Wednesday, 22 January 2014

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል ዙሪያ ጥር 13 ሕዝባዊ ስብሰባ ይደረጋል

habtamu
መንግስት ከሕዝብ በመደበቅ ለሱዳን ለመስጠት እየተደራደረበት ስላለዉ የኢትዮጵያ ድንበር መሬት ዙሪያ ከሕዝብ ጋር የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በእለቱ የትሪክ ባለሞያዎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ስለሁኔታዉ ለማስረዳት ከሰሜን ጎንደር ፣ መተማ እና አምርጭሆ ነዋሪዎች የሚገኙ ሲሆን ፣ በአቶ ሃብታሙ አያሌዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ፣ ስለ ኢትዮጵያ ድንበር ታሪክ ጥናታዊ ጽሁፍ ይቀርባል።
በመሆኑም በዚህ ታሪካዊ ስብሰብ ላይ በመገኘት ኢትዮጵያዊ ግዴታዎችን እንዲወጡ ፓርቲዉ ጥሪዉን ያስተላለፋል።

No comments:

Post a Comment