ሥልጣን መያዝ አንችልም፤ ብቸኛ አማራጫችን ኃይልና ጉልበት ነው” ብለው ካመኑ በየትኛውም ሁኔታ አስቸጋሪ ናቸው – የማይነቃነቁ ዓለቶች ሆነው ለብዙ ጊዜ ሊያስቸግሩ ይችላሉ፤ በሂደት ግን እንደጤዛ መርገፋቸው እንደጉምም መብነናቸው አይቀርም፡፡ እስከዚያው ግን ይሞቷታል አንጂ ሥልጣንን በፈቃዳቸው አይለቁም – “ሰላማዊ ትግል” የሚሉት ቀልድም እነሱ ዘንድ ከጨዋታነት ባለፈ በፍጹም የማይሞከር ነው፡፡ እነዚህን መሰል ጨቋኞች ዓለም የሠራቻቸውን ወንጀሎችና ሸሮች ሁሉ እያከናወኑ በሥልጣናቸውና ሥልጣናቸው በሚሰጣቸው ጥቅም ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ይኖራሉ፡፡ እናም የእነዚህን መዥገሮች ድርጊት ስናገር መጥፎ ድርጊት በደምና በዘር አይተላለፍምና ጤነኞች ትግሬዎች መናደድ አይገባንም፡፡ እውነቱ ባጭሩ እንግዲህ ይህን ይመስላል፡፡




ከትግሬዎች በስተቀር ሌሎች ኢትዮጵያውያን ድርሽ የማይሉባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል የደኅንነትና መከላከያን የመሳሰሉ የፀጥታ መሥሪያ ቤቶች፣ ጅምሩክንና ማዕድናት የመሳሰሉ ከፍተኛ ጥቅም አስገኚ ቦታዎች በዋናነት ይገኙበታል፡፡ እነዚህን የመሰሉት ቦታዎች ከትግሬ በስተቀር ለሌሎች ጥብቅ ምሥጢር ናቸው – አጮልቀው እንኳን እንዲያዩዋቸው የማይፈቀድ፡፡ የማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አመራር ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በትግሬዎች የተያዘ ነው – በስም ደግሞ አትመን (ወያኔ በስም የማታለልን ሸር የተካነበት ገና በረሃ ሳለ ነው- “ወርቅነህ በረደድ” ወይም “ደቻሣ ኩምሣ” ቢልህ እውነት አይምሰልህ – የዚህ ተጋዳላይ እውነተኛ ስም “ሐጎስ ግደይ” “ወዲ ዕንቋይ” ሊሆን ይችላል)፡፡ የትኛውንም የመንግሥት መሥሪያ ቤት አመራር ከላይ እስከታች ብንመለከት ሁሉም ትግሬ ነው፡፡ ውሸታም አትበሉኝ፡፡ እንዳልሆንኩ በተገቢ መረጃ አስደግፌ ልናገር ነው፡፡ ለምሳሌ የአንድ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትር እንደ ታሪካዊ ‹መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ› ትግሬ አይደለም እንበል፡፡


 ያ ሰው አማራ ነው እንበልና እንውሰድ – እዚህም ላይ ለሥርዓቱ ዕኩያንና ዕቡያን ትግሬዎች ይህ ክስተት እንደ ‹መጥፎ የታሪክ አጋጣሚ› ተቆጥሮ፡፡ አንተ አማራ ነህ ልበልህና ደስ አለህ አይደል አሁን? አዎ፣ ደስ ይበልህ እንጂ! “ወንድምህ” – ‹ዘርህ› – ተሾሞልህ ያልተደሰትህ መቼ ልትደሰት! ግን አይምሰልህ ወንድሜ፡፡ መሾምና መሻር በችሎታና በብቃት መሆኑን ዘንግተህና አንተም ወያኔ ሆነህ በደምና በአጥንት የምታመልክ ሰው ሆነህ ዘረኝነቱ ወዳንተም ተጋብቶ የኔ የምትለውን ሰው ሥልጣን ላይ ወጥቶ ያየኸው ከመሰለህና በዚያም ከተደሰትህ ተሳስተሃል ብቻ ሣይሆን ለወያኔው ወጥመድ ተመቻችተሃል እንደማለትም ነው፤ ያ ሚኒስትር የተቀመጠው ለስምና ለፖለቲካዊ ታይታ ብቻ ነው – ከግርጌውና ከራስጌው ታኮና ትራስ ሆኖ በዐይን ጥቅሻና በስልክ የሚያንቆራጥጠው ትግሬ አለ – ለዚህ ነው ሁሉም አዛዥ ናዛዥ ትግሬ ነው የምልህ፤ ለዚህ ነው የሀገሪቱ እስትንፋስ መቶ በመቶ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር መሆኑን በድፍረት የማረዳህ ማለትም የማስረዳህ – አንድም ቦታ ሳይቀር ሁሉም በነሱ እይታና ቁጥጥር ውስጥ ነው፤ ያ ቦታ ከመንግሥት ኅልውና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ለነሱ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የቆሻሻ ገንዳም ይሁን መጸዳጃ ቤት ጥበቃ፣ ስፖርት ኮሚሽንም ይሁን የዱር እንስሳት ጥበቃ ብቻ በአለቅነት ወይም በስለላ መልክ የሌሎች ወንድሞቹን እንቅስቃሴ የሚከታተል የሥርዓቱ ታማኝ እስከተቻለ ትግሬ አለዚያም የወያኔነት ሶፍትዌር የተገጠመለት ሌላ ሆድአደር ይመደባል፡፡


ለታይታ ከላይ የሚቀመጥ የሌላ ብሔር “ባለሥልጣን” ግን አሻንጉሊት ጉልቻ እንጂ ከራሱ አእምሮ አንቅቶ የሥልጣን ወንበሩ የሚፈቅድለትን ተግባራት ሊያከናውን የሚያስችል ቅንጣት የማዘዝ ሥልጣን የለውም ለዚህ ለዚህማ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ከወላይታ ተሾሞልህ የለም እንዴ? ቲያትሩን እያስታወስኩህ እንጂ አዲስ ነገር እየነገርኩህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ የምነግርህን ነገር ደግሞ ለራሴው ተግባራዊ ግንዛቤ ስል ራሴው በየመሥሪያ ቤቱ እየዞርኩ የተረዳሁት ነው፡፡ ያልሄድኩበት ቦታ የለም፡፡ ከብዙ ገጠመኞቼ አንድ ሁለቱን ያህል ብቻ ለአብነት እዚህ ላይ ልንገርህ፡፡ ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል ባለፈው ሰሞን ሄድኩ – አንድ ዘመድ ለማሳከም፡፡ ህክምናው አነስተኛ ቀዶ ህክምና ነበር፡፡ ዘመዴን ለማከም የቀረቡት ዶክተሩም ነርሶቹም ዕቃ አቀራራቢዎቹም አራቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ በዚህ ብቻ አይግረምህ፡፡


 የከሰዓት ተቀያሪዎቹም ሦስቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ በሆስፒታሉ ተዘዋወርኩ፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ሁሉም የአስተዳደርና የህክምና ሠራተኞች ትግሬዎች ናቸው – የግቢው ብሔራዊ ቋንቋም ትግርኛ ነው – በዚህስ አልከፋኝም፡፡ ይህ ሁኔታ በአጋጣሚ ነው ከተባለ በትንሹ ሞኝነት ወይንም “አጋጣሚ” የሚለውን ቃል ካለመረዳት የሚመነጭ የዋህነት ነው፡፡ አንድ ወቅት አንድ ወታደራዊ ሰርቪስ መኪና ውስጥ በአጋጣሚ ተገኝቼ እንደታዘብኩት ከነበሩት አሥራ ምናምን ሰዎች ውስጥ ትግርኛ የማይናገረው ሾፌራችን ብቻ ነበር፡፡ እንዴ፣ እውነቱን እንነጋገር ካልንማ ጉዳችን ብዙ እኮ ነው፤ ለምን እንተፋፈራለን? ባይሆን እናውራውና ይውጣልን እንጂ፡፡


ወደ መንግሥት ባንኮችና ኢንሹራንሶች ሄድኩ፤ ወደ አየር መንገድ ሄድኩ፤ ወደ ዩኒቨርስቲዎችም ሄድኩ፡፡ ሁሉም በትግሬ ተጥለቅልቋል፡፡ የከተማዋ ጠረን ከዳር እዳር ወደትግሬነት ተለውጧል – ምናልባትም ‹መቐለ› ላይ ያለህ ሊመስልህ ቢችል አይፈረድብህም፡፡ አነጋገሬ ዘና ያለ እንዲሆን ያደረግሁት ሆን ብዬ ነውና ብዙም አይሰማችሁ፡፡ እናም ብዙ ቦታዎች ሄድኩ – ያው ነው፡፡ ሰዎች “ይህ ዘመን የትግሬዎች ብቻ ሆኗል” የሚሉትን ሃሜት ሊያስተባብልልኝ የሚችል አንዳች ነገር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ፡፡ ነገር ግን አልተሳካልኝም፡፡


ትግሬ በአንዳች ምትሃታዊ ነገር እየተባዛ መላዋን የወያኔ ኢትዮጵያ በምልዓት ያዳረሳት ይህል ተሰማኝ – ማዳረሱ ለበጎ ነው ችግሬ የመድሎና የጥፋት ኃይል መሆኑ ላይ ብቻ ነው፤ ሌላውን ሕዝብ ምን በላው እስክትሉ ድረስ በትግሬዎች የመንግሥትን መሥሪያ ቤቶች በበላይነት መቆጣጠር ትገረማላችሁ – ትግሬ ስልህ ደግሞ በአባቱ ወይ በእናቱ ሊሆን ይችላል – እንዲያውም ትግርኛ የማያውቅና የማይናገርም ትግሬ ልታገኝ ትችላለህ – መሃል አገር የተወለደና ያደገ፡፡ “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የምትለዋ ብሂል በወያኔ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አላት፤ ሌላውን ስለማያምኑ በተለይ ሹመት ላይ የሚያስቀምጡት ሰው ከነሱ ቁጥጥርና አመኔታ የማይወጣ እንዲሆን ይጠነቀቃሉ፡፡


 አሁንም አንድ ነገር ግልጥ ላድርግ – ሌሎች ዜጎች በኃላፊነትም ሆነ በተራ ሠራተኛነት አይቀጠሩም ወይም የሉም ማለቴ አይደለም፤ እያልኩ ያለሁት ትርጉም ባለውና ወሳኝ በሆነ ደረጃ ፈላጭ ቆራጮቹ ትግሬዎች ናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ ከመቶ ሠራተኞች መካከል አምስቱ ብቻ ትግሬዎች ቢሆኑ ዘጠና አምስቱ ሠራተኞች የሚሽቆጠቆጡትና የሚያሸረግዱት ለአምስቱ ትግሬዎች ነው – ከመስቀያው ነው – በጌታዋ የተማመነች ፍየል እኮ ቀንዷን በጎች መሃል ነው የምትሰካ፤ በዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያን ያለንን የማሸርገድ ብቃትና ለተሹዋሚ የማጎብደድ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ መረዳት ይቻላል፡፡ ጊዜ ዘምበል ሲል ደግሞ እንዴት የመሰለ አክሮባት እንደምናሳይ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡


በበኩሌ በትግሬ ሁሉንም የሥልጣን ቦታዎች መቆጣጠር ብዙም አልከፋም፡፡ የሚያስከፋኝ ባለሥልጣናቱ ቦታውን የሚያገኙት በችሎታና በትምህርት ሳይሆን በዘር ቁርኝት በመሆኑና ያም ሥራን ክፉኛ እያበላሸ በመሆኑ ነው፡፡ አለበለዚያ ሥራውን በሚችሉ የተማሩ ትግሬዎች ሁሉም ቦታ ቢያዝ ግዴለኝም፡፡ አሁን ያለው ችግር ግን አይነሳ፡፡ አንድም ትምህርት የሌለው ምናልባትም የሁለተኛና የአሥረኛ ክፍል ወያኔ ትልቅ ቢሮ ይይዝና የተማረው የሌላ ጎሣ አባል በሥሩ ሆኖ ከኅሊናው ባፈነገጠ አሠራር በዚህ ማይም ወያኔ እየተረገጠ ስታዩ የሥራው መበላሸት ብቻ ሣይሆን ዘረኝነት አንዲትን ሀገር በምን ዓይነት ደረጃ ድራሹዋን እያጠፋት እንደሆነ በመገንዘብ ታዝናላችሁ፡፡


