Wednesday, 16 July 2014

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

July 16th, 2014                   
ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ተስማምቷል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀቀ ሲሆን የጉባኤ ተሳታፊዎች የውህደቱን ግዜ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱ ፓርቲዎች ተዋህደውና ሌሎች ፓቲዎች ወደ መሰባሰብ መጥተው የተጠናከረ የተቃውሞ ሃይል እንዲፈጠር ብርቱ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያውያንና የውህደት አመቻች ኮሚቴው ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
በመቀጠልም እስከ ውህደቱ ፍፃሜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥል በመተማመን ለውህደቱ ድጋፍ የምታደርጉ ኢትዮጵያውያን፡-
መኢአድ፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ቦሌ ቅርንጫፍ፤ የባንክ አካውንት ቁጥር፡- AEUP – SP 235
አንድነት፤ አቢሲንያ ባንክ፤ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ የባንክ አካውንት፡- UDJ – A/C 47
በኩል እንድታስገቡ የውህደት አመቻች ኮሚቴው አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስንተባባር እናሸንፈላን!!
ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባudJAEUP

በደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ አወጣ

July 16th, 2014
ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- የአቋም መግለጫን ስለማሳወቅ፡
ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው የደቡብ ወሎ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ 06/11/06 ዓ.ም በፓርቲው ጽ/ቤት በመሰብሰብ የፓርቲውን የስራ እንቅስቃሴና በቅርቡ በታሰሩ የፓርቲው የበላይ አመራሮች በአቶ ሀብታሙ አያሌው እና በአቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በሰበብ አስባቡ በሚታሰሩ ሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ህገ ወጥ ድርጊት አባላቱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. የዜጎች የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና ከፈለጉት ፓርቲ ጋር የመወገን መብታቸውን መንግስት እንዲያከብርና እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡
2. በህገ መንግስቱ የተፈቀዱት የዜጎች መብቶች ሳይሸራረፉ በስራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ እንዲያከብርና እንዲያስከብርእንጠይቃለን፡፡
3. ዜጎች ለመብታቸው መከበር ፍላጎታቸው እየሰፋና እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን በማወቅ ገዢው ፓርቲ ከድርጊቱ እንዲታቀብና የዜጎች መብት እንዲከበር እንጠይቃለን፡፡
4. ለዲሞክራሲ እውን መሆንና መዳበር ሰዎችን ማሰር መፍትሄ አለመሆኑን ገዢው ፓርቲ ጠንቅቆ በማወቅ ለሰላማዊ ትግሉ መዳበር መንግስት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን በማለት ያቋ ም መግለጫ ያወጣን ሲሆን
በመጨረሻም የፓርቲያችን የላእላይ ምክር ቤት ያለአግባብ የታሰሩ ወንድሞቻችን ሁኔታ ያሳዘነው ቢሆንም ነገር ግን የነሱ መታሰር የትግሉን ምእራፍ ከማስፋትና የበለጠ ከማቀጣጠል ባሻገር አንድም እርምጃ ወደ ኋላ የማይመልሰውና ሁሉንም አባል የበለጠ ለትግሉ ያነሳሳ መሆኑን አምኖ ከእስካሁኑ በበለጠ የትግል ስልቱን በማስፋት በዜጎች መብት ላይ እየዘመተ ያለውን የገዢው ፓርቲ በአደባባይ እና በአዳራሽ በህዝብ የምናወግዝበትን የሰላማዊ ትግል ስልት ፓርቲው እንዲያመቻችልን በማለት የዞኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የአቋም መግለጫ ያወጣ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!10462481_668385689913035_7014532587449142359_n