በባህር ዳሩ ሰልፍ ከሰባ ሺህ በላይ ሕዝብ ነበር። በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይደረጋል (መግለጫ ከአንድነት)

February 27th, 2014    
የአንድነት ፓርቲ ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚሆን ሕዝብ ድምጹን ለማሰማት መዉጣቱ ገልጾ፣ ለባህር ዳር ሕዝብ ያለዉን አክብሮኢትና አድናቆት የካቲት 20 ቀን 2006 ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ።
ፓርቲ የባህር ዳሩ አይነት እንቅስቅሴ በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎችን እንደሚደረጉ ያሳወቀ ሲሆን በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሰጡና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ከባዶ ጭንቅላት ይሻላል ባዶ እግር


 ከነጻነት አድማሱ
የካሀዲ መንጋ ቃሉ የሰበረ


የሀገር ደላላ ህዝቡን ያሳፈረ


ነፃነቱን ሽጦ ለጌታው ያደረ


በፍቅረ ንዋይ ዓይኑን የታወረ


ማንታ ምላሱ ምን ብሎ ተናገረ?



እሪ በሊ ጎንደር የፋሲል መኖሪያ


እሪ በሊ ጎጃም የጀግናው በላያ


ሰምቷል ወይ ወሎ ዴሴና ወልዲያ


ሁሉም ብሄረሰብ መላ ኢትዮጵያ።


አዎ!! እውነት ነው!!


ወገን ይደፈራል ባለቤቱ ሲተኛ


ከሽ ጦር ይብሳል አንድ ውሸተኛ


ህዝቡን የካደ የቁራ መልእክተኛ


ባህል የማይገዛው ባለጌ ነውረኛ


ሕግ የማያውቅ አፋኝ መተተኛ


ታሪክ አጉዳፊ አጉል እብሪተኛ


ምን አሉ ምን አሉ ስለኛ ስለኛ?

ገና ጉድ ይታያል ከተገኘ ሰሚ


ህልናው የሸጠ እናቱን አስማሚ


ህዝብን አዋራጅ ሀገር አውዳሚ


በኢትዮጰስያ ተፈጠረ ዛሬ


ከጫካ የመጣ የዱር አውሬ።

ከደንቆሮ መንጋ የብአዴን ካድር


ለሆዱ ያደረ የወያኔ አሽከር


ከባዶ ጭንቅላት የባንዳ ንግግር


ይሻላል አማራው በባዶ እግር።

አንተ ወጣቱ አደራ ተቀባይ


የወገን መከታ አንትንኩኝ ባይ


የለውጥ አርበኛ ሽቦ አቀጣጣይ


ኮርቻለሁ ባንተ ድምፅህ ስሰማ


ብርሃን ሲፈነጥቅ ከድቅድቅ


ከዚያው ከባህር ዳር ከጎጃም


ከበላይ ዘለቀ የወረስከው አርማ።


አዎ!!


