Wednesday, 16 July 2014

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

July 16th, 2014                   
ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-
መኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤ የባንክ አካውንት ቁጥር፡- AEUP – SP 235
አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የባንክ አካውንት፡- UDJ – A/C 47
በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስንተባባር እናሸንፈላን!!
ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባudJAEUP

በደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ አወጣ

July 16th, 2014
ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የአቋም መግለጫን ስለማሳወቅ፡
ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ 06/11/06 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት በመሰብሰብ የፓርቲውን የስራ እንቅስቃሴና በቅርቡ በታሰሩ የፓርቲው የበላይ አመራሮች በአቶ ሀብታሙ አያሌው እና በአቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በሰበብ አስባቡ በሚታሰሩ ሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ህገ ወጥ ድርጊት አባላቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. የዜጎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና ከፈለጉት ፓርቲ ጋር የመወገን መብታቸውን መንግስት እንዲያከብርና እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡
2. በህገ መንግስቱ የተፈቀዱት የዜጎች መብቶች ሳይሸራረፉ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ እንዲያከብርና እንዲያስከብርእንጠይቃለን፡፡
3. ዜጎች ለመብታቸው መከበር ፍላጎታቸው እየሰፋና እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን በማወቅ ገዢው ፓርቲ ከድርጊቱ እንዲታቀብና የዜጎች መብት እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡
4. ለዲሞክራሲ እውን መሆንና መዳበር ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን ገዢው ፓርቲ ጠንቅቆ በማወቅ ለሰላማዊ ትግሉ መዳበር መንግስት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን በማለት ያቋ ም መግለጫ ያወጣን ሲሆን
በመጨረሻም የፓርቲያችን የላእላይ ምክር ቤት ያለአግባብ የታሰሩ ወንድሞቻችን ሁኔታ ያሳዘነው ቢሆንም ነገር ግን የነሱ መታሰር የትግሉን ምእራፍ ከማስፋትና የበለጠ ከማቀጣጠል ባሻገር አንድም እርምጃ ወደ ኋላ የማይመልሰውና ሁሉንም አባል የበለጠ ለትግሉ ያነሳሳ መሆኑን አምኖ ከእስካሁኑ በበለጠ የትግል ስልቱን በማስፋት በዜጎች መብት ላይ እየዘመተ ያለውን የገዢው ፓርቲ በአደባባይ እና በአዳራሽ በህዝብ የምናወግዝበትን የሰላማዊ ትግል ስልት ፓርቲው እንዲያመቻችልን በማለት የዞኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የአቋም መግለጫ ያወጣ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!10462481_668385689913035_7014532587449142359_n

ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና የመጀመሪያ እርከን ተግባሪዊ የትግል ጥሪ

July 6th, 2014
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
በየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።
አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።
ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶች ጋር ንቅናቄዓችን ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ የቻለ መሪ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ለወያኔ የጉሮሮ ቁስል የሆነበት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ጋር ግንቦት 7 የፈጠረው ጠንካራ ትብብር ነው። በትህዴን ጋር በመሆን አቶ አንዳርጋቸው ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ጀርባ መንጠልጠል እንዳይችል አድርጎታል። እናም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ከዘረኝነት ፀድቶ መገኘት ማለትም ጭምር ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት በኢትዮጵያዊያን እኩልነት እና እኩል ባለመብትነት ከልብ ማመን እና ለእኩልነት በጽናት መታገል ማለት ነው።
አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን የግድ የግንቦት 7 አባል መሆንን አይጠየቅም። አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን ለመልካም ዓላማዎች መሳካት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀትን እንጂ የግድ ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር መወገንን አይሻም። ያም ሆኖ ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የሆነ ሰው በጠንካራ ድርጅት የታገዘ ትግል አስፈላጊነት ይረዳል።
በመጨረሻም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ኦኪሎ ኦኴኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እዚህ ዘርዝረን ልንጨርሳቸው የማንችላቸው ጀግኖቻችንን ሁሉ መሆን ማለት ነው።
የ“ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ዘመቻ ትኩረቶችን በየጊዜው የምንገልጽ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል ያለበት የዓለም ዓቀፍ ዘመቻው የመጀመሪያ እርከን ትኩረቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
የዘመቻው የመጀመሪያው እርከን ትኩረቶች
ይህ የመጀመሪያ እርከን ሶስት ቦታዎች ላይ ያተኩራል፡- የመን፣ ብርታኒያ እና ወያኔ
የመንን በተመለከተ
የየመን መንግሥት የዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ የየመን የራሷን ህግ በመተላለፍ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለየመን መንግሥት የተደረገው ተማጽኖ ሰሚ ጆሮ አላገኘም። እስካሁንም ድረስ የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውን ማሠሩንና ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን በይፋ አላመነም። እኛ ባለን መረጃ መሠረት በአይሮፕላን ማረፊያው ከማገት ጀምሮ በልዩ በረራ ወደ ኢትዮጵያ እስከ መላክ ድረስ ያለውን የውንብድና ሥራ በየመን በኩል ሆኖ የሠራው ቀጥታ ተጠሪነቱ ለየመን ፕሬዚዳንት የሆነው የስለላ ድርጅት ነው። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ሊቀለበስ የማይችል እና በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የየመን መንግሥትና ሕዝብ ይህን እንዲያውቁት ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው የተግባር እንቅስቃሴ አካል ነው።
የመንን በተመለከተ የሚቀጥለው ሳምንት ዘመቻችን ግብ ቁጣችንን የየመን ፕሬዚዳንት እና የየመን መንግሥት ብቻ ሳይሆን የየመን ሕዝብም እንዲያውቅ ማድረግ ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ያህል ተጠቅሰዋል።
1.ለየመን ፕሬዚዳንት አዲስ መረር ያለ ደብዳቤ ተጽፎ በፋክስና በኢሜል በየመን መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶችና ኤምባሲዎች አድራሻዎች መላክ። በመልዕክት መጨናነቅ ከሚገባቸው የየመን ተቋማት አንዱ አዲስ አበባ የሚገኘው የየመን ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ በዘመቻው የምትሳተፉ ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ እናሳስባለን፤ የኢንተርኔትና የፋክስ መልክቶችን ስትልኩ ራስን ለጉዳት በማያጋልጥ መንገድ መደረግ ይኖርበታል።
2.የየመን ኤምባሲዎችን ሥራ ማወክ በሚችሉ ሰልፎችና ተቃውሞዎች ማጨናነቅ። የፕሬዚዳንቱን ፎቶና የአገሪቱን ባንዲራ ማቃጠል። ይህ በውጭ አገራት ብቻ መደረግ ያለበት ነው።
3.በውጭ አገራት በየከተሞች ለሚገኙ የየመን ኮሚኒቲዎች ደብዳቤ መፃፍና መንግሥታቸውን እንዲቃወሙ መገፋፋት፤ ይህንን ካላደረጉ ግን ከመንግሥታቸው ጎን ተሰልፈው በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዳወጁ የምንቆጥረው መሆኑን በማያሻማ መንገድ መንገር፤
4.በየመን አየር መንገድና በማናቸው የየመን የንግድ ድርጅቶችና ቢዝነሶች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በቢዝነሶቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ ተግባር በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጭም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መተግበር የሚኖርበት አቢይ ተግባር ነው።
5.በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የየመን ቢዝነሶችን መርጦ ምርቶቻቸው እና አገልግሎቶቻቸው እንዲጠሉ ማድረግ። ከእንግዲህ በየመን ገንዘብ የተሠራ ወይም ከየመን የመጣ ብስኩትም ይሁን ሲጃራ የወገናች ደም የነካው እቃ ነው።

ብርታኒያን በተመለከተ

የእንግሊዝ መንግሥት ማድረግ የነበረበትን እና ማድረግ ይችል የነበረውን ሁሉ አድርጓል ብለን አናምንም። እርምጃው ፈጣን አልነበረም፤ አሁንም አይደለም።
ስለሆነም እንግሊዝን በተመለከተ የዘመቻችን ግብ የእንግሊዝ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመንፈጉ መክሰስ እና ከአሁን በኋላም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና መሪያችን እንዲያስፈታ መወትወት ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ተዘርዝረዋል።
1.የእንግሊዝ መንግሥትን በህግ መክሰስ (ይህ በንቅናቄው ጽ/ቤት የሚሠራ ሲሆን ዝርዝሩ ወደፊት ይገለፃል)፤
2.ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ደብዳቤ ጽፎ በፋክስና በኢሜል ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለኤምባሲዎች በብዛት መላክ። አንዱ ትኩረት የሚደረግበት ኤምባሲ አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመቻው የሚሳተፉ ወገኖች አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
3.በለንደን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደጃፍ፤ በሌሎች አገሮች ደግሞ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቁጣ የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄድ።
ወያኔን በተመለከተ
ወያኔን በተመለከተ የሚደረጉ ትግሎች በሙሉ ወያኔን ከስልጣን በማስወገድ ላይ ያነጣጠሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ወያኔን ለመጣል ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ፡ ከቁም ውርደትና ባርነት ለነጻነትና ለፍትህ ከወያኔ ጋር ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁ እየጣሉ ለመውደቅ ፤ መስዋእት ለመሆን በወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንና የህዝብ ሃይሎች የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቅሴ ነው ፤ እንቀላቀላቸው።
በተለያዩ ምክንያቶች ወሳኙን ትግል መቀላቀል የማይችሉ ወገኖቻችን በያሉበት ሆነው ከወያኔ የስለላ መረብ ተጠነቅቀው ራሳቸውን በቡድን ያደራጁ፤ ይህንኑ የሚያግዙ ተግባራት ለመፈጸም ራሳቸውን ያዘጋጁ። እነዚህ ተግባራት ወያኔን በገቡበት እየገቡ በማሳፈር ፤እረፍት በመንሳት፤ የፈፀሟቸውን ወንጀሎች በአደባባይ በመናገር እንዲሸማቀቁ በማድረግ፤ ማንነታቸው ለሸሪኮቻቸው ወይም ለሥራ ባልደረቦቻቸው በመንገር ወዳጅ በማሳጣት፣ ንግዶቻቸውን ኩባንያዎቻቸው እንዲከስሩ በማድረግ የፋናንስ አቅማቸው በማዳከም ረገድ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ከዚህ አኳያ ሊደረጉ ከሚገቡ ተግባራት የሚከተሉት በምሳሌነት ተዘርዝረዋል።
1.በምዕራቡ ዓለም በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያሉት እና የሚመላለሱ ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ መደራጀትና እንደየሀገሩ ሁኔታ አግባብ ያላቸውን የህግ መሳሪያዎች መጠቀም፤
2.በመላው ዓለም የወያኔ ኤምባሲዎችና የኮንሱላር ጽ/ቤቶች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤
3.በመላው ዓለም የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (ከሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣ ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ፡ የሥራ ፤ የማኅበራዊ ትብብርና ግንኙነት አለማድረግ፤ ፊት መንሳት ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን ማካሄድ። የወያኔ አባላትንና ደጋፊዎችን በሁሉም ዓይነት ግንኙት ማግለል፡ አለመተባበር በኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።
4.በማናቸውም የዓለም ክፍል ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ሲቪል፣ የወታደራዊና የደህነት ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣ ማስነወር፣ መውጫ መግቢያ ማሳጣት፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀባይነት እንደሌላቸው በሕዝብ ላይ ለፈጸሙት ወንጀሎች ሁሉ የሕዝብ ቁጣ ዒላማ እንዲሆኑ እንደልባቸው መፏላል እንዳይችሉ ማድረግ። በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ራሱ በቡድን አደራጅቶ ለወያኔ ታጣቂዎች ጥቃት ሳያጋልጡ አድብቶና አስልቶ ተመሳሳይ ድርጊቶች መፈፀም
5.የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ አገዛዝ የሚመሩ እንዲሁም በወያኔ ኤፈርት ስር ያሉ ኩባንያዎች፤ቢዝነሶች ላይ እቅባ ማድረግ፤ የሸቀጥና የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ አለመሆን፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ሥራቸውን ማጨናገፍ ማደናቀፍ፤ አሻጥሮችን በተደራጀ መልክ፣ በጥናትና በብልሃት ተግባራዊ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተግባሪዊ መደረግ ይኖርበታል።
6.በዌስተር ዩኒየን፣ በመኒ ግራም እንዲሁም በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በወያኔ ደጋፊዎች በመሠርቷቸው ልዩ ልዩ የገንዘብ ላኪ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ የገንዘብ መላኪያ መንገዶችን መፈለግ፤ እነዚህ በሌሉባቸው አካባቢዎች የፈጠራ ችሎታን በመጠቀም ገንዘብ ለዘመድ አዝማድ በወያኔ በኩል ሳይላክ የሚደርስበትን ሁኔታ መፍጠር፤ የወያኔን የፋሽታዊ አገዛዝ አንዱና ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ የማድረቂያ ዘዴዎችን ሁሉ በመፈለግ ተግባሪዊ በማድርግ የወያኔን በዘረኝነትና በዘረፋ የተገነባ የገንዘብና የኢኮኖሚ አቅም ማዳከም፤ መቦርቦር፤ መናድ።
7.ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያ ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ። (የእነዚህን ዝርዝሮች በተከታታይ ይገልጻሉ)
8.የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በተለይ ደግሞ ሳያስተምሩ ለወያኔ ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር (ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣ እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)
9.ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጆሮችና ከወያኔ ጋር የተያያዙ የንግድ ቤቶችና ኩባንያዎች የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ። (ዝርዝራቸውን በተከታታይ እናወጣለን)
በመጨረሻም የወጣቱ የማያልቅ የፈጠራ ችሎታ ከላይ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተቱ ሆኖም ግን ውጤታማ የሆኑ የተቃውሞ መግለጫ ዘዴዎች ያፈልቃል ብለን እናምናለን። ስለሆነም ዘመቻውን በየአካባቢው በሚገኝ ሀሳብና ፈጠራ ማዳበር ይቻላል። ይህ ዘመቻ ወያኔ ከስልጣን እስኪባረር ድረስ በየጊዜ እየከረረ መሄድ እንዳለበት ታሳቢ አድርጎ መነሳት ይኖርበታል። ስለሆነም በየጊዜው አዳዲስ ነጥቦችን ተግባሪዊ የትግል ስልቶችን እንጨምራለን።
ለመላው የአትዮጵያ ሕዝብ፣ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሁሉ፣ ለሁሉም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሁሉ በኅብረት በጋራ ሆነን፤ ትከሻ ገጥመን ለተግባሪዊ ትግል በቁርጠኝነት እንድንነሳ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።
ይህ ዘመቻ ወያኔን ከስልጣን ለማባረር ምድር ላይ ከምናደርገው የመረረ ትግል ጋር ሲቀናጅ የሚፈለገውን ውጤት ስለሚያስገኝ ለነፃነቱ ግድ ያለው ዜጋ ሁሉ በሙሉ ኃይሉና አቅሙ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ ጥሪ ያቀርባል።

Tuesday, 10 June 2014

The moving message of Swedish journalist Martin Schibbye about Eskinder Nega



By WAN-IFRA
June 10, 201


Swedish journalist Martin Schibbye accepts the award on behalf of Eskinder Nega
“This Golden Pen is more important than food, medicine and water. It materializes the support and shows that he is not forgotten. That he is one of us. That an attack on one journalist is an attack on us all and that jailing a journalist is a crime against humanity,” Swedish journalist Martin Schibbye said, accepting the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA), on behalf of imprisoned Ethiopian publisher, journalist and blogger Eskinder Nega.
The honour was formally bestowed on Nega in a ceremony at the 66th World Newspaper Congress, under way in the Italian city of Torino this week, where more than 1,000 media industry representatives have gathered. Nega is serving an 18-year jail sentence in Addis Ababa’s notorious Kaliti prison, convicted on trumped-up terrorism charges after daring to wonder in print whether the Arab Spring could reach Ethiopia, and for criticising the very anti-terrorism legislation under which he was charged. Arrested in 2011, he was sentenced on 23 January 2012, and denounced as belonging to a terrorist organisation. Imprisoned at least seven times in the past decade for committing fearless acts of journalism, Nega is a celebrated intellectual and a relentless fighter for freedom of expression. “Eskinder Nega has become an emblem of Ethiopia’s recent struggle for democracy,” World Editors Forum President Erik Bjerager said, delivering the Golden Pen during the opening ceremony of the World Newspaper Congress and the World Editors Forum in Torino. “No stranger to prison, he is also an unforgettable warning to every working Ethiopian journalist and editor that the quest to create a just, free society comes with a heavy price,” Bjerager said. Nega’s former prisonmate, Swedish journalist Martin Schibbye, accepted the award on the jailed journalist’s behalf, at the invitation of Nega's family. He painted a dark picture of life inside Kaliti Prison. “The rooms are more like barns with concrete floors, and it is so crowded that you have to sleep on your side,” he said. “Prisoners are packed likes slaves on a slaveship. Once a month an inmate leaves with his feet first.” But disease and torture are not the hardest part of life inside Kaliti, according to Schibbye. “It (is) the fear of speaking. It's not the guard towers with machine guns that keep the prison population calm. It is the geography of fear. People who speak politics are taken away. They disappear.” Schibbye is a freelance journalist who was jailed for 14 months in Kaliti Prison, along with his photographer Johan Persson. They were pardoned and released in September 2012. “In (Kaliti), fearless people like Eskinder Nega helped the whole prison population to keep their dignity. By still writing. Protesting. Not giving up. He helped us all maintain our humanity. But there is one thing I know that even Eskinder fears. That is to be forgotten,” Schibbye says. “When you’re locked up as a prisoner of conscience, this is the greatest fear, and the support from the outside is what keeps you going. This Golden Pen Award will not set him free tomorrow, but it will ease his day today. He will go with his head high knowing that he is there for a good cause. That the pain and suffering has a meaning.” WEF President Erik Bjerager told the ceremony that the world needs to watch the creeping threat of anti-terrorism legislation being used to target journalists. “Ethiopia continues to resort to anti-terrorism legislation to silence opposition and shackle the press. Alarmingly, beyond Ethiopia, countless states around the world are misusing anti-terrorism legislation to muzzle journalists, bloggers and freedom of expression advocates," Bjerager said. "Research suggests that over half of the more than 200 journalists in jail last year were being held on 'anti-state' charges. Let me be clear: Journalism is not terrorism. Politicians should not abuse the notion of national security to protect the government, powerful interests or particular ideologies, or to prevent the exposure of wrongdoing or incompetence.” Schibbye concluded his acceptance speech, reading from a moving letter penned by Nega to his eight-year-old son. It was smuggled out of Kaliti prison: “The pain is almost physical. But in this plight of our family is embedded hope of a long suffering people. There is no greater honour. We must bear any pain, travel any distance, climb any mountain, cross any ocean to complete this journey to freedom. Anything less is impoverishment of our soul. God bless you, my son. You will always be in my prayers.” Schibbye told a tearful audience: "When I read these words by Eskinder I know that they will never break him. Because he is in peace with himself. He knows that even though he is chained, robbed of his physical freedom, the freedom to talk or to be silent, the freedom to drink or eat, and even to shit. He knows, as do all prisoners of conscience, that you have it in you to keep the most valuable, the freedom that nobody can take from you, the freedom to determine who you want to be. Eskinder is a journalist. And every day he wakes up in the Kaliti prison is just another day at the office." Nine more journalists were jailed in the past month in Ethiopia, as the election campaign started ahead of next year's poll. "The crackdown was a flashing alarm to the world that no one is safe. That there is a hunting season for journalists in Addis Abeba. But despite this difficult situation, there is light," Schibbye said. "Eskinder Nega's courage has turned out to be contagious; a new generation is stepping up. A generation of young cheetahs have been taking enormous risks writing, tweeting and speaking truth to power, demanding the jailed to be released. It is hopeful. It shows that they can jail journalists but they can never succeed in jailing journalism. Words led Eskinder Nega to the Kaliti prison. And in the end it must also be words that set him free," Schibbye told a clearly emotional audience.

"When I see this Golden Pen of his, I look back, and think of Eskinder who is left behind in the chaos, on the concrete floor, between walls of corrugated steel I feel sick to the stomach. But then I remember his smile and his strength and I think that at the end of the day, it’s not us that are fighting for his freedom – but rather he who is fighting for ours. Ayzoh Eskinder! Ayzoh! (translation: be strong, chin up).”

በአንድነት እና በመኢአድ መካከል የተደረገው ውህደት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ (የሰሜን አሜሪካ የአንድነት የድጋፍ ማህበራት)

June 9, 2014

ተሰናክለን ነበር፤ አሁን ግን ጸንተናል!

«ዉጊያዉን ተሸነፍን እንጂ ጦርነቱን አልተሸነፍንም» ነበር ያሉት የፈረንሳዩ የ2ኛው ዓለም ጦርነት መሪ፤ ጀነራል ቻርለስ ደጎል፣ አገራቸው በናዚዎች ሥር በወደቀች ጊዜ። ልክ እንደ ዉትድርናዉም፣ በሰላማዊ ትግል ዉስጥ መሸነፍ፣ መዉደቅ፣ መሳሳት አለ። መነሳትም እንዲሁ፡፡ ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉትም፤ «በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነገር ፈትሞ አለመውደቅ ሳይሆን፤ በወደቁ ቁጥር መነሳት ነው»ANDINET NORTH AMERICA ASSOCIATION OF SUPPORT ORGANIZATIONS (ANAASO)
በአገራችን የሰፈነዉን አምባገነንነት በመቃወምና በአገራችን ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ላለፉት አያሌ አመታት ትእግስት አስጨራሽ ትግል ቢደረግም፤ የተደረጉ ጥረቶች የተፈለገውን ዉጤት ሳያመጡ ቀርተዋል፡፡
በተለይ በምርጫ ዘጣና ሰባት ወቅት፣ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚያነቋንቅ ትልቅ ሥራ ተሰርቶ የነበረ ቢሆንም፣ ቅንጅትን በመሰረቱ ድርጅቶች መካከል ልዩነቶች ስለተፈጠሩ፣ የቅንጅት አመራር አባላትም በተለያዩ ምክንያቶች ስለተከፋፈሉ፣ የአገዛዙ አፈናና የረቀቀ ከፋፋይ ሴራ ተጨምሮበት፣ ያኔ የነበረዉ የቅንጅት አብዮት እንዲቀዘቅዝ ሆኗል፡፡። ይህም የአምባገነኖች ደስታ ሆኖ ቆይቷል።
ነገር ግን ደጎል እንዳሉት፤ ለግዜው ተሰናክለን ወደቅን እንጂ ተስፋ አልቆረጥንም። ተነሳን እንጂ፤ ወድቀን አልቀረንም፡፡ ላለፉት ሶስት አራት አመታት የመቀራረብና አብሮ የመስራት መንፈስ በተቃዋሚዎች መካከል ሥር እየሰደደ ሲመጣ ታዝበናል። አገር ቤት አሉ ከሚባሉ ጠንካራ ደርጅት መካከል፣ የአንድነት ፓርቲ፣ ከብርሃን ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ከሶስት አመታት በፊት ውህደት የፈጠረ ሲሆን፣ አንድነት ከሌላው አንጋፋ ድርጅት መኢአድ ጋር ለመዋሃድ ንግግሮችን ሲያደርግ ቆይቷል።
ሲደረጉ የነበሩ አድካሚ ንግግሮች ፍሬ አፍርተዉ፣ በመኢአድና በአንድነት መካከል የቅድመ ዉህደት ስምምነት ሰኔ አንድ 2006 ዓ.ም ተፈርሟል። ይህ ታሪካዊ ክስተት ለድርጅታችንም ሆነ ለመላዉ ነጻነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ደስታና ተስፋ ፈንጣቂ ነው ብለን እናምናለን። የመኢአድና የአንድነት አመራር አባላትን ድርድራቸው ለዚህ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፤ ይህን አይነት መልካም ዜና ስላሰሙንም ልናመሰግናቸው እንወዳለን። ውህደቱም ሙሉ ለሙሉ እንደሚሳካ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ማህበራችን በምኞትና በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር፣ የዚህ ታሪካዊ፣ ወሳኝ ትግል አጋር በመሆን የድርሻዉን እንደሚወጣ በዚህ አጋጧሚ ቃል እንገባለን።
ሌሎችም በሰላማዊ ትግል አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችም ፣ መኢአድ እና አንድነትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ እያቀረብን፣ በዉጭ ያሉ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ደርጅቶችም ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ሲሉ ይህን ውህደት እዲደግፉና እንዲሰባሰቡ ጥሪ እናቀርባለን።
አንድነትና/መኢአድ ትግሉን በስሜት ሳይሆን በማስተዋል፣ በችኮላ ሳይሆን በእርጋታ፣ በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር፥ በማራቅ ሳይሆን በማቅረብ እንዲመሩት እንመክራለን። ስህተቶች ይሰራሉ፤ ነገር ግን በስህተቶች የመደናገጥና በቀላሉ ተስፋ የመቆረጥ ዝንባሌያችን አስተካክለን፣ ለፈታኝ እና ወሳኝ ትግል ሁላችንም እንዘጋጅ። ሁላችንም የድርሻችንን ለመወጣት እንነሳ።
በአጭር ግዜ የድርጅቱ ሙሉ ውህደት ተጠናቆ፤ ውህድ ድርጅቱ ለመጪው ምርጫም ይሁን ቀጣይ ትግል የሚያዘጋጁ የፖሊሲ ውይቶችን እንደሚጀምር፤ የበሰለ አመራር በመስጠት እንደ 1997ቱ ሁሉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚወጣ እንጠብቃለን፡፡
በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የድጋፍ ማህበራት፤ በሁለቱ ድርጅቶች ደጋፊዎች መካከል ውህደት እንዲኖር እንደምንተጋ፤ እንዲሁም ውህድ ድርጅቱን በገንዘብ፤ በቁሳቁስ፤ በሞራልና በዲፕሎማሲ እንደምንረዳ ቃል እንገባለን፡፡

ሰማዕታትን እንዘክር፤ እራሳችንንም እንጠይቅ! (ግንቦት7)

June 10, 2014
ሰኔ 1997 በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የተለከፉ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው። ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፋፍኖ የቆየው የህወሓት እውነተኛ ባህርይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በወርሃ ሰኔ አደባባይ ወጣ። በሀውዜን ላይ የደረሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ቡድን ሌላ ሀውዜን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈጠረ። ይኸኛው ሀውዜን ግን በአንድ ቦታ ተወስኖ የቀረ አልነበረም። ጭፍጨፋው በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አዋሳ፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞችና ገጠሮች ተዛመተ። “አግዓዚ” የተሰኘው ገዳይ ሠራዊት በሰላማዊ እናቶችና አባቶች፤ ወጣቶችና ህፃናት ላይ ዘመተ። ደብተርና እርሳሶቻቸውን እንደያዙ ከትምህርት ቤት የሚመለሱ እምቦቃቅላ ህፃናትን ሳይቀር በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ።Ginbot 7 Ethiopian opposition party
በ1997ቱ ሚያዝያ መጨረሻና ግንቦት መጀመሪያ ላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታና ተስፋ ተሞልቶ ነበር። የሚያዝያ 30 ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የግንቦት 7 ጨዋነት የተላበለው ምርጫ የፈጠሩት ተስፋ ቃላት ሊገልጹት በሚችሉት በላይ ነበር። ሆኖም በህወሓት የተመራው የሰኔው ጭፍጨፋ ያንን ሠናይ ስሜት አደፈረሰው፤ አጨለመው።
በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የታወረው ወያኔ ከራሱ አባላት ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው መኖሩ አይታየውም። በህወሓት ጎጠኞች እሳቤ መሠረት ወጣት ሽብሬ፣ ህፃን ነቢዩ፣ ወ/ሮ እቴነሽ፣ ሌሎች እናቶችና አባቶች ሰዎች አይደሉም። ስለሆነም ያለአንዳች ምክንያት ተገደሉ። እስከዛሬ ድረስም ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን ተጠያቂ አልሆነም። በግልባጩ ገዳዮች በመግደላቸው ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህ ሁሉ ያሳምማል።
የሰኔ 1997 ሰማዕታትን የምናስባቸው በጥልቅ ሃዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህ ጭምርም ነው። ወገኖቻችን እንደሰው ባለመቆጠራቸው ተገደሉ። አሁንም እንደሰው የማይቆጠሩ በመሆኑ ሙት ዓመታቸውን መዘከር ወንጀል ነው። መቸ ነው ይህ ውርደት የሚያበቃው?
ሰማዕታት ወገኖቻችን የሕይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነትን የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል። እኛስ ይህንን ኃላፊነት ለመሸከም ብቁዎች ነንን? እያንዳንዳችን የገዛ ራሳችንን እንጠይቅ።

Wednesday, 4 June 2014

ሁለት ምርጫዎች ለህወሀት/ኢህአዴግ (ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ)

June 3rd, 2014
ትዝ ይለኛል በ1997 ዓ.ም ይወጡ ከነበሩ ፕሬሶች ‹‹ነፃነት›› ጋዜጣ ትመስለኛለች በፊት ለፊት ገጽዋ ‹‹ንቢቱ መናደፍ ጀመረች!!›› የሚል ርዕስ ይዛ ነበር፡፡ የመለስን ‹‹እንከን የለሽ ምርጫ እናካሂዳለን›› የአደባባይ ቃል በጥይት ለመቀልበስ ሲሞከር የተሰጠ ርእስ ነበር፡፡
እነዚህ ሰዎች በርግጥም ዴሞክራሲን በወረቀት እንጂ በተግባር ለማረጋገጥ አልቻሉም፡፡ በአንድ እጃቸው ምዕራባዊያን እንዳይከፋቸው ዴሞክራሲን በሌላ እጃቸው ደግሞ የዴሞክራሲ መቀልበሻ ክላሽ ይዘው 23 ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡
አሁንም ዴሞክራሲንና ክላሽን አንግተው ሁለቱንም እንዳስፈላጊነቱ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ሁለቱ ግን ፈፅሞ የሚቀላቀሉ አይደሉም፡፡ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ ኢህአዴግም አንዱን መምረጥ አለበት፡፡
አንደኛው ምርጫ ክላሹን ለድንበር መጠበቂያ ብቻ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ እንዲረጋገጥ ማድረግ ነው፡፡ አፈና፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ እስርና ግድያን በማቆም ስልጣን ከምርጫ ኮሮጆ ብቻ እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡
ይህንን ማድረግ ካልቻለ ሁለተኛ ምርጫም አለው፡፡ ደፈር ብሎ ‹‹ከዚህ በኋላ ምርጫ፣ መድብለ ፓርቲ፣ ነፃ ፕሬስ፣ በነፃ መደራጀት፣ መቃወም አይቻልም፡፡ መፃፍም አይቻልም፡፡ ያለውም አንድ ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ወይም ሞት…›› የሚል አዋጅ አውጆ ቢያርፈው፡፡ ሶቅራጥስ እንዳለው ዓለም በሁለት ተቃርኖዎች ውስጥ ናት፡፡ ኢህአዴግም ከሁለቱ ተቃርኖዎች (ዴሞክራሲና ጠመንጃ) አንዱን መምረጥ አለበት፡፡ እኛም ቁርጡን አውቀን እንቀመጥ ነበር፡፡

ሕድሮም: ህወሓት የፖለቲካ አማካሪየን ሊታስርብኝ ነው

June 4th, 2014
ጓዶች ዓረና ባደረገው እንቅስቃሴ በትግራይ ክልል ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አረጋግጧል። ይሄን ጉዳይ ህወሓትም ተረድቶታታል። እናም የህወሓት አመራር አባላት ዓረናን ለማዳከም አባላቶቻችን በጥቅም በመደለል፤ ካልተሳካ ደግሞ በማስፈራራት እንዲሁም በድንጋይ በመውገር ህዝብን የማነሳሳት እንስቅስቃሴያቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ሞክረዋል። አልሆነም። እናም አሁም የዓረና አባላትን (አስተባባሪዎችን) ለማሳሰር ዉሳኔ ተላልፈዋል። አሁን በግፍ ማሰር ጀምረዋል። አባላትን በማሳሰር ዓረናን ማዳከም ግን አይቻልም። ምክንያቱም ዓረና በህዝብ ልብ ገብቷል። ሁላችንም ቢያጠፉን እንኳ ዓረናን ማሸነፍ አይችሉም። አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ህዝብን ያነሳሳና ከአንድ ወረዳ አንድ ሺ አምሳ ሁለት (1052) አባላትን ያፈራ የዓረና ጀግና አቶ ሕድሮም ሀይለስላሴን ለማሳሰር ወስነዋል። የሕድሮም ተባባሪዎች ናቸው የተባሉትና እንዲታሰሩ የተወሰነባቸው የሚከተሉት ናቸው።
“በሰበብ አስባቡ” እንዲታሰሩ ዉሳኔ የተላለፈባቸው የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ የዓረና አስተባባሪዎች:
(1) ሕድሮም ኃይለስላሴ
(2) ሓምሳለቃ ኪሮስ ሓደራ
(3) አስራለቃ ክንፈ ገብረህይወት
(4) አቶ ወልደገብር ኤል ኃይሉ
(5) ወይዘሮ አለማት ብርሃን ገብረገርግስ
በደረሰኝ መረጃ መሰረት እነኚህ ሰዎች ይታሰራሉ። ምናልባት ያልሰሙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ይደረግ። የሚታሰሩበት መንገድ “በሰበብ አስባቡ” ነው የሚለው። ስለዚህ በፍርድቤት ክስ ተመስርቶ በፍርድቤት ዳኛ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር ሊከናወን ይችላል። በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ብዙ ዳኞች ከስራቸው ተባረዋል። ፍትሕን ለማስፈን ጥረት በማድረጋቸው፤ በካድሬዎች ትእዛዝ ሳይሆን በሕገ መንግስት መሰረት ነው የምንፈርደው በማለታቸው ምክንያት። ዳኛ ካሕሳይ ዘገየ ጥሩ ምሳሌ ነው።
ሕድሮም ኃይለስላሴ አርሶአደር ሲሆን የታጋይ ልጅም ነው። አባቱ አቶ ኃይለስላሴ አሰፋ የቀድሞ የህወሓት ታጋይ ሲሆን ተሰውቷል። አቶ ሕድሮም አሁንም ለነፃንቱ የሚታገል ጀግናችን ነው። የፖለቲካ አስተማሪዬ ነው። ሌሎቹ ደግሞ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ሲሆኑ አሁንም የነፃነት ትግላችን በሸፍቶች ተጠልፏል ባዮች ናቸው። ወደ ህወሓት ከመቀላቀላቸው በፊት በደርግ ስርዓት በደል ይደርስባቸው እነደነበረና አሁን ተመሳሳይ ግፍ እንደሚፈፀምባቸው ይናገራሉ። በዓረና ለዓረና እየታገሉ ብዙ ሰዎች ከጎናቸው ያሰለፉ ጀግኖች ናቸው።
ሕድሮም ኃይለስላሴ የፖለቲካ መምህሬና አማካሪየ ነው።
ሕድሮም! It is so!!!10155685_627468584000753_4676346970037171962_n

