Monday, 17 February 2014

አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲጀመር ወሰነ

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለተኛውን የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚው ተግባራዊ እንዲደርግ ወሰነ፡፡
ብሔራዊ ምክር ቤቱ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2006 ባደረገው አስቸኳ ስብሰባ በሶስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከነዚህ ውሳኔዎች መካከል ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ይገኝበታል፡፡


934939_487240494685925_524628143_n
የፓርቲው ፕሬዝደንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ በመሬት ባለቤትነትና አስተዳደር ጉዳይ ላይ ያተኮረ እንዲሆን መወሰኑን በመግለፅ ብሔራዊ ምክር ቤቱም ለዚሁ ውሳኔ ይሁንታው እንዲሰጥ በመጠየቅ፣ ህዝባዊ ከንቅናቄው ስለሚጠበቀው ውጤት ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ስዩም፣ የማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊው አቶ አለነ ማዕፀንቱ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ሰለሞን ስዩም በሀገራችን ከመሬት ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ስለፈጠራቸው ውስብስብ ችግሮች ጥልቅ ጥናታቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብና ጥናት ላይ ግብአት ከሰጠና ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ሁለተኛው የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ በመሬት ጉዳይ ላይ ተኮረ እንዲሆንና ይህንኑም ተግባራዊ እንዲያስደርግ ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኃላፊነት በመስጠት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

39ኛ የካቲት ለማክበር ሽርጉድ እና የተሟጠጠው የትግራይ ህዝብ ስሜት

የትግራይ ህዝብና ታጋዮቹ የህ.ወ.ሃ.ት ትጥቅ ትግል የተጀመረበት ቀን ከ1967 ዓ/ም የካቲት ወር ጀምሮ እስከ 1983 ዓ/ም በየአመቱ ለምትመጣዉ የካቲት 11 ለማክበር በናፍቆት የሚጠብቁት ነበር። በአሉን ለማክበርም የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ የሚለበስ ያላቸውን ሃብት በማሟጠጥ አስቀድመዉ ይዘጋጁበት ነበር የትግራይ ህዝብ ይቅርና በነፃ መሬት በጠላት ውስጥ በስደት በተለይ ደግሞ በ1977 ዓ/ም በድርቅ፣ በደርግና በሻዕቢያ ወረራ ወደ ሱዳን ተሰዶ በለጋሾች በተሰጣቸዉ ዱቄትና ስንዴ ጠላ ጠምቆ ዳቦ ጋግሮ በሰላማዊ ሰልፍ ያከብራት ነበር። በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በሌሎች ክፍለ አለማት በስደት ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችም በተለያየ መንገድ ያከብሩ ነበር።
ይህ የሆነበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በፋሽስታዊ ደርግ ይደርስበት ለነበረዉ ግፍ በየላቲት 11 የተወለደዉ ህ.ዋ.ሃ.ት ከችግሬ ያላቀቀኛል ከሚል መንፈስ ነበር የካቲት 11 ሲያከብር የነበረዉ። የትግራይ ህዝብ የካቲት 11 ከአማልክት በላይ ያመልካት ነበር የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችም የህዝቡን ስሜት በመጠቀም እንደ የመነሳሻ ጊዜ በመጠቀም ይጠቀሙበት ነበር ህዝቡም በህ.ዋ.ሃ.ት ተጠቃሚ እንሆናለን ከሚል ስሜት ደርግ ከተወገደ በኃላ የህ.ዋ.ሃ.ት ካድሬዎችና መሪዎች የሚሉትን ይሰማ ነበር ለትግራይ ህዝብ ብለዉ ለመላዉ የሃገራችን ህዝብ የገቡለት ቃል የክህደት ሁኔታ ስላሳዩት የካቲት 11 በአል የማክበር ስሜቱ እያሽቆለቆለ መጣ። በአሉን አክበር ሲባል እምቢታ አሳየ። እየተገደደ ወደ ሰልፍ ሲገባም የመሪዎች ዲስኩር ሲጀመር እየጠላቸዉ ፈርሶ ይሄድ ነበር። በክልል ደረጃ በዞን ፣ በወረዳ፣ በቀበሌ ህዝቡ እየተገደደ ገንዘብ በማውጣት በግብዣ ይምበሻበሽ ነበር። በዛን ጊዜ
የ.ህ.ዋ.ሃ.ትመሪዎችና ጥቂት ካድሬዎች ኪሳቸዉ ይሞላ ነበር ህዝቡ የካቲት 11 ለማክበር ይጓጓ የነበረዉ ሌላ ቀርቶ ልጆቹን ወደ ትግል ሜዳ ለመስዋእት ሲሸኝ በየካቲት 11 ነበር ያነበረዉ እምነትና አምልኮት የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ምንም የማይጠቅሙት መሆናቸዉን እያወቀ ሲመጣ ፍላጎቱ ተሟጦ የካቲት የራሱ እንዳልሆነች በማወቁ በአሉን ላለማክበር ተቃውሞ እያሳዩ መጣ።