የትግልህ ቋያ በሌላም ይቀጥላል


ከዳር እስከ ዳር በሁሉም


የኢትዮጵያ ጠላት እንደጨው


ታሪክ ምስክር ነው ህዝባችን


ጨለማ


ከተማ


ያስተጋባል


ይሟሟል


ያሸንፋል።





በኢትዮጵያ የማዕድን ሙስናን ለመሸፋፈን የሚደረገው ዘበት

February 26, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በማዕድኑ ዘርፍ የሚያካሂደውን ሙስና በማደብዘዝ እና በመሸፋፈን ንጹህ መስሎ ለመታየት እና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ለማግኘት በማሰብ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት(Extractive Industries Transparency Initiative (EITI)) ለተባለው ድርጅት ዕጩ አባል ለመሆን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ይፍጨረጨራል፡፡ የገቢ ምልከታ ተቋም/Revenue Observation Institute የቦርድ ሊቀመንበር እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የቦርድ አባል የሆኑት አንቶኒ ሪቸር እንደሚሉት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2010 ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ነበር፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ (Proclamation on Charities and Societies) የሲቪክ ህዝብ ማህበራት ቡድኖች ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው እና በሂደቱም ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚከለክል ደንቃራ በመሆኑ ነው የሚል ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡ ቦርዱ ‘የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት አዋጅ’ በስራ ላይ እንዳይውል ኢትዮጵያ ‘እስካልሰረዘች ድረስ የዓለም አቀፉ ድርጅት አባል እንድትሆን በተጨባጭ እንደማይፈቅድ ውሳኔ አስተላልፏል’፡፡ አንድ አገር ለአባልነት ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ሲደረግበትበአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነትተነሳሽነት/EITI ታሪክ የመጀመሪያው ብቸኛው ድርጊት መሆኑ እና እንዲሁም ደግሞ ለዚህእርምጃ መሰረት ሆኖ የቀረበው በግልጽከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዘ መሆኑ ነበር፡፡The regime in Ethiopia is seeking EITI membership
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI “የመንግስታት፣ የኩባንያዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እና የዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጥምረት“ ሲሆን ይህም “በጠንካራ ሆኖም ግን ለለውጥ ክፍት የሆኑ የኩባንያዎች ክፍያ እና ከተፈጥሮ ዘይት፣ ጋስ እና ከማዕድን የሚገኙ የመንግስት ገቢዎች በሰነድነት የሚታተሙበት እና የሚከሰቱ ውስንነቶች የሚቀነሱበት የአሰራር ሂደት“ የሚተገብር ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ነው፡፡ በግልጽ ለማስቀመጥ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ተጠያቂነትን እና ግልጽነትን ለማሳደግ በአባል አገራት የሚገኙ ኩባንያዎች እና መንግስታት በአምራች ማአድን ኢንዱስትሪዎቻቸው የሚገኙትን ገቢዎች በግልጽ ለማሳወቅ ዓላማን ያደረገ ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው፡፡ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI “የገቢን ግልጸኝነት በአካባቢ ደረጃ መስፈርት በማውጣት “ እንዲተገበር በማደረግ በስፋት ይታወቃል፡፡
በአትዮጵያ ያለው ገዥው አካል፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት አባል መሆንን ይፈልጋል፡፡ አባል ለመሆን የሚፈልገው ግን በማዕድኑ ዘርፍ በእውነተኛነት ላይ የተመሰረተ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለማስፈን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው ዓላማው በሙስና የተዘፈቀውን የማዕድን ዘርፍ ለውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ገበያ ለማቅረብ እንዲመቸው የእውነተኛነት መታወቂያ እና ለመልካም አስተዳደር እና ለጥሩ ገበያ መለመድ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ፈቃድ እና በገዥው አካል የአባልነት ጥያቄውን ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ያቀረበው ከተቋሙ የእወቅና ድጋፍ በማግኘት የወደፊት ዓለም አቀፍ የመዋለ ንዋይ አፍሳሾችን እና የገንዘብ ተቋማትን በአገሪቱ መልካም አስተዳደር እንዳለ እና ደህንነት እንዲሰማቸው ለማስመሰል ታማኝነት በጎደለው መልክ የማታለል ዘዴ በመጠቀም ገዥው አካል ከፍተኛ ለሆነ ግልጽነት እና በእርግጥም ተጠያቂነት ለማስፈን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደረገ መሆኑን እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ለማታለል ድፍረት የተሞላበት ንቀት፣ ስልታዊ የድርጊት መርሀ ግብር እና በሀሰት ላይ በተመሰረተ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት እንዳለ በማስመሰል እና በማዕድኑ ዘርፍ አስተማማኝ የሆነ ደህንነት መኖሩን እንዲጠብቁ በማድረግ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ያልጠረጠሩትን ነገር በላያቸው ላይ ለመጫን ነው፡፡
እውነታው ግን ገዥው አካል ለእራሱ ዜጎች የግል ንብረት ወይም መዋዕለ ንዋያቸውን በአገር ውስጥ ለሚፈያስሱ ባለሀብቶች ንብረት ዋስትና የሌለው እና አጠቃላይ በሆነ መልኩ ሲታይ ግን በተቃራኒው ምቹ ያልሆነ ከባቢያዊ የንግድ ስርዓት ሁኔታ ዘርግቶ የሚገኝ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ኮፋክ/COFACE የተባለው ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ባቀረበው ዘገባ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአገሮች መካከል የሚሰጥ የኢንሹራንስ ብድር እና የብድር አገልግሎት አስተዳደር ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንዲህ በማለት ድምዳሜ ሰጥቷል፣ “አስቸጋሪ የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታ በተንሰራፋበት፣ የማህበራዊ ዘርፍ መረጃ እጥረት ባለበት ሁኔታ፣ ሙስና እና የግል ዘርፉን በማስገደድ ከውድድር ውጭ ማስወጣት“ እንደ መርህ በተያዘበት ሁኔታ ልማት እንደማይታሰብ ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ “ሙስናን ማዕከል“ ያደረገ ነው፣
በኢትዮጵያ ያለው የማዕድን ዘርፍ የሙስና ማዕከል እና የተግባር መገለጫ እንዲሁም የባለስልጣኖች የሙስና ድርጊት እና የማታለል ወንጀል ማሳያ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ባቀረበው መጠነ ሰፊ ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ በሙስና ተተብትበው ከተያዙ የኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል የማዕድኑ ዘርፍ አንዱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ” ውስጥ “ሰባት ዓይነት የሙስና አደጋዎችን” ነቅሶ ያወጣ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ “ሶስቱ ዋነኛ አደጋዎች” ተብለው የቀረቡት “ፈቃድ በማውጣት፤ በፈቃድ አያያዝ ላይ በሚደረጉ ስምምነቶች እና በማዕድን ገቢዎች ላይ” የሚደረገው ሙስና ነው፡፡“ ሌላው አሳሳቢው የሙስና ዓይነት “ከካሳ ክፍያዎችና ከአካባቢ ነዋሪዎች ግዴታ፤ ኮንትራክተሮችና አምራቾች ከማዕድን ካምፓኒዎች ጋር ከሚያደርጓቸው የስምምነት ውሎች፤ ከካምፓኒዎች ምርቶች ጥራት መዝቀጥ እና የማዕድን ምርቶችንና መሳሪያዎችን ከመዝረፍ“ አንጻር የሚደረጉ የሙስና ዓይነቶች ናቸው፡፡
የዓለም ባንክ በግልጽ እንዳስቀመጠው “ፈቃድ በማውጣት ሂደት ጊዜ” “ባለስልጣኖች ፈቃድ ለማውጣትና ለመስጠት፤ ፈቃድ በቶሎ አውጥቶ ለመስጠት ወይም ደግሞ ብዙ ጉዳት የማያመጡ የፈቃድ ሁኔታዎችን ለመስጠት ከማዕድን ካምፓኒዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ይወስዳሉ ወይም ጉቦ ይቀበላሉ፡፡ ሌላው ተመሳሳይ አደጋ ባለስልጣኖች ፈቃድ በሚሰጡበት ወቅት ፈቃድ ከሚሰጡት ካምፓኒ ጋር በስውር ለእራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው ስምምነት ያደርጋሉ፤ ፈቃድ ለመስጠት የመሬት ባለቤትነትን ሊያገኙ ይችላሉ፤ የተወሰነ ድርሻ በአክሲዮን መልክ ወይም ከትርፍ የተወሰነ ድርሻን ይጠይቃሉ፤ ለእራሳቸው ወይም ለጓደኞቻቸው ቅድሚያ ምዝገባ እንዲያደርጉላቸው ከፈቃድ አውጭዎች ጋር ይሞዳሞዳሉ፡፡” በፈቃድ ስምምነት አያያዝ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ሆን ብለው የማዕድን ስምምነቶችን (ለምሳሌ ያህል የአካባቢ፤ የጤና እና የደህንነት ህጎችን እንዲሁም በአካባቢው የማዕድን ካምፓኒው በኃላፊነት የመጠየቅ ደረጃና ሁኔታን ያካትታል) በስራ እንዳይውሉ ያጨናግፋሉ፡፡
በማዕድን ገቢ አሰባሰብ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ለመሬት መጠቀሚያና ለታክስ የሚያደርጓቸውን ወጭዎች ለመቀነስ ሲባል ሆን ብለው ያመረቱትን ምርት መጠንና ትርፋቸውን በማሳነስ ወጭዎችን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ገዥው አሰተዳደር ከማዕድን ካምፓኒዎች የሚገኘውን ገቢ በትክክል ለማወቅ ነጻ የሆነ የማረጋገጫ አካል የለውም፡፡ ለመሬት መጠቀሚያና የገቢ ግብር መጠን በአጠቃላይ የሚወሰነው የማዕድን ካምፓኒዎች በአመኑት የምርት መጠንና ትርፍ ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ምክንያቱም በፌዴራል፤ በክልልና በከተሞች አስተዳደር ያሉ የፈቃድ ሰጭ ባለስልጣኖች በካምፓኒዎች ስላለው ሀብት የሚገልጽ ዝርዝርና ተጨባጭ መረጃ ስለማይገኝ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የማዕድን ካምፓኒዎች ካፒታላቸውንና የስራ ማስኬጃ ወጫቸውን ከፍ ሲያደርጉ ምርቶቻቸውንና የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥና የገቢ ማጭበርበር ክስተት መኖሩ ሲረጋገጥ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች በመንግስት አካላት እርምጃ እንዳይወሰድባቸውና የሚመለከታቸው አይተው እንዳላዩ እንዲያልፏቸው ኃላፊነቱ ላላቸው ባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