Saturday, 31 May 2014

ለውጥን ፈልገን ለውጥንም ፈርተን በጭራሽ አናመጣውም

May 31, 2014
ዳዊት ዳባ
የለውጥ አስፈላጊነት ላይና ወያኔ መራሹ መንግስት ይበቃው ዘንድ ባብዛኛው ዜጋ ከተቻለ የሚለው እንዳለ ብዥታ የለም። ይህ ፍላጎት የብዙ ስረአቱ ውስጥ ያሉ ዜጎችም ጭምር መሆኑን የተለያዩ መረጃዎችን ጨምቆ ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል። በርግጥ የለውጡ አስፈላጊነት ላይ የሚስማሙና አይቀሬነቱን የሚያውቁ ነገር ግን ለውጡ የተረጋጋና ችግሮች ያልበዙበት እንዲሆን ይረዳል ብለው አገዛዙ ድርሻ በሚያደርግበት እንዲከወን የሚመኙ አሉ። ፈራ ተባ እያሉ ሀሳቡን አንዳንዴ ያነሱታል። ይህ ሀሳብ ክፋት ባይኖረውም ጥሩ ምኞት ብቻ ነው የሆነው። በትንሹ እንኳ ተቀባይነት እንዲያገኝ አይደለም እንዲሰማ ለማድረግ አገዛዙ ጉልብት አልሰጠው እያለ ብለጭ ድርግም ይላል። አውቆ የሚያደርገው በሚመስል ገና እነዚህ ጥሩ አሳቢ ዜጎች ቁምነገሩን ሲያነሱት አገዛዙ አንጀት ቁርጥ የሚያስደርግ ሰማይ ሰማይ የሚያካክል አጋረዊ ጥፋቶችን አከታትሎ እየፈጸመና እያላገጠበት ያስቸግራል። ለምን ብሎ ለሚጠይቅ?። ቀንደኛ ለሆኑት የስርአቱ ሰዎች ከኛ በላይ ይህ መንገድ እንዳማያዋጣቸውና እድሜያቸውን ማሳጠር ብቻ እንደሆነ አሳምረው ስለሚያውቁ ነው። እውነት ለመናገር ትክክልም ናቸው። የትኛውም ለውጥ የሚመጣበት መንገድ የመጨረሻ ውጤቱ ለነሱ መቶ በመቶ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። አስፍተንና እርቀን አስበን፤ ሆደ ሰፊ ሆነን፤ ይቅር ብለናል ብለን መጫኛ ነክሰን ብንለምንም ልንሳምናቸውና ሀሳብ እንዲቀይሩ ለማድረግ አይቻለንም። የሰሩትን ያውቁታል። ስለዚህም ላልቆረጡ ይቁረጥ። እነሱ ገፍተን እንዲሸሹ እንድናደርጋቸው ነው የሚጠብቁት። ያም ሆኖ አዙረንና በጥልቀት ስላላየነው ነው እንጂ ለውጡ ላይ ይገጥሙናል ብለን የምናስባቸውን ችግሮች በማስቀረት ረገድ ለውጡ ላይ ድርሻም አደረጉ አላደረጉ ቅንጣት ታህል የሚጨምሩትም የሚቀንሱትም ነገር የለም። እንደውም ያወሳስቡታል። በሌላ በኩል ለለውጥ የቆመው ክፍል ከምር ይህን ቁም ነገር አሳስቦት መላ ላድርግበት ቢል መፍትሄ ሊያበጅለት የማይችል አይደለም። የሚካበደውን ያህልም በጭራሽ አስቸጋሪም አይደለም። የዚህ ክፍል ዋን ትኩረት መሆን የነበረበት ይህ ነበር።Revolution coming to Ethiopia
ለውጥ ሊመጣ ነው። አዎ ለውጡ እየመጣ ነው። እንዲሁ በምንም አይነት ለውጥን ፈርቶ ትግሉን በማለዘብ ማዘግየት ይሆናል እንጂ ይገጥሙናል የምንላቸውን ችግሮች ማስቀረትም አይቻልም። ይህን አይነት አሳብ በድጋሚ ግራ የገባን መሆናችንን ብቻ ነው የሚያሳየው። እንደውም ችግሮች ገዝፈውን ተወሳስበው በሗላ መፍትሄ ልንሰራላቸው የማይቻለን ማድረግ ብቻ ይሆናል። እየታየ ያለውም ይሄ ነው። እስካሁን ማሸነፍ አቅቶንና ወያኔን ፈርተን አሁን ደግሞ ለውጡን ፈርተን እድሜ አንቀጥልላቸው። በዛ ላይ የተገኘውን ያህል እድሜ ማግኘቱን እንሱም የሚፈልጉት ነው። ምክንያቱም በሚያገኙት እድሜ ደግሞ ችግሮችን በመፈልፈል፤ በማግዘፍና በማወሳሰብ ፈርተን ይቆዩ ይሆን? እንድንል ይጠቀሙበታል።
አገዛዙን ማሸነፍ ትግል ነው። አገዛዙን ማሸነፍ መሰዋትነት የሚሻ ነው። ለውጡን ሉአላዊነታችንን የማይነካ በማይከፋፍለንና በማያገዳድለን፤ ሁሉ ደስተኛ በሚሆንበት መንገድ መከወን ግን እንደማየው ትግል ልናደርገው ካልፈለግን ትግል በጭራሽ አይደለም። ትግልም ቢባልም አውዳሚ ትግል አይደልም። አውዳሚ የሆነ መተጋገልንም በዋናነትም አያሻም። የሚፈልገው ፍቃደኝነትን፤ አስፍቶ ማሰብን፤ ተጨባጩን ያአገራችን ሁኔታ ማጥናትንና፤ አማካኝ የሚያስማማ መፍትሄ አምጦ መውለድንና ማስቀመጥን ነው። ለሁሉም በጠረቤዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ መወያያትንና መስማማትን ብቻ ነው። በዚህ ጽሁፍ ትግል ያልኩት ሲቀነቀን የማየው በሂደቱ ሉአላዊነታችንን ሊጎዳ የሚችል ፤ ደም የሚያፋስስና አውዳሚ የሆነውን ነው። ያሁኑ ደግሞ እንደከዚህ በፊቱ በድርጅቶችና በተከታዬቻቸው መሀል የሚደረግ አይደለም። በህዝቦች መሀል የሚደረግ እንደሆነም ስለማውቅ ነው። አዲሱ ትውልድ ከሰማና ግድ ካለው ነው እንጂ የአቢዬት ልጆች ታላለቆቻችን ዛሬም ከማይታረቅ ቅራኔ፤ ከመስመር ልዩነት ከሚል ታስቦት የወጡ አይመስለኝም እንደሚከብዳቸው አውቃለው።
ይህ ግልጽ በሆነበት ነው አገዛዙን ነገ ለመጣል ባሰበ በሙሉ ሀይላችን መግፋቱን ለደቂቃም ማቆም ግን የለብንም የምለው። ለምን ቢባል ከላይ ከሰጠሁት ምክንያት በተጨማሪ ለውጡን ችግሮች የማይኖሩበት ማድረጉ ድሮ ድሮ መሰራት የነበረበት ነው። በቀላሉም አዎ በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ውዝፍ የቤት ስራ ነው። ወዝፈንዋል። ያም ሆኖ የተጀመረው ትግል በሚጨምርበት በተጓዳኝ በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ደግሞ ነው። ሁለት ሲደመር ሁለት ይሆናል አይነት መፍትሄ ካላልን። ስለማይቻል መቶ ፐርሰንት ሁሉም የሚደሰትበትና ፍፁም መፍትሄ ለማምጣት ካላሰብን። የጋራ መፍትሄ መስራቱ ላይ ድርሻ አላደርግም ብሎ ርካሽ ፖለቲካ ሊሰራበት የሚያሰላ ድግሞ ካልተነሳ። ሂደቱ ህክምና መጀመር መሆኑ ቀርቶ አንድ ክኒን በመዋጥ ከሁሉም አይነት መሀበረሰባዊ ችግሮቻችን ባንዴ ለመፈወስ አይነት ያላሰበ ካልሆነ። ቢቻል ጥሩ ነበር ከአለም ላይ የመጀመርያዎቹ እንሆን ነበር። በየትኞቹም አገሮች እንደኛው ቸግሮች መኖራቸውም መፍትሄ ላይ መስራቱም ቀጣይ ሆሌም የሚኖር ሂደት ነውና። አላማው ውስን በዋናነት ሽግግሩን ሰላማዊ ማድረግ ደም የማያፋስስና የአግር ደህንነትን ማረጋገጡን ብቻና ብቻ ታሳቢ አድርጎ ከተሰራበት።
አሁን የትኞቹም ድርጅቶች ከላይ የገለጽኩትን አይነት ድም አፋሳሽን አውዳሚ ትግል ውስጥ ሳይገቡ ሽግግሩን እናሳካለን ብለው ሊያሳምኑኝ፤ ሊያሳምኑም የሚችሉ የሉም። ለዚህም ነው ለውጥ እጅግ አስፈሪ የሆነው። ካላችሁ እጃችሁን አውጡና አሳምኑን። ያለበለዚያ አንድ ድርጅቶች ፕሮግራማችሁን በማስፋትና ተጨባጩን ያገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በይበልጥም ለውጡን የሚሸከም ማድረግ። ሁለት በቶሎ በጠረቤዛ ዙሪያ ቁጭ ብላችሁ የዝች አገር ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ጋር ሁሉ አግላይነት በሌለበት ተወያይታችሁ ፍጽም ባይሆንም በሁሉም ዜጎች ዘንድ ማለፊያ ተደርጎ የሚወሰድ ስምምነት መቋጨት ብቻ ነው መንገዱ። ከሁለቱ አንዱን እንኳ ሳታደርጉ በርግጠኝነት በየትኛውም መንገድ የሚመጣ ለውጡን አውዳሚ ትግል ውስጥ ሳይከተን በሰላም ልታሻግሩን በታአምር ካልሆነ አይቻልም። ሳይቻል ቀርቶ ለሚደርሰው ውድመት ደግሞ ሀላፊነት አለባችሁ።
እንዲሁ እውነት እውነት እላችሗለው ይህን ካላደረጋችሁ በቀጣይም ዲሞክራሲያዊ መንግስት አዝች አገር ላይ አሁንም አይመጣም። ዜጎች ይህን ቁምነገር አጽኖት ሰጥተን እንየው። ብዙዎች በዘር የተደራጁ ድርጅቶች ዲሞክራሲን ሊያመጡ አይችሉም ይላሉ። ይህ ግልጽ ነው አይችሉም። እነሱም ባዛ ወይ በዚህ ዘር ተደራጅተው ለሁሉም የሚሆን ዲሞክራሲ ብቻችንን ሆነን እናመጣለን ብለው አላሰቡም። አይሉምም። ከዚህ በሗላ አይመጡምም። መነሳት ያለበት በዘር አልተደራጀንም የሚሉት ወደስልጣን ሲመጡ ይህ ሁሉ የዘር ድርጅት፤ የመብት ጥያቄና፤ ጥልቅ ሴሚትና ፍላጎት ብንን ብሎ ይጠፋል ወይ የሚለው ነው?። መንግስት ስሆኑ ሊመልሱት ወይ ሰላማዊ መፍትሄ ሊሰሩለት ከሆነ አደጋ ባለው በሳት ውስጥ ዛሬ ለምን እናልፋለን?። በኔ እይታ ሀሳባቸው ያ ቢሆን ዛሬውኑ ይመልሱት ወይ በሁሉ ተቀባይ መፍትሄ አሁን ይኖራቸው ነበር።
መታወቅ ያለበት ነገ ዲሞክርያሲያዊ ለመሆን ስትሞክሩ ጥያቄው በነፃ መድረክ ፋፍቶ በሚሊዬኖች ይቀጥላል። ሲትጨፈልቁትና ሲታፍኑት አንባገነን ሆናችሁ ማለት ነው። ለማፈንና የተወሰነ አመት ደግሞ ለማስኬድ በገፍ መግደልንም ስለሚሻ ገዳይ አንባገነን ትሆናላችሁ ማለት አይደለም ወይ?። ይህን ደግሞ ከዛሬው አምርሬ እቃወማለው። መብት የሚከበረብት ከማለት መብትን መበለቱ መፍትሄ አይደለም?። ለኔ ያው አመል የሆነው ወዛድር ላባደር አድካሚ ሙግት ነው። አንድ ሚሊዬን ሆነው ሲጠይቁ የግለሰብን መብት ማክበር የመንግስታችን መሰረት ስለሆነ እናንተ ደግሞ ብዙ ስለሆናችሁ ወይ ያፍንጫችሁ ቅርጽ ስለሚመሳሰል ተለያይታችሁ ጠይቁ ሊባል ነው ማለት ነው።
በዚህ ምክንያት ተሰሚነት ያላቸው ተስፋም የማደርግባቸው የበዙትን ተቃዋሚ ድርጅቶች አሁን የያዙትን ወይ መፍትሄ የሚሉትን መንገድ ፈርቼዋለው። ፍራቻዬ በቀጣዬ ምርጫ ከስትራተጂ አኳያ አዋጭ ሆኖ ስላልታየኝም ነው። ያሸባሪ ህጉ ላይም ሆነ ያአባይ ጉዳይ ላይ ተቃዋሚዎች ካገዛዙ ጋር ካደረጉት ክርክር በቀጣይ በመጪው ምራጫ ከገዛዙ ጋር የሚኖሩ ከርክሮች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ ስለወኩም ነው። ኮሌታ ይዞ ግርግዳ አስደግፎ የመሰለ ቁርጥ ያለ መልስ የሚሹ ጥያቄዎችን እንጠብቅ።
አሁን ያለውን ቋንቋን መሰረት ያደረገ አከላል መቃወም እንጂ መነሻ የሚሆን እንኳ አከላል የለም። ይዘውም ወደምርጫው አይገቡም። ውለዱ ግን ይኖራል። ቆያይቶ ቢሰራም ቆይቶ መምጣቱ በራሱ ኒይውትሮል ቦንብ ነው። በዛ ላይ ለሚሸነሽነውና ለሚለያየው ዜጋ ለምን እንዴት እንደሚጠቀምው ማስረዳቱ ካቅምና ከመድረስ አኳያ እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን ነው የምለው። ተችሎም ተቀባይነት ማግኘቱ ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው።
ድርጅት የግለሰቦች ስብስብ ነው። የኛ ድርጅቶች ደግሞ የስብጥራዊነት ችግር አለባቸው ። በቅርበትና በመተዋወቅም ነው። በንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፖሊሲና እቅድ የሚወጣው ካለው ነባራዊ ሁኔታና አሸናፊ ማድርጉ ተሰልቶ ሳይሆን የሚመኙት፤ እንዲሆን የሚፈልጉትና ትክክል ነው ብለው ሚያስቡት ተፅኖው በበዛበት ይመስለኛል። አሁን አሁን አፈናውም ሚና እያደረገ እንዳለ እያየው ነው። ለዘጠና ሚሊዬን ያንድ አገር ልጆች ብንሆንም ልዬነትና የተለየ ብዙ…. ላለን የሚሆን ፖሊሲና እቅድ አለመቀመሩ በሗላ ብዙ አጣምረው የሚያዩ፤ ድምጽ የሚነፍጉ፤ አልፈውም የሚታገሉ አብዝቶ ይፈጥራል። ስለዚህ አሁን አሁን ያለውን አከላለል መንካቱ ትርፉ ኪሳራ ማጨድ ብቻ ሆኖ ነው የሚታየኝ። ለምርጫ ብቻ ሳይሆና ለሌች የትግል አማራጮችም በይበልጥም ለህዝባዊ አመጹም ሁሉ ድርሻ እንዲያደርግ ሳይሆን መሄዱ የሚፈለገውን ጉልበት አያመጣም። አሁን ያለው አከላል አይነካ የምለው ግን በዋናናት ዲሞክራሲያው በሆነ ስርአት ውስጥ ጠቃሚና ጎጂነቱ መጀመርያ መታየት ስለሚገባው ነው። መፍትሄ ብለን በቀጣይ የምናስኬደው ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ የልጆች ጫወታ መሆንም ስለሌበትም ነው። መሬት ላራሹ የወያኔው የዘር ፖለቲካ አይነት ስር ነቀል ለውጥ ከትርፉ ኪሳራው ትልቅ መሆኑን ስለማውቅም ነው።
ቆም ተብሎ እንደገና ይታሰብበት የምለው እየገሰገሰ በአለው ለውጡ በግርግር ያገር ሉአላዊነት አደጋ ውስጥ እንዳይገባ። ከላይ የገለጽኩት አይነት አውዳሚ ትግል ውስጥ የማይከተን፤ ለዘውም በዜጎች መሀል። ትግላችንን ካገዛዙ ብቻ ጋር የሚያደርግና ጉልበት የሚያስገኝልን መፍትሄ ስላልሆነ ነው። በቀጣይም እንዳልኩት ዲሞክራሲን ያለችግር ለመተግበር ስለማያስችልም ነው። የመብት ጥያቄዎች ሊለጠጥ የሚችልበት የመጨረሻው ደረጃ ድረስ እንደው አንዴ ተለጥጧል። በቀጣይም ሁሌም ጥያቄዎች ብሶቶች ይኖራሉ። ከዚህ በሗላ የሚመጡትን ለመመለስ ካሁኖቹ አይከበዱም። ደግሞም ይኑሩ። አይኑሩምም አልልም። ጤናማም ነው። በአጠቃላይ ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ የትግል አግባብ የሚቀጥሉበትን መንገድ ማበጀት እንደሚቻል ስለማውቅ። የተያዘው አያያዝ ወደዛ የሚገፋ ስላልሆነም ነው። ከዚህ መለስ መገንጠል የሚለውን የእብዶች ሃሳብ የሚያከስምና የወያኔን አንቀጽ 39 መሰረዝ ላይ መስማማት ላይ መድረስ በቀላሉ እንደሚቻል ስለማውቅ ነው። ባንዲራዉ ላይ ያስቀመጡትን አንባሻም ከድል በሗላ በክብር ማንሳቱም ላይ። ኢትዮጵያዊነታችንን በየወንዙ እየቆምን መጠየቁ መፍትሄ የማይሆነውን ያህል ለሁሉ ችግር ኢትዬጵያዊነት መልስም አይመስለኝም። ለኔ ወሳኝ ሰዎችችን እንጂ ኢትዬጵያዊነት የማይሸከመው የመብት፤ የማንነት.. እነዲሁ ፍላጎትና የማያስተናገድው ብሶት…የለም ብያለው። ብንወድቅ የሚያወድቁን አንድና አንድ ወሳኝ ሰዎቻችን ናቸው።
እንደገና ባግባቡ ይታሰብበት የምለው አሁን ካለኝ አጠቃላይ ያገራችን ፖለቲካ መረዳትና አሁን ባለው የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ከላይ የገልጽኳቸውን በወርቅ ሚዛን ሊመዘኑ የሚገባቸው አገራዊ ፋይዳዎች ዛሬ መፍትሄ ተብሎ የሚቀርበው ሀሳብ ውስጥ በመነሻ ደረጃ እንኳ ያስገባና የታሰበበት ሆኖ ስላልታየኝ ነው። የተያዘው አማራጭ ለውጥን ሳንፈራ መታገል እንዳላስቻለን እያየው ስለሆነም ነው። በዜጎች መሀል የበለጠ መጠላላትን መፈራራት በየቀኑ በሚያድግ ሲፈጠር ስላየሁ ነው።
የመብት ጉዳይ ላይ ሁሌም የትል ወገብ ነው ያለን ለማጣዎች ነን። ይባስ ብሎ ዛሬ ጠበን ስለተነሳን ከራሳችን እንዳንቃረን፤ ፈርተንና ድንጋጤም አለበት የሰሞኑን የስምንት አመት ህጻን ጨምሮ የንጹፈን ዜጎቻችንን ፍጅት ጠንከር ብለን መቃወም እንኳ አልቻልንም። እንደውም ደጋግመን ገድለናቸዋል። ለምን በዲዲቲ ከሚሉ ጀምሮ ዱላ ይዞ የሆነ ሰው አስገድዶ ያጻፋቸው የሚመስሉ የድርጅት የመግልጫዎች ጋጋታ፤ የዘር ፖለቲካ ነው። ዘረኞች ናቸው የትንታኔ መአት …ብቻ ሁሉም ስህተትም አሳዛኝም አስተዛዛቢም ነበር።
ለኔ የተፈጁት ኢትዬጵያዊያን ናቸው። ኦሮሞዎች ናቸው። የደሀ እናት ልጆች ናቸው። ዘመዶቼ ናቸው። ባታወቋችው ነው እንጂ ይህቺ አገር የሂወትና የደም መሰዋትነት ግድ ባላት ጊዜ ታላላቆቻቸው ሁሌማ የበዛ መሰዋትነት የከፍሉ ናቸው። የፈጇቸው የትግሬ ወያኔዎች ናቸው። የፈጇቸው ደስታን ስለሚሰጣቸው ነው። ጦርነትን ሰርተን ያህዬች ብለሀት መሆኑ ነው። በቀጣይም ምርጫ ብለው ሲሸነፉ ሊፈጅ ስላሰቡ ነው። ምርጫ የሚባል ነገር የለም ያባት ነው። እንደምትሸነፍ እያወክ ምርጫ ብሎ መግደል ያህያ ካልሆነ ሌላ ምን ይባለል። ለማንኛውም የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄያቸው ጥርት ያለ የመብት ጥያቄ ነው። ጥያቄያቸው ጥርት ያለ ህጋዊ ጥያቄ ነው። የዘር ፖለቲካ የደረግነው ተሳደድንና ተገደልን አይደለም ተሰደብን ብለው መቃወማቸው ትክክል ሲሆን አባቶቻችን መሬታቸው በዘረኛ በትግሬ ወያኔዎች እየተቀማ ባሬላ ተሸካሚ ለምን ይሆናሉ ብለው ጠየቁ ብለን ሙግት የገጠምን፤ የከፋንና ትንታኔ ያበዛን ጊዜ እኛ ነን። መወገዝ ባለበት ደረጃ ያወገዝንና ድምጻችንን ያሰማን ኢትዬጵያዊ ግዴታችንን ነው የተወጣነው። የሚያኮራን ነው። ወደተነሳሁበት።
እድሜ ለገዢዎቻችን ጫካ ቆይተው መጥተው ወደሗላ መልሰውን እንጂ የዛሬው መፍትሄ ያኔ ሊተገበር የሚችል ነበር። ላሁኑ አስተማማኙ መፍትሄ አሁን አንገብጋቢ ወሳኝና ግድ የሚል ፖለቲካዊ አቋም በመያዝና ጠጠር ያሉ ፖለቲካዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ሰላማዊ ሽግግርን አረጋግጦ በቀጣዩ በጊዜ ሂደት በመሀበረሰብ ጠቅላላ እድገትና ማእከላዊ መንግስቱን በማጠንከር፤ በማስተማር መሄዱ አዋጭ ነው። የየትኛውንም ዜጋ የፈለገበት ቦታ ሄዶ የመኖር መብትም ሆነ የዘር ሀረግና የትውልድ ቦታ እያጣሩ ማፈናቀል በህግ አግባብ በቀላሉ ልክ ማስገባት የሚቻል ነው። ከሁሉ በላይ ይታሰብበት የምለው እንደዜግነቴ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ድምፄን ማሰማትና የተሻለ የምለውን የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ግዴታ ስላለብኝም ነው። ጉረኛም ቢያስመስለኝ ሽግግሩን ችግር የሌለበት የሚያደርገውንና በጋራ የሚያታግለነን እንዲሁ የማያጠላላ መፍትሄ ካዛም ከዚህም ወገን ያለውን ሀሳብ አይቼ እኔም እንኳ መሀል ያለ መነሻ መፍትሄ ባንድ ገጽ ላይ አጣፍጬ ማስቀመጥ ስለምችልም ነው።
ከዛ ውጪ ጥሩም ሆነ መጥፎ ታሪክ ላይ በቻ በመንተራስ መፍትሄ መስራት አይቻልም። ትናንት ላይመለስ ሞቷል። ይቁረጥ። ስድብና ንቀትን የሚገለጽባቸውን አገላለፆችን እየፈበረኩ መቀስቀሱም ሆነ አንዱን ዘር ሴጣን በዳይ፤ዘረኛ፤ ጠይ፤ ጨቋኝ በማድረግ ፍፅም ውሸትና መሰረት የሌለው ዘመቻ ማካሄድ መፍትሄ መስሎን እያደረግነው ካለን አይደለም። {የምምለስበት ቢሆንም እነዚህን አገላለጾች ብዙ ጊዜ ስንናገርም ሆነ ስንፅፍ የምንጠቀመው አውቀን ለርካሽ ፖለቲካችን እንዲያመችና ለሌሎች ያለንን ጥላቻ ለማሳየት አስበን አሳስተን ነው።} ይህ የሚደረገው ይህን ወይ ያንኛውን ክፍል በማሸማቀቅ ዝም ለማሰኘት ታስቦ ነበር ። የጅሎች መላ ስለሆነ አይሰራም። በዚህ ከቀጠለ ግን የሚያስፈጅ ወይ የሚያፈጃጅ መሆኑን ግን ማወቅ ሁሉም አለበት። እንደውም መልካም አሳቢ ዜጎች ሁሉ እየወጣን ወገንታዊ ሳንሆን ሀይ ካላልነው ሽግግሩን ያከብዳል። ለአብሮነታችንም አደጋ ነው። እዚህ ሀላፊነት የጎደለው ጸያፍ ተግባር ላይ ድርሻ የምታደርጉትን በሙሉ አጥብቄ አወግዛለው። ይህ በተደራጀና በተቀናበረ መንገድ የሚደረግ መሆኑን መረጃዎች በግልፅ ያሳያሉ። በዚህ እውነት ፅሁፌን አበቃለው።

