May 4th, 2014
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ትላንት ማታ የአንድነትን ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ በፌስቡክ ማሳወቃቸው ይታወቃል። ዛሬ ጠዋት ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ ሰማያዊ አርማ ያለበት ልብስ በመልበስና የሰማያዊ ፓርቲ አርማ በመያዝ፣ አስቀድመው የሰልፉን አዘጋጆች ሳያሳውቁ ወደ አንድነት ጽ/ቤት ጥቂት የሰማያዊ ወጣቶች ይመጣሉ።

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በሰልፉ እንዳይሳተፉ በአንድነቶች ተከለከሉ የሚል አንዳንድ ትሽቶች በሰማያዊዎች በሶሻል ሜዲያዎች ተለቀዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ፣ አንድነት ሰልፍ ለማዘጋጀት እየሞከረ ባለበት ወቅት ጣልቃ በመግባት፣ ለአንድነት ፓርቲ እውቅና ተነፍጎ ለሰማያዊ በመፈቀዱ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወቃል። በሰልፉም ወደ 3፣ 4 መቶ የሚገኙ ዜጎች የነበሩ ሲሆን፣ በሰልፉም ወቅት ከፖሊስ ጋር ግብግብ እና ረብሻ መፈጠሩን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ተመልክተናል።
የአንድነት የሰልፉ አዘጋጆች፣ ሰልፉን በሰላም እንዲጠናቀቅ ለመርዳት፣ አላስፈላጊ መፈክሮችና ባነሮች እንዳይንጸባረቁ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭቶች እንዳይፈጠሩ፣ ብዙ ዝግጅቲች አስቀድመው ሲያደርጉ እንደነበረ የሚገልጹት የአንድነት አደራጆች፣ የሰማያዊ ፓርቲ በኦፊሴል ሰልፉን እንደሚቀላቀሉ የገለጹበት ሁኔታ እንደሌለ አስረድተው፣ አስቀድሞ አብሮ መገናኘት ቢቻል ኖሮ መፈክሮችን ፣ ፋልየሮች፣ ቅስቀሳዎች አብሮ ማድረግ በተቻለ ነበር ሲሉ ያስረዳሉ።
ሰማያዎች በድንገት ከሰልፉ አዘጋጆች እውቅና ዉጭ፣ ከሌላው ህዝብ የተለየ፣ የሰማያዊ ፓርቲን አርማዎች ይዘው መምጣታቸው፣ ትክክል እንዳልነበረ ሰማያዊዎች በሚነገራቸው ጊዜ «አንድነት ሂዱልን አለን» በሚል በአንድነት ላይ ዘመቻ መክፈታቸው፣ አሳዛኝ እንደሆነ ይናገራሉ።
«ሰማያዊዎች ለምን አንድነትን እየተከታተሉ ረብሻ እንደሚፈጥሩ አይገባኝም። ያለፈው ሳምንት የነርሱ ሳምንት ነበር። ማንም በነርሱ ሥራ ጣልቃ አልገባም። አሁን ሌሎች ድርጅቶች በሚያዘጋጁት እንቅስቃሴ ላይ እንደ ሌላው ሕዝብ በአክብሮት መቀላቀል እንጂ፣ የሌሎችን ሥራ ለማበላሸት መሞከሩ ማን ይባላል ? » ሲሉ በሰማያዊዎች የታየው አፍራሽ ተግባር እንደሆነ ይናገራሉ።
«ከአንድነት ፓርቲም ሆነ ከሌሎች ጋር አብረው መስራት ከፈለጉ፣ መጀመሪያ ቪጂላንቲ ባህሪያቸውን መቀየር አለባቸው። ተቋማዊ መግባባት፣ መክበባር፣ ምን ማለት እንደሆነ መረዳት አለባቸው። በስሜት ሳይሆን በቁም ነገር በአመራር ደረጃ አብሮ መነጋገርና መመካከር ያስፈልጋል» ሲሉ የሰማያዊዎች «ሂዱልን ተባልን » የሲሻል ሜዲያ ዘምቻን አሳፋሪ ብለዉታል።
ዳዊት ሰለሞን የነበዉን ሁኔታ በዚህ መልክ አስቀምጦታል፡
« ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ለመካፈል የሰማያዊ አምስት ወጣቶች የሰማያዊ ፓርቲ ስያሜና አርማ ያለበትን ቲሸርት በመልበስ ሰልፉ ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብለው ወደ አንድነት ቅጥር ግቢ መጡ፣ ሰልፉን የሚያደራጁ የአንድነት አባላት በሰልፉ ስለሚለበስ ልብስ፣ስለሚያዙ መፈክሮችን በተመለከተ ቀደም ብለው ሲሰሩ ስለነበሩ የሰማያዊ አባላት የፓርቲውን ልብስ ለብሰው መምጣታቸውን በመመልከታቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት የሆነውን ብርሃኑ ተክለያሬድን ለማናገር ጠራሁት። «ብርሃኑ በሰልፉ ለመካፈል ስለመጣታችሁ አክብሮት አለን ነገር። ግን ቲሸርቱን ለብሳችሁ እንደምትመጡ ብትነግሩን ጥሩ ነበር፡፡» አልኩት። ብርሃኑ አላስጨረሰኝም «መሄድ እንችላለን» አለኝ፡፡
«ያንን ማድረግ የራስህ ምርጫ ነው፣ ሂድ ሳይሆን ያልኩህ በእንዲህ አይነት መንገድ እንደምትመጡ ብትነግሩን መልካም ይሆን ነበር» አልኩት። እናም ከአራት ጓደኞቹ ጋር በመሆን ግቢውን ለቅቀው ሄዱ።፡ከደቂቃዎች በኋላ «114 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአንድነት ሰልፍ እንዳይገኙ ተባረሩ» በማለት ማውራት ጀመሩ፡፡(መጥተው የተመለሱትን የሰማያዊ አባላት የሚያሳይ ፎቶግራፍም ለማስረጃነት ይመልከቱ፡፡)