እ.ኤ.አ የ2012 የዓለም ባንክ ዘገባ በማዕድን ዘርፉ እስከ አሁን በተጨባጭ በተግባር የታዩና የተመዘገቡ የሙስና ዓይነቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ ጉቦ መቀበል፤ የሀሰት መረጃ መስጠት፤ በህገወጥ መንገድ ከማዕድን ካምፓኒዎች ገንዘብ መውሰድና ነጻነታቸውን ዝቅ አድርጎ ማየት፤ እና የውስጥ ህገወጥ መረጃዎችን በመጠቀምና ነጻነት የሌላቸወን ካምፓኒዎች በማጭበርበር ለአካባቢው ነዋሪዎች የተመደበውን ካሳ መስረቅ ሲሆኑ ሰፋ ባለ መልክ በማዕድን ዘርፉ የሚካሄዱ የሙስና ዓይነቶች ናቸው፡፡ በዓለም ባንክ ተመዝግበው የሚገኙ በመጥፎ ምሳሌነታቸው በግልጽ የሚታዩ ለህሊና የሚሰቀጥጡ የሙስና ዓይነቶች የሚከተሉትን ያካትታል፣
አንድ የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት ከፍ ያለ ገንዝብ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ታላላቅ ባለስልጣኖችና የካምፓኒ ባለቤቶች ይህንን ገንዝብ በሚስጥር ይይዙና ገንዘቡ በውጭ ባንክ አካውንት ለባለስልጣኖች እንዲደርስ ይደረጋል፡፡
አንድ ባለስልጣን የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቱን የስራ ፈቃዱ በቶሎ እንዲወጣለት ከፈለገ ለለጋሽ ድርጅት በርከት ያለ ገንዘብ መስጠት እንደሚጠበቅበት ይነግረዋል፡፡ ለጋሽ ድርጅቱ ሀቀኛ መስሎ ቢታይም ለባለስልጣኖች ለግል ወይም ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው ጥቅም ከመዋል ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ ክፍያ ሊውል ይችላል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት እንዲችል ካለው አሰራር አንጻር የጤናና የደህንነት ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ባለስልጣኑ ለካምፓኒ ባለቤቱ ጉቦ ካልከፈለ በስተቀር ተጨማሪና አላስፈላጊ የጤናና የደህንነት ግዴታዎች እንደሚጭንበት ይነግረዋል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት የአካባቢ ጥበቃ ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ይህም የሚያቀርበው ዕቅድ የአካባቢውን የውኃ አቅርቦት ከመርዛማ ኬሚካሎች በአስተማማኝ ሁኔታ ላያስወግድ ይችላል፡፡ አስተማማኝ የመርዛማ ኬሚካሎች ቁጥጥር ለማድረግ ወጭው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰለዚህ የተጓደለውን የቁጥጥር ስርዓት በመከተል ካምፓኒው ብዙ ወጭ ላለማውጣትና በተጓደለው ሁኔታ ለመስራት እንዲችል የስራ ፈቃዱን ለሚሰጠው ባለስልጣን ጉቦ ይሰጣል፡፡
ባለስልጣኖች ከማዕድን ካምፓኒው ትርፍ ድርሻ እንዲኖራቸው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ካምፓኒው ባለቤት የስራ ፈቃድ በባለስልጣኑ ውሳኔ መሰረት አገኛለሁ በሚል እምነት ለባለስልጣኑ ዘመድ ከማዕድን ፕሮጀክቱ ነጻ የትርፍ ድርሻ ሊሰጠው ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች በድብቅ በእራሳቸው ለተያዙ ካምፓኒዎች የስራ ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ ሊጠየቅበት የሚችል መሬት በድብቅ ያገኛሉ፡፡
አንድ ባለስልጣን የአንድ የማዕድን ቦታ የስራ ፈቃድ ይወጣበታል የሚል ግንዛቤ ካለው ባለስልጣኑ የስራ ፈቃዱ ከመውጣቱ በፊት መሬቱን ቅድሚያ ሊያከራየው ይችላል፡፡ የስራ ፈቃዱ ከተሰጠ በኋላ ግን የመሬቱ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ ወይም ባለስልጣኗ በመሬቱ ላይ ያለውን ወይም ያላትን የመሬት ባለቤትነት መብት በመጠቀም ለመሸጥ ወይም ለካምፓኒው የስራ ፈቃድ በመስጠት ለማከራየት ይችላሉ፡፡
ካምፓኒዎች የተሰጣቸውን የስራ ፈቃድ በህገወጥ መልክ ሊሸጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ የምዝገባ ስራን ማጭበርበር ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
አንድ በመንግስት መ/ቤት መምሪያ የማዕድን ስራ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችል ባለስልጣን አንድ ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ማውጣት እንደሚፈልግ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ካለው ግንኙነት አንጻር የቢዝነሱ ሰው በዚያ ቦታ ላይ በፍጥነት የስራ ፈቃድ ማውጣት እንዲችል ሊያሳስበው ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ለቢዝነሱ ሰው የስራ ፈቃዱን ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚያም የማዕድን ካምፓኒው ከቢዝነሱ ሰው ጋር የስራ ፈቃዱን ይገዛውና የቢዝነሱ ሰው ከባለስልጣኑ ጋር ትርፍ ሊጋራ ይችላል፡፡
አንድ አሳሽ ማዕድን ያለበትን ቦታ ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቦታውም ላይ ምልክት በማድረግ ጉዳዩ ወደሚመለከተው የስራ ፈቃድ ሰጭ አካል በመቅረብ የባለቤትነት ሰርቲፊኬት ማግኘት እንዲችል ሊያመለክት ይችላል፡፡ ሙሰኛ ባለስልጣን ግን ይህንን ግኝት ተቀብሎ አስሶ ባገኘው ስም አይመዘግብም፤ ይልቁንም የቢዝነስ ጓደኛ በመፈለግ በቢዝነስ ጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡ ይኸ ሙሰኛ ባለስልጣን በመጀመሪያ አስሶ ያገኘውን ሰው ሀሰት በመንገር የማዕድኑን ሀብት ከእርሱ በፊት ሌላ እንዳገኘው ይነግረዋል፡፡
ባለስልጣኖች ዘመዶቻቸው የኮንትራት ስምምነት በመፈራረም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ህገወጥ በሆነ መልኩ ከማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ጋር እንዲፈራረሙ ያደርጋሉ፡፡ ፈቃድ ሰጭው አካል ኮንትራቱን ከመስጠት አንጻር ወይም ማህበረሰባዊ የልማት ዕቅድን ከማምጣት አኳያ በካምፓኒው ሙሉ ወጭ ብዙ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ለካምፓኒው ይነግረዋል፡፡ ለምሳሌ ካምፓኒው መንገድ፤ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል እንዲገነባ ወይም አንዲጠግን ሊገደድ ይችላል፡፡ በዚህ መሰረት የመንግስት ባለስልጣኑ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን የመሰረተ ልማት ስራዎች ኮንትራት በድብቅ ለባለስልጣኑ ዘመድ በኮንተራት እንዲሰጥ ይነገረዋል፡፡
ባለስልጣኖችና የአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መድረስ ያለባቸውን ካሳዎች ይበላሉ፡፡ የማዕድን ስራ ካምፓኒዎች ለማህበረሰቡ የሚሰጡ ካሳዎች ዋጋ ከትክክለኛው ግምት በታች ዝቅ እንዲል ለባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
የአካባቢ ኗሪ ማህበረሰብ አባላት በመሬት የስራ ፈቃዱ መሰረት በሀሰት መሬቱን እንዳገኙ ይናገራሉ፡፡ ኮንትራክተሮችና አምራቾች በተጭበረበሩ የጨረታ፣ ይዞታዎችና ችግር ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅና በማጽደቅ ይሰማራሉ፡፡
የማዕድን ካምፓኒዎች ስለማዕድኖች ዓይነትና ጥራት ወይም ደግሞ ለአጽዳቂዎች ጉቦ በመስጠት የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሙስና ይሰራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዙ ይህ ዓይነቱን ሙስና በሚመለከት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ እንደማስመሳያነት?
በስልጣን ላይ ያለው ገዥው አካል ከማዕድኑ ዘርፍ ከሚገኘው ገቢ ጋር በተያያዘ መልኩ በሀሰት ላይ የተመሰረተ የማስመሰያ ምናባዊ የማታለል ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡ የገዥውን አካል ዋቢ በማድረግ በወጡ መረጃዎች መሰረት “የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ዓመት የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት ከማዕድኑ ዘርፍ በአገሪቱ ውስጥ በባህላዊ የአመራረት ዘይቤ በተሰማሩ አምራቾች አማካይነት ተመርቶ ወደ ውጭ ከተላከው ምርት 419 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ አግኝቷል፡፡ ከዚሁ ወደ ውጭ ከተላከው የማዕድን ምርት በመጠን የወርቅምርት ከፍተኛውን ደረጃ በመያዝ 409.1 ሚሊዮን ዶላር የውጭምንዛሬ ያስመዘገበ ሲሆን ለጌጣጌጥ የሚውል ድንጋይ እና ታንታለም እንደየቅደም ተከተላቸው 9.3 ሚሊዮን እና 1.6 ሚሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የሁለተኛ እና የሶስተኛነት ደረጃን ይዘዋል፡፡ ይህም ገቢ የተገኘው 7,878.3 ኪ/ግ ከሚመዝን ወርቅ፣ 20,126.3 ኪ/ግ ከጌጣጌጥ ከሚውል ድንጋይ እና 32.95 ቶን የሚመዝን ደግሞ ከታንታለም የተገኘ ነው… ከፍተኛ የሆነ የአመራረት ዘይቤን በመከተል በአገሪቱ ውስጥ ወርቅ በማምረት ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ሚድሮክ/MIDROC የተባለው ብቸኛ ኩባንያ ነው፡፡“ ሌሎች ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት “በአጠቃላይ ከአገሪቱ ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት ውስጥ የማዕድን ምርት 23 በመቶ ድርሻ በመያዝ ለኢትዮጵያ ሁለተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ለመሆን በቅቷል፡፡“ እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ዋናው ጉዳይ ግን የሳጥኑን መክፈቻ ቁልፍ ከያዙት ሰዎች በስተቀር በማዕድን ዘርፉ የተመረተው ምርት በትክክል ምን ያህል ገቢ እንዳስገኘ በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ ገዥው አካል ከማዕድኑ ዘርፍ የተገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነ የሚያጣራ ነጻ የሆነ ምንም ዓይነት የአሰራር መንገድ ስለሌለ ከኩባንያዎች በሚገኙ ዘገባዎች ላይ ብቻ በመመስረት መገመት እንደሚኖርበት ይናገራል፡፡ እንዴት የሚመችነገር ነው እባካችሁ! እውነታው ግን ከማዕድኑ ዘርፍ ምርት ከሚገኘው ገቢ ዋናዎቹ ተጠቃሚዎች ሀብቱን በብቸኝነት የተቆጣጠሩ የገዥው አካል ቡድኖች፣ ለእነዚህ ቡድኖች አቀባባይ ሆነው በማዕድን ምርት ንግዱ ስራ ላይ በግንባር የተሰማሩ ሰዎች እና “በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ” ቁጥጥር ስር ያሉ ሌሎች ድርጅቶች ናቸው፡፡ ከማዕድን ፈቃድ ሽያጭ እና በህገወጥ መንገድ ከማዕድን ምርት ዘርፉ የተገኘው ገንዘብ በተያያዘ መልኩ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና ስፋት እና ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም፡፡ ሆኖም ግን ከወርቅ ማምረቻ ቦታዎች በቅርብ ርቀት ከሚገኙ ጥርጊያ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በመቶዎች ኪሎ የሚቆጠር የወርቅ ምርት ያለምንም ፍተሻ በአውሮፕላን እየተጫነ ከአገር እንደሚወጣ አስተማማኝነት ያላቸው የዓይን እማኞች ምስክርነታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት እና ዓይን ያወጣ የማዕድን ምርት ዘረፋ በተንሰራፋበት ሁኔታ ነው ገዥው አካል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዓለም አቀፋዊ ተቋም አባል ለመሆን በመፈለግ የአባልነት ጥጣቄ እያቀረበ ያለው፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ለምንድን ነው የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅያደረገው?
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI እ.ኤ.አ በ2011 ባረቀቃቸው ህጎቹ የሲቪል ማህበረሰቡ ነጻ ሆኖ መስራት እና ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ መቻል ለዕጩነት እና ለአባልነት የመምረጫ መስፈርት የመሰረት ድነጋይ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ለአባልነት ብቁ ሆኖ ለመገኘት በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል “የሲቪል ማህበረሰቡን ተሳትፎ ሊያዉኩ የሚችሉ እንቅፋቶችን ማስወገድ እና ገዥው አካል “የሲቪል ማህበረሰቡን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እና በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI የሚሳተፉ ኩባንያዎች ተወካዮችን መብት ማክበር ይኖርበታል፣“ ገዥው አካል “ለሲቪል ማህበረሰቡ እና ለኩባንያዎች በስራ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ሂደት ጊዜ ምንም ዓይነት እንቅፋቶች እንደማይኖሩ ማረጋገጥ አለበት፡፡“ እንዲሁም “ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ኩባንያዎች አስፈላጊ የሆኑ ህጎችን፣ ደንቦችን እና አስተዳደራዊ ህጎችን እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ተግባራት በተጨባጭ ለመተግበር የሚያስችሉ ማዕቀፎችን ለማመቻቸት ዋስትና መስጠት አለበት፡፡“
ከዚህም በላይ ገዥው አካል “የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን የስራ ማዕቀፎችን ከሚያጠቡ ወይም ደግሞ የህብረተሰቡን በነጻነት የመወያየት ዕድል ከሚያደናቅፉ ተግባራት መታቀብ አለበት፣“ እንዲሁም “የሲቪል ማህበረሰቡ እና የኩባንያዎች ተወካዮች በግልጽነት እና በተፈጥሮ ሀብቶች አያያዝ ጉዳዮች ላይ ነጻ ሆነው መወያየት እንዲችሉ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡“ ገዥው አካል የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች የብዙ ባለድርሻ ቡድኖች አባላት ሆነው እንዲሰሩ ማረጋገጥ አለበት፡፡ እንዲሁም “በፖሊሲ ጉዳዮችም ከመንግስት እና/ወይም ከኩባንያዎች ነጻ ሆነው መስራት አለባቸው፣“ እናም “ያለምንም መሰናክል ወይም ጭቆና ከሚፈልጓቸው ቡድኖችም ጋር አብረው ነጻ ሆነው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI በግልጽ የሚፈልገው “የሲቪል ማህበረሰቡ ቡድኖች፣ ኩባንያዎች እና ወኪሎቻቸው ስለ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ሀሳቦቻቸውን ያለምንም ስጋት፣ ግዳጅ እና የበቀል ስሜት ሳይኖርበት በነጻነት ሀሳቦቻቸውን መግለጽ እንዲችሉ“ ለማድረግ እና “በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ላይ ተሳትፎ ያላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች በEITI በሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ግልጽ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሙሉ ነጻነት ማግኘት አለባቸው፡፡“ በማለት ህጉን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በኢትዮጵያ ባለው ገዥው አካል ከእንቅስቃሴ ውጭ ተደርገዋል፣
እ.ኤ.አ የወጣው የ2009 የገዥው አካል የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ህግ አዋጅ ቁጥር 621/2009/Charities and Societies Proclamation No. 621/2009 በኢትዮጵያ ያሉ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለማጥፋት አዋጁን መሳሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 ረቂቅ አዋጁን በጥሞና በማየት “የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ረቂቅ አዋጁን መመርመር“ በሚል ርዕስ ረዥም ትንታኔ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትንታኔዬ ላይ አዋጁ ጠቀሜታ የሌለው መሆኑን በማመን ይህ አዋጅ የማይጠቅም በመሆኑ ለምን መወገድ እንዳለበት 10 አሳማኝ ምክንያቶችን ዘርዝሬ አቅርቢያለሁ፡፡ እንዲህ በማለትም የክርክር ጭብጤን አቅርቢያለሁ፡፡ የአዋጁ ዋና ተልዕኮ ገዥው አካል የህግ ማፈኛ አድርጎ በማቅረብ ያነጣጠረው የሲቪል ማህበራት ተቋማትን በመገደብ እና ህልውናቸውን በማጥፋት ተቋማቱ የዴሞክራሲያዊ ተግባራትን በማሳለጥ ስጋት ይፈጥሩብኛል በሚል ልሳናቸውን አስቀድሞ ለመዝጋት እና ከሚጠብቀው ፍርሀት ለመገላገል የታለመ ነው ብዬ ነበር፡፡ አዋጁ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን በዘፈቀደ እና ምንም ዓይነት የህግ ምርመራ ሳያደርግ መቆጣጠር የሚያስችል የዘፈቀደ እና ያልተጠበቀ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል የተለጠጠ እና ያልተገደበ ስልጣን እንደ ፍርድ ቤት ዳኛ መርምሮ ሳይሆን እንደፈለገው እንዲያደርግ ለበጎ አድራጎት እና ማህበራት ድርጅት ኃላፊ ስጥቷል፡፡ አዋጁ ሳይፈለግ የመጣ በበጎ አድራጎት ደርጅቶች እና ማህበራት የውስጥ ጉዳዮች ላይ በኃይል የተጣለ፣ ለጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ትኩረት በመስጠት በተቋሞቹ የውስጥ ጣልቃገብነት ላይ እጁን ያስገባ እና ምክንያታዊ ያልሆኑ እና በጣም አስቸጋሪ የሆኑ እንዲሁም እራሱ ገዥው አካል የማይተገብራቸውን የገንዘብ ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ከሚታሰበው በላይ የተንዛዙ መስፈርቶችን በማቅረብ ድርጅቶቹ እንዳይሰሩ ሽባ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ አዋጁ ለመቅጣት የወጣ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አባል መሆን እና ተሳትፎ ማድረግም እንዳይቻል ለማስፈራሪያነት የወጣ ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ጭብጤም ላነሳው የምፈልገው ጉዳይ አዋጁ ህገመንግስታዊ ያልሆነ፣ የማይመች እና የሚቆጠቁጥ እንዲሁም አድሏዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch የአዋጁን መውጣት ተከትሎ አዋጁ የማያሰራ መሆኑን ለመግለጽ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፣ “የዚህ አዋጅ የታሰበው ውጤት እና በተግባር እየታየ ያለው ተጨባጩ እውነታ እንደሚያሳየው ማንኛውም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መንግስት ሳያጸድቀው እና ሳይፈቅድ ምንም ዓይነት ስራ መስራት እንደማይችል በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡“ በተደጋጋሚ እንደምለው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላለው ገዥው አካል ስለህገመንግስት፣ የህግ የበላይነት እና ስለተጠያቂነት ማስተማር ማለት መስማት እና መናገር ለተሳናቸው ዱዳዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሱ እንደመስበክ ወይም ደግሞ በጥቁር የባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡
እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2010 የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት ጸሐፊ ማሪያ ኦቴሮ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅን አስመልክቶ ያላቸውን ስጋት በቅርቡ ላረፉት ለአቶ መለስ ዜናዊ እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር፣ “ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰቡን ሚና የሚጎዳ ነው“ ብለው ነበር፡፡ አቶ መለስ ግን የሴትዮዋን ስጋት ወደ ጎን ገሸሽ አደረጉት፡፡ ሆኖም ግን አዋጁ በኢትዮጵያ ያሉትን የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ተቋማትን ወዲያውኑ ማክሰም ጀመረ፡፡ እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ “እ.ኤ.አ በ2010 መጀመሪያ አካባቢ ብዛታቸው 4,600 የነበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብዙዎቹ እንዲከስሙ ተደርገው በመንገዳገድ ላይ የሚገኙ 1,400 ብቻ ሆነው ተገኙ፡፡ ከመክስም የተረፉት ወደ 30 በመቶ ብቻ መሆናቸው ሲታይ ሁኔታው አስደንጋጭ መሆኑን ያመላክታል፡፡ መረጃዎቼ እንደሚያስረዱት በህይወት ከተረፉት ድርጅቶች መካከልም የአብዛኞቹ ድርጅቶች የሰው ኃይል በ90 በመቶ ወይም በበለጠ ቅናሽ አሳዬ፡፡“ በግልጽ ለማስቀመጥ አዋጁ በኢትዮጵያ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ከስራ ውጭ አድርጓል! በተመሳሳይ ወር ገዥው አካል ቀደም ሲል የተቋቋሙትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን የእነዚህን ሁለት ጠንካራ ተቋማት አቅማቸውን ለማሽመድመድ በማሰብ ዓላማቸው እና የሚፈጽሟቸው ተግባራት ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ወንጅሎ የባንክ ሂሳቦቻቸውን በመዝጋት ንብረቶቻቸውን አገደ፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 ገዥው አካል አስር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን/NGOs ከአዋጁ በተጻራሪ መንገድ ሲንቀሳቀሱ አገኘኋቸው በሚል ሰበብ መዝጋቱን እና ሌሎች በደርዝን የሚቆጠሩት ደግሞ የማይገባ ባህሪ በማሳየት ላይ ናቸው ያላቸውን ተቋማት እውቅና እንደሚሰርዝ በመዛት አወጀ፡፡ ገዥው አካል በተጨማሪም የሌሎች 17 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳይ በመጣራት ላይ ያለ መሆኑን ተናገረ፡፡ ገዥው አካል እርምጃውን 400 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከአዋጁ በተጻራሪ እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ሰበብ ከሰጠ በኋላ በቀጣይ አስፈላጊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በማስረገጥ ዝቷል፡፡ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2012 ሄንሪክ ቦል ፋውንዴሽን/Heinrich Boll Foundation የተባለ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰራ የጀርመን አገር መንግሰታዊ ያልሆነ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ንብረቱን ሸክፎ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ የተጣሉትን እገዳዎች በመቃወም ከሀገር ለቅቆ ወጣ፡፡
እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2013 ገዥው አካል በሶስት መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ማለትም አንድ ኢውሮ/ One Euro፣ የእስላም ባህላዊ እና የምርምር ማዕከል/the Islmaic Cultural and Research Center፣ እና የጎሄ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ሴቶች የልማት ድርጅት/the Gohe Child, Youth and Women Development Organization የተባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን “ህገወጥ የኃይማኖት እንቅስቃሴ” ማድረግ የሚል ክስ በማቅረብ ስራቸውን በማቆም ከሀገር እንዲለቅቁ አድርጓል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2013 “በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት/US Agency for International Development የገንዘብ ድጋፍ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት 29 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ 27ቱ ከአዋጁ ህግ በተጻራሪ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ብሎ ፈርጇቸዋል፡፡“ እ.ኤ አ. በ2013 ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አዋጁን በማስመልከት የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣ “የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በዓለም ላይ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ከወጡ ጨቋኝ ህጎች ውስጥ አንዱ ነው… እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰቡ የእንቅስቃሴ ምህዳር፣ የፕሬስ ነጻነት፣ እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የመግለጽ መብት እየጠበበ መጥቷል፣“ በማለት ዘገባውን ቋጭቷል፡፡
እ.ኤ.አ የ2014 የቤርቴልስማን የሽግግር አመላካች መለኪያ/Bertelsmann Transformation Index የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣ “በጨቋኝ ህጎች ምክንያት የብዙሀን መገናኛ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ተዘግቷል፣ የሠራተኛ እና የሙያ ማህበራት መንግስት ቀንብቦ ባስቀመጠው ማዕቀፍ ውስጥ መግባት ወይም ደግሞ እንደ ቀድሞው የመምህራን ማህበር መክሰም፣“ የሚል ሆኗል፡፡ የሚያስገርመው እውነታ ግን በአሁኑ ጊዜ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIየሚገኙት የሲቪል ማህበረሰብባለድርሻ አካላት ማለትም ግሎባል ዊትነስ/Global Witness፣ ኦፕን ሶሳይቲ ረቨኑ ዎችኢንስቲትዩት/Open Society Revenue Watch፣ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽል/Transparecny International፣ ከብዙጥቂቶቹ ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያእንዲንቀሳቀሱ ቢፈልጉ አይፈቀድላቸውም! እንዲህ ሆኖ እያለም ገዥው አካል በሚያስገርምቀልድ ነገር አቀራረብ እና እራሱን በሀሰት ጀቡኖየሞራል ስብዕና ያለው በማስመሰል ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር ለመገናኘት እና የሲቪልህብረተሰብ ተቋማት በነጻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉበተግባር ያለውን ቁርጠኝነት በአስመሳይነት ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅየሚያደርገው ሽርጉድ የማለቱ ጉዳይ ነው፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ስነስርዓቶች ላይ መቀለድ፣ በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካልየማጭበርበር ድርጊት መቆም አለበት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ላይ የጀመረው ማጭበርበር እና የዕጩ አባልነት ማመልከቻ ሰነድ ማቅረብ በተቋሙ ስነርዓት ላይ እያደረገ ያለውን ቀልድ ያመላክታል፡፡ ገዥው አካል የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዋና ዋና መርሆዎች እና ለሲቪል ማህበረሰብ መብቶች ጥበቃ በግልጽ የተቀመጡትን መስፈርቶች በሚገባ እያወቀ በዓይነ ደረቅነት የተቋሙ አባል ልሁን ብሎ የአባልነት ጥያቄ ማቅረቡ በእውነቱ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ የዕጩ አባልነት ማመልከቻው ለምን ጉዳይ እንደቀረበ በመጀመሪያ ሊመረመር ይገባል… የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን አባላት እና የእራሱን የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ክብር እና የድርጀቶቹን መርሆዎች የሚጥስ እና የሚያዋርድ ግልጽ ዘለፋ እና እንዲሁም ድርጅቶቹ ከአስርት ዓመታት ባላይ የሙስና ገመድ በሚገመድባቸው ሙሰኛ አገሮች ላይ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማምጣት አበርትተው ሲሰሩ በቆዩ ድርጅቶች ላይ ማፌዝ ነው፡:
የገዥው አካል የንቀት ዘለፋ መርሀግብር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ማህበረሰብ ለመታየት አለመቻል እና የተቋሙን የቦርድ አባላት ለማጭበርበር፣ ለማታለል እና በቦርዱ ዓይን ላይ አፍዝዝ አደንግዝ ለመጣል መሞከር የዱሮ አባባልን ስለተኩላ እና የበግ ለምድ ሁኔታ በተለይም ስለኢትዮጵያ ተኩላ መሰሪነት በበጎች መካከል ገብቶ ጸሎት ላድርስ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ገዥው አካል እውነተኛ ባህሪውን ማለትም ተኩላዊ፣ ገዳይ፣ ስግብግብ፣ ለሙስና ክፍት የሆነ፣ ሙሰኛ፣ ትርፍ አጋባሽ እና በማንኛውም ሞራላዊ ብቃቱ የበከተ መሆኑን ለዓለም ህዝብ በማሳወቅ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዕጩ አባል ለመሆን ማመልከቻ ለማስገባት ይፈልጋል፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ያሉት ሁሉም ሀሳቦች ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ማስፈን ናቸው፡፡ ገዥው አካል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያሉትን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ የማቋረጡን ኃላፊነት ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆነ ብቸኛ ዓላማው ግልጽነት እና ተጠያቂነት ከሆነ ድርጅት ጋር በእርግጠኝነት አባል ለመሆን ግምት ሊኖረው የሚችለው በምን ዓይነት መስፈርት ነው? የቀበሮ ባህታዊ በበጎቹ መንጋ መካከል ጸሎት ማድረስ ይችላልን? የትኛው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI አገር ነው ከእንደዚህ ያለ የዘቀጠ ዕጩ አባል ጋር አብሮ መወያየት የሚሻው?
የገዥው አካል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI ዕጩ አባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ከማግኘቱ በፊት እራሱገዥው አካልበአሁኑ ጊዜ ያለውን አፋኝ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ በመሻር በምትኩ ሲቪል የሆነ የሲቪል ማህበረሰብህግ፣ ግብረገብነት ያለውእና የሰለጠነ ህግ በማውጣት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITI- ኢትዮጵያ የተቋማዊግልጽነት እና እውነተኛ ጽኑአቋም/Ethiopia Institutional Transparency and Integrityንን ማስፈን ይጠበቅበታል ግዳጅም አለበት፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/EITIን ክህደት በተሞላበት ስብዕና ለማታለል የመሞከር ጨዋታ እና ከዕውነተኛ ስብዕናው ውጭ በሆነ መልኩ ተገቢነት የሌለው ዓለም አቀፋዊ ክብር ለማግኘት የሚደረገው ሚስጥራዊ ሸፍጥ መጋለጥ እና መቆም አለበት!