ኢትዮጵያ እውነተኛ ልጇን አጣች

May 30, 2014
በልጅግ ዓሊ – ፍራንክፈርት
ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።Karlheinz Böhm1
ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ ነበር። ጀርመን ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ ስለዚህ ሰው ደግነት በሰፊው ልረዳ ችያለሁ።
ካርልሃይንዝ በተወለደ በ86 ዓመቱ ያለፈው ሐሙስ ሌሊት ሳልዝቡርግ – አውስትሪያ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ካርልሃይንዝ በኦስትርያ፣ በጀርመን እና በሲዊዘርላንድ የተከበረ የፊልም ተዋንያን ነበር። ካርልሃይንዝ የታወቀው ንጉስ ፍራንዝ( Kaiser Franz Joseph) ሆኖ በሠራው ፊልም ነበር። ከዛም በኋላ በተከታታይ ብዙ ፊልሞች ሰርቷል። ይህ ሰው በፊልም ታዋቂነቱ ሳያግደው ፣ የተንደላቀቀው ኑሮው ሳያጓጓው የሃገራችንን ሕዝብ ኑሮ እዛው እየኖረ ሕዝብን መርዳት የወሰነው 1976 ኬንያ ውስጥ ሆኖ ስለ አፍሪካ ችግር ባወቀበት ወቅት ነበር።
በጀርመን፣ በኦስትሪያና በስዊዘርላንድ ለሦስት ሃገሮች በሚተላለፈው የቴሌቪዥን የውድድር ፕሮግራም (“Wetten, dass..?”) ላይ በ1981 በእግድነት ቀርቦ ከሕዝቡ ጋር የውድድር ሃሳብ ያቀርባል ። በአፍሪካ ለደረስው ችግር እርዳታ የሚሆን ይህንን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሚመለከተው ሕዝብ አንድ ሦስተኛው . . . አንድ የጀርመን ማርክ ወይም አንድ የስዊስ ፍራክ ወይም 7 የኦስትሪያ ሽልንግ ከሰጠ ችግሩ ባለበት ቦታ ሄጄ እረዳለሁ ብሎ ይወዳደራል።
ካርልሃይንዝ ምንም እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠር እርዳታም ቢያገኝም የተከታተለው ሕዝብ አንድ ሦስተኛው የተወዳደረበትን ገንዘብ አልሰጠም። በዚህ ምክንያት ውድድሩን ያሸንፍና ወደ አፍሪካ መሄድ ግዴታው አይሆንም። ቢሆንም ግን ይህ ታዋቂ የፊልም ሰው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በዓላማው በመጥናት የተንደላቀቀውን ኑሮውን እርግፍ አድርጎ በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ የችግረኛውን ኑሮ እየኖረ እርዳታውን ለመስጠት ወሰነ። ከ1982 ጀምሮ ከፊልም ስራው ተለያይቶ በእርዳታው ላይ ብቻ አተኮረ።
ካርልሃይንዝ “ሰው ለሰው“ . . . “Menschen für Menschen” የሚባል ድርጅት አቋቁሞ ከ1981 ጀምሮ እርዳታ ሲደርግ ቆይቷል። እዛው ሃገራችን ውስጥ ካርልሃይንዝ ከወይዘሮ አልማዝ ጋር ተጋብቶ ይኖር ነበር። ወይዘሮ አልማዝ ካርልሃይንዝ ከታመመበት ጊዜ ጀምሮ የእርዳታ ድርጅቱን ሲመሩ ቆይተዋል። ካርልሃይንዝ 7 ልጆች ሲኖሩት ሁለቱ ከወይዘሮ አልማዝ የተወለዱ ናቸው።
ለካርልሃይን ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ።

Ethiopia: Mr. Obang Metho Accepted Annual SEED Award

May 27, 2014

Mr. Obang Metho’s Acceptance Speech: “The Journey to a New Vision for Ethiopia” At the 22nd SEED Annual Award ceremony

May 25, 2014
Washington DC.
I would like to deeply thank distinguished members of the Society of Ethiopians Established in Diaspora (SEED) and my fellows’ citizens of Ethiopia for this recognition. I am both humbled and honored to be here tonight as a recipient of this award. I receive this honor with deep gratitude and great humility. I want to acknowledge others who have helped make this possible because, although I am accepting this award, this is not only about me. I did not come to this point alone, but must recognize the countless individuals, too many to name, who have contributed to this work along the way. Without them there would not be anything to acknowledge, just like the African proverb that says, “If you want to go faster, go alone, but if you want to go further, go together.” My thanks and appreciation goes to all of these people who have helped us go further. Our journey together has been one of many challenges, but because it has been shared, it has brought unexpected friendships, joys and fruit.
Mr. Obang Metho Accepted Society of Ethiopians Established in Diaspora Award
I was told that this award was in appreciation for the work done in defense of the freedom and civil rights of our people, especially, the under-represented Anuak. I am very emotionally touched by this statement, especially the inclusive phrase, “our people,” which embraces Anuak, as well as other Ethiopians, both mainstream and minorities, as part of the whole of people of Ethiopia. Do you realize how revolutionary this is? Ten years ago this never would have happened. It is an indication of a major paradigm shift in our thinking. It is a cornerstone of a New Ethiopia where humanity comes before ethnicity or other identity factors and where we care about our Ethiopian brothers and sisters because no one will be free until all are free! The journey has not been easy, nor is the journey over, but if we travel together, we will go further and possibly faster, than any of us expected.
This journey began on December 13, 2003, with a desperate phone call from Gambella, Ethiopia. A massacre of Anuak leaders had begun in Gambella, perpetrated by the TPLF/EPRDF Defense Forces, accompanied by civilian militia groups, incited and equipped by the military. Within three days, over 425 Anuak had been brutally killed in an effort to eliminate the strongest opposing voices to the extraction of possible oil reserves on Anuak indigenous land without first consulting the people.Obang Metho speaking at Society of Ethiopians Established in Diaspora (SEED)
When I first saw the names of those killed, I knew over 300 of the victims. They were family members, friends and colleagues in the development work I was carrying out in Gambella. As I grieved for the loss of their lives in the days and weeks that followed, I realized that the only option for a better future for the Anuak and the people of Ethiopia would not come from retaliation, but only from transformation to something better than the cycle of revenge we had seen played out in the past. Yet, despite this personal revelation, today’s reality of me standing up for the freedom of Ethiopians and speaking for a united Ethiopia did not come easily.
For example, being a minority—who looks very different from mainstream Ethiopians—complicates the journey even more than the ethnic differences among those in the mainstream, many of whom look alike. However, for the same reason, having to work through the obstacles these differences presented has been a critical component in finding my way in the journey to a more inclusive Ethiopia. Even though Ethiopians have often spoken of Ethiopia as the symbol of black pride; on the ground, the most dark-skinned, African-looking Ethiopians have suffered the greatest discrimination and marginalization.
How we value other human beings says a lot about our society and in the Ethiopia of 2003, we were in grave trouble. Thankfully, it is improving today; but not because of the faked unity under the TPLF/EPRDF’s model of ethnic federalism, which is simply a pretension of such, but instead because Ethiopians are actually changing. Back in 2003, things were very different.
Shortly following the 2003 massacre in Gambella, the handful of Anuak living in Washington DC organized a protest in front of the Whitehouse to condemn the killing of the Anuak. The protest was announced on Ethiopian radio, through flyers at Ethiopian shops and restaurants and through word of mouth; however, despite the fact that there were over 300,000 Ethiopians in DC at the time, only ten Anuak and four other Ethiopians from the mainstream—close friends of the Anuak—showed up for the rally. Anyone can give various reasons for the poor response; but regardless, it was a sign to the Anuak that they were in this crisis alone. Because they had no one else standing with them, they realized how vulnerable they were and that if they were going to survive as a people in Ethiopia, they had to stand up by themselves.
This led to my advocacy work, which began immediately, but later to the formation of an organization, the Anuak Justice Council (AJC). Its mission was to protect the rights and well being of the Anuak wherever they were found. Initially, the work for the Anuak stayed focused on the Anuak; however, three things happened to change our direction and to bring us along the journey to where we are today.
1. In February 2005, I was in Washington DC on my way to meet with former Senator Russell Feingold when I hailed a taxi to take me to the Senate building. A very friendly Ethiopian taxi driver picked me up and warmly greeted me, calling me his African brother. He asked me where I was from. I suggested he guess. He rang out a series of countries, including Kenya, Uganda, Tanzania, Nigeria, Sudan, Cameroon, and Senegal when I stopped him and told him to go back to East Africa. He said he had mentioned almost every country in East Africa and I said, no, not all of them. He then added Burundi, Rwanda, the Congo and the Central African Republic before giving up. I urged him to continue. He then asked for a multiple choice question. I said: a) Ethiopia, b) Eritrea, c) Somalia or d) none of the above. Before I could finish the last, he said it was none of the above. I told him he had gotten it wrong. He argued with me, telling me he was not wrong for I didn’t look Ethiopian, Eritrean or Somali. I told him, no, I am from Ethiopia. He again argued saying, “For sure, you are not an Ethiopian—prove it!” I then said, “How are you?” in Amharic, Oromo and Tigrinya. When I said this, he said, “Wow, you speak Amharic?” Yet, he still was not convinced until I told him I was an Ethiopian from Gambella and he finally got it. When I arrived at the Senate building, he refused to take any money for my fare; saying with warmth that I was his countryman.
Our conversation impacted me and changed my entire viewpoint. He knows this now as he and I have talked about this since that time; however, as I walked into the Senate building for my appointment, I thought, wow, here I am, coming to meet with US policy makers to advocate for the rights of the Anuak and yet, with someone from my own country, I had to speak the Amharic language to convince them I was Ethiopian. I began to grasp the fact that the battle ahead was much larger than I had thought. I realized that not only were other Ethiopians not standing with the Anuak as we were trying to seek justice, but also that I had to even prove my belonging as an Ethiopian. In other words, the justice I was seeking would never come to the Anuak unless it came to all Ethiopians, which required acknowledging our common cause and common bonds that at this point were nonexistent. The problem was deeply entrenched in the system and required a systemic approach and a change of thinking.
As I met with the senator, I wondered how many other Ethiopian people, especially from the minorities, had no one abroad to advocate for them in situations of distress. After this experience, I brought it up to the AJC board, making a case that from then on, we had to advocate for all Ethiopians. Some of those on the board agreed and some did not, but later the decision was approved by all members.
2. The second impactful event on this journey occurred on June 11, 2005 following the flawed 2005 national election. This was the day the first report came out documenting the first killings of protestors by Ethiopian security forces. That day, nine Ethiopians from the mainstream had been killed as they were peacefully demonstrating on the streets of Addis Ababa. By that same afternoon, a rally to condemn the killings had been called by Ethiopians, which took place in front of the Whitehouse. Because I was in Washington DC at the time, I attended the rally. Even before the event started, nearly a thousand people had gathered. Many more people continued to join them as time progressed. There were slogans, the reading of poems, and loud speakers amplifying phone conversations with family members of victims in Ethiopia so all in the audience could hear.

የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

May 29, 2014
(ነገረ-ኢትዮጵያ) – የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡Ethiopia's Semayawi (Blue) party logo
ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

የኢህአዴግ የዝምታ ፍራቻ (Sedate-phobia) እና ስርወ-ምክንያቱ

May 26, 2014
ዳጉ ኢትዮጵያ (Dagu4ethiopia@gmail.com)
እመኑኝ ወዳጆቼ፣ ኢህአዴግ የዝምታ ፍራቻ በሽታ (በሙያዊ አጠራሩ ሴዳትፎቢያ – Sedate-phobia) ይዞታል! ዝምታ ሲሰፍን፣ ፀጥታ ሲረብ፣ እርጋታ ሲነግስ ይጨንቀዋል፡፡ ለዚህ ነው ያለማቋረጥ፣ ያለአንዳች ዕረፍት ግርግር የሚፈጥረው፡፡ ይህ የሥርዓቱ በሽታ ሥር የሰደደ ቢሆንም የለየለት ደግሞ ከምርጫ 1997 ማግስት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህም አንዱን የቴሌቪዥን ጣቢያ በ14 ቻናል ከፍሎ 14 ስም እየሰጠ ያንኑ ጩኸት የሚጮኸው፡፡ ስሙን ኢቴቪ፣ አማራ ቲቪ፣ ትግራይ ቲቪ፣ ኦሮሚያ ቲቪ፣ ፋና፣ ዛሚ ወዘተ ብሎ ቢለያየውም ጩኸቱ ግን አንድ ነው፡፡ ዜማው፣ ቅኝቱ፣ ቀለሙ ልዩነት የለውም፡፡ ዋናው ፀጥታውን መስበሩ፣ እርጋታውን መግሰሱ ነው፡፡ሳስበው ሳስበው ኢህአዴግ ታሟል!
ለጩኸቱ ብዙ ብዙ ሰበብ ይፈልግለታል፡፡ ሚሊየነም፣ ህዳሴ፣ የብሔር ብሔረሰብ ቀን፣ የአባይ ግድብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት… ሌላም ሌላም፡፡ ዋናው ፀጥታው ይሰበር… ዝምታው በኳኳታ ይሸፈን… የቀረው ዕዳው ገብስ ነው፡፡
ይህ የዝምታ ፍራቻው ገፍቶ ገፍቶ ከመሠረታዊ ዕምነቶቹ ሳይቀር አቃቅሮታል፡፡ ባንዲራን “ጨርቅ ነው” ብሎ ያጣጣለ ፓርቲ የባንዲራ ቀንን ለምን ሊያከብር የተነሳ ይመስልሃል? ድንገት የባንዲራ ክብር ተገልጦለት? አይደለም ወዳጄ፡፡ ዝምታውን እስከ ገፈፈለት ድረስ ርዕሠ-ጉዳዩ ለኢሕአዴግ ሁለተኛ ነው፡፡ ዋናው ጩኸት ይፍጠርለት፣ አታሞ ያስደልቅለት፣ ቸበር ቻቻ ያንግስለት፣ ኳኳታ፣ ግርግሩን ያድምቅለት፡፡
መሪዎቹ ይሰበሰባሉ፡፡ አጀንዳ – “ቀጣዩ ጩኸት በምን ሠበብ ይሁን?” የብሔር ብሔረሠብ በዓል ግርግሩ ሳይበርድ የአባይ ግድቡ ይለጥቃል፡፡ የኢኮኖሚ እድገቱ ዳንኪራ ጋብ ሳይል የግንቦት ሃያው አስረሽ ምቺው ይጀመራል፡፡ ዕድሜ ግንቦት 20 ለተቆጣጠራቸው የፕሮፖጋንዳ አውታሮች፡፡ ዕድሜ የተሰጣቸውን ርዕስ ሳያላምጡ ውጠው አስረሽ ምቺውን ለሚያስተናብሩ ካድሬዎቹ፡፡ ዕድሜ የአበሉንና የኮሚሽኑን አወፋፈር እንጂ ይዘቱን መረዳት ለማይችሉ “ልማታዊ አርቲስቶች”፡፡ ሙዚቃው ይሞዘቃል፣ መነባንቡ ይነበነባል፣ ግጥሙ ይተረተራል…ጩኸት፣ ግርግር፣ ሁካታ ይሆናል፡፡ ያኔ ኢህአዲግም ለጸጥታ ፍራቻ በሽታው ማስታገሻ አገኘ ማለት ነው፡፡ በጩኸቱ ውስጥ ሆኖ ጩኸቱን ስለማስቀጠል መጨነቁ እንዳለ ሆኖ (ልክ እንደ ሌጋሲው)፡፡
አመክኒዮው ግልጽ ነው- ዕሳት በሌለበት ጭስ አይኖርም፡፡ ስለዚህ – “መቼም ይህ ሁሉ ጩኸት አንዳች ነገር ቢኖር ነው” የሚል ስዕል መፍጠር፡፡ “መቼም ይህ ሁሉ ዳንኪራ በባዶ ሜዳ አይሆን? – እኔ ያልታየኝ አንድ የሚያስጮህ፣ የሚያስፈነጥዝ ነገር ቢኖር ይሆናል እንጂ?” የሚል ጥርጣሬን በዜጎች አዕምሮ ማኖር፡፡ “ሌላው እየጮኸ እኔ ዝም ብል ምን ይባላል? ቀበሌ ስኳር ብከለከልስ? ግብር ቢጨምሩብኝስ? ከቀበሌ ቤቴ ቢያፈናቅሉኝስ?” ወዘተ የሚል ስጋት በዜጎች ልብ አኑሮ ጩኸቱን እንዲቀላቀሉ በዕጅ አዙር ማስገደድ፡፡ “አበል እስከተከፈለኝ፣ ብድር እስከተሰጠኝ… አብሬ ብጮህ ምን አገባኝ” ማሰኘት፡፡
ለዚህ ነው ጩኸቱ ዜማ የሚጎድለው፡፡ ሺዎች ተሰብስበው አዳራሹ ግን ባዶ የሚሆነው፡፡ ዜናው እየተተረተረ መረጃው ዜሮ የሚሆነው፡፡ ፕሮፖጋንዳው እየዘነበ ቅቡልነት ኢምንት የሚሆነው፡፡ ለዚህ ነው በየወንዙ መማማል… በየስብሰባው መገዘት ልማድ የሆነው፡፡ ግጥሙ ባዶ የቃላት ኳኳታ የሚሆንብህ፣ ዘፈኑ ባዶ ቀረርቶ የሚሆንብህ፡፡ ከስብሰባው፣ ኮንፍረንሱ፣ ሲምፖዚየሙ… ስትወጣ “ምን አገኝህ?” ብትባል ምን እንደምትል ግራ የሚገባህ – ለዚህ ነው፡፡ ግማሽ ሰዓት ዜና አዳምጠህ፣ አንድ ሰዓት ዶክመንተሪ ተከታትለህ፣ ሙሉ ቀን አውደ ጥናት ተካፍለህ አንዳች አዲስ ነገር የማትጨምረው ለዚህ ነው፡፡
ይብላኝ በዚህ ግዜ ለጠያቂ ነፍስ! ከዲሞክራሲው ግርግር ማዶ፣ ከዕድገቱ ጩኸት ባሻገር፣ ከፍትሕ ዜማው እልፍ ብሎ፣ ከዕኩልነቱ ኦርኬስትራ ጀርባ አሻግሮ የዲሞክራሲውን ቋት፣ የዕድገቱን ሌማት፣ የፍትሑን መንበር፣ የዕኩልነቱን መድረክ ባዶነት ላየ የጩኸቱን ከንቱነት መረዳቱ ቀላል ነው፡፡
ይብላኝ ያን ጊዜ ለራሱ ለኢህአዴግ፡፡ የአበሉ ሙቀት የበረደ ጊዜ፣ የፍርሐቱ ቆፈን የተገፈፈ ጊዜ፣ “የልማታዊ አርቲስቱ” ዜማ ዕጅ ዕጅ ያለ ጊዜ፣ ዜጎች ከቲሸርት ነፃነት፣ ከአበል እውነት ብለው የተነሱ ጊዜ፡፡
ፀጥታው ሲሰፍን የእውነት ድምጽ መሠማት ይጀምራል፡፡ ለራሱ ለኢህአዴግም፡፡ ያኔ የፀጥታ ፍራቻው ለዕውነት ፍራቻው ስፍራ ይለቃል፡፡

በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል

May 27, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እ.ኤ.አ ሜይ 2/2014 ቢቢሲ/BBC እንደዘገበው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል የጸጥታ ኃይሎች ከመናገሻ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ቢያንስ 47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ረሽነዋል፡፡ ስብዕናው በውሸት እና በሀሰት ውንጀላ የበከተው ገዥ አካል ይህንን እልቂት እንደተለመደው ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች በቆሰቆሱት እና በአስተባበሩት አመጽ“ ምክንያት የሚል የሀሰት ፍረጃ በመስጠት በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ቁጥር ለማሳነስ ጥረት አድርጓል፡፡ ይህ በወጣት ተማሪዎች እና ህጻናት ላይ የተፈጸመው የማንአለብኝነት የእብደት አሰቃቂ እልቂት በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘንድ ሰፊ ሽፋን አልተሰጠውም፡፡Crimes Against University Students and Humanity in Ethiopia
ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጅማ እና በሌሎች ከተሞች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ንጹሀን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ እና ድብደባ ይቁም“ የሚል መግለጫ በማውጣት እኩይ ድርጊቱን አውግዟል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በኦሮሚያ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ህብረተሰብ አቀፍ ገጠራማ እና ከተማ ቀመስ አካባቢዎችን ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የወሰን ክልል የሚያካትተው እና የኦሮሞ አርሶ አደሮችን እንዲሁም ሌሎች ኗሪዎችን የሚያፈናቅለው የአዲስ አበባ የተቀናጀ መሪ የልማት ዕቅድ ሀሳብ ተዘጋጅቶ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተማሪዎች የተቃውሞ አመጽ ገነፈለ“ ብሏል፡፡ በማስከተልም ሂዩማን ራይትስ ዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ተማሪዎች ላይ የገዥው አካል የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ያሉትን የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠይቋል፡፡
በዚህ መረን በለቀቀ ዕኩይ ድርጊት የተሰማኝን ሀዘን በቃላት ለመግለጽ ተስኖኛል ምክንያቱም ልብን ሰብሮ የሚገባው ይህ የአሰቃቂ እልቂት ሀዘን ልሸከመው ከምችለው ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛልና፡፡ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት እና የነገይቱ ኢትዮጵያ ተረካቢ የሆኑት እምቦቀቅላ ተማሪዎች ገና በወጣትነት ለጋ እድሚያቸው ኃላፊነት በማይሰማው መንግስት ነኝ ባይ የወሮበላ ቡድን ስብስብ በጥይት ውርጅብኝ በመጨፍጨፋቸው ታላቅ ሀዘን ተሰምቶኛል፣ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስሜቴን እየቆጠቆጠኝ ይገኛል፡፡ ተማሪዎቹ የሚሰማቸውን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ህገመንግስታዊ ያልተገደበ መብት ነበራቸው፡፡ ያንን መብት በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ምክንያት ብቻ የጥይት በረዶ ተርከፍክፎባቸዋል፡፡ እናም ሁላችንም ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ ኃላፊነት በጎደለው ገዥ አካል በተፈጸመው እልቂት ምክንያት የምርጥ እና የባለብሩህ አእምሮ ባለቤት የነበሩትን ወጣቶች ኢትዮጵያ በማጣቷ አጅግ በጣም ለኢትዮጵያ አዝናለሁ፡፡ የእልቂቱ ሰለባ ለሆኑት ወጣቶች ወላጆች እና ጓደኞች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ መጽናናትን እንዲሰጣቸውም ለኃያሉ አምላክ ጸሎቴን አደርሳለሁ፡፡
በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸምን እልቂት አጥብቄ አወግዛሉ፡፡ እ.ኤ.አ የሜይ 2005 የኢትዮጵያን ድህረ ምርጫ ውዝግብ ተከትሎ ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ተቃውሟቸውን በአደባባይ ለመግለጽ በወጡ ንጹሀን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ኃላፊነት የጎደለው እልቂት ምክንያት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንድሆን ተገድጃለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ በፊት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወት ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አልነበረኝም፡፡ መለስ ዜናዊ የሚለውን ስም “እገሌ ወይስ እገሌ” ከሚባል ሰው ለየቼ አላውቀዉም ነበር፡፡ ከድህረ ምርጫው ውዝግብ ጋር በተያያዘ መልኩ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ንጹሀን ዜጎች ላይ በሟቹ በአቶ መለስ ዜናዊ ቁጥጥር እና ልዩ ትዕዛዝ ከአንድ አካባቢ ተሰባስበው በመጡ አግዓዚ እየተባሉ በሚጠሩ ደም የጠማቸው ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች አነጣጥሮ ተኳሽነት 200 የሚሆኑ ወገኖቻችን ሲገደሉ 800 (ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚሆን በማስረጃ ተረጋግጧል) የሚሆኑት ደግሞ የከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሰለባ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚያ እኩይ ምግባር እንደ ሰማሁ አሳብዶኝ ነበር፡፡ መለስ እና በወንጀል የተዘፈቁት ግብረ አበሮቹ እንደዚያ ዓይነት አሰቃቂ ወንጀል ፈጽመው ለህግ ሳይቀርቡ እና ከፍርድ አንዳያመልጡ ጥረቴን ጀመርኩ፡፡ እነሆ ላለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እና የዴሞክራሲ አስተሳሰቦች እንዲጎለብቱ በማሰብ ለአንድም ሳምንት ሳይስተጓጎል የሰኞ ዕለት ትችት/Monday Commentary በሚል ርዕስ በተከታታይ እያዘጋጀሁ በማሰራጨት ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመሞገት እና የሰብአዊ መብት ትምህርቶች እንዲስፋፉ ጥረት በማድረግ ላይ እገኛለሁ፡፡
እ.ኤ.አ በሜይ 2005 በወቅቱ የገዥው አካል ቁንጮ በነበረው በአቶ መለስ ልዩ ትዕዛዝ ከሁለት መቶ በላይ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሲገደሉ እንደ እብድ እንደዘለልኩት ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ በአምቦ እና በሌሎች አካባቢዎችም በደርዘኖች የሚቆጠሩ ያልታጠቁ ሰላማዊ የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በግፍ በዘፈቀደ እንደ ዋዛ ሲጭፈጨፉ ስሰማ እንደ እብድ በመሆን ዘልያለሁ፡፡ ይህ ድርጊት በእውነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ህዝቦች ሊፈጸም የማይችል እና ለመናገር የሚዘገንን አሳፋሪ እና ዕኩይ ድርጊት ነው፡፡ አሁንም እንደ እብድ ሆኘ እንድዘል የሚያደርገኝ ሌላው ነገር የዱር አራዊት መብት እንኳ ተከብሮ በዘፈቀደ በአንድ ሰው ወይም ቡድን ፍላጎት ምንክያት ብቻ በማይገደሉበት ወቅት በኢትዮጵያ ሰላማዊ ዜጎችን፣ የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በህዝብ ገንዘብ በሚገዛ ጥይት እና ክላስተር ቦምብ እንደ ቅጠል እያረገፉ እነዚህን በህዝብ ደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች ለህግ ቀርበው ተጠያቂ የሚያደርግ ነባራዊ ሁኔታ ባለመፈጠሩ ማንም በተዘፈቀበት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆን በአዲስ አበባ እና በሌሎች መንገዶች ላይ ደረታቸውን ነፍተው እየተጎማለሉ የአገሪቱን ሀብት በብቸኝነት በመያዝ በመዝረፍ ላይ የመገኘታቸው ሁኔታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በህግ ተጠያቂ ያለመሆን ለረዥም ጊዜየቆየ አሳፋሪ የባህል ችግር አለ፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በህዝብ ላይ እልቂትን ፈጽመዋል ሆኖም ግን በሰራው የግፍ ወንጀል እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ተጠያቂ አልሆነም፡፡ እኒያ የብዙህን እልቂት ፈጻሚ እና አስፈጻሚ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ እንዲሉ በስልጣን ወንበራቸው ላይ በነበረበት ወቅት በሃፍረትቢስ አንደበቱ “ትንኝ እንኳ አልገደልኩም” በማለት ተሳልቆ ነበር፡፡ በተጨባጭ ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን ገድሏል፣ እንዲገደሉም አድርግዋል፡፡ ስለሆነም በእድሜው የመጨረሻዎቹ ዓመታት ዝምባብዌ በምቾት ተቀምጦ የልብ ወለድ ድርሰት እና በስልጣን ዘመኑ አድርጊያቸዋለሁ የሚ ለውን የተረት ገድሎች ትረካ በመጻፍ ላይ ይገኛል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በእብሪት ተሞልቶ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል እና ሲያስገድል የተከበሩ ሰዎችን ሲዘልፉ እና ሲያዋርድ ቆይቶ በታላቁ አምላክ ፈቃድ ፍትህ ተበይኖበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቀሩት ደቀመዝሙሮቻቸው እና የምግባር ጓደኞቻቸው በፍትህ ላይ አፍንጫቸውን ነፍተዋል፡፡
እ.ኤ.አ. የ2005 ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት ሰላማዊ እና ንጹሀን ዜጎችን በአደባባይ ግንባር ግንባራቸውን እና ደረታቸውን በጥይት እየሰነጠቁ ይረኩ የነበሩት ወሮበላ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ ያለምንም ተጠያቂነት በአዲስ አበባ መንገዶች ደረታውን ነፍተው ሲንገዋለሉ ይውላሉ፡፡ በአንድ ወቅት ፍትህ በዓለማዊ ወይም በሰማያዊ ኃይል የማትመጣ መስሏቸው ልባቸው ደንድኗል፡፡ በዚያ እልቂት ላይ መሪ ተዋንያን የነበሩትን ወሮበላ “የፌዴራል ፖሊስ” እና አግዓዚ እየተባሉ የሚጠሩትን መንደርተኛ አነጣጥሮ ተኳሾችን ስም ዝርዘር ከነመልካቸው አንድ በአንድ እናውቃለን፡፡ “የኢትዮጵያን የውስጥ ደህንነት ጉዳይ ዘመናዊ ማድረግ” በሚል ርዕስ የእንግሊዝ ጦር የጸረ ሽብር ባለሙያ የሆኑት ኮ/ል ሚካኤል ዴዋር ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወርቅነህ ገበየሁ የነገሯቸውን በመጥቀስ እንዲህ በማለት ገልጸዋል፣ “እ.ኤ.አ የ2005 ድህረ ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ 237 የፖሊስ አባላትን በቀጥታ ከስራ አባረናል“ ተባለ፡፡ ድንቄም ማባረር! ከእነዚህ ወንጀሉን ፈጽመው በወንጀል ተዘፍቀው ከሚገኙት ወይም ደግሞ ከወንጀለኞቹ አለቆች አንዳቸውም ቢሆኑ እስከ አሁን ድረስ የፍትህ በሯን የረገጠ ማንም የለም፡፡ የሰውን ልጅ ያህል ክቡር ፍጡር ህይወት በቀን ብርሀን እና በይፋ በአደባባይ በጥይት እየቀጠፉ ላሉ የአዕምሮ በሽተኛ ወንጀለኞች ከስራ አባረርናቸው ብሎ ከመናገር የበለጠ መሳለቅ ያለ አይመስለኝም፡፡
እ.ኤ.አ ከ2005 ምርጫ ጋር ተያይዞ የተፈጸመውን እልቂት አጣርቶ ዘገባ እዲያቀርብ በአቶ መለስ ትዕዛዝ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን እ.ኤ.አ በ2007 ባቀረበው ዘገባ መሰረት ፖሊስ ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀሙን፣ በሰላማዊ መንገድ ምንም ዓይነት ትጥቅ ሳይዙ ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ በወጡ ንጹሀን ዜጎች ላይ ግድያ የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ ለተቃውሞ የወጡ ዜጎች ምንም ዓይነት ጥፋት የሌለባቸው መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡
እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2003 የአቶ መለስ ጦር የጋምቤላ ከተማን በመውረር ተከታታይ ጥቃቶችን በማድረግ 400 የአኙዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን የገደለ ሲሆን 1000 ቤቶች ደግሞ እንዲወድሙ ተደርጓ፤፡፡ የአቶ መለስ አገዛዝ በቀጣይ በድርጊቱ ላይ በግንባርቀደምትነት ተሳታፊ እንዳልነበረ እና ከሰለባዎቹ ጎን የቆመ ለማስመሰል እንዲሁም ፍትህ የሚሰጥ በማስመሰል ይቅርታ አዘል መግለጫ ቶ ነበር:: በዚያን ጊዜ ገዥው አካል በደርዘኖች የሚቆጠሩ የአኙዋክ ተጠርጣሪዎች እንደሚያዙ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እስከ አሁን ድረስ አንድም ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ደግሞ የደህንነት ባለስልጣን ለፍርድ አልቀረበም፣ እናም ተጠያቂ አልተደረገም ወይም ደግሞ በጋምቤላ በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙት ወንጀሎች በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች የሉም፡፡
እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 2007 መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ አቶ መለስ ዜናዊ በኦጋዴን አካባቢ የሚንቀሳቀሱትን ሽምቅ ተዋጊዎች ለመደምሰስ በሚል ሀሳብ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ ከከፈተ በኋላ ወዲያውኑ የጥቃት አድማሱን በማስፋት የኦጋዴንን ሰላማዊ ህዝብ የጥቃቱ ሰለባ የሚያደርግ ጥቅል የጥቃት ፕሮግራም በመንደፍ ዘመቻውን አጠናክረው ቀጠለበት፡፡ የአቶ መለስ ጦር በጠቅላላ ያገኛቸውን መንደሮች ሁሉ ደመሰሰ፣ አስገድዶ የመድፈር እና የንብረት ዘረፋ ወንጀሎቸን መፈጸም ጀመረ፡፡ ህዝቡን ለማስፈራራት እና ለሌሎች መቀጣጫ ይሆናል በሚል የደንቆሮ አስተሳሰብ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን እየያዙ በአደባባይ መስቀል እና ጭንቅላታቸውን ቆርጠው ለህዝብ እይታ ማቅረብ እንደብልሀት ወሰዱት፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘጋቢ ለዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ እና ለዓለም ጤና ድርጅት እንደጠቆመው “ኦጋዴን ዳርፉር ሱዳን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኦጋዴን እየተደረገ ያለው ሁኔታ ሲታይ ከዳርፉር ጋር በሚመሳስል የዘር ማጥፋት መልኩ በአስፈሪ ሁኔታ ከዳርፉር ባልተለየ መልኩ ተከታታይ ድርጊቶች እየተፈጸሙ በመምጣት ላይ ናቸው“ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በጡረታ ላይ የሚገኙት ጀኔራል እና የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው የመንግስት ቃል አቀባይ የነበሩት ኮሊን ፓውል በዳርፉር የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ነው በማለት አውጀው ነበር፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እ.ኤ.አ ከ2007 -08 በአጋዴን “መጠኑ አነስ ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ተፈጽሟል፡፡ በኦጋዴን ለተፈጸመው እልቂት ማንም ለፍትህ አካል የቀረበ ወንጀለኛ የለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የእልቂት ተግባራት ዝርዝር እጅግ በጣም ግዙፍ ነው፡፡
በአምቦ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም በሌሎች ተቋማት እና ከተሞች የተፈጸሙትን አሰቃቂ እልቂቶች በተግባር ላይ ያዋሉትን እና መሪ ተዋንያን የነበሩትን ግፈኛ ወንጀለኞች በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያላው ገዥ አካል ለህግ ያቀርባቸዋል የሚል ሀሳብ የለኝም፡፡ እነዚህን ወንጀለኞች ለህግ አለማቅረብ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም አሁን በህይወት የሌለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ለታዕያታ ያህል ለማስመሰል ያደረገዉን የይስሙላ የማጣራት ምርመራ እንኳ አያስደርግም፡፡ የህዝቡ ጫና እያየለ ከመጣ እና የሚገደድ ከሆነ ገዥው አካል ሊያደርግ የሚችለው በአሻንጉሊቱ የፖሊስ ምርመራ ለታዕይታ የዝንጀሮ ምርመራ እንዲደረግ ማድረግ ነው፡፡ በእርግጥ ይህም ሊደረግ የሚችለው ለማስመሰያነት እንጅ ከልብ ታምኖበት በወንጀለኞች ላይ ፍትህ የሚያስገኝ የዳኝነት ስራ እንዲሰራ ታስቦ አይደለም፡፡ የዚያ የዝንጀሮ የምርመራ ውጤት የመጨረሻ ዘገባ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች የቆሰቆሱት እና ያስተባበሩት ብጥብጥ” በማለት ማጠቃለያውን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በአገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ አመራሮች እና በውጭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በአምቦ እና በሌሎች አካባቢዎች በገዥው አካል ታጣቂ ኃይሎች የተፈጸሙትን ግድያዎች በአስቸኳይ የሚያጣራ ገለልተኛ የሆነ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ተጨባጭነት ያለው ዘገባ እንዲያቀርብ እና የንጹሀን ዜጎች ደም በከንቱ ፈስሶ እንዳይቀር በአንድ ድምጽ መጠየቅ አለባቸው፡፡ ከሞራል ውግዘት ባሻገር ከፍ ብለን በመሄድ ጉዳዩ በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት እና በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎቶች አደባባይ ላይ እንዲቀርብ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የእልቂት ወንጀሉን በኢትዮጵያ ላለው ለገዥው አካል የዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት በማቅረብ በዓለም አቀፍ ሀብረተሰብ ዘንድ እንዲጋለጥ ማድረግ አለብን፡፡ በለጋሽ መንግስታት በዓለም አቀፍ አካላት እና በፖለቲካ ተቋማት የሚገኙትን መፍትሄዎች የመጠቀም ብልጠት የተሞለባት አካሄድን መምረጥ ይኖርብናል፡፡
በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በሌሎች ሰላማዊ ተቃውሞ ባካሄዱ የነቀምት፣ የጅማ እና የሌሎች አካባቢዎች ዜጎች ላይ የተፈጸመውን እልቂት የሚያጣራ ገለልተኛ ተቋም በማቋቋም ስራው በአስቸኳይ እንዲጀመር በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል እጠይቃለሁ፡፡ ገዥው አካል የማ ቀረበውን ሀሳብም ሆነ ምክር ይቀበላል የሚል እምነትም ሆነ የተስፋ ጭላንጭል ኖሮኝ አይደለም፡፡ ለእያንዳንዷ ለወረወርኳት ምክር ሁሉ ቅንጣትም ያህል ትኩረት እንደማይሰጡ አውቃለሁ፡፡ ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል መቋቋም አለበት የምልበት የእራሴ ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ይኸውም እንደ መርህ ይዘው (የአንድ ሰው መሞት አሳዘኝ ድርጊት ነው፣ የብዙ ሰዎች መሞት ግን የቁጥር ጉዳይ ነው) በማለት በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተንፈራጥጦ በመቀመጥ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የሆኑትን ምርጥ ዜጎች እየጨፈጨፈ እየተመለከቱ በየዓመቱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚለግሱትን የኦባማን አስተዳደር፣ የእንግሊዙን የዲቪድ ካሜሩን መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ የዓለም ባንክን፣ የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት እና ሌሎችን (ከቻይና በስተቀር) ያሉትን አንድ በአንድ ስም በመጥራት (ሀፍረተ ቢሶችን) ለማሳፈር ፈልጌ ነው፡፡ በአሜሪካ፣ እግሊዝ እና አውሮፓ ከሚኖሩ ግብር ከፋዮች ኪስ እየተሰበሰበ በሚመጣ ገንዘብ በኢትዮጵያ ለሚገኙት ወጣቶች መግደያ ጥይት መግዣ እየዋለ እንደሆነ እንዲያውቁት ለማስገንዘብ በማሰብ አምባገነኑን ገዥ አካል ከመርዳት እንዲቆጠቡ ለማድረግ ከንቱ ጥሪ ለማቅረብ ነው፡፡ ይህንን ጥሪ የማቀርብበት ዋናው ምክንያት እንደዚህ ያለ አሰቃቂ ድርጊት በትምህርት ቤት ልጆች እና በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ የምዕራቡ ዓለም በጠባ በነጋ ቁጥር በልጆች ላይ የሚፈጸም ሰብአዊ ወንጀል እና ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደረግ የሰብአዊ መብት ጥሰት በማስመልከት ጧት ማታ የሚያላዝኑለትን የይስሙላ ጩኸት በመጠቆም ትኩረት እንዲያገኝ ለማስቻል ነው፡፡
በአምቦ የትምህርት ቤት ልጆች እና በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በፖሊስ እና በደህንነት ኃላፊዎች የተፈጸመውን እልቂት እንዲሁም ይህንን እርኩስ ተግባር እንዲፈጽሙ ያዘዟቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች ወደ ፍትህ አደባባይ ለማምጣት እንዲቻል ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል እንዲሰየም ለማድረግ የገንዘብ ጡንቻው እና የመጠየቅ አቅሙም ያላቸው የምዕራቡ ዓለም ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ብቻ ናቸው፡፡ ለገዥው አካል ገንዘብ የሚለግሱት የምዕራብ ገንዘብ ለጋሽ ድርጅቶች ኃላፊነት በማይሰማው የወሮበላ ቡድን ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻችን ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጥረት ያደርጋሉ የሚል ሀሳብ እንደማይኖረኝ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ልጆች ደንታ የላቸውምና፡፡ ይኸኔ እንኳን ይህን ያህል ብዛት ያለው ሰላማዊ ዜጋ ይገደል ይቅርና አንድ ዜጋ እንኳን በዚህ አይነት አሳፋሪ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መብቱን በመጠየቁ ብቻ በእነርሱ አገር ቢሞት ኖሮ ዓለምን ሁሉ ያናውጡት ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ግን አሁንም ቢሆን ጥሪየን ከማቅረብ ወደ ኋላ አላፈገፍግም!!!
አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም በማቀርበው ጥያቄ የኦባማን አስተዳደር፣ የካሜሮንን መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ የዓለም ባንክን እና የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት ከስሻቸዋለሁ፣ ምክንያቱም በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመውን የየእለት ወንጀል እየተመለከቱ ለገዥው አካል እርዳታ መለገሱን ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለውበታል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የሚፈጽሙ ወንጀለኞችን የሚረዱ ሁሉ እነርሱም ጥፋተኛ ተብለው ወንጀሉን እንደፈጸሙት ወንጀለኞች ይፈረጃሉ የሚለውን ህጋቸውን በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ጆርጅ ቡሽ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ይህንን የወንጀል ድርጊት በፈጸሙት አሸባሪዎች እና ለእነዚህ አሸባሪዎች ከለላ በሚሰጡት አካላት መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለውም”፡፡ አኛም ገዳዮችንና የገዳዮቺን ደጋፊዎች አንለይም::
አንድ የግል የሆነ ነገር ግልጥ ላድርግ ላንብያብዬ፡፡ ምናልባትም በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ልጆች እንዲሁም በሌሎች ዜጎች ላይ በተፈጸመው እልቂት ለምን እንደ እብድ እዳደርገኝ ላብራራ፡፡ ለኔ የአምቦ እልቂቶች ዝም ብሎ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ተብለው የሚታዩ ጉዳዮች ብቻ አይደሉም፡፡ እነዚህ እልቂቶች ለኔ ልዩ ናቸው፡፡ ነገሮችን እንደማስበው በተለየ ጊዜ በተለየ ቦታ ሆኖ ነው እንጂ የተጨፈጨፉት ተማሪዎች የእኔን ተማሪዎች ሊሆኑ ይችል ነበር፡፡ በእኔ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ወይንም ደግሞ በእኔ ከፍ ወዳለው ልዩ የሆነው የሴሚናር ክፍል ውስጥ ገብተው ተቀምጠው ሊማሩ ይችል ነበር፡፡ እያንዳንዳቸውን በስም ለይቸ ላውቃቸው እችል ነበር፡፡ ያዘጋጇቸውን የጽሁፍ ስራዎች ገምግሜ የስራ ውጤት መለያ የሆነውን ዋጋ እና ፈተናቸውንም አርሜ ማግኘት የሚገባቸውን ውጤት ልሰጣቸው እችል ነበር፡፡ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ አስቁሚያቸው እና ለምንድን ነው በትምህርት ሰዓት ሳትገኙ የቀራችሁ እና የትምህርት ጊዜ ያባከናችሁ ብዬ ጠይቂያቸው ይቅርታ ለመጠየቅ ያደርጉ የነበረውን ስሜታዊነት የተሞላበት ሂደት እየተመለከትኩ እስቅም ነበር፡፡ በትምህርታቸው ብልጫ እንዲያሳዩ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ተጽእኖ አሳድር ነበር፡፡ የእኔ ተመካርዎቺም ሊሆኑ ይችሉ ነበር፡፡ በህግ ሙያ ለማሰልጠን እና ሙያቸውን በዚያው መስክ ወይም ደግሞ በህዝብ አስተዳደር ፖሊሲ ማድረግ እንዲችሉ ክትትል አድርግላቸውም ነበር፡፡ የምስክር ደብዳቤዎችንም ለትምርት ቤት ለሰራ መፈለጊያ እፅፍላቸው ነበር፡፡ ከዚህም በላይ በጣም ለየት ያለ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች በዓለም ላይ በጣም የተሻሉ እና ምርጥ የተባሉ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የሚያካሂዱ ዩኒቨርስቲዎችን እንዲቀላቀሉ ድጋፍ አድርግላቸው ነበር፡፡ የእኔ ተማሪዎች እኮ ሊሆኑ ይችሉ ነበር!!!
እነዚህን በግፈኛው ስርዓት የተጨፈጨፉት ተማሪዎች የእኔ ተማሪዎች ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በጣም የምኮራባቸው ይሆን ነበር፡፡ በተመስጦ እና በጥንቃቄ እንዲያስቡ ተጽእኖ አደርግባቸው ነበር፡፡ ከሳጥኑ ውጭ እንዲያስቡ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የእራሳቸውን የሀሳብ ሳጥን መፍጠር እንዲችሉ አደርግ ነበር፡፡ ቀኖናዊ እና ሊገሩ የማይችሉ አስተሳሰቦቸን እንዲተው እና ሁልጊዜ ግትር የሆኑ ደንቃራ አስተሳሰቦችን ተጠራጣሪ እንዲሆኑ አስተምራቸው ነበር፡፡ ግልጽ እና በእራሳቸው የሚተማመኑ ዜጎች ሆነው እንዲወጡ እና በመላምት እና ባልተጨበጠ ነገር ላይ መሰረት አድረገው ከመወሰን ይልቅ በተጨባጭ መረጃ ላይ መሰረት አድርገው መወሰን እንዲችሉ አስተምራቸው ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአመኑበት ዓላማ ያለምንም ማወላወል በጽናት እንዲቆሙ እና በምንም ዓይነት መልኩ ለአምባገነኖች የማይበገሩ እውነትን ከመናገር ለአንዲት ሰከንድ እንኳ ወደ ኋላ የማይሉ ጠንካሮች እንዲሆኑ አስተምራቸው ነበር፡፡ የእነርሱ መምህርና አለማማጅ መሆን ምን ያህል የሚያኮራኝ ይሆን ነበር!
የኢትዮጵያ ወጣቶች የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተረካቢዎች መሆናቸውን እንደማመኔ ሁሉ የአሜሪካ ወጣቶችም የወደፊቷ አሜሪካ አገር ተረካቢ አለኝታዎች ናቸው፡፡ የአሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች የማህበራዊ እና የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት በጦር ዛቢያ ላይ ያሉ የጦር ጫፍ ብረቶች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ እንደዚሁ ናቸው፡፡ በበርክለይ ከንግግር ነጻነት ንቅናቄ ጀምሮ እስከ 1960ዎቹ ጸረ ጦርነት ንቅናቄ ድረስ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በማህበራዊ እና የፖለቲካ ለውጦች እንቅስቃሴ ላይ የማይበገሩ ጠንካሮች ሆነው ዘልቀዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ተማሪዎችም ከዘውዳዊው አገዛዝ ጀምረው የማይበገሩ የማህበራዊ እና የለውጥ አራማጆች ሆነው ቀጥለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ሜይ 7/1970 በኦሃዮ ግዛት የኦሃዮ ብሄራዊ የጥበቃ አባላት በኬንት ስቴት ዩኒቨርስቲ ባልታጠቁ የኮሌጅ ተማሪዎቸ ላይ ተኩስ በመክፈት ለ13 ሰከንዶች ያህል 67 ዙር የፈጀ ተኩስ ባደረጉ ጊዜ በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ግቢዎች ነገሮቸ ሁሉ ከመቅጽበት መለዋወጥ ጀመሩ፡፡ እነዚያ ተማሪዎች ፕሬዚዳንት ኒክሰን ከቬትናም ወደ ካምፖዲያ የሚያካሂዱትን የመስፋፋት ፖሊሲ ጦርነት በመቃወም አመጹ፡፡ የኬንት ስቴት ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች እልቂት በአሜሪካ ታሪክ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሳተፉበት ተቃውሞ በመሆን የትምህርት ተቋማት በሙሉ የተዘጉበት ብቸኛው እና የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የኬንት ስቴት የተማሪዎች እልቂት የግመሏን ጀርባ የየሰበረ ገለባ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1973 አሜሪካ የታጠቀ ጦሯን ከቬትናም ማስወጣት ስትጀምር የቬትናም ጦርነት በእርግጠኝነት መጠናቀቅ ጀመረ፡፡
ባለፉት 44 ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የኬንት ስቴት ዩኒቨርስቲ ግድያን በሚመለከት ኃላፊነት ለመውሰድ እንቢተኛ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ድርጊት ግን ጀግኖቹን የአሜሪካ አርበኞች መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ የአሜሪካ መንግስት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ፊት ተጠያቂ እንዲሆን ጥረታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ የኬንት ስቴት እልቂት ፈጻሚዎች ወደ ፍትህ አደባባይ በፍጹም አይቀርቡም ሆኖም ግን አሁን እየተደረገ ያለው ጥረት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እምነታቸውን በመግለጸቻው ብቻ የአሜሪካ መንግስት የታጠቀ የጦር ኃይሉን ወይም ሰው አልባ አጥቂ አውሮፕላኖቹን (ድሮኖችን) በመጠቀም ሰላማዊ ህዝብ መግደል ወይም ደግሞ ሰላማዊ የህዝብ ተቃውሞን መደፍጠጥ እንደማይችል ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል፡፡፡
የአምቦ ዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ቢያንስ እንደ ኬንት ስቴት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሄዱበትን መንገድ በመከተል ተጠያቂነት እንዲኖር ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ በንጹሀን ወገኖቻችን ላይ ጥይት ያርከፈከፉት ህሊናቢስ ጭራቆች በአገር ውስጥ ባሉ ፍድቤቶች እና በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለፍትህ እንዲቀርቡ የተቀነባበረ ትግል ከማድረግ በፍጹም ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን ማቋረጥ አይኖርብንም፡፡ ለተፈጸመው እልቂት አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጥሪ የማቀርበው የገዥውን አካል ዓለም አቀፋዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለማሳፈር ብቻ ብዬ አይደለም ሆኖም ግን ጀምስ ሩሴል ሎዌል እንዳሉት “እውነት ለዘላለም ተቀብራ አትቀርም ወይም አምባገነን ሸፍጠኞች ለዘላለም በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው አይኖሩም “ በሚለው መርህ ላይ ሙሉ እምነት ያለኝ በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡ “የማይታየውን ረቂቅ ድብቅ ነገር በጨለማ ውስጥ መርምሮ የራሱን ውሳኔ የሚሰጥ አምላክ“ እንዳለ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ ማንም ይህን የረከሰውን ምድራዊ ስጋ ተሸክሞ በግፍ ተሞልቶ እና በደም ተጨማልቆ ከህዝብም ሆነ ከአምላክ ተሰውሮ ማምለጥ አይችልም፡፡
በአምቦ ዩኒቨርስቲ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የግፍ እልቂት የፈጸሙት ወሮበላ ጭራቆች ወደ ፍትህ አደባባይ እንዲቀርቡ ድምጻችንን ከፍ አድርገን እናሰማ፣ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡም እንጠይቅ!
በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ኃላፊነት የማይሰማው ወሮበላ አገዛዝ እልቂትን ሲፈጽም ሁሉም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድርጊቱን ለመቃወም አልወጡም፡፡ ብዙዎቹ ጸጥታን መርጠዋል፡፡ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድርጊቱን ለማውገዝ ለተቃውሞ አልወጡም፡፡ ዝም ብለው ተቀምጠው ጊዚያቸውን አሳልፈዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋ እና በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ተማሪዎች ሁሉ ጸጥታን መርጠው አሳልፈዋል፡፡
በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸምን ወንጀል እያየን ዝም ማለት — የእኔ ዝምታ፣ የእናንተ ዝምታ፣ የኦባማ አስተዳደር ዝምታ፣ የዴቪድ ካሜሩን መንግስት ዝምታ፣ የአውሮፓ ህብረት ዝምታ፣ የዓለም ባንክ ዝምታ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዝምታ እና የአፍሪካ ህብረት ዝምታ — የጀርመንን ጸረ ናዚ አቋም ሲያራምዱ የነበሩት የነገረ መለኮት እና የሉተራን ፓስተር የነበሩት ማርቲን ኔሞለር የተባሉት ምሁር ከቀመሩት እንደተማርነው ሁሉ ሁላችንም ከወንጀለኛነት አናመልጥም:፡ ኔሞለር እንዳሉት:-
ናዚዎች ኮሙኒስቶችን ሲያጠቁ ዝም አልኩ፣ ኮሙኒስት አልነበርኩምና፡፡
ሶሻል ዴሞክራቶችን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ሲያጉሯቸው ዝም አልኩ፣
የሶሻል ዴሞክራት አባል አልነበርኩምና፡፡
የሰራተኛ ማህበራትን ሲያጠቁ አንድም ቃል ትንፍሽ አላልኩም፣
የሰራተኛ ማህበራት አባል አልነበርኩምና፡፡
አይሁዶችን ነጥለው ሲያጠቁ እንደተለመደው ጸጥ ብዬ ተመለከትኩ፣
ከአይሁድ ዝርያ አልነበርኩምና፡፡
በመጨረሻ ወደ እኔ መጥተው ጥቃት ሲሰነዝሩብኝ ለእኔ የሚጮህ እና ድምጹን የሚያሰማልኝ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እኔም እንደ ኔሞለር ተመሳሳይ ስሜት ይሰማኛል፡፡
ገዥው አካል በቤንች ማጅ “ከምስራቅ ጎጃም በመጡ አማራዎች” ላይ አገራችሁ አይደለም
ጨርቄ ማቄን ሳትሉ አሁኑኑ ከአካባቢው ለቃችሁ ውጡ የሚል ጥቃት በሰነዘሩ ጊዜ፣
እንዲሁም አማራዎችን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የዘር ማጥራት እኩይ ምግባር ሲፈጸምባቸው
ዝም አልኩ፣
አማራ አልነበርኩምና፡፡
በጋምቤላ የአኙዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን አየነጠሉ ለይተው
እንደ ድሮው የአውሬ ግድያ ባህል እያደኑ ሲገድሏቸው፣ ሲጨፈጭፏቸው እና
በዶዘር እየዛቁ በአንድ ጉድጓድ ሲከምሯቸው እያየሁ ዝም አልኩ፣
አኙዋክ አልነበርኩምና፡፡
በኦጋዴን ህዝብ ላይ ጥላቻን በመፈልፈል በቦምብ ሲያጋዩ እና መንደሮቻቸውን በእሳት ሲያቃጥሉ ዝም አልኩ፣
ኦጋዴናዊ አይደለሁምና፡፡
የኦሞቲክ ህዝቦች ለዘመናት ከኖሩበት ቦታቸው በግድብ ስራ ሰበብ ምክንያት
መብታቸው በግፍ ተጨፍልቆ ሲባረሩ ዝም አልኩ፣
ሙርሲ ሱሪ ያንጋቶም ዲዚ ወይም ሚን አልነበርኩምና፡፡
በአምቦ የኦሮሞ ተማሪዎቸን ሲጨፈጭፉ ዝም አልኩ፣
የኦሮሞ ተማሪ አልነበርኩምና፡፡
በመጨረሻ ወደ እኔ በመምጣት ጥቃት ሲሰነዝሩብኝ
ለእኔ የሚጩህ ወይም ድምጹን የሚያሰማልኝ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
ኦሮሞ ብትሆን፣ ትገሬ ብትሆን፣ አኙዋክ ብትሆን፣ ጉራጌ ብትሆን፣ አማራ ብትሆን፣ ኦጋዴኒያዊ ብትሆን፣ ሙርሲ ብትሆን ለእኔ ጉዳዬ አይደለም… ለእኔ አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ፡፡ ባለህበት ሁኔታ እወድሃለሁ አከብርሀለሁ! በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች መብትህ በሚደፈርበት ጊዜ እና የጉዳቱ ሰለባ በምትሆንበት ጊዜ በፍጹም በፍጹም ዝም አልልም!
በቅርቡ ከባራክ ኦባማ ተለያይቻለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 የእርሳቸው ታማኝ ደጋፊ እንደነበርኩ ሁሉ አሁን በ2014 ደግሞ በአፍሪካ ላይ በሚከተሉት የተሳሳተ ፖሊሲ ምክንያት ታማኝ ትችት አቅራቢያቸው ሆኛለሁ፡፡ ሆኖም ግን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ላይ በያዟቸው መሰረታዊ እሴቶች ላይ ምንጊዜም ቢሆን እስማማለሁ፡፡ “ወግ ለቀቅ አሜሪካ እና ወግ አጥባቂ አሜሪካ የለም – ያለችው ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ናት፡፡ ጥቁር አሜሪካ እና ነጭ አሜሪካ የለም፣ እንዲሁም ላቲኖ አሜሪካ እና የኢስያ አሜሪካ የለም – ያለችው ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ናት፡፡“
በእኔ እምነት አሮሞ፣ ትግራዋይ፣ አማራ፣ ጋምቤላዊ፣ ኦጋዴናዊ፣ ሙርሲ ጉራጌ… የሚባል ነገር የለም – ያለችው የተከበረች እና በፍቅር ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለእኔ የእኛ ስብዕና በኢትጵያዊነት ጥላ ስር የተዋቀረው የአንድነት እና የፍቅር ቀንዲል በጎሳ ላይ ከተመሰረተው ማንነት በላይ መጨረሻ በሌለው መልኩ የበለጠ ጠቃሚነት አለው፡፡ ይህ ለእኔ ቀላሉ እምነትም መርሄ ነው!!!