እነዚህ ዘመናዊ ግራዚያኒ መሰል መሪዎች ግን ህዝቡን ያለፍላጎቱ አስገድደዉ ሰልፍ እያሰወጡ በህ.ዋ.ሃ.ትና የመንግስት ብዙሃን መገናኛ በማስተጋባት ለአለም በማደናገር በህዝብ ተወዳጅ እንደሆኑ ያደናግራሉ። የኃላ ኃላ ደግሞ ለህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ወደ ስልጣን ያወጡት የህዝብ ልጆች አገር አትሽጡ ብለዉ ተቃውሞ ባሳዩ ታጋዮች በጅምላ አሰርዋቸዉ ያለ አንዳች መቋቋሚያ ጣልዋቸዉ በዛን ወቅት የትግራይ ህዝብ ጥላቻዉን ገለፀ ቆየት ብሎም በትግራይ የሚገኙ 120 ሺ አካለ ጉዳተኞች በስማቸዉ የተለመነ ሃብት ቀምተዉ ሜዳ ላይ ጣልዋቸዉ የህዝቡ ጥላቻ ተባባሰ ። በቃ የካቲት 11 የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችና የጥቂት ተጠቃሚ ካድሬዎች መፈንጠዣ ሆነች ደርግ ከተወገደ ከ1983 ዓ/ም ወዲህ የካቲት 11 በአል ለማክበር የባከነ ሃብት መበቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል የሚከፍቱት ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ያሰራ ነበር ይህ የአብዮት በአል እየተባለ የሃገር ሃብት ማባከን በህ.ዋ.ሃት መሪዎች ታጥሮ የቀረ አልነበረም። በአፋር፣ በአማራ፣ በሱማሌ፣ በጋንቤላ፣ በደቡብ ህዝቦች የፓርቲዎች የልደት በአል እየተባለ ለማክበር በቢሊዮን የሚገመት ሃብት ባክነዋል እነዚህ ፓርቲዎች በአላቸዊ ሲከበር የአውሮፕላን፣የመኪና ትራንስፖርት የመንግስት መኪኖች በዛ በአል ማክበር ተጠምደዋል ባጠቃላይ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች የጀመሩት የሃገር ሃብት ማባከን እንደ ወረርሽን በሽታ አገር ኣጠፉ ።


ያለፈዉ አልፎ የዘንድሮ 2006 የካቲት በአል አከባበር
የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ የየካቲት 2006 የበአል አከባበር ምክንያት በማድረግ ህዝቡን የህ.ዋ.ሃ.ት ስርአት በፈጠረበት ችግር ልቡ ስለሸፈተ ለውጥ ፈላጊ በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በ58 ወረዳዎች በ7 ዞኖች ለሁሉም ቀበሌዎች ህዝብ የውል አበል እየተሰጠ በስብሰባ በመናጥ ህ.ወ.ሃ.ት አለች ወይ በሚል ጥያቄ ሲያወያዩት ህዝቡ ደግሞ ህ.ዋ.ሃ.ት የለችም ከድታለች ነዉ ያላቸዉ።

