Wednesday, 1 January 2014

የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር

ቀን 31.12.2013
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ እሁድ ታኅሣሥ 20 ቀን፥ 2006 ዓም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራውን በከፍተኛ ድምፅ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።
«አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ» እሁድ ዕለት የመረጣቸውን አዲሱ ሊቀመንበሩን በተመለከተ ከፓርቲው አመራሮች አንዱ የሆኑት አቶ ስዩም መንገሻን ደውዬ አነጋግሬ ነበር።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ ከትናንት በስትያ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራውን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።
 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቸኛው የምክር ቤት አባል የሆኑት የተከበሩ ግርማ ሠይፉ እና በኋላ ላይ ራሳቸውን ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ውድድሩ ያገለሉት አቶ ተክሌ በቀለ ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸውም ተነግሯል።
አቶ ስዩም መንገሻ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ፓርቲው ታኅሣሥ 19 እና 20 በጠራው የልዩ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው።
አንድነት ፓርቲ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።
 የምርጫ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር? ስል የመጀመሪያ ጥያቄን አቀረብኩላቸው። አንድነት ፓርቲ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለመዋሀድ ተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ እንደሆነና ይህን የውህደት ጥሪ የፓርቲው አዲሱ ሊቀመንበርም አበክረው ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል።

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች ለድርድር መዘጋጀት

ቀን 01.01.2014

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ልዑካን ወደ 3 ሳምንታት ከተጠጋ የአርስ በርስ ውጊያ በኋላ ለሰላም ድርድር ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።
የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት IGAD አባል ሃገራት ናይሮቢ ላይ ቀደም ሲል ተወያይተዉ ሁለቱ ወገኖች ተኩስ በማቆም ለሰላም ድርድር እንዲዘጋጁ ባሳሰቡት መሠረት ተቀናቃኞቹ ወገኖች ለዉይይት መስማማታቸዉን አስታዉቀዋል።

በሰላሙ ውይይት፣ ቅድሚያ የሚሰጠው የተኩስ አቁሙን ስምምነት መቆጣጠር የሚቻልበት መላ ሳይሆን አይቀርም ።

 ዛሬ አዲስ አበባ ስለገቡት ደቡብ ሱዳናውያን ተደራዳሪዎችና ቀጣዩ እርምጃቸው ወደ ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፣ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በስልክ አነጋግሬአቸው ነበር።