በማተብዋ ልዳኝ – ወድቃ የተነሳችው

February 27, 2014
ከስንሻው ተገኘ
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።The Green, Yellow and Red Ethiopian National Fla
“ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ…
አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ (ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት ነበር። የሁሉም አገር – ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት።
ዓይናችሁን ጨፍኑና ጊዜን አጣጥፋችሁ ወደዚያ ዘመን (1952-53) ብረሩልኝ። መጀመርያ ስለዚህ ጉዳይ ዴቪድ ሜሬዲት The first dance of freedom ን መጽሐፍ አነበብሁና (በ1985) ወዲያው እጅግ ወዳጄ ለነበሩት ለልጅ ሚካኤል እምሩ አነሳሁባቸው። በወቅቱ በእንግሊዝ አገር ስለነበሩ በግል በትኩረት የሚያውቁት መሆናቸውን አረጋገጡልኝ። ከላይ ያቀረብሁት ዘገባም የማርቲን ሜሬዲትና የልጅ ሚካኤል እምሩ ጭምቅ ሪፖርት ነው። (ልጅ ሚካኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄዱ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።)
የወቅቱ ተራማጅ ሁሉ ይህንን በጽሞና ሲከታተል ኋይት ሖል (የእንግሊዝ መንግሥት) በዚያው ሰሞን (1953) በኢትዮጵያና አንድነትዋ ላይ ትልቅ ሴራ ሲያቀጣጥል ነበር። ሊቆራርጠን። አርነስት ቤቪን የተባለው የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶማሊያ ነፃ ስትሆን የኢትዮጵያን ኦጋዴን፣ ሪዘርቭድ ኤርያና – ሐውድ እንዲሁም ጅቡቲንና የኬንያን ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት አጠቃልላ ታላቅዋን ሶማሊያ ስትመሠርት በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ከአለውሀ ባሻገር ያለው መሬት በሙሉ (ማለትም ትግራይና ኤርትራ ተዋህደው ትግራይ ትግርኝ የሚባል አገር ለመፍጠር ሽርጉድ ይዘው ነበር።) lyndon larouche የተባለውና በመደበኛው አስተሳሰብ አክራሪና የተወናበደ የፖለቲካ ነውጠኛ የአገሩን ፖለቲካ ጨረሰና ዛሬ በመላው ዓለም እየደረሰ ያለው ችግር እንግሊዝ ዘርታ ያበቀለችው አድርጐ ነው የሚያቀርበው። ይኽ አይጠረጠርም። በበኩሌ እንደማውቀው እንግሊዙ አርነስት ቤቪን የጀመረውን አይኤም ሌዊስ ካልፈጸምሁት ብሎ እነ በረከት ሀብተ ሥላሴን፣ እነ መለስ ዜናዊን ይዞ ለዓመታት ተንደፋድፎአል። (መለስ በዜግነት ሶማሊያዊ ነበር)- በነገራችን ላይ እነ በረከት ሀብተሥላሴ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ ተወልደው ያደጉባት፣ ተምረው የተሾሙባት ኢትዮጵያ፥ ዓለማቸውን ያዩባት ውብ አዲስ አበባ- ወደ ኢምንትነት እንድትመለስ ሲፍጨረጨሩ እንደ ራስ ተፈሪ ያሉ ሕዝቦች “ቤታችን መግቢያችን (ራስታ የምንላቸው)” በማለት ወደዚያች አገር መጉረፍ ይዘው ነበር።
ተመስገን ደሳለኝ ወደ ጐንደር ሄዶ ነበር አሉ። ባዶ እጁን አልተመለሰም። ወያኔ ያነወራት፣ እንደ ተስፋዬ ሐቢሶ ያሉ (በተቆላበት የሚያፈሉ) ሰነፎች የተሳለቁባት፣ በመንፈሳዊና ሕዝባዊ ክብርዋ መለስ ያሾፈባት፣….ወያኔዎች በባዶ እግራቸው የረጋገጡአትና የኮሾሮ (የአምባሻ) መያዣ ያደረጉአት….በእኔ ዕድሜ ጅማሬ ላይ “ወድቃ የተነሳችው” እየተባለች ስትጠቀስ የቆየችው ሰንደቅ ዓላማ በጐንደር ምንኛ ታላቁን ክብርዋን ይዛ – እንዳለችና እንደምትኖር የምሥራቹን ነግሮናል። ብሥራት ነውና ምሥር ብላ! ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ይኸ ወጣት ጋዜጠኛ ነው።
ኢጣሊያ የኤርትራን ደጋማ አውራጃዎች ለመያዝ የቻለችው በ1889ዓ.ም እንደ አ.አ ነው። እዚህ ላይ የንጉሠ ነገሥቱን (አጤ ዮሐንስ) አጐት ራስ ደበብንና በኋላ ጊዜ የራስ ሥዩምን ሴት ልጅ ያገቡትን ደጃዝማች ገብረሥላሴን ማውገዝ ወይስ ማወደስ ይገባ እንደሆነ አላወቅንም እንጂ በእነሱ ድጋፍና መሪነት ነው ኤርትራ የተያዘችው። ዛሬ አኪሩ ዞሮ ባንዳ የሚወደስበትና የሚቀደስበት፣ ወደል ወደል መጽሐፍም በውዳሴ መልክ የሚቀርብበት በመሆኑ ነው ግራ የተጋባነው። አዎን ዓላማዬ በማንም ዜጋ ላይ የፍትሕ ድንጊያ ለመወርወር አይደለም። የእግዜሩን መንገድ ካወቅነው ጸሎታችን “ማረን” እንጂ “አፈራርደን” መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያን የሚታደጋት የራስዋ የኢትዮጵያ ልጅ መሆን እንደሚገባው ስንነጋገርና ስንስማማ ከቆየን በኋላ ሁሉም ነገር የተለዋወጠ ሆኖአል። ኢትዮጵያውያን አገራቸውንም ራሳቸውንም ማዳን አቅቶአቸው በአገሪቱ የሚጫወቱት ወገኖች የተነሱለትን አጥፊ ዓላማ ለመፈጸም አንዳች እንቅፋት አልገጠማቸውም። በተናጠል መስዋዕትነት የሚከፍሉ ግለሰብ የፖለቲካ ተዋናያውያንና ጋዜጠኞች ደግሞ የሚሞቱለትን ሕዝብ ሊቀሰቅሱ አልቻሉም። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያሉአት ልጆች እነዚህ ብቻ ናቸውን? እስከማለት የደረሱ አሉ። “የኢትዮጵያ ልጆች በደማቸውም በአጥንታቸውም ኢትዮጵያን ከእልቂት ለማዳን ካልቻሉ ወዴት ይኬዳል? ወደ ማን ይጮኻል?” ነቢዩ ዳዊት (ልበ አምላክ የሚባለው) ለዚህ አምላክ ራሱ በጆሮው የነገረው ቁም ነገር ነበር ይላሉ መጽሐፉን የሚተረጉሙ ሰዎች። “በልጆችዋ መተማመን ያቃታት፣ ልጆችዋ በግፈኞችና በጨቋኞች ያለቁባት ኢትዮጵያ ናት፤ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው” ይሉናል። ተስፋ ከመቁረጥ የመጣ አሳብ አይደለም። የአምላኩንም ሚና እንዳንረሳ ለማሳሰብ ነው። ውዳሴ ማርያምም ባይሆን ጥቂት እግዚኦታ!
እንደ ዛሬዋ ጐንደር ሁሉ ጣልያን ኤርትራን ከያዘ በኋላ ለስድሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ነፃነት ምልክትና የክብርዋ ዘላለማዊ መግለጫ የሆነችው አረንጓዴ፣ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ቢዘን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ ስትውለበለብ ቆይታለች። እግዚአብሔር በቤቱ (ቤተክርስቲያኑ) ላይ ያዋላት ለዚህ ሕዝብ መልእክት ኖሮት ይሆናል በማለት የገዳሙ አበምኔት በ1980 ገልጠውልኛል። በዚያን ዘመን ኤርትራ በጣልያን ሥር ብትወድቅም በየበዓላቱ ሕዝቡ ይዞት የሚወጣው ሰንደቅ- አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። አንድ ኤርትራዊ ሲሞት የአስክሬኑ ሳጥን በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃል። ሠርጐች ግርማማ የሚሆኑት በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ሲንቆጠቆጡ ነው። አብያተ ክርስቲያናት ይኽ ሰንደቅ ዓላማ ተለይቶአቸው አያውቅም። ለብዙ ዓመታት ወደ ኤርትራ ስመላለስ የኖርሁ፣ ሕዝቡን የማውቅና የማከብር ስለነበርሁ ዛሬ ይኽ ወገኔ ከዚያች ከታቦት እኩል ከሚያያትና የሕልውናው ተስፋ ከነበረችው ሰንደቅ ዓላማ ሲለይ ምን ተሰማው? እያልሁ ራሴን እጠይቃለሁ። ወይስ አዲሱ የኤርትራ ትውልድ ይኽንን ቁም ነገር አያውቀውም ነበር? እዚህ ባለሁበት አገር እንደኔው በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን አረጋውያን አውቃለሁ። ለሁሉም እንደ ቀልድ “አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ የሚለመድ ነው?” እላቸዋለሁ። በሻዕቢያ ውስጥ ከአሥርና ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ መቆየታቸውን የሚነግሩኝ ብዙ ጐበዞችን በየቀኑ አገኛቸዋለሁ። ሁለቱ በአንድ ቀን የአሜሪካ ዜግነት እንዳገኙ ሲነግሩኝ እንደ ቀልድ አድርጌ “አሜሪካዊ ለመሆን ነው ሰላሳ ዓመት የወጋችሁኝ?” እላቸዋለሁ።