 ትግሬ መሆን ብቻውን ለሥልጣንና ለሀብት ካበቃ፣ አማራ መሆን ብቻውን ጉራን ለመቸርቸርና በትምክህት ለመወጠር ካበቃ፣ ጠምባሮ መሆን ብቻውን ለንቀትና ለተዋራጅ ኑሮ ከዳረገ … ሰብኣዊነትና የጋራ ብሄራዊ ማንነት አዲዮስ! በኢትዮጵያ እየታዘብን ያለነው ጉደኛ ትንግርት ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ባለፉት 23 ዓመታት የጠፋውን ጥፋት ለማረም ስንት ዓመት እንደሚፈጅ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ በማይማን የተሞላውን በቅርጽ ያለ የሚመስል በይዘት ግን ደብዛው የጠፋውን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሰው ኃይል አደረጃጀት ለማስተካከል ራሱ ከሩብ ምዕተ ዓመት ያላነሰ ጊዜን መውሰዱ አይቀርም፡፡ የተማረ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ ለማግኘት፣ በሥነ ምግባር የታነጸና የሥራ ተነሳሽነት ያለው ዜጋ ለማፍራት ብዙ ጥረት ይጠይቃል፡፡


 በአሁኑ ወቅት ለእስታቲክሳዊ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር የመንግሥት ሥራ በአግባቡ ይሠራል ማለት አንችልም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሕይወት ያላቸው የሚመስሉት እዚህና እዚያ በለጣጠፏቸው የማይተገበሩ መፈክሮችና “ራዕይ፣ ዓላማ፣ ተልዕኮ፣…” በሚባሉ ትላልቅ የወረቀት ጀንዲዎች ላይ በጉልህ በተቀመጡ የሚያማምሩ ጽሑፎች አማካይነት ብቻ ነው፡፡ በተረፈ የዚህና የዚያ የሥራ ሂደት ባለቤት እየተባለ በሥሩም ዕውቀትና በቂ ሥልጠና የሌለው ሠራተኛ በዘመድና በፖለቲካ አመለካከቱ እየተመደበ አለተጨባጭ ሥራ ስላውደለደለና ሕዝብን በጉቦ ስላስለቀሰ ሀገር ትለማለች ብሎ መጠበቅ የሚቻል አይደለም፡፡ አዲስ የሚቋቋሙት መሥሪያ ቤቶችም በአብዛኛው የሥርዓቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚጠቅሙ የሀገር ሀብት አባባካኝ እንጂ ለሕዝብና ለሀገር ዕድገት የሚውሉ አይደሉም፡፡ ገመናችን ብዙ ነው፡፡

 ንግዱን ያየን እንደሆነ አነስተኛና ጥቃቅን ከሚባሉት የሥርዓቱ ዕንባ ጠባቂዎች ጀምሮ የአንበሳውን ድርሻ ይዘው ያሉት ወያኔዎች ናቸው – ከአዲስ አበባ የንግድ ማዕከላትና ሱቆች ውስጥ፣ በአዲስ አበባ አስፋልት ከሚሽከረከሩ ዘመናዊ አውቶሞቢሎች ውስጥ፣ በየምሽቱ ዳንኪራ ከሚረግጡ ዜጎች ውስጥ፣ በየሉካንዳውና በየመጠጥ ቤቱ በጮማና ዊስኪ ከሚቀማጠሉ ‹ኢትዮጵያውያን› ውስጥ ስንቱ መቶኛ ኢ-ትግሬ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ መናገሩ ሆድ ሊያስብስ ስለሚችል ሆድ በሆድ ይፍጀው ይቀመጥ፡፡ (እዚህ ላይ ቅድም በኢሳት የተከታተልኩት አንድ ቃለ መጠይቅ ትዝ አለኝ፡- አሥራት አብርሃም የተባለ ሰሜነኛ ከግዛው ጋር ሲነጋገር እንደሰማሁት የኢትዮጵያ ችግር እርሱና መሰል አመለካከተኞች እንደሚሉት የንግሥናው ነገር ከሸዋ ወደ ትግራይ ወይም ከትግራይ ወደሸዋ የመምጣት ጉዳይ አይደለም፡፡


 እንደዚያ ያለው ንትርክ ጉንጭ አልፋ የሽፋን ተኩስ ዓይነት ነው፡፡ ዋናው ትግሬ ነገሠ ወይም አማራ ተሻረ የሚለው ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው፡፡ ትግሬና አማራ በሥልጣን መፈራረቃቸው እንግዳ ነገር አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ባመጣው የዘር በሽታ መነደፉና በግፍ አገዛዝ ክፉኛ መሰቃየቱ ግን በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ እንግዳ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ችግሩን እስከዚህ አታሳንሱት – አታውርዱት፤ ችግራችን ከነገሥታት ምርጫ ጋር ፈጽሞውን የሚያያዝ አይደለም – ከጭቆና መግረር ጋር እንጂ፡፡ በከፊል አማራ ያልነበረው መንግሥቱ 17 ዓመታትን በገዛ ጊዜ የዘር ችግር እንዳሁኑ በፈጠጠ ሁኔታ አልነበረም፤ ሕዝቡም ‹ኦሮሞ ገዛን፤ የሸዋ አማራ ይሁንልን!› ብሎ አልጮኸም፡፡ አማራው መልካም ገዢ ካገኘ ሥልጣን ቀረብኝ ብሎ አካኪ ዘራፍ የሚል አይመስለኝም – ትግሬም ሆነ ሌላውም ሕዝብ እንዲሁ፡፡ ይቺ ማምታቻ ናት፡፡ እዬዬም ሲዳላ ነው ወገኖቼ፡፡ ጥድቁ ቀርቶብኝ አሉ …)

ትግሬ ሆኖ ፖለቲካን ከጠላ ወደንግዱ መግባትና ለሌሎች በተዘጋጋ ለርሱ ግን በተመቻቸ የጨዋታ ሜዳ “በመነገድ” በአንድ አዳር ሊከብር ይችላል፡፡ ንክኪ ከሆንክ አንድም ሳንካ ሳይገጥምህ የሀብት መንገድህ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆንልሃል፡፡ ሌላ ከሆንክ ግን ሁሉም ይከረቸምብህና ብቸኛ አማራጭህ ስደትና ድህነት ይሆናል፡፡ አንዲት እህቴ አንድ ንግድ ትጀምራለች፡፡ ሰዎቹ ይመጡባትና እርሷ በወር የተጣራ ሁለት ሺህ ለማታገኝበት ንግድ በዓመት 62 ሺህ ብር ግብር ክፈይ ይሏታል – ወያኔ ጋ ማሰብ ብሎ ነገር የለም፡፡ በግልጽ ሂድ ላይሉህ ይችላሉ – እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፤ ውጣ አይሉህም እንድትወጣ ግን ያስገድዱሃል፡፡ ያቺ ዘመዴ ምን ከምን ታምጣና ትክፈል? ኪሣራዋን ተከናንባ የባሏን እጅ እያየች ተቀምጣለች፡፡ አንተን በእነሱነት ከጠረጠሩህ ምንም ምክንያት ሳያስፈልጋቸው እንዳትኖር ማድረግ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከንግድ ውጪ እያስወጡ ሙልጭ ድሃ ያደረጓቸውን ወገኖቻችንን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡


የምትሠራበት ቤት የመንግሥት ከሆነ ለነሱ አሸወይና ነው – ኪራይና ግብር ይቆልሉብህና ተማርረህ በራስህ ጊዜ ውልቅ ብለህ እንድትወጣ ያደርጉሃል፤ በማግሥቱ በጥንቱ አነስተኛ ኪራይና በዝቅተኛ የፍሬ ግብር ግምት የነሱን ሰው ያስገቡበታል፤ ስንትና ስንት የትግሬዎች ሱቅና ትላልቅ ንግድ ቤት በግልጽ ካለቫት ሲሸጡ እያየህ ባጠገባቸው የምትገኝ ሚጢጢዬ የሌላ ሰው ሱቅ ግን ካለቫት ስትሸጥ ብትገኝ አሣር ሲገጥማት ታያለህ – እነሱን ማንም አይቆጣጠራቸውም፤ በአንዲት ሀገር ውስጥ ብዙ ዓይነት ዜጎችና ሁለት መንግሥታት በግልጽ የሚታዩት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ስትገነዘብ በደረስንበት የዝቅጠት ደረጃ ታርር ትደብናለህ – ግን እውነትም ሰዎች ስንባል ከእንስሳትም የወረድን ምን ያህል ከንቱዎች ነን? የሚሠራውን ግፍ ስትሰማ ይሰቀጥጥሃል፡፡

 ባለኝ መረጃ መሠረት በውድ ትምህርት ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የነሱ ልጆች ናቸው፤ ሌላው መንደር ያውደለድላል ወይም እንደሚፈጭ ጥሬ ጎዳና ላይ ተሰጥቶ ይውላል፡፡ የመንግሥት ት/ቤት ተብዬዎቹ ውሎ መግቢያ እንጂ ትክክለኛው የመማር -ማስተማር ሂደት የሚካሄድባቸው አይደሉም፡፡ በየቦታው የሚገነቡ ሕንጻዎችና የንግድ ተቋማት የነሱው እንደሆኑ ሁሉም ይናገራል፡፡


ከነሱ ውጪ ሌላው ነግዶም ሆነ ሠርቶ መብላት እንዳይችል በህግ የተገደበ ይመስላል፡፡ ለነገሩ ህግ የሚባል ነገር የለም፤ ሀገሪቱ በኳስ አበደች ዓይነት ጰራቅሊጦሳዊ ያልተለመደ የጉሽ ጠላ ስካር ውስጥ ትገኛለች፡፡ ለምሳሌ አትቀደም እንጂ ሰው ቢገድልህ ተከታትሎ በደለኛን ወደህግ የሚያቀርብ አካል ለማግኘት ትቸገራለህ፤ በኪነ ጥበቡ ይነጋል፤ ይመሻልም፡፡ የሙስናው ነገርም የጉድ ነው፡፡ በፖለቲካ አይሁን እንጂ ወንጀለኛን ወይም በሕግ ሥር የሚገኝን ሰው ለማስፈታት ጉቦ ከከፈልክ ባደረበት ወይም በዋለበት ማረፊያ ቤት አይውልም ወይም አያድርም ፡፡ ከሚነዳው የሕዝብ ትራንስፖርት መኪና አንድ ሰው በር ከፍቶ ዘልሎ ሲወርድ በመሞቱ ምክንያት የተከሰሰ አንድ ሾፌር ፍርድ ቤት በነጻ ካሰናበተው በኋላ ፖሊሶች አሥረው 17 ሺህ ብር ገደማ በሚስቱ በኩል አስመጥተው እንደተከፋፈሉ የሰማሁት በቅርቡ ነው፡፡


ሀገርህ ያለች ትመስላለች እንጂ በቁሟ ሞታልሃለች፡፡ ህግ ወደ ተራ ነገርነት ተለውጦ የምንተዳደረው በጉልበትና በሙስና ብቻ ሆኗል፡፡ በደሞዝ መተዳደር ስለማይቻልና ስለቀረም በሙስና የማይሠራ ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ብትሄድ ጥሩ የመቃብር ቦታ ለማግኘት፣ ረጂም የጸሎት ፍትሀት ለማግኘት፣ የሰበካ ጉባኤ አገልግሎት ለማግኘት፣ የልደት ሠርቲፊኬት ለማግኘት፣ አገልጋይ ከሆንክ ደህና ገቢ ወዳለው ደብር ለመዛወር፣ የድቁና ወይም የቅስና ማዕረግ ለማግኘት፣ በጠያፍ ድርጊት የክህነት ሥልጣንን ላለማጣት፣በቄሰ ገበዝነት ጥሩ ቦታ ለመሾም/ለመመደብ… ካለጉቦ አይሞከርም፡፡ ውድቀት ከዚህ በላይ ካለ እኔ አላውቅም፡፡