 በሌላ በኩል ህዝቡ በሁሉም የወረዳና ዞኖች ፣ ከተሞች ተገዶ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግና ለሰላማዊ ተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመነጠል ዘመቻ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። በተጨማሪም በሺ በሚቆጠሩ ቀበሌዎች በካድሬዎች እየተገደዱ ጠላ ተጠምቆ፣ እንጀራ ተጋግሮ ግብዣ እንዲደረግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ሁሉም ከተሞች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ስለ ህ.ወ.ሃ.ት ታሪክ አጀንዳ በመያዝ በፕላኔት ሆቴልና በሃወልቲ ሰማእታት አዳራሽ የትግራይን ክልል እድገት ተሞክሮ እና የህ.ዋ.ሃ.ት ታሪክ ይሰለጥናሉ። በመላዉ ክልልና ዞን ቀበሌዎች እንደ አዲስ የተበረዘና አሁን ላሉ መሪዎች ታሪክ በሚያድስ መንገድ ታሪክ እያስተማሩ ይገኛሉ።


በተለይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የትግራይን ተሞክሮ ለመውሰድ ተብሎ ከመላዉ ኢትዮጵያ ክልሎች የኢ.ህአ.ዴ.ግ.ና አጋር ድርጅቶች ወጣት ዜጎች በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለአንድ ወር ያህል ምግብና ውል አበል ተዘጋጅቶላቸዉ የውሸት ታሪክ እየሰለጠኑ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ የሚደረገዉ አሁን ያለዉ የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የተበላሸ ስርአትና በህዝቡ ያለዉ ችግር እንዳይታወቅና ለመሸፈን የሚደረግ አሻጥር ነዉ።
የየካቲት ውጤት
ከ1983 የካቲት 11 እስከ 2006 የካቲት 11 የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ምን ተጠቀመ? ሁሉም ህዝብ የገጠርና የከተማ የመሬት ባለቤትነት የተቀማበት፣ ዜጎች በግላቸዉ መሬት አግኝተዉ መጠለያ ሰርተዉ እንዳይኖሩባት የተደረጉበት፣ መብታቸዉ ተነጠቁበት፣ ዜጎች የግል ሃብት የማፍራት መብታቸዉ የተከለከሉባት፣ ከግለ-ሰብ እስከ ብሄር -ብሄረሰቦች ህዝቦች መብታቸዉ ፍፁም የታፈኑባት፣ በስም ብሄር ወኪሎች የኢህአዴግ ቡድን የሚፈነጩባት፣ የህግ የበላይነት መከበር ቀርቶ ከዳኛ በላይ የፖሊስ ስልጣን የነገሰበት፣ እቺ ለሁሉም ክልሎች እንደሰርቶ ማሳያ ሞዴል የተባለች ትግራይ የስራ አጥነት ተስፋፍቶ አምራች ሃይል ወጣቶች ወደ ስደት የፈለሱባት፣ ህዝብ ነፃተኑን አጥቶ ተጨቁኖ የሚኖሩባት፣ ህዝቡ ወደ ኃላ ተመልሶ ልጆቹን ለመስዋእት መክፈሉ የሚቆረቆሩባት፣ የተማሩና ያልተማሩ ወጣቶች ስራ አጥተዉ በጎዳና የተዘረጉባት ፣ ዜጎች ምክንያቱ ባልታወቀ ሞተዉ በጎዳና የሚገኙባት፣ ሁሉም ህዝብ በ1ለ5 በ1ለ10 በ1ለ30 እየተደራጀ በስለላ መርበብ የታፈነባት፣ ነዋሪ ህዝብ አስተማሪዎች መላዉ የመንግስት ሰራተኛ በከባድ የኑሮ ውድነት ምክንያት ሊኖሩ የማይችሉበት ሁኔታ የተፈጠረበት ፣የህዋህት መሪዎችና ጥቂት ካድሬዎች የሚናጥጡበት የካቲት 11 አካል ጉዳተኞችና የተሰዉ ታጋይ ወላጆች አረጋውያንን ለልመና የተዳረጉበት፣ የህፃናት መብት የማይከበርበት፣ህፃናትና ቦዘኔዎች ተደራጅተዉ በዝፅ ደንዝዘዉ ለሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲ የሚደበድቡባት፣ የሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የታገዱባት ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋዜጠኞች በእስር ቤት የሚማቅቁባት፣ የፓርቲ አባላት በግልፅ ባደባባይ የሚደበደቡበት፣ የተማሩና ያልተማሩ ሴቶች በድህነት ምክንያት ወደ ዝሙት ስራ የተሰማሩባት፣ ትምህትቤት መስጊድ ፣ቤተክርስቲያን፣ ዩኒቨርሲቲዎች የህ.