Saturday, 24 May 2014

ሌሎች የሕዝብ ግንባታዎች እየተራዘሙ ባለበት ወቅት በቅርቡ የተመረቀዉን የጄነራል አልመሸትን ፎቅ ይመለከቱ

May 23rd, 2014                
General20Alemeshetጀነራል አለምሸት፣ በባለቤታቸው ወ/ሮ አንሻ ሰይድ ስም፣ በቅርቡ ያሰሩት ፎቅ፣ ግምሹ በወር 500000 ብር፣ ለአንድ ባንክ፣ ለበርካታ የቻይና ኩባንያዎችና አንድ ሬስቶራንት ተከራየ።
በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እየተጓተቱ ባለበት ወቅት የአገዛዙ ቱባ ባለስልጣናት ግንባታዎቻቸውን በተቀላጠፈ መንገድ ማጠናቀቅ መቻላቸው፣ አገዛዙ ምን ያህል በስልጣን ብልግና የተጨማለቀ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ፤

May 23rd, 2014
ቤታቸው የፈረሰባቸው
በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ በተሰማሩበት ቅጽበት ከጸጥታ ሰራተኞች ጋር አካባቢውን የወረሩት አፍራሽ ግብረ ሃይሎች መኖሪያ ቤቶቹን ማፍረሳቸውን በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በድንገት መፍረሳቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊሶች ክፉኛ መደብደባቸውንና መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል፡፡ቤቷ ሲፈርስ የደነገጠች እመጫት ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ ቤቱ በመፍረሱ መሄጃ ያጣ አባወራ ላስቲክ ዘርግቶ በተኛበት ጅብ ጎትቶት ወስዶት በልቶታል፡፡በጅብ የተበላው አባወራ ስርዓተ ቀብርም ዛሬ መፈጸሙ ታውቋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና እንደተዳረጉ የሚናገሩ ሰዎች‹‹ኢትዮጵያዊነታችን ተሰርዟል፣ቪዛ ይሰጠንና ሌላው ቢቀር ወደ ሶማሊያ እንድንሄድ ይደረግ ›› ብለዋል፡፡

መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ!