  ሥርዓቱ የሞሰነ (የጠፋ) ስለሆነ የዚህ ሁሉ ጥፋት እስፖንሰሩ ወያኔ ነው፡፡ (በአንዲት ጨዋታ ለምን ፈገግ አላሰኛችሁም – አንድ ሦስት የሚሆኑ ሙስሊም ጓደኛሞች ሶላት ላይ ናቸው፡፡ አንድ በቅርባቸው የነበረ ሌላ ሙስሊም ሣንቲሞችን በብዛት ከኪሱ ያወጣና እየሰገዱ እንዳሉ ሆጨጭ አድርጎ አጠገባቸው ይበትናል፡፡ በተንቃጨለው የሣንቲም ድምፅ ሰጋጆቹ ከስግደቱ ተናጥበው ወደተንቃጨለበት ሥፍራ ሁሉም በአንዴ በደመ ነፍስ ዘወር ይላሉ፡፡ ያኔ ያ ተንኮለኛ ሰውዬ “ይህንን ዱኣ እንኳን አላህ እኔም አልቀበለውም” አላቸው ይባላል፡፡ ለምን ትዝ አለኝ ግን?አዎ፣ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሞኝ የሚመስለን የሃይማኖት ሰዎች እጅግ ብዙ ነን፡፡ እርሱንና የርሱን እየረሳን ወደ ዓለም ብንጠፋና ከወንበዴዎች ጋር ብንወግን የወንበዴዎቹን የመጨረሻ ዕጣ እንጋራለን፡፡)


ትግሬዎች ተሳስተዋል፤ “የትኞቹ ትግሬዎች? “ በሚል ፀጉር አንሰንጥቅ፡፡ ኩይሃ ወይም እንደርታ ገጠር ውስጥ በላቡ አፈር እየገፋ የሚኖር ገበሬ መቼም ተሳስተሃል ልል አልችልም፡፡ ስለዚህ የተሳሳቱት ትግሬዎች ሕወሓትን አምልከውና አምነው ኢትዮጵያን ለማውደም ታጥቀው የተነሱትን እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህኞቹ ትግሬዎች ይህን ያህል ገሃድ የወጣ ዘረኝነት ውስጥ መግባት አልነበረባቸውም፡፡ መሪዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ተራዎቹ ዜጎች ግን ከትዝብት በሚያልፍ እስከዚህ ደረጃ ጭልጥ ብለው ወርደው በተሳሳቱ መሪዎች የጥፋት ጎዳና መትመም አይጠበቅባቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም “ነገ” የሚባል ጦሰኛ ቃል አለ፡፡


የትናንትን ታሪክ ማንበብ ያሰኘኝ – ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት – ዛሬን ከትናንትና ትናንትንም ከዛሬና ከነገ ጋር በማስተያየት መጪው ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት ለመተንበይ ነው፡፡ እንደዚያም ይቻላል፡፡ እናም እተነብያለሁ – ነገ ለትግሬዎች ክፉ ቀን ይሆናል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ እንደሚታየኝ የእኔን መሰል ደጋግ ትግሬዎች ሸክም ከባድ ነው፡፡ በትግሬነቴ ብዙ መሥራት የሚገባኝ አሁንና ለወደፊትም ብዙ የሥራ ጫና እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ በወንድሞቼና በእህቶቼ ተላላነት ምክንያት እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ አዝናለሁ፤ ማዘን ብቻውን ግን የታሪክን ቅጣት እንደማያስቀር እረዳለሁ፡፡


 እናም በትግሬነቴ ሸክሜ ብዙና የሚያጎብጥም መሆኑን የምገነዘበው ከዚህ አኳያ ነው፡፡ ዶክተር ኃይሉ አርአያ፣ አብርሃ በላይ፣ ኤልያስ ክፍሌ፣ አብረሃም ደስታ፣ አስገደ ገ/ሥላሴ፣ ፀጋዬ ገብረ መድኅን፣ ጌታቸው ረዳ(የኢትዮሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)፣ … እና ሌሎችም ጥቂት የማይባሉ ብርቅዬ ትግሬዎች እየደከሙ ያሉት ሦስተኛውን ዐይናቸውን ፈጣሪ ስለከፈተላቸውና የነገን የፈጣሪና የታሪክ ፍርድ ከወዲሁ በማወቃቸው እንጂ እንደትግሬነታቸው ቢሆን ውጪ ያሉት ወደሲዖሊቱ ኢትዮጵያ በመግባት ቢፈልጉ ሚኒስትር ቢፈልጉ የናጠጠ ነጋዴ ሆነው በደናቁርት ወንድሞቻችን አገዛዝ ሥር ሥጋቸውን በምቾት ሊያኖሩ በቻሉ ነበር፡፡


 ግን ግን “ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” እንዲሉ ነውና እነዚህ በሁለት እሳት ውስጥ ሆነው እየተለበለቡ የሚገኙ ትግሬ ወገኖቻችን ሁሉንም እንዳመጣጡ እንዲቋቋሙ ፈጣሪ ትግስቱንና ችሎታውን ሰጥቷቸው ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ እኩል ሀገር እንድትሆን እየተደረገ ባለው ሁለንተናዊ ትግል የበኩላቸውንና አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔር ከነሱም ጋር ይሁን፡፡
የወደፊቱ ጊዜ ከአማራነት ስሜት፣ ከትግሬነት ስሜት፣ ከኦሮሞነት ስሜት፣ … በጥቅሉ ከጎጠኝነት ስሜት በአፋጣኝ መውጣት የሚጠበቅብንና የምንገደድበትም ጊዜ ነው፡፡ በተመሳሳይ የቂሎች ዘፈን ነጋሪት እየደለቅን በከንቱ የምንጠፋፋበት ዘመን ማብቂያው ላይ የደረሰ ይመስለኛል፡፡


ለዚህ አስከፊ አደጋ ያጋለጡን ብዙ ታሪካዊ አጋጣሚዎች መኖራቸው እውነት ቢሆንም የአሁኑ ትውልድ ከአንጋፋዎቹ ንዝህላልነት ብዙ የሚማርና የራሱን መፃኢ ዕድል የተቃና እንዲሆን ጥረት የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡ በተቆፈረለት ጉድጓድ እየገባ ለማለቅ የቆረጠው ትውልድ በሂደት ለአዲሱ ትውልድ ሥፍራውን እየለቀቀ ይሄድና ወደመላው ዓለም የተበተነው ሥልጡኑ ኢትዮጵያዊ በአዲስ የአብሮነት ስሜት አዲሲቷን ኢትዮጵያ ገንብቶ እያንገሸገሸው ካለው የስደት ኑሮ ሊገላገል የወሰነ ይመስለኛል፡፡ አሮጌው ትውልድ ከነተንኮሉና ከነከፋፋይ ቅራቅንቦው ወደታሪክ መዝገብነት የሚከተት ይመስለኛል፡፡


 በዘር መሳሳብና በአንድ ቅጽበት የናጠጠ ከበር የሚኮንት ጊዜ ተወግዶ በወዝና በላብ ተሠርቶ የሚከበርባት ኢትዮጵያ ልትፈጠር ዳርዳርታው የተጀመረ ይመስለኛል፡፡ (የአንድ ባለሥልጣን የዘመድ ልጅ አሠራ ሁለተኛ ክፍል እምቢዬው ይለዋል፡፡ በአንዲት ቀጭን ደብዳ ከሞሰበ ስሚንቶ በዱቤ ስሚንቶ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ወዲያውኑ ያን ስሚንቶ ሸጦ ከወጪ ቀሪ 4 ነጥብ ምናምን ሚሊዮን ብር በከፈተው የባንክ አካውን ውስጥ ዘጭ ይልለታል – በድንጋጤ አለመሞቱ እሱው ሆኖ ነው – በአሁኑ ሰዓት ቢጠሩት የማይሰማ የልጅ ቱጃር ነው፤ እሱን መሰሎች ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አሉ፡፡ እኔ ብሆን በደስታ ብዛት ሞቻለሁ፡፡ እኛ እንዲህ ነን፡፡ ወያኔ እንዲህ ነው፡፡ በአንድ ሌሊት ወገኑን ማክበርና በአንድ ሌሊት ተመሳሳይ ደግሞ የሚጠላውን ወደ አሰቃቂ ድህነት በማውረድ ማማቀቅ የሚችል ሕወሓት ብቻ ነው፡፡)


የሸዋ አማራ ለቀብራራው ጎንደሬ እንደባሪያ የሚቆጠርበት ዘመን ነበር፤ አማራነት እንደ ልዩ ትምክህት እየተቆጠረ በባዶው የሚኮፈሱበት፣ ከባዶ እግር ሳይወጡና ትከሻ ላይ ያለቀን መርዶፋና አቡጄዲ ሳይቀይሩ እንዲሁ በከንቱ በዘር የትውልድ ሐረግ የሚኩራሩበት ዘመን ነበር፡፡ በአማራነት ሥራ መያዝ ወይም አለመያዝ፣ በትግሬነት ሥራ መያዝ ወይም አለመያዝ፣ በኦሮሞነት ሥራ መያዝ ወይም መልቀቅ የገሃዱ እውነታ አሳዛኝ ነፀብራቅ ነበር፤ አሁንም በባሰ ደረጃ እንደቀጠለ ነው፡፡ ደረጃው ይለያይ እንጂ የአሁን ጥፋቶች አሁን አልተጀመሩም ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡


 እውነትን እንዳለ መቀበል የንስሃ መጀመሪያና የፅድቅ መንገድ ስንቅ ነው፡፡ የነበሩን ችግሮች ናቸው ግዘፍ ነስተው ኅልውናችንን እስከመፈታተን የደረሱት፡፡ ወያኔ የጀመረው ጥፋት የለም፤ ግን አራቀቀና ጫፍ አደረሳቸው፡፡ ስህተትን ወርሶ በዐዋጅ ማፅደቅና የመንግሥት መለያ ማድረግ የወያኔ ተፈጥሮ ሆነ እንጂ ቀድሞም ስህተቶች ነበሩብን፤ አልነበሩብንም ማለት ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ግን ከራሱ ታሪክና ከየሚሰደድበት ሕዝብ ብዙ እየተማረ የወደፊት ሕይወቱን አስተካክሎ በዘልማድ ሳታጣ ያጣች የምትባለዋን ሀገሩን በቁጭትና በእልህ በጋራ ለመገንባትና በፍቅርና በመተሳሰብ ለመኖር የሚረባረብ ይመስለኛል – ነገ፡፡


 ምን እስክንሆን እንጠብቃለን? በዓለም ፊት ከዕቃነት ከመቆጠር የበለጠ ምን ሊደርስብን ይችላል? ከአሁን ዘመን በበለጠ ብሔራዊ ክብራችን የተዋረደበት ዘመን የለም፡፡ እናም ሁሉም ነገር እንደሚፀነስና እንደሚወለድም፣ እንደሚያድግና አርጅቶም እንደሚሞት በወያኔ አድጎና ጎምርቶ ለአካለ መጠን የደረሰው የብሔራዊ ክብራችን ውድቀትና የጋራ ማንነታችን መደብዘዝ አሁን በማርጀቱ የማይቀርለትን ሞት እየሞተና በአንጻሩ የወደቀው ክብራችን ትንሣኤውን የሚቀዳጅበት ብሩኅ ዘመን እየመጣ ይመስለኛል፡፡ ብዙ እውን ሊሆኑ የሚችሉ የሚመስሉኝ ነገሮች እየታዩኝ ስለሆነ ወያኔዎች በተስፋ መቁረጥ አትውቀሱኝ፡፡ በል በል የሚለኝ አንዳች ነገር ስላለ ነው እንጂ እናንተን ለማስቀየም ፈልጌ አይደለም፡፡


ወደነማን እናንጋጥ? መሲሆቻችን እነማን ናቸው? ወጣቱ ምን ከነማን ይማር?
እመለስባቸዋለሁ ወዳልኳቸው ሁለት ነገሮች ልመለስ፡፡ ሰው በጠፋበት ዘመን አንዲት ሴት ልጅ ከርቸሌ ውስጥ ተገኘች፡፡ ይህች ልጅ ርዕዮት ዓለሙ ናት፡፡ አንድ የዐረብ ሀገር ተረት ባማርኛ ላስታውሳችሁ፡፡ “እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳም፡፡” ተፈጥሮም እግዜርም አንድ ተመሳሳይ ሕግ ያላቸው ይመስላል፡፡ በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንዲጸነስ ያደርጋሉ፤ በብርሃንም ውስጥ ጨለማ፡፡ እነዚህ ነገሮች እየተፈራረቁ የሕይወትን ምንነት በአሉታዊና በአወንታዊ መልኮች ጎልተው እንዲታዩ ያደርጋሉ – አንዴ ይነጋል፤ አንዴ ይጨልማል፡፡ ምናልባት ባይነጋና ባይጨልም ኖሮ ማን ያውቃል ሕይወት ትርጉም አልባ ልትሆን ትችል ነበር፡፡