ኤርትራውያኑ ራሳቸው በአጸፋው “እናንተስ ሰንደቅ ዓላማውን መቸ አስከበራችሁና ነው እኛን የምታሽሟጥጡን?” ሊሉን ይችላሉ። እግዜር ይመስገን የወያኔ ሕግ በማይሰራበት በዋሽንግተን፣ በለንደን፣ በጄኔቫ…በስዊድን…የምናምንባት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደ ልብ ትውለበለባለች። ስለዚህ ለኤርትራውያን ወገኖቻችንም “የተዋችኋትን ሰንደቅ ዓላማ በምትመለሱበት ጊዜም በዚያው ሞገስ ታገኝዋታላችሁ” ለማለት ይቻላል። (የኢትዮጵያ ሕግ በማይሰራባቸው በስዊድን ወዘተ ስል እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ ትዝ ትለኛለች። ለካንስ ስቶክሐልም ላይ የተናገሩት አዲስ አበባ ላይ ያስቀጣል?)
ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያከብር የኖረው የኤርትራ ሕዝብ ነበር ስል ሌላው ሕዝብ ደንታ እንዳልነበረው መግለጤ አይደለም። ግመሎቻችን፣ በጐቻችን፣ የጋማ ከብቶቻችን፣ የቤትና የዱር እንስሶቻችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የክብር ዓርማ ያውቁታል እያሉ የሚያወጉአችሁ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ብዙ ናቸው። የአውሳው ርእሰ መኳንንት ቢተወደድ አሊሚራሕ አንፍሬ በአንድ ወቅት “እንኳን አፋሩ ሕዝባችን ግመሎቻችንም ሰንደቅ ዓላማችንን ያውቁታል” ማለታቸው ይጠቀሳል። አጋጣሚ ነገር ላንሳና ኮማንደር ለማ ጉተማ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የመሥሪያ ቤቴን ቅርንጫፍ ሥራ ለማስተባበር ወደዚያ እመላለስ ነበር። ሁለት ጊዜ ያህል የኢሳውን ባላባትና ሱልጣን ደጃዝማች ዑጋዝ ሐሰንን ተዋውቄአቸው ነበር። “ትልቁ ልጄን ትመስለኛለህ” ሲሉኝ ልዩ ፍቅር አደረብኝ። ታዲያ በ1983 አካባቢ ቢትወደድ አሊ ሚራሕ የተናገሩትን ቃል በቃል ደጃዝማች (ዑጋዝ) ሐሰን ሲናገሩት ሰምቻቸዋለሁ። ማጋነን ባይመስል ግመሎቹ ቀጥ ብለው እንደሚቆሙ ይናገራሉ። ጐበዝ! “ግመሎቻችን ለኢትዮጵያ ከእኛ የበለጠ ታማኝ ናቸው” ብል በድፍረት ትወስዱብኝ ይሆን? ግመሎቻችን ጭምር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውቁታል! እነመለስ ከዚያች ቅርጽ የለሽ እንስሳ ማነሳቸው ከተሰማችሁ አብሬአችሁ ልከሰስ እችላለሁ።
ፋሺስቶች ባላደረጉት ድፍረትና ብልግና በቀለም እኛን ይመስል የነበረው መለስ የሕገ መንግሥት ጉባዔ ሲመራ ያቺን ሰንደቅ ዓላማ እንዴት እንዳብጠለጠለ ታስታውሳላችሁ። እዚያ ጉባዔ ውስጥ በጀግንነትና በታላቅ ወኔ ይቺን ሰንደቅ ዓላማ ያወድሱ፣ የቆሙላትና ስድቡን ሁሉ የተሸከሙላት ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ (ነፍሰ ሄር) ብቻ ነበሩ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ መንጋ ወሮበሎች ፋሺስቶች ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ በመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያሰሙ ያሰማሩባቸውን ሥራ ፈቶችና ማጅራት መችዎችን አስታውሶኝ ነበር። ይችም አገር ዛሬ (በ21ኛው ክፍለ ዘመን) በዋልጌዎች፣ በጫካ አደጐች፣ በቀማኞች…እጅ እንደገባች ሁላችንም ተከሰተልን። ያን ጊዜ ከመታኝ ብራቅ እስካሁን አላገገምኩም።
እኛ ኢትዮጵያውያን – ከእኛም በፊት የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ትውልዶች- በነፃነት ተጸንሰን፣ በነፃነት ተወልደን በነፃነትም ተጠልለን ኖረናል። የሰውን ልጆች እኩልነት የምትመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝባችንን የታሪክ ቅሬቶች፣ ሐውልቶችና የነፃነት ምልክቶች–የክብርና የማዕረግ ሀብቶቻችንን ስንንከባከብ ኖረናል። አገሪቱ ትኖር ዘንድ በሰንደቅ ዓላማቸው ሥር ተንበርክከው የፈጸሙትን መሐላ ያከበሩትን ጀግኖች በፈንታችን አክብረናቸዋል። በእስዋ ተመርተን ወደ ሞት አደባባዮች ነጉደናል። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ከሁለት መቶ ሺህ ከማያንስ ሠራዊትና መሪዎቻቸው ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አድዋ ዘምታ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ድል የሆነውን ግዳይ ተወጥታለች። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ እኛ ባለቤትዋ ሆንን እንጂ የዓላም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ አለኝታ ነበረች። ያስረዳሁ ይመስለኛል።
የዚያድ በሬ ወራሪዎች ያሳደዱአት አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የክብርና የአንድነት ምልክታችን በጐዴ፣ በካራማራ፣ በጅጅጋ በገላዲ…እንደገና ስትውለበለብ አይቻለሁ። በወረራው ወቅት የሶማሊያ እብሪተኛ ኅይል ባደረሰብን ጥቃት የተቃጠለና ያለቀሰ አንጀታችን ሰንደቅ ዓላማችን ዳግመኛ ስትውለበለብ እንደገና ማልቀሳችን ትዝ ይለኛል። አልፎ አልፎ እንደዚያ ያለ ጥቃት አይጠላም። ለነፃነትህና ለአንድነትህ ዘወትር እንደ ቆቅ ተጠንቅቀህ መቆምና መሞት ግዴታ መሆኑን እንዳትረሳ ያስገነዝብሃል።
የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ሲነሣ – አሁንም ተመስገን ደሳለኝ አነሳብኝና- ከውስጤ አንድ እሳተ ጐመራ መሳይ ነገር ሊፈነዳ ይደርሳል። ትዝታዎች አሉኝና። በኤርትራ በረሃዎች፣ ቅጥልጥል የሆኑ የመስሐሊት ሸንተረሮች፣ በሰሎሞና፣ በሸኢብ…ከኢትዮጵያ የአንድነት ሠራዊት ጋር የዘመቱት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰንደቅ ዓላማዎችን ዛሬ ዓይኔን ጨፍኜ አያቸዋለሁ። እዚያው ከሰንደቅ ዓላማው አጠገብ ክንዳቸውን እየተንተራሱ እየጣሉ የወደቁትን፣ በኋላም ነጭ የሰላም ዓርማ እያውለበለቡ እንኳ በፈሪዎች (ካወርድ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ጠንካራ መልእክት አለው) የተረሸኑት ኅልቁ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ። የብዘዎቹን አዛዦች አውቃቸዋለሁ። ለወረራ የተሰማራ ኅይል የለንም። ይልቁንም የኤርትራን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ፣ እያስጠበቀም ለመሞት በሰንደቅ ዓላማው “ምሎ” የተመመ ነበር። ተሳስተን ነበር ያለቅነው? ተሳስተን ነበር እንደወጣን የቀረነው – ሬሳችን የአራዊት ሲሣይ – የሆነው- ቀባሪ ያጣው….? የኤርትራ ሕዝብ ምነው አስቀድሞ ቢነግረን ኖሮ! በአርማጌዶን እንድንገናኝ ቀጠሮ መያዝ እንችላለን።
ከጥንት ጀምሮ- ለእኔ ጥንት ከሰባ ዓመት የማይበልጠው ነው- ከዚች ሰንደቅ ዓላማ ጋር የሚያስተሳስር ታሪክ አለኝ። የራሴ ትንሽ ታሪክ! ትንሽም ትዝታ። ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ውርስ-አረፍ ልዑልአየሁ የፋሺስቶችን እርግጫና ጡጫ ታስታውሳለች። በዚህ የተነሣ ዘወትር የአገር ልብስዋ ጥለት በሙሉ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። ይኸ ብቻ አይደለም። በአሥራ አራት ዓመቴ ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ከ17 ዓመት በፊት ወደ ስደቱ ዓለም እስክዛወር ድረስ በየዓመቱ ጋቢ ፈትላ ትልክልኛለች። ሌሎች ዘመዶቼ ጋቢ አስለምደውኛል። የወይዘሮ ውርሰአረፍ ጋቢ ግን ሁልጊዜ በአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ጥለት የደመቀ ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት (በሞት ያረፈችበት ዘመን) የመጨረሻውን ጋቢ ልካልኛለች። ታዲያ ይኽንን ልማዴን ታውቅ የነበረችው ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ይታይሽ ልዑልአየሁ “እቴቴን (ሟች እህታችንን) እንድታስባት ብዬ በእስዋ ምትክ ጋቢ ልኬልሃለሁ” ብላ ወደዚህ በመጣ ሰው አደራዋን ተወጣችው። አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ። ይቺኛይቱ እህቴም ወደ ታላቅዋ ዘንድ ሄደች። አላውቅም፥ ይገናኙ አይገናኙ። ለእኔ ግን ሰንደቅ ዓላማዬ ናፍቆቴ ሆኖአል። ተከናንቤው የምተኛው ጋቢ ባላጣም። (በነገራችን ላይ ውድ ወዳጄ ጐሹ ሞገስ በዚህ ረገድ ረስቶኝ አያውቅም።)