May 24th, 2014  
በ10 ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባን አጥለቅልቋታል።
ስላማዊ ሰልፉን የጠራው በፕሮፌሰር መራራ ጉድና የሚመራው መድረክ ፓርቲ ነው።
ሃሳባችንን በነጻነት መግለጽ እንፈልጋለን ! ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ይከበር!!!
ተቃውሞ ባሰም የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን !!!
መድረክ ለኦሮሞ ተማሪዎች ያለውን አጋርነት ይገልጻል !! ቪቫ መድረክ !!!
መድረክ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከሚጠበቀው በላይ በድምቀት የተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሱን መርጃዎች ይጠቁማሉ።
ግምቱ በ10ሺዎች የሚገመት የአዲስ አበባ እና አካባቢ ከተሞች ህዝብ ዋና ከትማዋን በሰልፍ አጥለቅልቋታል፤ የዛሪው ሰላማዊ ሰልፍ ድንቅ ነው፤ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዘኛ መፈክሮች ያነገቡ ከአዛውንት እስከ ወጣት እና ሴቶች ሰልፈኞች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
“Stop the massacre!. Bring culprits to justice!
Free all political prisoners! Stop the land grab!”
Hiriira nagaa Madrek. “Stop killing peaceful protesters”
” Stop eviction of farmers in the name of development”.1939864_10152474121284743_977829773025148542_n
10300805_881910458504953_7373829237705832672_n
10338305_881910225171643_7532438988631167186_n
10349138_881910438504955_3488204613342913393_n

Friday, 23 May 2014

የአረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል – ፍኖተ ነጻነት

May 23rd, 2014
አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡arena-structure

የአዳማው የአንድነት ሰልፍ ለሰኔ አንድ ተላለፈ

May 23rd, 2014
ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!
የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆትየነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንናይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲሁም የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆናችሁ ነጋዴዎች፣ተማሪዎችና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰልፋችን ላይ በመገኘት በገዢው ፓርቲ ላይ የተባበረ የተቃውሞ ድምጻችንን በሰላማዊ የትግል ስልት መንፈስ እንድናሰማ ጋብዘናችኋል፡፡ ሰኔ አንድ አይቀርም!
መነሻችን 4፡00ሰዓት ፣አዳማ ራስ ሆቴል (የቀድሞው መነን ሆቴል) ሆኖ፣ በፍራንኮ ሆቴል አርገን ወደ ምንጃር ጎዳና እንወጣና፤ ከሳር ተራ በአዲሱ ግንብ ገበያ ወደ መብራት ሐይል አቅንተን፤ ቁልቁል በአንደኛ መንገድ (ግርማሜ ነዋይ ጎዳና) ከደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት ካለው የፖስታ ቤት ሜዳ ላይ ማሳረጊያ እናደርጋለን፡፡ በጳጉሜ ሶስት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የሚሊየኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርተን በሀገሪቱ ስላለው ኢፍሀዊ የመሬት ስሪት እንጮሀለን! በመልካም አስተዳደር ዕጦት ስለሚደረጉ የሙስና ወንጀሎች የተቃውሞ ድምጽ እናሰማለን!-ኑ ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!10305607_726441860747899_1605322284415562929_n

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ባለቤት ናት?

May 23, 2014
ኪዳኔ ዓለማየሁ
መግቢያ፤
በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን፤ በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በገዛ ወንዟ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል።
እንደሚታወቀው፤ ሰሞኑን በየድህረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፤ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው በኢትዮጵያ በመገንባት ስላለው ታላቅ የአባይ ግድብ ነው። ስለ ግድቡ የተንጸባረቁት የተለያዩ አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው፤ የአባይ ወንዝ ባለቤትነት የማን እንደ ሆነ፤ ውሱን በሆነ መንገድ ተነካ እንጂ በጥልቀት በተከናወነ ምርመራና በዓለም-አቀፍ ሕግ ላይ በተመሠረተ አስተማማኝ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ አልቀረበም። የዚች ጦማር ዓላማም ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር በምታከናውናቸው ውሎች ያሁኑንና የመጪውን ትውልድ ሁሉ መብት በሚጠብቅ ሥልት መጠቀሟን እንድታረጋግጥ ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅትና ጥንቃቄ እንድታደርግ ለማሳሰብ ነው። በዚህ አጋጣሚም፤ ተሞክሮው ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ስለሚመስለኝ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት፤ የለሶቶ (Lesotho) መንግሥት የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በነበርኩበት ጊዜ ስለዛች ሐገር ወንዝ፤ በዓለም ባንክ ድጋፍ፤ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር እኔ ራሴ በመራሁት የልዑካን ቡድን ስለ ተከናወነው ድርድርና ስለ ተገኘው ውጤትም ባጭሩ እገልጻለሁ። Rile river facts and information in Amharic
የአባይ ወንዝ በረከት፤
አባይ፤ ኢትዮጵያ ካሏት እጅግ ታላቅና አኩሪ የተፈጥሮ ሐብቶች አንዱ ነው። ክልዩ ልዩ ወንዞች የተጠራቀመው ወደ 80 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር (cubic metre) ውሀ በአባይ አማካኝነት እየተዥጎደጎደ ሱዳንንና ግብጽን እያለማ አቋርጦ ከሚተነው ውሀ የተረፈው ሚዲቴሬኒያን ባሕር ይገባል። አባይ ከኢትዮጵያ ሰንቆ የሚጓዘው ውሀ ብቻ ሳይሆን ለም አፈር ጭምር ነው። ስለዚህ ግብጽና ሱዳን የሚታየው ለም መሬት፤ አብዛኛው በአባይ ወንዝ አማካኝነት ከኢትዮጵያ በሚጎርፍለት ውሀና ለም አፈር ችሮታ ነው። በተጨማሪም፤ እስካሁን ሳንጠቀምበት የቆየነው፤ ምናልባት በመሠራት ላይ ያለው ግድብ ለውጤት ከበቃ፤ ለኢትዮጵያና ለአካባቢዋ ከፍ ያለ የኃይል ማመንጪያ ሐብት ሊያስገኝ የሚችለው ሌላው የአባይ ወንዝ በረከት ሊሆን ይችላል።
በአባይ ወንዝ በረከት የተጠቀመው ማን ነው?
በእንግሊዝኛ Blue Nile (በአማርኛ፡ አባይ) ከተሰኘው፤ በዓለምና በታሪክ ታዋቂ ከሆነው ወንዝ ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ሱዳንና ግብጽ ናቸው። ከሌሎች ሐገሮች ጭምር ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚፈሰው ውሀ ሲታሰብ ከኢትዮጵያ የሚዘልቀው የአባይ ወንዝ አስተዋጽኦ ከጠቅላላው የውሀ መጠን 86% እንደ ሆነ ይታወቃል። የሚያሳዝነው ከባድ ጉዳይ ግን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ የሆነችው፤ ኢትዮጵያ፤ ለብዙ ዘመናት ተጠቃሚ ሳትሆን መቅረቷ ነው። ይህን ሁኔታ ከባድ የሚያደርገው፤ ባንድ በኩል አባይን የመሰለ አኩሪ የውሀ ሐብት እያላት፤ ኢትዮጵያ በድርቀት ምክንያት በመደጋገም ረሀብና እልቂት የተፈራረቀባት ሐገር መሆኗ ነው።
በዚህ አጋጣሚ፤ አንድ የማልረሳው ነገር፤ በተባበሩት የዓረብ ኤሚሬትስ እሠራ በነበረበት ጊዜ፤ በዚያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ባዘጋጀልን አንድ ስብሰባ አንድ ግብጻዊ የውሀ መሐንዲስ ጎኔ ተቀምጦ ስለ ነበር፤ በውይይታችን መሀል የአባይ ወንዝ ጉዳይ ተነሳና አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚመነጭ መሆኑን ሳስታውሰው፤ ወዲያውኑ የሚያስቆጭ መልስ ሰጠኝ፤ “አዎን፤ እኛ (ግብጽ) እንጠቀምበታለን።” “እኛም (ኢትዮጵያም)” የምልበት ጊዜ በሕይወት እያለሁ ይደርስ ይሆን?!
ለመሆኑ፤ የአባይ ወንዝ ባለቤት ማን ነው?
ዶር. ሚንጋ ነጋሽ፤ ዶር. ሰይድ ሀሰንና ዶር. ማሞ ሙጬ በቅርቡ ባበረከቱት “Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam” በተሰኘው ጽሑፋቸው፤ ክታዋቂው ከሪቻርድ ፓንከርስት (Richard Pnakhurst) በመጥቀስ፤ በጥንቱ፤ ቱርኮች ግብጽን በሚገዙበት ዘመን፤ የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ መሆኗ ታውቆ፤ 50000 (ሃምሳ ሺ) የወርቅ መሀለቅ (gold coins) ለሐገራችን በየዓመቱ ይከፍሉ እንደ ነበር ታውቋል።
ከላይ እንደ ተጠቀሰው፤ ምንም እንኳ ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚነጉደው የአባይ ወንዝ ምንጭ ኢትዮጵያ ብትሆንም፤ በቅርብ ዘመናት የታየው፤ ለጊዜው ተጠቃሚ የሆኑት ሐገሮች እያንጸባረቁት የቆየው ተጨባጭ ክስተት ባለቤትነቱ የነሱ እንደ ሆነ ዓይነት መሆኑ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ምሑራን እንደ ገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችባቸው ውሎች፤ (ሀ) እ.አ.አ በ1929 በእንግሊዝና በግብጽ መሀል በተፈጸመው ውል 48 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለግብጽ፤ 4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን እንዲመደብ፤ በኋላ ደግሞ (ለ) በ1959 በግብጽና በሱዳን መሀል በተከናወነው ውል 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ለግብጽ፤ 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን ተመድቧል። የሚያስገርመው፤ ዋናዋ የውሀው ምንጭ የሆነችው የኢትዮጵያ መብት ምንም ዋጋ አልተሰጠውም።
ባሁኑም ጊዜ ተከስቶ ያለው ሁኔታ፤ ግብጽ “የአባይ ስጦታ” (“Gift of the Nile”) መሆኗን ስለምታውቅ በተለይ በቅርቡ ዘመን የለመደችውን ልቅ የሆነ በአባይ ወንዝ የመጠቀም ችሮታ ያለገደብ እንድትቀጥል መብቷ እንደ ሆነ እያስመሰለች ኢትዮጵያ በመብቷ ከተጠቀመች እርምጃ የሚያስከትል መሆኑን በመጠቆም የማስፈራራት ሥልት እያናፈሰች፤ በሌላ በኩል የዚህ ዓይነት አጉል ዘዴ የማያዋጣ መሆኑን ግንዛቤ ያለው በሚመስል ሥልት ለመደራደር ፈቃደኛነት ትጠቁማለች። ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ለማስከበር በቁርጠኛነት ከወሰኑ፤ ማንም ሊገድባቸው እንደማይችል ግብጽም ብትገነዘብ መልካም ነው። በታሪክ እንደምናውቀው፤ ግብጽ፤ የሕልውናዋ ምንጭ የሆነውን አባይን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ፤ ከአሥር ጊዜ በላይ ኢትዮጵያን ወርራ፤ ሐረርን እስከ መያዝ ደርሳ፤ በመጨረሻው ግን ሳይሳካላት ቀርቷል። በተቃራኒው፤ ከታሪክ የምንማረው፤ ኢትዮጵያ ከኃያሎቹ ሐገሮች አንዷ በነበረችበት ዘመን፤ ግብጽንም ተቆጣጥራ እንደ ነበር ነው። ለዚህ ማስረጃ ካስፈለገ፤ የጥንት ግብጻዊ ነገሥታትን ታሪክ መመልከት ይበቃል። ስለዚህ፤ ግብጽ ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነት የምትከተለው ሥልት የትም ስለማያደርሳት፤ ይልቁንስ ሚዛናዊ በሆነ፤ የሁሉንም የወንዙን አካባቢ ሐገሮች መብት በትክክል ማስተናገድ የተሻለ ዘዴ ነው። መብቷን የማስከበሩ ዋናው ኃላፊነት ግን የኢትዮጵያ ነው።
ሱዳንን በተመለከተ፤ ምንም እንኳ፤ ከመገናኛ ብዙኃን መገንዘብ እንደሚቻለው፤ በመገንባት ላይ ስላለው ግድብ ደጋፊ መሆኗ ቢገለጽም፤ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ስላላት መብት አቋሟ ምን እንደ ሆነ በይፋ አልተገለጸም።
ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ፤ ከሚነጉደው ውሀ 86% የምታበረክተው፤ 100 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የኢትዮጵያ ድርሻ በትክክል እንዲታይ ያስፈልጋል። የውሀ ሐብቷ እያለ፤ ኢትዮጵያ በድርቅና በረሀብ መሰቃየቷ መቀጠል የለበትም። ኢትዮጵያም፤ የወንዝ ምንጮች እንደሆኑ እንደ ሌሎች ሐገሮች፤ በአባይ ወንዝ በረከቷ፤ በውሀዋ፤ በኃይል ማመንጫዋና በአፈሯ በስፋት እየተጠቀመች ልማቷን ማጣደፍና ማሳደግ መብቷ ነው። ይህም ሲባል ግን፤ የሌሎቹ ሐገሮች፤ ማለት የሱዳንና የግብጽ በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብት አይኑር ማለት አይደለም። የዓለም-አቀፍ ሕግ መመሪያዎችን መሠረት ባደረገ ሚዛናዊ በሆነ የጋርዮሽ አጠቃቀም ሥልት ይከናወን ማለት ነው። ይህንንም ለማስገኘት በጥሞናና በመከባበር ለዘለቄታው ተቀባይነት በሚያስገኝ ዘዴ መደራደርና መዋዋል ያስፈልጋል ማለት ነው።
የለሶቶ (Lesotho) በወንዟ ሐብት የመጠቀም ተሞክሮ፤
በመግቢያው እንደ ገለጽኩት፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ለሶቶ (Lesotho) አገልግዬ ነበር። እዚያች ሐገር የሠራሁትም እ.አ.አ በ1972-78 ሲሆን፤ ለአራት አመቶች በፖስታ፤ ቴሌኮሙኒኬሽንና ሲቪል አቭዬሽን ዋና ዲሬክተርነት ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመቶች ደግሞ የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በመሆን ነበር። የሥራ ሚኒስቴሩም የሚያጠቃልላቸው አገልግሎቶች፤ የመንግሥት ሕንጻዎችና መንገዶች ግንባታዎችና ጥገናዎች፤ የውሀ ልማትና አቅርቦት፤ የመብራት ኃይል አገልግሎትና፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ነበሩ። በነገራችን ላይ፤ ስለዚህ ሥራዬና ስለ ሌሎችም አገልግሎቶቼና ተያያዥ ጉዳዮች በቅርቡ በሚወጣ መጽሐፌ በሰፊው ለመግለጽ እየተዘጋጀሁ ነው።
ለሶቶ፤ ደቡብ አፍሪካ መሀል የምትገኝ አንድ ትንሽ ሐገር ናት። ትንሽ ብትሆንም፤ እንደ ኢትዮጵያ የውሀ ሐብት በረከት ያላት ሐገር ናት። እኔ ለሶቶ በነበርኩበት ጊዜ የለሶቶ ወንዝ የሚፈሰው ደቡብ አፍሪካ ለልማትና ሌላም ጥቅም ወደምትፈልገው አቅጣጫ ስላልነበረ፤ አስፈላጊው የማስተካከል ተግባር ተከናውኖ ሙሉ ተጠቃሚ እንድትሆን በለሶቶና በደቡብ አፍሪካ ድርድር ተጀምሮ ነበር። በዚህም ምክንያት በቋሚ ተጠሪነት ተግባሬ በድርድሩ ተካፍዬ ነበር። ከዚሁ በተለይ የማስታውሰው፤ እ.አ.አ. በ1977 በኔ መሪነት ኬፕ ታውን (Cape Town) በመጓዝ የለሶቶ ባለሥልጣኖችና ከየዓለም ባንክም ተወካይ የተገኘበት ልዑካን ከደቡብ አፍሪካ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣኖች ጋር ተደራድረን ነበር። የድርድሩ ጭብጥም ለሶቶ በውሀ ሐብቷ (ለኃይል ማመንጪያ ጭምር) የመጠቀም መብቷ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚፈሰው ውሀ ለሶቶ ተገቢውን ክፍያ እንድታገኝ ለማድረግ ነበር።
ያ ሁሉ ድርድር ውጤቱ አምሮ፤ የለሶቶን ተራራ በመሸንቆርና የወንዙን ፍሰት አቅጣጫ በማስለወጥ ለደቡብ አፍሪካ የሚያስፈልገው ውሀ በሚገባ እንዲቀርብ ለማድረግ ከቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሆነበት ሥራ ተጠናቆ፤ ባሁኑ ጊዜ ለሶቶ በያመቱ፤ በአማካኝ፤ $50 ሚሊዮን በደቡብ አፍሪካ እየተከፈላት ነው።
ለሶቶ ብሔራዊ መብቷንና ጥቅሟን ከላይ እንደ ተገለጸው ማስከበር ከቻለች፤ በታሪኳም ነጻነቷንና ክብሯን በማስከበር የምትታወቀው ኢትዮጵያ ከዚያ ያነሰ ይጠበቅባታል?
ማጠቃለያ፤
የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ ታላቅ የተፈጥሮ ሐብት ነው። ኢትዮጵያ የሱዳንንና የግብጽን ተገቢ መብት እያከበረች የራሷንም ጥቅም መጠበቅና ማስከበር ይኖርባታል። ለዚህም፤ በወንዝ ውሀ አጠቃቀም መርሆ፤ ሥልትና እቅድ ባለሞያዎች በመታገዝ ዝርዝር ጥናቶች በማከናወን ከጎረቤት ሐገሮች ጋር የሚደረገው ድርድር የኢትዮጵያን የዘለቄታ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ማረጋገጥና ሒደቱም ግልጽነትና ቁጥጥር የሰፈነበት እንዲሆን፤ የአባይ ወንዝ ዋናው ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሙሉ መብቱ እንዲጠበቅ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

May 23, 2014
ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።
Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።
ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።
በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።
ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።
ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!

Thursday, 22 May 2014

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ባለቤት ናት?