ስለዚህም ይመስላል እልም ባለ የተስፋ መቁረጥ ዘመን ውስጥ ተስፋን የሚያጭሩ ጥቂት ዜጎች ከወደቀው ትውልድ ውስጥ ብቅ የሚሉት፡፡ ስለዚህም ይመስላል ቆመናል የሚሉት በወደቁበት ሰዓት ከታናናሾች መካከል ታላላቆች የሚነሱትና የአርአያነትን መቅረዝ ከፍ አድርገው ይዘው እንደመጥምቁ ዮሐንስ በምድረ በዳ የነጻነትን ፋና የሚያበሩት፡፡ ስለዚህም ይመስላል ብዙዎች ወድቀው እንደዓሣማ የገማ ጭቃ ውስጥ ሲርመጠመጡ ጥቂቶች የኅሊናቸውን ጥሪ ተቀብለው በአካላዊ ስቃይ ለሚገኝ መንፈሣዊ ሃሴት የሚተጉትና ታሪካቸውን በወርቃማ ቀለም የሚጽፉት፡፡ ሕይወት ታላቅ ዩኒቨርስቲ ናት፤ ብዙ አየን – እያየንም ነው፡፡




ርዕዮት እግዚአብሔርና አላህ የሰጡን የኢትዮጵያ ዕንቁ ልጅ ናት፡፡ ርዕዮት በችግራችን ጊዜ ፈጣሪ የሰጠን እንስት ኤፍሬም ናት – “ኤፍሬም” ማለት “በመከራዬ ጊዜ የሰጠኸኝ ልጅ” ማለት ነው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ ርዕዮት ብዙ ያነበበች መሆንዋን ከመጽሐፏ መረዳት ይቻላል፡፡ መስዋዕትነት ከማወቅ ጋር ሲሆን የሠመረ ይሆናል፡፡ ማወቅ ብዙ ትናንሽ ግን አዘናጊ የሆኑ ዓለማዊ ነገሮችን እንድንንቅ፣ ታጋሽና አስተዋይ እንድንሆን፣ ከሚጠፋና ከሚጠወልግ ዝናና የዓለም ሀብት ይልቅ ለማይሞት የሀገርና የወገን ክብር እንድንተጋ… ያደርገናል፡፡ ይህን በርዕዮት፣ በእነእስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌ አማካይነት እያየነው ነው፡፡ ብዙዎች ሊሸከሙት የከበዳቸውን ቀምበር እነሱ ተሸከሙት፡፡ የኛ ክርስቶሶች እነሱ ናቸው፡፡


 የኛ ቤዛዎች እነሱ ናቸው፤ ብዙዎች ሲከዱን እነሱ ከጎናችን ሆነው ስለኛ የኛን መስቀል ተሸከሙ፡፡ ልደቱ አያሌውን የመሰለ ከሃዲ በወጣበት ማኅጸን እስክንድር ወጣበት፡፡ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ በወጣበት ማኅጸን አንዷለም አራገጌ ወጣበት፡፡ ገነት ዘውዴ በወጣችበት ማኅጸን ርዕዮት ዓለሙ ወጣችበት፡፡ ለጊዜው ማለት የምንችለው እንዲህ ብቻ ነው – ሌላ ምን ማድረግ እንችላለን? ምንም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት ጊዜ ሲመጣ ግን በተለይ ይሁዳዎች ተገቢ ፍርዳቸውን እንዲያገኙ በፍትህ አደባባይ በግልጽ እንጮሃለን፡፡


ባነበብኩት የ204 ገጽ ስብስብ ሥራዎቿ ውስጥ ይህች ወጣት ሴት ጋዜጠኛና ለዜጎች መብት ተሟጋች ያልዳሰሰችው ማኅበራዊ ችግር የለም፡፡ ከይዘቶቹ በመነሣት ነው ልጂቱ ብዙ ያነበበች መሆንዋን የተገነዘብኩት፡፡
 ለስኬታማው ውድቀታችን እንደ አንድ ማሳያ ይሆነኛል ብዬ ካሰብኩት ውስጥ የአንድ ዘምቦለል ኢትዮጵያዊን ታሪክ ከርዕዮት መጽሐፍ ጠቅሼ መናገር እፈልጋለሁ፡፡
“… በዘመናችን ከሚገኙ ታዋቂ ሰዎቻችን መካከል አንዱ የሆኑት አንጋፋው የማሰታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ በአንድ ወቅት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ይታወሰናል፡፡
 በቃለ ምልልሳቸው ሴትና መኪናን ቶሎ ካልቀያየሩት ባሕርይው እንደሚበላሽ ሊያስረዱን የሞከሩት አቶ ውብሸት ሁሌም ለብሰው ከሚታዩት ካባ ጋር አብረው የጠቀስነውን ብቃት (የሕዝብ ሰው የመሆንን ብቃት ማለቷ ነው) አለመጎናጸፋቸውን እንረዳለን፡፡” (ገጽ 177)
ርዕዮት የጻፈችበት ርዕሰ ጉዳይ እንስታዊነት (ፌሚኒዝም) በኢትዮጵያ ያለበትን ችግር ነው፡፡ የጠቀሰችው ሰውዬ ታዋቂና ዝነኛ ነው – አርአያ ሊሆን ይገባው የነበረ ነገር ግን እንደኔ አመለካከት ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ገደል የከተተ ብኩን ዜጋ ነው – መፍረድ ቀላል ነው መቼም፡፡
ታዋቂነት ዕዳ ነው፡፡ ብዙ መዘዝ አለበት፡፡ አንድ ሰው ታዋቂ ከሚሆን ይልቅ የማይታወቅ ቢሆን ይሻለዋል፡፡ ከታዋቂነት ጋር የሚመጡ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ውሎውና አዳሩ ሁልጊዜ በክትትል ውስጥ ነው – እሱ ተኝቶ የማይተኙለት ሰዎች አሉ፤ በበጎም በክፉም፡፡ ታዋቂ ሰው በባህርይው እንደ መላእክት የሆነ ያህል ወይም እንዲሆን የሚጠበቅበት መሆኑን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች ሞልተዋል፡፡ ለአንዳንድ የዋህ ታዛቢ ታዋቂ ሰው የማይጠጣና የማይሰክር፣ የማይቆጣና የማይሳደብ፣ ከእንትን የራቀ ድንግላዊ፣ የማይዋሽና የማይቀጥፍ፣ … በጥቅሉ ፍጹም ሰው አድርጎ የማየት አዝማሚያ አለ፡፡


ግን ስህተት ነው፡፡ ሰዎች እንደመሆናቸው ሰው የሚሆነውን ይሆናሉ፤ ሰው የሚያደርገውን ያደርጋሉ፤ ሰው የሚኖረውም ይኖራቸዋል፡፡ ልዩነቱ ግን በነሱ ጎልተው እንዲወጡ የማንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች መኖራቸው ነው፡፡ እነሱም መጠንቀቅ የሚገቧቸው እኛም ከነሱ የምንጠብቃቸው በአነስተኛው ማሟላት የሚገቧቸውን ሥነ ምግባራት ማሟላት ሲያቅታቸው ካስቀመጥናቸው ከፍ ያለ ቦታ አውርደን እንፈጠፍጣቸዋለን – እንደውብሸት፡፡


ለኔ ውብሸት ማለት አርአያ ሊሆን የማይችል እንዲሁ ተራና ቅሌታም ሽማግሌ ነው፤ ዕድሜውም ሆነ ያሳለፈው ተሞክሮ ያላስተማረው ከነማሙሽነቱ የሸበተ የእንጨት ሽበት ነው፤ ካባውን የሚያወልቅልኝ ሰው ስንት ጊዜ ፈልጌ አጣሁ፡፡ በባህል ማፌዝ ነው ሰውዬው የተያያዘው፡፡ ካባውን እንዲያወልቅ ብትነግሩልኝ ውለታ አለብኝ፡፡ ከ15 እና ከ16 ዓመት … ነውር ነው!
ይህን መሰል የእንጨት ሽበት በሞላባት ሀገራችን ውስጥ ነው እንግዲህ እነቴዲ አፍሮ ስለጨዋ ባህላችን እየዘመሩ እነውብሸት እያፈራረሱት የሚገኙትን ባህላችንን እየጠገኑ የሚገኙት፡፡ እግዚአብሔር የነዚህን ደጋግ ዜጎች ጸሎት ምህላቸውን ይቀበል ዘንድ፣ ምድራችንን ዳግም የጨዋዎች መፍለቂያ ያደርግልንም ዘንድ እንለምነው፡፡

 ወደፕሮፌሰር መጽሐፍ ስመጣ፡-
በዩንቨርስቲ ኮሌጅ የክፍል ኃላፊ የሆንኩት በመከራ ሰው ጠፍቶ ነው፤ ገፋፍቶ የክፍል ኃላፊ እንድሆን ያደረገኝ ዠቪ ያቬትዝ የሚባል እሥራኤላዊ ዲን ነበረ፤ ወደ አገሩ ለዕረፍት ሲሄድ ተጠባባቂ ሆኜ በሱ ቦታ እንድሠራም አግባባኝ፤ … (ገጽ 8)
የዩንቨርስቲው ሠላሳኛ ዓመት ሲከበር የአገልግሎት ሽልማት ስለሚሰጠኝ በበዓሉ እንድገኝ ፕሬዝደንቱ [ዶክተር]ዱሪ መሀመድ ነግሮኝ ነበር፡፡ በዩንቨርስቲ ኮሌጅ አንዲት ኤሊ አለችና እስዋ ትቀድመኛለች፤ ለስዋ ስጣት፤ አልመጣም፤ ስሜን አትጥራ ብዬው ነበር፡፡ ግን ባልነበርሁበት ስሜ ተጠራ፡፡ የደርግ አሥረኛ ዓመት ሲከበርም ልሻን እንደሚሰጠኝ ሰምቼ የጥሪ ካርዱ ላይ ባለ ስልክ ደውዬ እንደማልገኝ አስታውቄ ቀረሁ፤ በሌለሁበት አሁንም ስሜ ተጠራ፤ በጃንሆይ ዘመንም ወደ ፅሕፈት ሚኒስቴር ሄጄ ልሻን እንድቀበል ተነግሮኝ አልሄድኩም፡፡ … (ገጽ 13)


ፕሮፌሰር በነዚህ አባባላቸው ምን ማለት እንደፈለጉ ባውቅ ደስ ባለኝ፡፡ በመሠረቱ ሥልጣንን መውደድና መጥላት ግለሰባዊ ጉዳይ ነው፡፡ አያጣላም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ሥልጣንን ቢጠላ ሀገርን የሚመራት ሰው እንደማናገኝ መረዳት ይገባል፡፡ ስለዚህም ሥልጣንን መጥላት ወይም ከሥልጣን መሸሽ ሁልጊዜ የጤናማነት ምልክት እንደሆነ ተደርጎ መወሰድ ያለበት አይመስለኝም፡፡ መተኮር ያለበት ሥልጣንን በአግባብ የመጠቀም ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ሥልጣንና ሽልማትን መጥላትን ለመግለጥ የሚከድበት መንገድ ደግሞ የጨዋነትን ፈር የተከተለ ሊሆን ይገባዋል፡፡ አንድ ሰው አደረገው ተብሎ ለሚታመን መልካም ተግባር እንሸልምህ ሲሉት ለዔሊዋ ስጧት ብሎ ማጣጣል ከሞራል አንጻር ምን ሊባል እንደሚችል በበኩሌ ይጨንቀኛል፤ ለዚህም ነው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይህን ክፍል ሳነብ የሚገባኝ ነገር አጥቼ ወይም እንዲገባኝ የማልፈልገው ሊገባኝ ፈልጎ ሲፈታተነኝ ያን ጠልቼ በሃሳብ የናወዝኩት፡፡ ሰውን እንደመረዳት ያለ አስቸጋሪ ነገር የለም፤ ማለት በፈለገው ማለት ያልፈለገውን ወይም ማለት ባልፈለገው ማለት የፈለገውን ለመገንዘብ እንደመቃጣት የሚከብድ ነገርም የለም፡፡ በዚህ የፕሮፌሰር የሥልጣን አልወድም ገለጻ የገባኝ ነገር ሣይገባኝ ቢቀር እንደሚሻለኝ ተመኘሁ፡፡