የኢትዮጵያ ድምፅ፣ በኋላ ደግሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ከበደ አኒሳ እንደ እናቴ ልጅ የምቆጥረው ነው። በንጉሡ ዘመን በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ አራት ሰዓት ላይ ይመጣና “ና ቡና ጠጥተን እንመለስ” ይልና ይዞኝ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በኩል ይነዳል። ልክ ቤተ መንግሥቱ አጠገብ ስንደርስ እኔም እሱም አንገታችንን አውጥተን ግቢውን እንቃኛለን። ሁለት የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ የብረት ምሰሶዎች አሉ። አንደኛው አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበት ነው። ሁለተኛው (አጠር ያለው) ደግሞ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ዓርማ መሐል አንበሳ አለው። ያ የጃንሆይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን እሳቸው በከተማው ከሌሉ አይውለበለብም። የንጉሠ ነገሥቱ በከተማው መኖር አለመኖር ምልክት ያ ነበር። ስለዚህ ትንታጉ ጋዜጠኛ ከበደ አኒሣ “ዛሬ ጀንሆይ በአዲስ አበባ ስለሌሉ መንግሥት በሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” ይልና ወደ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ሶደሬ ወዘተ እንከንፋለን። ብቻ በየሳምንቱ ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሰበብ የምናደርገው የጃንሆይን ሰንደቅ ዓላማ አለመውለብለብ ይሆንና “መንግስት ከሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” እያልን እብስ ማለት እንደ ባሕል ተያዘ። በእኛ ዘመን ቡድናችን (የእግር ኳሱ-አለዚያም ጊዮርጊስ) ቢያሸንፍም በደስታ፣ ቢሸነፍም በንዴት በቢራው ማዝገም የተለመደ ነበር። ስትናደድም ትጠጣለህ፣ ሲከፋህም ትጠጣለህ።
ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረች እነ ማርከስ ጋርቪ ሦስት ሺህ ጥቁር ወታደሮች መልምለው በክተት ተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። አጤ ኅይለሥላሴ የእንግሊዝን ጦር እየመሩ በመሄዳቸው ራስ ተፈሪያውያኑ ማርከስ ጋርቪና ራስ መኰንን (ራስታ) ጃንሆይን ተቀይመው እንደነበረ በወቅቱ ሲወራ ነበር። በጽሑፍም ቆይቶናል። ይቺን አገር- ይህን ሰንደቅ ዓላማዋን- ይህን ጐላ ያለ ታሪክዋን- ወደፊትም አውስተን የማንጨርሰውን- ትዝታዋን እነዚህ ሳንቀጣቸው ያደጉ፣ በማይምነታቸው የማያፍሩ ደፋሮች ይዘን መጓዙ ራሱ ሕመም ነው። ኅብረተሰብ ይጠይቀናል። ሰላምን በሰንሰለት፣ ዳቦን በባርነት የሚሸምቱ ሰዎች ዘመን ላይ መድረሳችን ይገርመኛል። ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ የሚያውቁአትና የሞቱላት ሰንደቅ ዓላማ መደፈር እንደ እብድ አድርጐአቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ። ወዲያው ጋዜጠኞች ሰብስበው ንግግር አድርገው አንድ ብዕር በሽልማት መልክ ሰጡኝ። እኔም ለዚች ሰንደቅ ዓላማ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንሁ- የሻለቃ አድማሴን ቃልም ምን ያህል እንደጠበቅሁ አላውቅም። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ያለ ጠባቂ መሆንዋ እውነት ነው። ያለ እስዋ ነፃነታችን ባዶ መሆኑ ይሰማኛል። ባለ አምባሻዋን የመለስን ድሪቶ አደራችሁን በምትክነት አናንሳው!
የነፃነት እጦት የሚመሰክረው የሰንደቅ ዓላማ መዋረድና የአገር መደፈር ምን ማለት እንደሆነ ዘላለማዊው ሐዲስ ዓለማየሁ “ትዝታ” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጠውታል። ራስ እምሩ፣ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ…በኢጣልያ ደሴት ታስረው በቆዩበት ጊዜ የቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ የባሕር ማዶ ቅኝ ግዛት ኅላፊ ራስ እምሩን እንዲያነጋግር ታዝዞ ይሄዳል። ቆፍጣናው መስፍን በመኝታ ቤታቸው ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ሰውየው ቆሞ ሲያናግራቸው ይሉኝታ የያዛቸው የእኛ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ወደየ ክፍላቸው ሊሄዱ ሲሉ ራስ እምሩ “ወንበር ልታመጡለት እንዳይሆን፤ እንዳታደርጉት” በማለት ቅኝ ገዥውንና የሀገሩ ባለቤት የሆነውን ባለሥልጣን አቁመው አነጋገሩት። በኢትዮጵያዊ ክብርና ኩራት እየተደበቡ “ ወዳጄ እኛ ዘንድ ምን አመጣህ?” ይሉታል። እሱም እንደ ባለስልጣን ሳይሆን እንደ አሽከር ቆሞ “ ግርማዊ የኢጣልያ ንጉሥ ኢማኑኤል ሳልሳዊና የመንግስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ያለዎትን ሀብት ንብረትዎን፣ ርስትዎንና ሌሎችንም እንደ ገንዘብ ያለውን ሀብትዎን ሊመልሱልዎ ወስነዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሊረከብልዎ የሚወክሉት ሰው ካለ ይነገረውና ይረከብልዎ!” ይላቸዋል።
የራስ እምሩ ቃል ለሰውየውም እዚያ ላሉትም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርኮኞች እስደንጋጭ ሆነባቸው። ባልተጠበቀው መልሳቸው ራስ እምሩ “የእኔ ሀብትና ንብረት የቀረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በተደፈረ- አገሬ በእናንተ በተረገጠች ጊዜ ነው። አሁን ሀብትና ንብረት የለኝም። ይህን የምትጠቅበውን ሀብትና ንብረት ለምትወድደው ሰው ልትሰጠው ትችላለህ።” ይሉታል። አጭር መልስ። ዲቦኖ፣ ባዶልዩ፣ ዱካ ዳውስታ፣ ግራዚያኒ፣ ፍራንካ..ወዘተ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መርገጣቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም። ይልቁን ቀደም እንዳልሁት ይቺው ሰንደቅ ዓላማ በኤርትራ ምድር እንዲያ ስትከበር በማንም ላይ በምንም ጊዜ ስላደረሱት ጥቃት ብዙም አልሰማንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን አምባገነን ሥርዓት አወረድሁ በሚል ግለሰብ ዓርማችን ስትናቅና ስትገፋ ለማየት ችለናል። የት? በጣይቱ ከተማ- በአዲስ አበባ! ባዕድና ጠላት፣ አስገባሪና ወራሪ የተባሉትም በዚህ ነው። የበላዔ ሰብን፣ የሒትለርንና የስታሊንን፣ የቀያፋን፣ የሔሮድስንና የጲላጦስን፣ የአስቀሮቱ ይሁዳን….ኅጢአት የደመሰሰ አምላክ ይሁነውና መለስ እንደ ገና ሲያላግጥብን ትልቅዋን ዓርማችንን ቡትቱ አስመስሎ ከማምጣቱም በላይ “የነፃነት ቻምፒዮን” ሆኖ ተከሰተ። ከቶውንም የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን እንደ ማካካሻ ሰጠን። ጥሩ ተጫውቶአል። እግዜር ይመስገነው በውጭ ያለነው ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር አልተለያየንም። እንደኔማ ቢሆን ሰው ሁሉ “ወፈፌ” ወይም የጀማመረው ካላለኝ በየቦታው ለብሼ ብሔድ ደስታዬ ነበር።
ለእኔ ሰንደቅ ዓላማዬ ሁሉንም ነች። የነፃነት ብሥራት፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ በክብር የመንጐራደድ ዋስትናዬ ናት። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካ ታጋይ ኅይሎች እየተመለከቱአት ቅኝ አገዛዝን ድባቅ የመቱባት ኅይል ናት። የአፍሪካ አገሮች ወደ ፍጹም አንድነት ይመጡ ዘንድ ታሪካዊ ጥሪ ያስተላለፈች ናት። ዛሬ ደግሞ ከወደቀችበት ትነሣለች። ሰው ሁሉ ኢትዮጵያን ቢክዳት “ኢየሩሳሌም ሆይ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ” ያለው አምላክዋ ወደ ክብርዋ ይመልሳታል። እንደ ተዋረድን አንቀርም። ወደ ታሪካዊ አንድነታችን በእርግጥ እንመለሳለን። አንዳንድ ደካማ “ነፍሳት” (አዎን “ነፍሳት”) የሚያናፍሱት መፍረክረክ ከንቱ ከንቱ…ሆኖ ያልፋል። አሜን አሜን!