May 22nd, 2014
በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን፤ በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በገዛ ወንዟ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል።
እንደሚታወቀው፤ ሰሞኑን በየድህረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፤ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው በኢትዮጵያ በመገንባት ስላለው ታላቅ የአባይ ግድብ ነው። ስለ ግድቡ የተንጸባረቁት የተለያዩ አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው፤ የአባይ ወንዝ ባለቤትነት የማን እንደ ሆነ፤ ውሱን በሆነ መንገድ ተነካ እንጂ በጥልቀት በተከናወነ ምርመራና በዓለም-አቀፍ ሕግ ላይ በተመሠረተ አስተማማኝ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ አልቀረበም። የዚች ጦማር ዓላማም ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር በምታከናውናቸው ውሎች ያሁኑንና የመጪውን ትውልድ ሁሉ መብት በሚጠብቅ ሥልት መጠቀሟን እንድታረጋግጥ ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅትና ጥንቃቄ እንድታደርግ ለማሳሰብ ነው። በዚህ አጋጣሚም፤ ተሞክሮው ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ስለሚመስለኝ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት፤ የለሶቶ (Lesotho) መንግሥት የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በነበርኩበት ጊዜ ስለዛች ሐገር ወንዝ፤ በዓለም ባንክ ድጋፍ፤ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር እኔ ራሴ በመራሁት የልዑካን ቡድን ስለ ተከናወነው ድርድርና ስለ ተገኘው ውጤትም ባጭሩ እገልጻለሁ።
የአባይ ወንዝ በረከት፤
አባይ፤ ኢትዮጵያ ካሏት እጅግ ታላቅና አኩሪ የተፈጥሮ ሐብቶች አንዱ ነው። ክልዩ ልዩ ወንዞች የተጠራቀመው ወደ 80 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር (cubic metre) ውሀ በአባይ አማካኝነት እየተዥጎደጎደ ሱዳንንና ግብጽን እያለማ አቋርጦ ከሚተነው ውሀ የተረፈው ሚዲቴሬኒያን ባሕር ይገባል። አባይ ከኢትዮጵያ ሰንቆ የሚጓዘው ውሀ ብቻ ሳይሆን ለም አፈር ጭምር ነው። ስለዚህ ግብጽና ሱዳን የሚታየው ለም መሬት፤ አብዛኛው በአባይ ወንዝ አማካኝነት ከኢትዮጵያ በሚጎርፍለት ውሀና ለም አፈር ችሮታ ነው። በተጨማሪም፤ እስካሁን ሳንጠቀምበት የቆየነው፤ ምናልባት በመሠራት ላይ ያለው ግድብ ለውጤት ከበቃ፤ ለኢትዮጵያና ለአካባቢዋ ከፍ ያለ የኃይል ማመንጪያ ሐብት ሊያስገኝ የሚችለው ሌላው የአባይ ወንዝ በረከት ሊሆን ይችላል።
በአባይ ወንዝ በረከት የተጠቀመው ማን ነው?
በእንግሊዝኛ Blue Nile (በአማርኛ፡ አባይ) ከተሰኘው፤ በዓለምና በታሪክ ታዋቂ ከሆነው ወንዝ ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ሱዳንና ግብጽ ናቸው። ከሌሎች ሐገሮች ጭምር ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚፈሰው ውሀ ሲታሰብ ከኢትዮጵያ የሚዘልቀው የአባይ ወንዝ አስተዋጽኦ ከጠቅላላው የውሀ መጠን 86% እንደ ሆነ ይታወቃል። የሚያሳዝነው ከባድ ጉዳይ ግን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ የሆነችው፤ ኢትዮጵያ፤ ለብዙ ዘመናት ተጠቃሚ ሳትሆን መቅረቷ ነው። ይህን ሁኔታ ከባድ የሚያደርገው፤ ባንድ በኩል አባይን የመሰለ
አኩሪ የውሀ ሐብት እያላት፤ ኢትዮጵያ በድርቀት ምክንያት በመደጋገም ረሀብና እልቂት የተፈራረቀባት ሐገር መሆኗ ነው።
በዚህ አጋጣሚ፤ አንድ የማልረሳው ነገር፤ በተባበሩት የዓረብ ኤሚሬትስ እሠራ በነበረበት ጊዜ፤ በዚያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ባዘጋጀልን አንድ ስብሰባ አንድ ግብጻዊ የውሀ መሐንዲስ ጎኔ ተቀምጦ ስለ ነበር፤ በውይይታችን መሀል የአባይ ወንዝ ጉዳይ ተነሳና አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚመነጭ መሆኑን ሳስታውሰው፤ ወዲያውኑ የሚያስቆጭ መልስ ሰጠኝ፤ “አዎን፤ እኛ (ግብጽ) እንጠቀምበታለን።” “እኛም (ኢትዮጵያም)” የምልበት ጊዜ በሕይወት እያለሁ ይደርስ ይሆን?!
ለመሆኑ፤ የአባይ ወንዝ ባለቤት ማን ነው?
ዶር. ሚንጋ ነጋሽ፤ ዶር. ሰይድ ሀሰንና ዶር. ማሞ ሙጬ በቅርቡ ባበረከቱት “Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam” በተሰኘው ጽሑፋቸው፤ ክታዋቂው ከሪቻርድ ፓንከርስት (Richard Pnakhurst) በመጥቀስ፤ በጥንቱ፤ ቱርኮች ግብጽን በሚገዙበት ዘመን፤ የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ መሆኗ ታውቆ፤ 50000 (ሃምሳ ሺ) የወርቅ መሀለቅ (gold coins) ለሐገራችን በየዓመቱ ይከፍሉ እንደ ነበር ታውቋል።
ከላይ እንደ ተጠቀሰው፤ ምንም እንኳ ወደ ሱዳንና ግብጽ የሚነጉደው የአባይ ወንዝ ምንጭ ኢትዮጵያ ብትሆንም፤ በቅርብ ዘመናት የታየው፤ ለጊዜው ተጠቃሚ የሆኑት ሐገሮች እያንጸባረቁት የቆየው ተጨባጭ ክስተት ባለቤትነቱ የነሱ እንደ ሆነ ዓይነት መሆኑ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ምሑራን እንደ ገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችባቸው ውሎች፤ (ሀ) እ.አ.አ በ1929 በእንግሊዝና በግብጽ መሀል በተፈጸመው ውል 48 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለግብጽ፤ 4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን እንዲመደብ፤ በኋላ ደግሞ (ለ) በ1959 በግብጽና በሱዳን መሀል በተከናወነው ውል 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ለግብጽ፤ 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሀ ለሱዳን ተመድቧል። የሚያስገርመው፤ ዋናዋ የውሀው ምንጭ የሆነችው የኢትዮጵያ መብት ምንም ዋጋ አልተሰጠውም።
ባሁኑም ጊዜ ተከስቶ ያለው ሁኔታ፤ ግብጽ “የአባይ ስጦታ” (“Gift of the Nile”) መሆኗን ስለምታውቅ በተለይ በቅርቡ ዘመን የለመደችውን ልቅ የሆነ በአባይ ወንዝ የመጠቀም ችሮታ ያለገደብ እንድትቀጥል መብቷ እንደ ሆነ እያስመሰለች ኢትዮጵያ በመብቷ ከተጠቀመች እርምጃ የሚያስከትል መሆኑን በመጠቆም የማስፈራራት ሥልት እያናፈሰች፤ በሌላ በኩል የዚህ ዓይነት አጉል ዘዴ የማያዋጣ መሆኑን ግንዛቤ ያለው በሚመስል ሥልት ለመደራደር ፈቃደኛነት ትጠቁማለች። ኢትዮጵያውያን መብታቸውን ለማስከበር በቁርጠኛነት ከወሰኑ፤ ማንም ሊገድባቸው እንደማይችል ግብጽም ብትገነዘብ መልካም ነው። በታሪክ እንደምናውቀው፤ ግብጽ፤ የሕልውናዋ ምንጭ የሆነውን አባይን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ፤ ከአሥር ጊዜ በላይ ኢትዮጵያን ወርራ፤ ሐረርን እስከ መያዝ ደርሳ፤ በመጨረሻው ግን ሳይሳካላት ቀርቷል። በተቃራኒው፤ ከታሪክ የምንማረው፤ ኢትዮጵያ ከኃያሎቹ ሐገሮች አንዷ በነበረችበት ዘመን፤ ግብጽንም ተቆጣጥራ እንደ ነበር ነው። ለዚህ ማስረጃ ካስፈለገ፤ የጥንት ግብጻዊ ነገሥታትን ታሪክ መመልከት ይበቃል። ስለዚህ፤ ግብጽ ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነት የምትከተለው ሥልት የትም ስለማያደርሳት፤ ይልቁንስ ሚዛናዊ በሆነ፤ የሁሉንም የወንዙን አካባቢ ሐገሮች መብት በትክክል ማስተናገድ የተሻለ ዘዴ ነው። መብቷን የማስከበሩ ዋናው ኃላፊነት ግን የኢትዮጵያ ነው።
3
ሱዳንን በተመለከተ፤ ምንም እንኳ፤ ከመገናኛ ብዙኃን መገንዘብ እንደሚቻለው፤ በመገንባት ላይ ስላለው ግድብ ደጋፊ መሆኗ ቢገለጽም፤ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ስላላት መብት አቋሟ ምን እንደ ሆነ በይፋ አልተገለጸም።
ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ፤ ከሚነጉደው ውሀ 86% የምታበረክተው፤ 100 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የኢትዮጵያ ድርሻ በትክክል እንዲታይ ያስፈልጋል። የውሀ ሐብቷ እያለ፤ ኢትዮጵያ በድርቅና በረሀብ መሰቃየቷ መቀጠል የለበትም። ኢትዮጵያም፤ የወንዝ ምንጮች እንደሆኑ እንደ ሌሎች ሐገሮች፤ በአባይ ወንዝ በረከቷ፤ በውሀዋ፤ በኃይል ማመንጫዋና በአፈሯ በስፋት እየተጠቀመች ልማቷን ማጣደፍና ማሳደግ መብቷ ነው። ይህም ሲባል ግን፤ የሌሎቹ ሐገሮች፤ ማለት የሱዳንና የግብጽ በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብት አይኑር ማለት አይደለም። የዓለም-አቀፍ ሕግ መመሪያዎችን መሠረት ባደረገ ሚዛናዊ በሆነ የጋርዮሽ አጠቃቀም ሥልት ይከናወን ማለት ነው። ይህንንም ለማስገኘት በጥሞናና በመከባበር ለዘለቄታው ተቀባይነት በሚያስገኝ ዘዴ መደራደርና መዋዋል ያስፈልጋል ማለት ነው።
የለሶቶ (Lesotho) በወንዟ ሐብት የመጠቀም ተሞክሮ፤
በመግቢያው እንደ ገለጽኩት፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ለሶቶ (Lesotho) አገልግዬ ነበር። እዚያች ሐገር የሠራሁትም እ.አ.አ በ1972-78 ሲሆን፤ ለአራት አመቶች በፖስታ፤ ቴሌኮሙኒኬሽንና ሲቪል አቭዬሽን ዋና ዲሬክተርነት ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ዓመቶች ደግሞ የሥራ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ በመሆን ነበር። የሥራ ሚኒስቴሩም የሚያጠቃልላቸው አገልግሎቶች፤ የመንግሥት ሕንጻዎችና መንገዶች ግንባታዎችና ጥገናዎች፤ የውሀ ልማትና አቅርቦት፤ የመብራት ኃይል አገልግሎትና፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ነበሩ። በነገራችን ላይ፤ ስለዚህ ሥራዬና ስለ ሌሎችም አገልግሎቶቼና ተያያዥ ጉዳዮች በቅርቡ በሚወጣ መጽሐፌ በሰፊው ለመግለጽ እየተዘጋጀሁ ነው።
ለሶቶ፤ ደቡብ አፍሪካ መሀል የምትገኝ አንድ ትንሽ ሐገር ናት። ትንሽ ብትሆንም፤ እንደ ኢትዮጵያ የውሀ ሐብት በረከት ያላት ሐገር ናት። እኔ ለሶቶ በነበርኩበት ጊዜ የለሶቶ ወንዝ የሚፈሰው ደቡብ አፍሪካ ለልማትና ሌላም ጥቅም ወደምትፈልገው አቅጣጫ ስላልነበረ፤ አስፈላጊው የማስተካከል ተግባር ተከናውኖ ሙሉ ተጠቃሚ እንድትሆን በለሶቶና በደቡብ አፍሪካ ድርድር ተጀምሮ ነበር። በዚህም ምክንያት በቋሚ ተጠሪነት ተግባሬ በድርድሩ ተካፍዬ ነበር። ከዚሁ በተለይ የማስታውሰው፤ እ.አ.አ. በ1977 በኔ መሪነት ኬፕ ታውን (Cape Town) በመጓዝ የለሶቶ ባለሥልጣኖችና ከየዓለም ባንክም ተወካይ የተገኘበት ልዑካን ከደቡብ አፍሪካ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣኖች ጋር ተደራድረን ነበር። የድርድሩ ጭብጥም ለሶቶ በውሀ ሐብቷ (ለኃይል ማመንጪያ ጭምር) የመጠቀም መብቷ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚፈሰው ውሀ ለሶቶ ተገቢውን ክፍያ እንድታገኝ ለማድረግ ነበር።
ያ ሁሉ ድርድር ውጤቱ አምሮ፤ የለሶቶን ተራራ በመሸንቆርና የወንዙን ፍሰት አቅጣጫ በማስለወጥ ለደቡብ አፍሪካ የሚያስፈልገው ውሀ በሚገባ እንዲቀርብ ለማድረግ ከቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሆነበት ሥራ ተጠናቆ፤ ባሁኑ ጊዜ ለሶቶ በያመቱ፤ በአማካኝ፤ $50 ሚሊዮን በደቡብ አፍሪካ እየተከፈላት ነው።
4
ለሶቶ ብሔራዊ መብቷንና ጥቅሟን ከላይ እንደ ተገለጸው ማስከበር ከቻለች፤ በታሪኳም ነጻነቷንና ክብሯን በማስከበር የምትታወቀው ኢትዮጵያ ከዚያ ያነሰ ይጠበቅባታል?
ማጠቃለያ፤
የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ ታላቅ የተፈጥሮ ሐብት ነው። ኢትዮጵያ የሱዳንንና የግብጽን ተገቢ መብት እያከበረች የራሷንም ጥቅም መጠበቅና ማስከበር ይኖርባታል። ለዚህም፤ በወንዝ ውሀ አጠቃቀም መርሆ፤ ሥልትና እቅድ ባለሞያዎች በመታገዝ ዝርዝር ጥናቶች በማከናወን ከጎረቤት ሐገሮች ጋር የሚደረገው ድርድር የኢትዮጵያን የዘለቄታ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ማረጋገጥና ሒደቱም ግልጽነትና ቁጥጥር የሰፈነበት እንዲሆን፤ የአባይ ወንዝ ዋናው ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብም ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሙሉ መብቱ እንዲጠበቅ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
ቸሩ አምላክ፤ ኢትዮጵያ በሕዝቧ ያልተቆጠበ ጥረት መብቷን፤ ክብሯንና ጥቅሟን እንድትጠብቅ ይርዳ!

ህዝባዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ እና የተቃዋሚዎች የቤት ስራ በናትናኤል

May 22nd, 2014
ከሰሞኑ ወያኔ መራሹ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያወጣው አዲስ አበባ ዙርያ የኦሮሚያ ዞን ያካተተ ማስተር ፕላን እና የእዝ አስተዳደር ተግባራዊነትን በመቃወም በብዙዎች የኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች ሰፊ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ ተቀስቅሶ በመንግስት ቅጥ ያጣ ግድያና እስር ለጊዜው ጋብ ቢልም አሁንም ቢሆን በህዝቡ ውስጥ ሞልቶ ሊገነፍል የደረሰ ቁጣ አለ፡፡ በሌላ በኩል በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ ሲደረግ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ አሁንም ቢሆን የቀጠለ ቢሆንም እስካሁን ድረስም ቢሆን በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ በሚፈለገው መልኩ ሊስፋፋ አልቻለም፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት ሁለት ሲሆኑ አንደኛው የመንግስት ህዝባዊ ተቃውሞን አቅጣጫ በማሳት እና በህዝቦች መካከል የተነሳ የዘረኝነት ወይም የሀይማኖት የበላይነት የተፈጠረ በማስመሰል በህዝቡ ውስጥ መከፋፈልን በመፍጠር “የእብድ ገላጋይ” እንደሚባለው እንዳስታራቂ መጥቶ በህዝቦችና በሀይማኖት መሀከል ለረጀም ግዜ የቆውን መዋደድ (ልብ አርጉ መቻቻል አላልኩም) እንዳልነበር አድርጎ የኢትዮጵያ ህዝቦች የተባበረ አንድነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ሲሆን ሁለተኛወ ደግሞ የተቃዋሚዎች ሀዝባዊ ንቅናቄውን በማጠናከርና የጋራ አጀንዳ የሆነውን የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት መገርሰስ የተለየ አትኩሮት በመስጠት እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄው ሰፊ ሽፋን አንዲኖረው እምብዛም የጠነከረና የተቀናጀ ህዝባዊ የመብት ማስከበር ንቅናቄ አጠናክረው ባለማስቀጠላቸው ነው፡፡
በአብዛኛው ህዝባዊ ተቃውሞዎች ውስጥ የሚሳተፉ የወያኔ ካድሬዎች (Under Cover) እንደሚባለው በማዘጋጀት ዋና ተልዕኮዋቸው በህዝቦች መሀከል መቃቃር ሊፈጥሩ የሚችሉ አጀንዳዎችን በሰፊው እንዲሰራጩ እና በህዝባዊ ጥያቄዎች ውስጥ እንደ አንድ አጀንዳ እንዲካተቱ በማድረግ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በማክሸፍ እንዲሁም ተቃውሞዎችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በመጠምዘዝ ውጤታማ እንዳይሆኑ በማድረግ ከጅምሩ የህዝብ ንቅናቄን ፈር ማሳት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የተቃዋሚወች በአቋም መግለጫ ብቻ መወሰን የተቃውሞ ንቅናቄዎቹ ስኬታማ እንደዳይሆኑ አስተዋጽዎ አድርጓል፡፡ ለዚህ በማሳያነት በቅርቡ የተደረጉት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ምን አይነት ሙከራ እንደተደረገበት እንመልከት፡፡
የመጀመሪያው የሙስሊሞች ህዝባዊ ጥያቄ ሲሆን በመሰረቱ እስካሁን ከታዩት ህዝባዊ ንቅናቄዎች በተሻለ መልኩ የተደራጀ ቢሆንም በሚፈለገው መልኩ ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል አላካተተም (የሀይማኖት ነጻነት ሁሉንም ዜጋ የሚመለከት ቢሆንም) እንደውም ተደጋግመው በሚቀርቡ የመንግስተ መሰረተ ቢስ ፕሮፓጋንዳዎች (እስላማዊ መንግስት ማቋቋም በሚል ውሸት የታጨቀ) የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ሁኔታውን በጥርጣሬ የሚመለከቱበትና መንግስት የሚወስደውን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ በዝምታ ያለፉበት ሁኔታ የተፈጠረው፡፡ ለዚያውም ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በየአጋጣሚው ትክክለኛውን ጥያቄዎቻቸውን ለማስረዳት ጥረት እያደረጉ፡፡ በዚህ ረገድ ተቃዋሚዎች የመረጡት አካሄድ የጥያቄውን ትክክለኛነትና የገዠው ወያኔ መንግስት እርምጃ ትክክል አለመሆኑን አስመልክቶ መግለጫ መስጠት ብቻ ነው፡፡ጥያቄው የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ በማስረዳት በቂ የሆነ ቅስቀሳ ማድረግ እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ሲገባቸው የተለሳለሰ አካሄድን በመምረጣቸው ተቃውሞው ሰፊ ህዝባዊ ተሳትፎ ሳይኖረው ቀርቷል፡፡ አሁንም ቢሆን ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እድሉ ስላለ ተቃዋሚዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ቅርጽ በማስያዝ የጋራ አጀንዳ ወደሆነው የወያኔን ጨቋኝ ስርዐት ገርስሶ ወደመጣል ሊመሩት ይገባል፡፡
በሁለተኛነት ማየት የፈለኩት የአሁኑ በኦሮሚያ ክልል ተወላጆችና ሃገር ወዳዶች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞና ንቅናቄ ሲሆን፡ ህዝባዊ ተቃውሞውን እንደተለመደው ዋነኛው ጥያቄ የኦሮሚያ ክልል ህዝብን ብቻ የሚመለከት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር ችግሩ የጨቋኙ ስርዐት ያመጣው ሆኖ ሳለ እንደተለመደው የጥቂት ሀገወጦች እንደሆነና ችግሩም ከሌሎች ብሄረ ተወላጆች ጋር የተፈጠረ ግጭት ተደርጎ ቀርቧል፡፡
እውነታው ግን ዛሬ በኦሮሚያ ላይ እየተወሰደ ያለው ህገ ወጥ አፈና እና ጭፍጨፋ በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ክልል (መሬት ተቀርሶ ለሱዳን ሲሰጥ)፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች በተለያየ ግዜ ሲወሰድ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ እኔ የምለው ግን የብሄር ግጭት በኢትየጵያ ውስጥ ሆነ ተብሎ የሚጫር ነው ወይስ የብሔሮች አንድ ላይ ተከባበብሮ መኖር አለመቻል? የብሄር ግጭት የሚነሳው ወያኔ የመብት ማስከበር ጥያቄ ሲነሳበት ብቻ ነው እንዴ? በነገራችን ላይ የትኛው ብሄር ነው የእከሌ ብሄር ከክልሌ ይውጣልኝ ብሎ ሰልፍ የወጣው? ወያኔ ግን ሖነ ተብሎ አንዱን ብሄር ከሌላው የሚያጋጩ ነገሮችን በመቆስቆስና የተባበረ አጀንዳ እንዳይኖር በማድረግ የተባበረ ህዝባዊ ተቃውሞን ማጨናገፊያ ሁነኛ መንገድ አድርጎ ቀጥሎበታል፡፡
ስለዚህ የተቃዋሚዎች የቤት ስራም ማተኮር ያለበት ይህንን የወያኔ ሰይጣናዊ አካሄድ ማክሸፍን ዋና አጀንዳ አድርጎ መሆን አለበት ባይ ነኝ ፡፡ የሁሉም ህዝባዊ ጥያቄዎች መነሻቸውም መድረሻቸውም የወያኔ ጨቋኝ ስርዐት መሆኑ በገሀድ እየታወቀ እውነታው እየተድበሰበሰ ሌላ ቅርጽና ይዘት ሲሰጠው በቸልታ መመልከት ለወያኔ አገዛዝ መራዘም ዋነኛ ስትራቴጂ ከመመቻቸት ባሻገር ለወያኔ ህዝብን የመከፋፈል አጀንዳ ስር እንዲሰድ መፍቀድም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በአንድነት ጨቋኙን የወያኔን መንገስት ማስወገድ ዋና ዐጀንዳ አድርገን እንንቀሳቀስ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚነሱት ሁሉም ተቃውሞዎች የጋራ አጀንዳ የጭቆናው ስርአት መወገድ ነው ስለዚህ አዚህ አጀነዳ ላይ አናተኩር ያኔ የሁሉም ጭቆና ማብቂያና መቀበሪያ ይሆናል ተባብረን ወያኔን ከነአስከፊ ጭቆናው ጋር እናስወግደው!!!!