በመሠረቱ ሹመትን ጠልቶ ዋና ትኩረቱ ከሹመት ጋር ስለሚያያዘው ፖለቲካ ማውራት አይቻልም፤ ሹመት በዓለም ብቻም ሳይሆን በገዳማትም አለ፡፡ ሀገርን ለማቅናትም ሹመት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ እውነተኛና ለሕዝብ በቀናነት የሚሠራበት ሹመት ሊጠላ አይገባም፡፡ በሌላም አነጋገር ሹመትንና ሥልጣንን አምርሮ መጥላት ባለሥልጣናትንና ሹሞችንም አብሮ እንደመጥላት ያህል ሊያስቆጥር ይችላል፡፡ ሥልጣንን በመጥላትና በማስጠላትም ተጨባጭ ቁም ነገር መሥራት የሚቻል አይመስለኝም፤ ዓላማው ግልጽ አይደለምም፡፡ ሥልጣንን የሚጠላ ሰው ደግሞ ስለሥልጣንና ስለፖለቲካ የሚናገረው ነገር ላይ የተወሰነ ጥላ ማሳረፉ አይቀርም፡፡ ያልተዛባና ፍትሃዊ አስተያየት ስለመስጠቱም አጠራጣሪ ነው፡፡ ቀድሞውን አወንታዊ እይታ የለውም ተብሎ ስለሚገመት ነጻና ገለልተኛ አስተያየት ይሰጣል ተብሎ አይገመትም፡፡ …


ላጠቃልል ነው፡፡ የሕዝብ ሰው መሆን ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት ከባድ ነው፡፡ ሰውን ማክበር ያስፈልጋል፡፡ ትሁት መሆን ይገባል፡፡ ከአፈንጋጭ ስብዕና ለመራቅ ዘወትር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በዚህች ምድር የሚያኮራና እንድንታበይ ሊያደርገን የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡ ሁሉም አላፊና ጠፊ ነው፤ ሀብትን ብል ይበላዋል፤ ዕውቀትን ‹ምሥጥ› ያነክተዋል፤ የዝናን ወርቃማ ቀለም ዘመን ያደበዝዘዋል፤ መልክና ውበት የዕድሜ ሽብሽባት ያጠወልገዋል፡፡ ምን ቀረን? ምንም! አንድ በትምህርትም ሆነ በሌላ ነገር ዕውቅናና ስመጥርነትን ያገኘ ሰው ከግል ሕይወቱ ሥምረት ጀምሮ ለሌሎች አርአያ ለመሆን መትጋት ይጠበቅበታል፡፡


 ትዳርን ማክበር፣ ሃይማኖታዊ ትዕዛዛትን በተቻለው መጠን ማክበር፣ ሥነ ልሣናዊ የመግባባት ደረጃዎችን መለየትና በአግባቡ መጠቀምን መልመድ (ለምሳሌ አንተ እና አንቱ የሚባሉ አጠቃቀሞችን፣ የማዕረግ ስሞችን እንደዬሁኔታው መገልገልን ማወቅ …)፣ በወገን ችግር ጊዜ ቀድሞ መድረስንና ከልብ ለመርዳት መሞከር፣ ከምንም ዓይነት ዕብሪታዊና ትዕቢታዊ የአነጋገር ሥልት መለየት … ይጠበቅበታል፡፡ የተገነባ ስም እንደሚናድም መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ቢቻልም አላሙዲን ብቻ ይበቃናል፡፡ (ሰው ባጣንበት ዘመን ሰው የሆኑን እነቴዲ አፍሮና ታማኝ በየነ የሰይጣናዊ የልብ እብጠት ሰለባዎች እንዳይሆኑብንና እንዳይሰናከሉብን በበኩሌ እጸልያለሁ፤ ሁላችንም እነዚህን ወገኖች እንዲያበዛልን በአቋማቸው እንዲያጸናልንም እንጸልይላቸው፡፡
 የሰው ዐይን ድንጋይ ይሰብራልና ከዐይን ያውጣልን፡፡ ሰው አልበረክትልን ብሎ ተቸግረናልና ይህን ሾተላይ ፈጣሪ እንዲያነሳልን ወደላይ እንማጠን፡፡)
እንዲያው ግን ሌላውን ነገር ሁሉ ልርሳውና አርአያ የሚሆን ሰው ጌታ በኪነ ጥበቡ አስተካክሎ ይስጠን – ከየዘርፉ፡፡ ደግሞም ይችላል፡፡ ከቁጣ የራቀ፣ ከትዕቢት የተቆራረጠ፣ ከትምክህት የተፋታ፣ ከጥበብ የተጋባ፣ አስተዋይነትና ትህትና ሞልቶ የተረፈው፣ ቅን አሳቢና ለሀገር ለወገን ተቆርቋሪ የሆነ የሕዝብ ሰው ይስጠን፡፡ ሁሉን ነገር ማድረግ የማይገደው የኢትዮጵያ አምላክ እኛንም ባሕርያችንን ገርቶ እንደገና ይፍጠረንና እርስ በርስ የምንተሳሰብ፣ ደገኞችና አስተዋዮች ያድርገን፡፡ ለዘመናት ከሚጨፍርብንና እግር ከወርች በማሰር ኮድኩዶ ከያዘን የምቀኝነት አባዜ ነጻ የወጣን እንሆን ዘንድም ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን በሉ፡፡ ኧረ አቅላቀችንን ይመልስልን ወገኖች! ተበታትነን ቀረን እኮ፡፡ ብዙ ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልና በነገር እንዳላሰለቻችሁ ነገሬን ሳላንዛዛ ባጭሩ እዚህ ላይ ልቋጭ፡፡

ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!

የኃያላኑ የንዋይ ጥማትና የደቡብ ሱዳን የጎሣ ፍልሚያ
south sudan and the superpowers
ከተመሠረተች ምንም ያህል ያልሰነበተችው ደቡብ ሱዳን ሕዝቧ ሰላሙንና ነጻነቱን በደስታና በጸሎት አጣጥሞ ሳይጨርስ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከወደቀች አንድ ወር አልፏታል፡፡ ጎሣን መሠረት በማድረግ የተቀሰቀሰው ፍልሚያ ግን የተጀመረው ገና ደቡብ ሱዳን አገር ከመሆኗ በፊት እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በደቡብ ሱዳን ሣር ላይ የኃያላኑ ዝሆኖች የእጅ አዙር ጠብና ፍጥጫም አብሮ የሚጠቀስ ነው፡፡
አፍሪካ ከምዕራባውያን ቅኝ ግዛት ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ የመፈንቅለ መንግሥትና የእርስበርስ ጦርነት ትዕይንቶችን ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ ይህን “coup-civil war trap” አዙሪት በአብዛኛው የመከሰቱን ሁኔታ የፖለቲካ ተኝታኞች የሚስማሙበት ነው፤ ዋንኛውንም ምክንያት ጠንካራ ተቋማት ያለመመሥረታቸው ውጤት እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡
አዲስ አገርም ሆነ መንግሥት ምስረታ ወቅት የሚከሰቱ ሁለት አካሄዶች አሉ፡- በሕዝብ ይሁንታ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል ወደ ሥልጣን የሚመጣው ቡድን በአንድ በኩል የፖለቲካ ተቋማት እንዲመሠረቱና ሥልጣንን ለተቀናቃኞቹ በማካፈል ተቀባይነት ያለው አመራር ለመመሥረት ይፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሥልጣን ማጋራቱ ተቀናቃኞቹን ኃይለኛ እንዲሆኑ ስለሚያደርግ ወደፊት እነዚሁ ተቀናቃኞች ኃይላቸውን አስተባብረው መፈንቅለ መንግሥት ያደርጉብኛል የሚል ሥጋት ውስጥ ይገባል፡፡ የመፈንቅለ መንግሥቱ ስጋት ሥልጣንን ከማጋራትም ሆነ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ከማድረግ ስለሚበልጥበት አስቀድሞ ማካፈል የጀመረውን ሥልጣን በመፈንቅለ መንግሥት ፍራቻ መልሶ መሰብሰብ ይጀምራል፡፡
በቀጣዩም የራሱን ታማኞች በዙሪያው በማድረግ ራሱ ያጥራል፤ ሥልጣኑንም ያጠናክራል፡፡ የደኅንነቱንና የፖሊስ እንዲሁም የጦሩን ኃይላት በራሱ ጎሣ አባላት ወይም ቁልፍ ታማኞች ጠቅልሎ ይይዛል፡፡ ተቀናቃኞቹን በተወሰነ የሥልጣን ሣጥን ውስጥ በማስገባት በዓይነቁራኛ መከታተል ይጀምራል፡፡
የታማኝነት መለኪያው በጣም እየጨመረ ሲሄድ የሥልጣኑ አጥር ከጎሣ በማለፍ በቤተሰብ ደረጃ ይወርዳል፡፡ የፖለቲካ ተቋማትን በማጠናከር ሕዝብን ሙሉ የመብቱ ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ መፈንቅለ መንግሥትን በመፍራትና በሥልጣን ወሰን ለሌለው ጊዜ ለመቆየት ሲባል በሚወሰደው እርምጃ የራስ ወገኖችን በግልጽ የመጥቀም አሠራር ይንሰራፋል፡፡ ሙስና፣ ንቅዘት፣ ወንጀል፣ “የመንግሥት ሌብነት”፣ ወዘተ ይጠናክራል፡፡ በአንጻሩ ቀድሞ የትግል ጓዶች የነበሩ የሥልጣን ክፍፍሉ እያነሳቸው ሲሄድ ቂም፣ ጥላቻ፣ “እንዴት ተቀደምኩ”፣ ወዘተ የሚል እልህ ውስጥ በመግባት በራሳቸው ጎሣና ቤተሰብ ዙሪያ ኃይል ማስተባበር ይጀምራሉ፡፡
SudaneseSoldierሁኔታው በዚህ መልኩ እየተፋጠጠ ገሃድ ከመውጣቱ በፊት አሰቀድሞ የመፈንቅለ መንግሥት ፍራቻ የነበረበት ኃይል ቀድሞ የመምታት እርምጃ በመውሰድ በታማኞቹ ድጋፍ ሥልጣኑን የማዳን ጊዜያዊ ዕድል ይገጥመዋል፡፡ የተገፉትና የተገለሉት ኃይሎች ወዲያው የመቋቋም ኃይል ካላቸው ፊትለፊት ይገጥሙታል፤ አስቀድመው ከተመቱ ግን ለጊዜው ተሸናፊ ቢሆኑም ቀኑን ጠብቆ ሊነሳ ወደሚችል የጎሣና የዘር እንዲያም ሲል የቤተሰብ ግጭት ውስጥ መግባታቸው የጊዜ ጉዳይ ይሆናል፡፡
መፈንቅለ መንግሥትን ለመከላከልና በሥልጣን አለገደብ ለመቆየት ሲባል የአፍሪካ መሪዎች ወደ እንደዚህ ዓይነት የማያባራ ሰቆቃ ሕዝብን እየመሩ “ሕዝባዊ ነን”፤ “በ99%” አብላጫ ምርጫ አሸንፈን ወንበር ይዘናል፤ “ልማታዊ መሪዎች ነን”፤ “ሁሉም ነገር ወደ ልማት”፤ “ጉዞ ሕዳሴ፣ ውዳሴ” በማለት ራሳቸው ሰክረው ሕዝብን አስክረው ለማደንዘዝ ይሞክራሉ፡፡ ለዓመታት ሲረጩት የቆዩትን የጎሰኝነት መርዝ በልማት ማር ለመቀባት ይሞክራሉ፡፡ ሥልጣኔን ከማጣ የእርስበርስ ዕልቂት ይከሰት፣ ደም ይፋሰስ፣ ህጻናት በማያባራ ሰቆቃ ውስጥ ይግቡ፣ እናቶች ዕድሜላካቸውን ያልቅሱ፣ ዜጎች መቅኖ ቢስ ይሁኑ፣ … በማለት የራስን ዘርና ጎሣ ብቻ ለዘላለም ሲጠቅሙ ይኖሩ ይመስል ራሳቸውን መልሶ በሚያወድም የማያባራ መከራ ይጥላሉ፡፡ በሥልጣን ለመቆየት የእርስበርስ ጦርነትን ይጋብዛሉ፤ ራሳቸው የቀበሩት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳው ቦምብ ግን ልማትን ከዘርና ጎሣ እንደማይለይ የዘነጉት ይመስላል፡፡
በደቡብ ሱዳን የኃያላኑ ፍጥጫ
21ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች የመጣችውን ቻይና ልዕለ ኃያልነትን ለዓመታት በብቸኝነት የተቆጣጠረችውን አሜሪካ በሁሉም መስክ እየተገዳደረች ትገኛለች፡፡ ሁኔታው ያልጣማት አሜሪካ ይህንን የቻይና አካሄድ ለመገደብ ከተቻለም ለማስቆም ዕቅድ አውጥታ ስትንቀሳቀስ ቆይታለች፡፡ በተለይም ቻይና ከአፍሪካ አምባገነኖች ጋር በብድርም ሆነ በተዘዋዋሪ ስጦታ መልክ የምታከናውነው ስምምነት የምዕራባውያኑን በተለይም የአሜሪካንን ውቃቢ ያስቆጣ ተግባር ሆኖ ከርሟል፡፡
በዓለምአቀፍ ደረጃ ሸቀጧን እያራገፈች ያለችው ቻይና በፍጥነት እያደገ ያለውን ኢኮኖሚዋን ለማስቀጠል ከየትኛውም አገር ለምታገኘው ጥሬ ሃብት በተለይም ነዳጅ ከፍተኛ ዋጋ ትከፍላለች፡፡ ይህ የቻይና “ጭፍን” አካሄድ ደግሞ ምዕራባውያን ቻይናን ለማጥመድ የሚጠቀሙበት አይነተኛ መሣሪያ ሆኖላቸዋል፡፡
ከጅምሩ ከአልበሽር ሱዳን ጋር “በነዳጅ ፍቅር” የተለከፈችው ቻይና፤ ሱዳን ምዕራባውያን የሚያደርሱባትን ማዕቀብም ሆነ ማስፈራሪያ እንድትቋቋም በተለያዩ መንገዶች ረድታታለች፡፡ አልበሽር በዓለምአቀፉ ፍርድቤት ቢከሰሱም ሆነ ከምዕራብ መንግሥታት ውግዘት ቢደርስባቸውም ቻይና ከአፍሪካ አምባገነኖች ጋር በመሆን “አንለያይም” ስትቀኝባቸው ነበር፡፡ በመሆኑም ሱዳንን ለማንበርከክም ሆነ ለመቅጣት እንዲያም ሲል የቻይናን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማጨናገፍና ኢንቨስትመንቷንም ለመከፋፈል ድርብ ተጽዕኖ የሚያመጣው ዕቅድ በምዕራባውያን ተነደፈ – ሱዳንን መከፋፈል፡፡
ለዓመታት ደቡብ ሱዳንን ነጻ ለማውጣት ሲታገል የነበረው ኤስ.ፒ.ኤል.ኤ. ይህንን አጀንዳ የሚያስፈጸም ሁነኛ መሣሪያ ሆነ፡፡ በጆን ጋራንግ ዘመን ወደ ስምምነት እየመጣ የነበረው የአማጺያኑና የሱዳን ውዝግብ ጋራንግ ከሞቱ በኋላ አቅጣጫውን በመቀየር ደቡብ ሱዳን በአገር ደረጃ እንድትመሠረት አሜሪካ ግልጽ አቋም በመያዝ ተጸዕኖ አደረገች፤ ከበቂ በላይ ፕሮፓጋንዳም ነፋች፡፡south sudan oil
በሌላ በኩል የአልበሽርን ሱዳን ይበልጥ መልከጥፉ ለማድረግና የነጻዪቱን ደቡብ ሱዳን መመሥረት ለማፋጠን የዳርፉር ቀውስ በአሜሪካና እስራኤል ምሥጢራዊ ድጋፍ ያገኝ ቀጠለ፡፡ በመጨረሻም ከ2 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያለቀበት ጦርነት በደቡብ ሱዳን መገንጠል ተጠናቀቀ፡፡ የምዕራባውያን በተለይም የአሜሪካ ታላቅ ውለታ ያለባት ደቡብ ሱዳን ገና ነጻ አገር ሳትሆን የዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አባል ለመሆን ማመልከቻ በማስገባት ለአሜሪካ ቀብድ መክፈል ጀመረች፡፡
ለደቡብ ሱዳን ነጻ መውጣት ቀጥተኛና ግልጽ ድጋፍ ትሰጥ የነበረችው አሜሪካ ደቡብ ሱዳን ነጻ አገር ከሆነች በኋላ እንደታሰበው በአገሪቷ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ አልቻለችም፡፡ እጅግ ኋላ ቀር የሆነው የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ ከቻይና ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ ሊወጣ አልቻለም፡፡ ሱዳን ከመከፋፈሏ በፊት የ20 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የነበራት ቻይና ከክፍፍሉ በኋላ በደቡብ ሱዳን ብቻ የ8ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት አላት፡፡
ይህ ከፍተኛ የሆነ በነዳጅ ላይ ያተኮረ ኢንቨስትመንት የቻይናን የነዳጅ ጥማት የሚያረካ ባይሆንም የዛሬ ወር አካባቢ የእርስበርስ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በነበሩት 10ወራት ብቻ ቻይና ከደቡብ ሱዳን 1.9ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ወይም 14ሚሊዮን በርሜል ቀድታለች፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ ይህ የነዳጅ መጠን ቻይና ከናይጄሪያ በዓመት ከምታስመጣው በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ሬክ ማቻር ዲንካ እና ኑዌር በማለት ዘር ለይተው ፍልሚያ ከጀመሩ ወዲህ ግን የነዳጅ ምርቱ 20በመቶ ወርዷል፡፡ ዋናው የእርስበርስ ጦርነት በነዳጅ በበለጸጉት የዩኒቲ እና ኧፐር ናይል ጠቅላይ ግዛቶች አካባቢ መሆኑ የጦርነቱ ዋንኛ አካሄድ ምን ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገላጭ ነው፡፡
በትጥቅ ትግሉ ወቅት የአሜሪካንን እና የእስራኤልን ድጋፍ ሲያገኝ የነበረው የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ግምባር አሁንም በሳልቫ ኪር አገዛዝ ከሁለቱ አገራት የሚያገኘው ጥቅም አልቀረበትም፡፡ የቻይና ኢኮኖሚያዊ የበላይነትና በአፍሪካ መንሰራፋት የልዕለኃያልነት ጥያቄ ያስነሳባት አሜሪካና ተባባሪዎቿ ጉዳዩን ሲያጠኑና ተግባራዊ እርምጃ ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡ በተለይ በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ (አፍሪኮም – AFRICOM) መቋቋም አንዱና ዋንኛው የቻይናን የንግድ እንቅስቃሴ የመቆጣጠሪያ መንገድ መሆን እንዳለበት ወታደራዊ ጠበብቶች ስታቴጂካዊ ጥናቶች ያደረጉበት ነው፡፡
ደቡብ ሱዳን ነጻ ከወጣች በኋላ አሜሪካና ደጋፊዎቿ ወዲያውኑ የኢኮኖሚ የበላይነት ለመቆጣጠር ባይችሉም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ግን ቆይተዋል፡፡ በተለይ ከነጻነት በኋላ እስራኤል ከደቡብ ሱዳን ጋር ውሃ ለማጣራት፣ የውሃ ጨውነትን ለማስወገድ፣ ውሃ ለማመላለስ፣ እንዲሁም ለመስኖ ስምምነት ፈርማ ነበር፡፡ በእርግጥ ስምምነቱ በዚህ መልኩ ቢፈረምም ሥራውን በዋንኛነት የሚያከናውነው በውሃ ቴክኖሎጂ ሳይሆን በመሣሪያ ማምረት የታወቀው የእስራኤል ወታደራዊ ኢንዱስትሪ (አይ.ኤም.አይ.) መሆኑ በደቡብ ሱዳን ውስጥ የአሜሪካ ወዳጆችን አቅጣጫ የሚያሳይ ነው፡፡ በእርግጥ አይኤምአይ ከውሃ ጋር በተያያዙ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ እንደ አማካይ ሆኖ የሚሠራ ቢሆንም ወታደራዊ ተቋም እንደመሆኑ ለግጭቶች፣ ለጦር መሣሪያዎች እና ገንዘብ ዝውውር እንደ አማካይ ሆኖ እንደሚሰራ ጉዳዩን የሚከታተሉ ይጠቁማሉ፡፡
የቻይናን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የበላይነት ለመገደብ በተቀነባበረ ሁኔታ እየተካሄደ ያለው የደቡብ ሱዳን ግጭት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳሄድ አሜሪካ ግጭቱ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ “ዲፕሎማሲው” ላይ ተግታለች፡፡ የጋዳፊን አገዛዝ በመገርሰስ ቻይናን ከ20ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሣራ ላይ እንድወድቅ የተደረገበት የምዕራባውያን ዕቅድ፤ በደቡብ ሱዳን ላይ ተግባራዊ ሲሆን በአካባቢው ባሉ አገራት (በተለይ በኢትዮጵያ) ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ተሰግቷል፡፡ በመሆኑም “ሁኔታውን አስቀድሞ መቆጣጠር ኃላፊነቴ ነው” ያለች የምትመስለው አሜሪካ፤ የሳልቫ ኪር ወዳጅ የሆኑትን እና በአሜሪካ ጥቅም አስከባሪነታቸው የሚታወቁትን ዩዌሪ ሙሴቪኒን የመጀመሪያ ተሰላፊ አድርጋለች፡፡ ለአሜሪካ ሲሉ በጎረቤት አገር ጦርነት እስከመክፈት የሚታወቁት መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ ለዚህ ተላላኪነት ገጣሚ ሰው ነበሩ፡፡
ግጭቱ እንደጀመረ ሙሴቪኒ ጣልቃ ለመግባትና ሳልቫ ኪርን ለመደገፍ ጊዜም አልወሰደባቸውም፡፡ በቅልጥፍና የወሰዱት እርምጃም አስቀድሞ ትእዛዝ የተሰጣቸው ወይም ግጭቱን “በተስፋ” ሲጠብቁ የነበረ አስመስሎባቸዋል፡፡ 1,600 ወታደሮቻቸውን ወደዚያው በመላክ የተላላኪነት ሥራቸውን የጀመሩት የዑጋንዳው አምባገነን፤ ሬክ ማቻር በአዲስ አበባ ላይ በሚደረገው የሰላም ድርድር የማይስማሙ ከሆነ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን አስተባብረው ወታደራዊ ክንዳቸውን በማሳረፍ እንደሚያንበረክኳቸው አስጠንቅቀው ነበር፡፡ የሙሴቪኒ ሁኔታ መለስ ባይኖሩም ለሁለት እንተካለን ብለው የገቡትን ቴድሮስ አድሃኖምና ስዩም መስፍንን እንዲሁም ሌሎች የህወሃት ኃላፊዎችን “ያስደነገጠ” መሆኑን መናገራቸውን በቀጣናው ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑ ጠቅሶ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል፡፡
ዋንግ ዪ
ዋንግ ዪ
ቻይናም ግጭቱ እንደተጀመረ በደቡብ ሱዳን ካላት ጥቅም እና በምዕራባውያን ከተቀነባበረባት ጥቃት አኳያ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሁለቱም ወገኖች በአስቸኳይ ወደ ስምምነት እንዲደርሱ ስትመክር ነበር፡፡ አንዳንድ የሚዲያ መረጃዎች እንዳመለከቱት ሚኒስትር ዋንግ ዪ በግላቸው ሁለቱን ወገኖች ለመሸምገል ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ጥረቱ ባይሳካላቸውም ሁኔታው ቻይና ምን ያህል እንዳሳሰባትና በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንደሰጠች በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡
ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅና ከምዕራባውያን ጋር “በፍቅር” ዓለም ውስጥ ያሉትን ሳልቫ ኪርን “ዲንኮክራሲ” (የዲንካ ጎሣ የበላይነት) የዘር ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ አምባገነን፣ ወዘተ እያሉ ከኑዌር ጎሣ የሆኑት ሬክ ማቻር ቢከሷቸውም፤ እርሳቸውም ከዚሁ የዘርና ለሥልጣን የመስገብገብ ባህርይ ውጭ እንዳልሆኑ የቀድሞ ታሪካቸው ይመሰክራል፡፡ እንዲያውም በትጥቅ ትግሉ ወቅት “የቦር ዕልቂት” እየተባለ የሚጠቀሰውን በመምራት ኑዌሮች ከ2ሺህ በላይ ዲንካዎች ለጨፈጨፉበት ወንጀል ዶ/ር ሬክ ማቻርን የሚከሷቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ቀጥሎም ከአልበሽር ሱዳን ጋር በመስማማት የካርቱምን ስምምነት በመፈረማቸው “በከሃዲነት” የሚወነጅሏቸውም የዚያኑ ያህል በርካታ ናቸው፡፡ ሥልጣን አልያዙም እንጂ ከሚወቅሷቸው ሳልቫ ኪር ባልተናነሰ መልኩ ዘረኛና የሥልጣን ጥማተኛ በመሆናቸው መንበሩን ቢቆጣጠሩ “የተማረ አምባገነን” ከመሆን እንደማያልፉ የደቡብ ሱዳንን ጉዳይ የሚከታተሉ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ሬክ ማቻር ትምህርታቸውን ስኮትላንድ የተከታተሉ ሲሆን በስትራቴጂክ ዕቅድና ኢንዱስትሪ የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው፡፡
s sudan cease fireቀናትን ያስቆጠረውና “በርካታ ድርድር” ተካሄደበት የተባለው ስምምነት ባፈው አርብ እንደተፈረመ ህወሃቶቹ ስዩም መስፍንና ቴድሮስ አድሃኖም ትጉ ሠራተኞች መሆናቸውን በማስመስከር “መለስ ባይኖርም እኛ አለን” የሚያስብል ታዛዥነታቸውን ለምዕራብ አለቆቻቸው አብስረዋል፡፡ “የባድመ ድል አብሳሪ” አቶ ስዩም በዚህ ብቻ አላበቁም፤ “በመልካም እምነት የሚፈረሙ የሰላም ስምምነቶች በርካታዎች ናቸው፤ ተሳክቶላቸው ተግባራዊ የሚሆኑት ግን ጥቂት፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው … በደቡብ ሱዳን ግን ይህ እንዲሆን አንሻም” አሉ፡፡ ምክርም አከሉበት፤ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ነጥቦች ጠቀሱ “በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉትን በሺዎች የሚቆጠሩትን መልሳችሁ አቋቁሙ፤ የፖለቲካ ውይይቱን በመቀጠል ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ዕርቅ እንዲሆን እንሠራለን” አሉ፡፡ ከሳዑዲ አረቢያ ከተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ምሳ በመብላት መልሶ የማቋቋም ችሎታቸውን ያስመሰከሩት ቴድሮስ አድሃኖምም ከልምድ የምክሩ ተካፋይና አካፋይ ነበሩ፡፡
የፊርማ ቀለሙ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ወገኖች መካሰሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ በተለይ የሳልቫ ኪር ወታደሮች ስምምነቱን እንደ ጊዜ መግዢያ በማድረግ ኃይላቸውን አጠናክረው መልሶ በማጥቃት በአብዛኛው የነዳጅ ቦታዎችን የተቆጣጠረውን የሬክ ማቻርን ኃይል እየደበደቡ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡ የማቻር ኃይሎችም አጸፋ በመስጠት ጥቃቱ በጥቃት በመመለስ ጦርነቱን ቀጥለዋል፡፡ ከናይጄሪያና አንጎላ በመቀጠል ከሰሃራ በታች ካሉት አገራት በነዳጅ ክምችት ቀዳሚ የሆነችው ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እየነደደች ነው፤ ምድሪቱም ዳግም እያለቀሰች ነው፡፡Children displaced by the fighting in Bor county, who have just arrived, are standing on the side of a boat in the port in Minkaman
ቻይናን ለመምታት የተነደፈው የምዕራባውያን ዕቅድም እየሠራ ነው፡፡ በውጤቱም የሌሎች አገራት ነዳጅ ድርጅቶች መራራውን ጽዋ እየጠጡ ነው፡፡ የቻይናው ብሔራዊ የፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ጨምሮ የሕንዱ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ኮርፖሬሽን በራቸውን ቆልፈው ሠራተኞቻቸውን ከደቡብ ሱዳን አስወጥተዋል፡፡
ከዲንካ፣ ኑዌር፣ ወዘተ ጎሣዎች አልፎ ለበርካታ አገራት የሚበቃ ነዳጅ ያላት ደቡብ ሱዳን በጭፍን ጎሠኝነት መርዝ ተነድፋ ለምዕራባውያን መጠቀሚያ ሆናለች፡፡ ነጻነት የናፈቀው ሕዝቧም ለማያቋርጥ ስደትና ሰቆቃ ተጋልጦዋል፡፡ ከጎሠኝነት ወደ ሰብዓዊነት ከማደግ ይልቅ ወደ ቤተሰብ ደረጃ መጥበብ፤ በነጻ አውጪነት ተነስቶ በሆደ ሰፊነት አገር ከመምራት ይልቅ የምዕራባውያን አሽከርና መጠቀሚያ መሆን ውጤቱ ምን እንደሚሆን ደቡብ ሱዳን ጥሩ ትምህርት ትሰጣለች፡፡
እንዲህ ያለውን ውጤት ለማየት እንደ ደቡብ ሱዳን ሁለት ዓመታት ብቻ ሊወስድ ይችላል፡፡ “ይህንን አልፈናል” በማለት ጭንቅላታቸው ላበጠባቸው ደግሞ ሁለት ዓስርተ ዓመታት ይወስድ ይሆናል፡፡ የቱንም ያህል ዘመን ይውሰድ ለአንድ ጎሣ ወይም ዘር የበላይነት መቆም በሌሎች ተበዳዮች ዘንድ ቂም ከማስቋጠር አልፎ የምዕራባውያን አሽከርና መጠቀሚያ የሚደርግ ሲሆን “መብቱ አስከብራለሁ” ያሉትን ዘር መልሶ ለሰቆቃ መዳረግም ነው፡፡
dinka nuerደቡብ ሱዳን ያላትን ሃብት በቅጡ ሳትጠቀም እዚህ ደርሳለች፡፡ ሳልቫ ኪርና ሬክ ማቻር በአምባገነኖችና በምዕራባውያን አስመሳይ ሸምጋዮች አደራዳሪነት ሳይሆን በማንዴላ ዓይነት ሆደሰፊነት የወደፊቱን ትውልድ በማሰብ በእውነተኛ ዕርቅ ላይ የተመሠረተ ሰላም ማምጣት ካልቻሉ የዘረኝነታቸውን ውጤት በገሃድ ያገኙታል፡፡ “መብቱን አስከብራለሁ” ብለው የተነሱለትን ጎሣ/ዘር የሚያዋረድና አንገት አስደፍቶ ለትውልድ የሚዘልቅ ታሪክ ይተዋሉ፡፡ አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳንም ኅልውናዋ ከስሞ ዲንካ እና ኑዌር የተባሉ “አገራት” በመሆን የአፍሪካ “ኅብረትን” ይቀላቀላሉ፡፡ የጎሣ ፖለቲካው አዙሪትም ወደ አውራጃና ቤተሰብ ደረጃ እየጠበበ መድረሻ ወደሌለው አዘቅት ይወርዳል፡፡

ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!

image1

“ህወሃት” የሚባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ትግራይን መቼና ከማን ነጻ እንደሚያወጣ በውል የተቆረጠ ቀን ባይኖርም ህገ መንግስታዊ ዋስትና ግን አለው በሚል እየተተቸ 23 ዓመታትን አስቆጥሯል። አገር እየመራም ነጻ አውጪ፣ በረሃም እያለ ነጻ አውጪ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲወከልም ነጻ አውጪ!!
ይህንን የተለመደና ግራ የሚያጋባ እውነት ያነሳነው ወደን አይደለም። ይህ የህወሃት ግልጽ መለያና ከመለያው የሚነሳው ትንታኔ ለማንም የተወሳሰበ ይሆናል ብለንም አንገምትም። ኢህአዴግ የሚባለው የ”ሎሌዎች” ስብስብ ያበጀውና የሚመራው ህወሃት ከሌሎቹ በተለየ በነጻ አውጪ ስም 23 ዓመት አገር ሲገዛ ሌሎቹ “የነጻ አውጪ” ስም አለመያዛቸው ግን ሁሌም ሊመረመር የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ “ነጻ” መውጣት ያለባቸው ህወሃቶች ሳይሆኑ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች፣ የትግራይን ንጹሃንን ጨምሮ ነው። ህወሃት ሲጠነሰስ ጀምሮ የነበሩትን ቀደምት አመራሮች በሂደት እየበላ አራት ኪሎ የደረሰው፤ ህወሃት መጥበብ የጀመረው ገና ከጥንስሱ ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ህዋሃት የሚወጡ የምስክሮች ሪፖርቶችና መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ህወሃት በደም የታጠበ፣ በደም የተለወሰ፣ የበርካታ ንጹሃን ደም ያጨማለቀው፣ ታሪኩ ሁሉ በደም ዙሪያ የተሰራ፣ አሁንም ከዚሁ የደም ቁማር ነጻ መሆን ያልቻለ መሆኑን ነው።
ህወሃት ግዛቱን እያሰፋ ሲሄድና አጋጣሚው ሲያመቸው ከተቋቋመለት መሰረታዊ ሃሳቡ ዘሎ “መንግስት” መሆን ሲያምረው “ኢህአዴግ” የሆነው ዓላማውን በወጉ ከ”መጥበብ ወደ መስፋት” በመቀየር ሳይሆን “በሰፍቶ መጥበብ ውስጥ” እየተጫወተ አገርና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግን አሁን ድረስ “አገዛዝ” ከማለት በዘለለ በመንግሥትነት ሊጠሩት የማይፈልጉ የበረከቱት።
በግብር እንደታየው በህወሃት “የሰፍቶ መጥበብ” ጨዋታ ውስጥ ቅድሚያ ትግራይ መወለድ፣ ሲቀጥል የትውልድ ቦታንና ስምን በመቀየር ማጭበርበር፣ ከዛም ታማኝ መሆን፣ ከሁሉም በላይ አነስተኛ ክልል በሚል ስልታዊ አካሄድ ብርና ኮብራ እየሸለሙ ማታለል፣ የአገዛዙ መለያ ሆነ። አሁን ድረስም ይዘቱ ባይቀየርም አፈጻጸሙ ግን ከክልል ወደ አውራጃ፣ ከአውራጃም ወደ ወረዳና ቀበሌ፣ ከወረዳና ቀበሌ ወርዶ ስጋና ደም የሚቆጠርበት የስልጣን ቅርምት ደረጃ “እድገት” አሳይቶ ይገኛል።
በዚህ መልክ በተዋቀረው የህወሃት አገዛዝ ቁጥጥርና ክትትል አስቸጋሪ በመሆኑ አገሪቱ በሙስና በሰበሰች። ሙስናው ፈር ለቅቆ በድሃው ህዝብ ላይ ነገሰ። አወቃቀሩ ስርዓቱን በመታደግ ላይ የተመሰረተና የህወሃትን ባለጊዜዎች ስልጣን ማስጠበቅ በመሆኑ ሁሉም ነገር ሸተተ፤ ገለማ። ያቋራጭ ሃብታሞች ናኙ። ግንባታው ጨሰ። “ህዳሴው” ለተወሰኑ ወገኖች ፈንጠዝያ የተሰጠ ስያሜ ሆነ። ግድያ፣ እስር፣ እንግልትና አፈና እደግ ተመንደግ ተባለ። ነገሩ እንዲስተካከል ትግል የሞከሩ ተባረሩ፣ ታሰሩ፣ የተገደሉም አሉ። የተሰደዱ ጥቂት አይደሉም። አገር ውስጥ የቁም እስረኛ ሆነው ጊዜ የሚጠብቁ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
ሲጀመር በብሔር ብሔረሰቦች ስም ሲምሉና ሲገዘቱ የነበሩት የህወሃት መሪዎች፣ የራሳቸውን ሰዎች ሳይቀር ወረዳ እየለዩ የፈጸመባቸው ተግባር፣ በሌሎች የአገሪቱ ህዝቦች ላይ ከስርዓቱ መርህ በመነሳትና “በጥጋብ” የተፈጸመው በደል፤ “የገዢው መደብ ነኝ” በሚል ንጹሃንን ከስራና ከሃብታቸው ከማፈናቀል ጀምሮ የተሰራባቸው ግፍ ከጎሳ ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ጋር ተዳምሮ የተካረረ ደረጃ ደርሷል።
የከፋቸው በዝተው ቂማቸው እየተናነቃቸው ይገኛሉ። የህወሃት አመራሮች ከፊታቸው ክፉ ዘመን ስለመኖሩ ብዙም የተጨነቁ አይመስሉም። የቂም በትር ቀጠሮ የለውም። ቂም ቦታ አይመርጥም። የጎሳ ፖለቲካ በባህሪው ምሱ ደም ነው። የጎሳ ጣጣ ባለባቸው አገሮች የታየው ይኸው እውነት ነው። በተለይ ህወሃቶች አሁን ባጨመላለቁት ደረጃ እንለካው ከተባለ አደጋ አለ፤ ያውም ግልጽ የሆነ አደጋ። ችግሩ ሲነሳ፣ ቂም በትር ሲሰነዝር፣ ጥላቻ ልጓሙ ሲበጠስ፣ በብርና በመሳሪያ ብዛት መታደግ የሚቻል አይሆንም። ይህንን ስንል ላገራችን ችግርና የደም አታሞ ለመምታት አይደለም። የቆምንለት ዓላማና የሙያ ቃልኪዳናችን ከጎሠኝነት ይልቅ ሰብዓዊነትን ማስቀደም መሆኑን የሚጠሉንም ጭምር ያውቁታል፡፡ በዚህ የሰፋ ራዕይ ውስጥ ስላለን የመጥበብ አደጋ ምን እንደሆነ በግልጽ ይታየናል፡፡ ስለዚህ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንሰጣለን፡፡
ዛሬ ዳር ቆመን የምንመለከተው የጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን የጎሳና የዘር ጭፍጭፍ “እኛም ቤት እሳት አለ” ስለሚያሰኝ ነው። የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የበይ ተመልካች የሆኑ፣ የተገደሉ፣ አሁን ድረስ በስቃይ ላይ ያሉ … ቤቱ ይቁጠራቸውና ዘመድ፣ ወገን፣ ተቆርቋሪ፣ አለኝታ፣ ታዳጊ አላቸው። ብሶት ህወሃትን ብቻ አይወልድምና ሁሉም ረጋ ብሎ ያስብ። ህወሃት ብቻ የብሶት የበኩር ልጅ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። ሲያሻ ህግ እየተጠቀሰ፣ ሲያሻ በተቀነባበረ ድራማ፣ ሲፈለግ በተፈለገው መንገድ የሚፈነጭበት ጊዜ ሳያረጅ ለሰላም ሁሉም እጁን ያንሳ!! የጎሳ ፖለቲካ ምሱ ደም ነውና ሃዘን ሳይመታን በእውነተኛ እርቅ ጊዜው ሳያልፍብን የጎሳ ፖለቲካን ምስ እናምክን!! ተቃዋሚዎችም ጭምር!!

“ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ

eye treatment
የዚህ ሁሉ መነሾው ደግሞ ትራኮማ ነው፡፡ ቢበዛ በ10 ደቂቃ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊፈወስ የሚችለው ትራኮማ አንዳንዶች የድህነት በሽታ ይሉታል፡፡ በዓለማችን 2.2 ሚሊየን ህዝብ በትራኮማ ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣ ሲሆን በኢትዮጵያ ትራኮማ እጅጉን የተስፋፋው በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
10 ደቂቃ የማይሞላውን ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ካላገኙ 200 000 ያህል የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ eyetreatmentየሚለው ዘገባ…ዓለምን በ2020 ከትራኮማ ነጻ ለማድረግ ያቀደው የብሪታኒያ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጥምረት በኦሮሚያ ክልል እያካሄዱ ያሉትን የቀዶ ጥገና ህክምናና የባለሞያዎች ስልጠና ቢቢሲ በድረ ገጹ ዘግቦታል፡፡
ከቀዶ ጥገናው በኋላ እድን ይሆን በሚል ትዕግስት ማጣት እንቅልፍ አጥታ ያደረችው የ40 ዓመቷ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዋ ምስራቅ፣ እሽጉ ተነስቶላት ማየት ስትችል…“እንደገና የተወለድኩ ያህል ነው የተሰማኝ…” ትላለች፡፡
በዘገባው ላይ ባይገለጽም ለኦሮሚያ ጥቅም ቆመናል የሚሉ በፓርቲም፣ በነጻ አውጪም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ከሚያባክኑት ጊዜና ገንዘብ በጣም ጥቂቱን በዚህ ላይ ለማዋል ቢሞክሩና የሕዝባቸውን ስቃይ ለመታደግ ቢሠሩ በማለት በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ: BBC Report

ጀግናን ማወደስ!


ጀግናን ማወደስ!
(የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለ ተመስገን ደሳለኝ)
                                 
    


በአገራችን ውስጥ ታላቅ ተብለው (አተረጓጎሙ እንደ ሀገሩ እና ህብረተሰቡ ባህልና ልማድ የተለያየ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) ለማህበራዊ አክብሮት የበቁ ደራሲያን፣ ጋዜጠኞች፣ ወንጌላውያን፣ ፈላስፎች ወዘተ መኖራቸው አከራካሪ አይመስለኝም፤ በሌሎችም አገራት እንዲሁ፡፡ በጠቅላላው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ በአካዳሚያዊ እውቀትም ሆነ በልዩ ሙያዊ ክህሎት ተመርጠው የሚበቁ ሁሉም አይነት ታላላቆች መፈጠራቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁንና በየአገሩ እንዲህ አይነቱን ፀጋ የሚታደሉ ሰዎች ብዙ ሊሆኑ አለመቻላቸውም እውነት ነው፤ ተፈጥሮአዊ ህግ ነውና፡፡

   ይህንን ጉዳይ ያነሳሁበት ምክንያት ስለ አንድ ወጣት ጋዜጠኛ አንዳንድ ሀሳቦችን ጠቅሼ ስለእርሱ የማውቀውን ያህል ምስክርነት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ወጣት ጋዜጠኛ፣ ልቡ በሀገሩ (በኢትዮጵያ) ፍቅር የነደደ ነው፡፡ ከሕዝባዊ ተጋድሎ ለሚያሰናክለው ለፍርሃት ቦታ ሰጥቶ አያውቅም (በአንድ ቃል ቅንጣት ታህል ፍርሃት ውስጡ የለም) እንዲያውም ከሌሎች ወጣቶች የሚለይበት ትልቁ ፀጋው ፍርሃት የለሽነት ተፈጥሮው ነው፤ ብሩህና ታላቅ አእምሮ የታደለ ነው፡፡ በዚያ ላይ ሰው አክባሪ ሲሆን፣ ንግግሩም ምጥን ነው፤ ስሜታዊነት አያጠቃውም፤ ወገንተኛነት አያናውጠውም፡፡ ትግሉ ሁልጊዜ ከሀሳብ ጋር ነው እንጂ ከግለሰቦች ወይም ከቡድኖች ጋር አይደለም፡፡
የተለይ ሃሳብ የማስተናገድ አቅም ከሌለው የኢህአዴግ መንግስት ሊደርሱበት የሚችሉት የህይወት መስዋዕትነት፣ የአካል ጉዳት፣ እስራትአሳስቦት፣ ሃሳቦቹን ከማንፀባረቅ ወደኋላ ብሎ አያውቅም፡፡ ይህ ወጣት ኢህአዴግ ማስራብ፣ ማሰቃየት፣ መግደልእንደሚችል እያወቀ ከአላማው ፍንክች አይልም፡፡ አንድም ቀን እንዲህ አይነት አደጋዎችን ሲሸሽም አይተነው አናውቅም፡፡ ይህ የሆነው ግን ሞኝ ስለሆነ አይደለም፤ ላነገበው ሀገራዊ ዓላማና ለሚያነሳቸው እውነታዎች ታማኝ ስለሆነ ብቻ ይመስለኛል፡፡ በተቀረ የሚያደርገውን የሚያውቅ ብልህ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡
ሁልጊዜ ስለሚያጠና እና ስለሚተነትን አስቀድሞ ኢህአዴግ ምን ለመስራት እንዳሰበ መቶ በመቶ ባይሆንም አብዛኛውን ያውቀዋል ማለት ይቻላል፡፡ ያወቀውንም በድፍረት ለሕዝብ ያሳውቃል፡፡ ሲናገርም ህዝቡን በሚያሸብር አፃፃፍ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አሁን ኢህአዴግ በዴሞክራሲ ላይ ያለውን ንቀት እና አምባገነናዊ አመለካከት ቀደም ብሎ በአደባባይ ተችቷል፡፡ ኢህአዴጎች ፊታቸውን ወደ ደቡብ እስያ አዙረው ‹‹ልማታዊ ፓርቲ›› የሚባለውን የፖለቲካ ፍልስፍና ከታይዋን፣ ከቻይና እና ከሲንጋፖር ገልብጠው አዲስ ራሳቸው የቀመሩት ፍልስፍና አስመስለው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በግድ ለመጫን ታጥቆ ተነስቷል ብሎ አስቀድሞ በተደጋጋሚ ለህዝቡ አሳውቆ ነበር፡፡ አሁን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡

ይህ ወጣት ኦክስፎርድ፣ ሃርቨርድ፣ ሶርቦንን ወይም በሌሎቹ የዓለማችን ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች ገብቶ ፖለቲካል ሳይንስ፣ ታሪክ፣ ሶስዮሎጂ፣ ሳይኮሎጂንየመሳሰሉ ከማህበረሰብ ጋር በቀጥታ የሚገናኙ የትምህርት ዘርፎችን አልተማረም፡፡ ነገር ግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝቷል፡፡ በሰፊው እንዳነበበ እና ከባለሙያዎች ጋር እንደተከራከረ ንግግሮቹ እና ፅሁፎቹ በግልፅ ያስታውቃሉ፡፡ አሁን በህዝባችን ዘንድ በሰፊው የሚታወቅ ስመ-ገናና እየሆነ ነው፡፡
ይህ ሰው ማን ነው? …የፋክት መጽሔት አማካሪ እና አምደኛ የሆነው እጅግ በጣም ተስፋ የሚጣልበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው፡፡

የዚህን ልጅ ብሔር እስከ ዛሬ ድረስ አላውቅም፡፡ እኔም ጠይቄው፣ እርሱም ነግሮኝ አያውቅም፡፡ በእርግጥ ብዙ ሰዎች ስለኦሮሞ ጉዳይ ብቻ የምቆረቆር ይመስላቸዋል፡፡ ደጋግሜ እንደ ተናገርኩት ስለኦሮሞ ጉዳይ የምናገረውና የምፅፈው፣ በደንብ የማውቀው ይህንኑ ስለሆነ፣ እንዲሁም ለባህልና ወጉ ቅርብ ስለሆንኩ ብቻ ነው፡፡ በተቀረ የእኔ መቆርቆርና ትግል ከአምላክ ዕርዳታ ጋር ከተሳካ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼን ከዚህ ግፍና የመከራ ስርዓት ነፃ እንዲወጡ የሚያልም ነው፡፡


መቼም እንደኢትዮጰያ ባለ የአምባ-ገነን ስርዓት በነገሰባት አገር ህይወቴ የሚሉትን ነገር በሙሉ በመዘንጋት ትግሉን ህይወታቸው ያደረጉ ጥቂት ሰዎችን ለማየት ታድለናል፡፡ ዕጣ-
ፈንታቸው ሞትና እስራት እንደሆነ ቀድመው ተረድተው ዕጣው እስኪደርስባቸው ድረስ ያላቸውን ሁሉ ለሚወዷት አገራቸው ሰጥተዋል፤ እየሰጡም ነው፡፡ እንግዲህ ተመስገንም ከነዚህ ጥቂቶች መካከል የሚመደብ መሆኑን ስናገር በሙሉ ልቤ ነው፡፡ እርሱንም ለማወደስ ስነሳ ፍርሃትን ሰብረው ከኋላ የሚከተሉትን የእርሱን ፍሬዎች መብዛት እያስተዋልኩ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ህዝቡን በጠመንጃ ኃይል አስገዝቼዋለሁ ብሎ ሲፎክር እውቀትን ብቻ በተንተራሱ ትችቶቹ ብቅ ያለው ተመስገን

ነበር፡፡ ይኸው ዛሬ በእርሱ ብዕር የተነቃቁ ጎበዞችን አፍርቷል፡፡ ከዚህ በላይ ድልም ያለ አይመስለኝም፡፡ ልጁ ሊወደስ ይገባዋል የምለውም ይህን ምክንያት እንደ አንድ መነሻ በማድረግ ነው፡፡

ተመስገን ሙያውን ከልቡ መውደዱን የምናየው ከኢትዮጵያ ውጪ አገር እንደሌለውና ለመሰደድ እንደማይዘጋጅ ደጋግሞ ሲናገር ነው፡፡ ሙያው የሚጠይቀው ይህን ነበርና አደረገው፡፡ በስርዓቱ አስከፊ ጫና ምክንያት የተሰደዱ ጓደኞች እንዳሉት አውቃለሁ፡፡ በማገኘውና በማዋራው ጊዜም ለእነርሱ እውቅና በመስጠት ሲያወድሳቸው አደምጠዋለሁ፡፡ የጀግና ባህሪያት መገለጫ ከሆኑት መካከል ይህ አንዱ ነውና እኔም እርሱን ጀግና ለማለት ወድጃለሁ፡፡

በመጨረሻም ለፋክት መፅሄት አንባቢያንም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የማስተላልፈው አንድ መልዕክት አለ፤ ይኸውም እንደ ተመስገን ደሳለኝ ያሉ ጀግኖቻችንን ማወደሱ ወደ ምንፈልገውንና ምናስበው ለወጥ ሊያደርሱን የሚችሉ እልፍ አእላፍ ጀግኖችን ማፍራት የሚያስችለን መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ነው፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵን ይባርክ!