ዋ.ሃ.ት የፖለቲካ ማደራጃ የሆኑባት ፣የትምህርት ጥራት ትግራይ ኃላ የተሰለፈችበት የአስተማሪነት ስራ የተጠላበት፣ የሃይማኖት መብት የማይከበርባት የካቲት 11 2006
ህዝብ ታሞ ህክምና ኣጥቶ ወደ ጥንቆላና ደፍተራ ጥገኛ ሆኖ የቀሩባት የህ.ዋ.ሃ.ት አባል ፓርቲ ያልሆነ ስራና የትምህርት እድል ሌሎች እንደ ዜጋ ሊያገኘዉ የሚገባ ጥቅማ ጥቅም የተነፈጉባት፣ የተበላሸ አስተዳደርና የፍትህ አጥነት የነገሰባ፣ት የሃገራችን ሃብት በባለስልጣናትና ጥቂት ባለ ሃብቶች የተመዘበሩባት፣ የካቲት 11 የንግድ ስራ የቀዘቀዘባት፣ በመሬት ፖሊሲ ምክንያት የግል ኮንስትራክሽን ስራ ፍፁም የተቋረጠበት፣ መላዉ ትግራይ በውሃ እጦት የተቸገረበት፣ ጥቂት ሰዎች በምቾት የሚኖርባት ብዙሃኑ በረሃብ የሚታረዙባት፣ ቂም በቀልና ውሸት የነገሰበት፣ በውሸት ልማት የበለፀገች፣ የዲሞክራሲ ሽታ የማይታይባት የካቲት 11
በወሊድ ምክንያት ብዙ እናቶች የሚሞቱባት፣ ትላልቅ ከተሞች ከገጠር በሚሰደዱ አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ህፃናት በልመና የተሰማሩባት፣ የክለሉ ሃብት በህ.ዋ.ሃ.ት አመራር ቁጥጥር ስር የገባበት፣ ለህፃናት ለፍትህ ፣ ለእኩልነት ብለዉ የተሰዉ ጀግኖች የተከዱባት የካቲት 2006 በሚሊዮኖች መስዋእት የፀደቀዉ ህገ-መንግስት ፍፁም የተናደባት ፣በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በስደት የተዋረዱባት፣ የሃገራችን ሉአላዊነት የተቆራረሰባት፣   ከፌዴራል እሰከ ቀበሌ የተዘረጋ የህ.ወ.ሃ.ትና የአጋር ፓርቲዎች አመራር በሙስና የተበላሹበት፣ የካቲት 2006 የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ፋሽስታዊና ፀረ-ዲሞክራሲ ባህሪያቸዉ የተጋለጡባት የህ.ዋ.ሃ.ት ቁንጮዎች የሃገራችን ሃብት አሟጠዉ ውጭ ያሰፈሩባት ቤት ሰርተዉ ለልጆቻቸዉ ውጭ ያሰፈሩባት ፣ ህዝቡ አማራጭ አጥተዉ በጨለማ ቁጭ ያለባት፣ የሃገራችን ምሁራን ተገልለዉ ሃገሪቱ በጥቂት መሃይም ካድሬዎችና በቀበሌ ቦዘኔዎች የምትመራበት፣ ከስዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ዜጎች ማቋቋሚያ አጥተዉ ተመልሰዉ ወደ ስደት የፈለሱባት የካቲት 2006 ባጠቃላይ የካቲት 2006 ለህዋሃት መሪዎች ጨለማ ለህዝብ ብሩህ ተስፋ ሊፈነጥቅበትየሚያስችል ሁኔታ ነዉ ያለዉ ምክንያቱም የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች መዋቅራቸዉ ከድቷዋቸዉ የተቃውሞ ሃይል እየበረታ በመምጣቱ ስጋት ላይ ይገኛሉ።


ሁኔታዉ እንደዚህ እያለ የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ለመጭዉ 2007 ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝበ ጋር እንዳይገናኙ ለህዝብና ለፓርቲዎች አፍኖ መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል ይህ ተግባር ከወዲሁ ከህዝቦች የተባበረ ትግል ማገቻ ማግኘት አለበት እላለሁ።

እየተዋረዱ መገዛት እስከመቼ!?

አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል። 
የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ይህ የህወሀት የጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚመራው በዋና ዋናዎቹ የወያኔ  ሹሞች ቢሆንም ወያኔ የአማራን ህዝብ የሚገድለዉ፤ የሚያዋርደዉና የሚያሳደድዉ አማራ ነን በሚሉ ነገር ግን የአማራን ህዝብ በጅምላ በሚሰድቡና አማራዉ ሲገደል፤ ሲታሰርና ሲፈናቀል ይበልህ በሚሉ በእነ አለምነው መኮንን አይነት ወፍ ዘራሽ ካድሬዎች ነው። አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል እንዲሉ፡ የአማራው ህዝብ ዛሬ ቀን ጣለውና፣ በጠላቶቹ እጅ ወደቀ፣ የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሰው። አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል።
በርግጥ ወያኔ እንደፈረስ የሚጋልበው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ ሲያፈራ አልታየም። የአማራ ህዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በባዕድ ወረራ ጊዜ ለጣልያን ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖችን ይሰሙ ነበር። ብአዴን ግን ራሱን ከባንዳነትም አውርዶ ባርነት ደረጃ ላይ የጣለ ከመሆንም አልፎ  በባርነቱ የሚደሰት ድርጅት ነው። ብአዴን የህወሓት ወያኔ ወኪል እንጅ የአማራው ህዝብ ወኪል አይደለም፡፡ ብአዴን ሁሌም የአማራውን ህዝብ እንደ ሰደበ፣ እንዳዋረደ፤ እንዳስገዛ ነው፡፡ የብአዴን ፍሬ የሆነው አለምነው የተባለው የእናት ጡት ነካሽም በድጋሚ ያረጋገጠልን ይንኑ ነው። አለምነዉ እነዚያን እጅግ አሳፋሪና ከፋፋይ ንግግሮች የተናገረዉ ፀረ አማራና ፀረ-ኢትየዮጵያ ጌቶቹን ያስደሰተ መስሎት ወይም የሥልጣን ቆይታውን ያመቻቸና በሥልጣን መሰላል ሽቅብ የተወነጨፈ መስሎት ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም የአማራ ህዝብና ወገኑ የሆነዉ ሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የአንድን ህዝብ ስብእናና ክብር የሚያጎድፍ  ንግግር በምንም መልኩ ችላ ብሎ ሊያልፈዉ አይገባም፡፡
እንደሚታወቀው ዘረኛው ወያኔ የጸረ አማራነት አቋሙ እጅግ የከፋ ፣ ስር የሰደደ እና በድርጅት የታቀፈ ነዉ፤ እኛም በድርጅት ታቅፈን በድርጅት ካልገጠምነዉና ካልደመሰስነዉ በቀር የወያኔ ዘረኝነት መቆሚያና ማለቂያ የለዉም። ለምሳሌ ፋሽስቱ ወያኔ በቅርቡ በቤኒሻንጉልና በቤንች ማጅ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ዉስጥ አማራውን በማፈናቀል አማሮች ከአማራ ክልል ዉጭ መኖር አትችሉም ብሏል። የወያኔ ዘረኞች እነሱ በዘጠኙም ክልል እንዳሻቸዉ እየዞሩና ኃብት እያጋበሱ አማራዉን ግን እንደ ውጭ ዜጋ በማየት በገዛ አገሩ ውስጥ ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ አማራዉ ሳይወድ በግዱ የስደት ገፈት ቀማሽ እንዲሆን አድርገዉታል። ኧረ ለመሆኑ ይህ የግፍ ፅዋ ሂትለር በጀርመን በይሁዳዎች ላይ ከፈፀመው በምን ይለያል? እንደምናስታውሰው በሽግግሩ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር በነበረው ታምራት ላይኔና በወቅቱ ፕረዜዳንት በነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ በተፈራ ዋልዋ አቀናባሪነት በተሰጠ ትእዛዝ በወተር፤ አርባ ጉጉና በበደኖ ኦህዴድና ኦነግን በየፊናው አስማርተው የኋላ ድጋፍ እየሰጡ ውድ ወገኖቻችን ህይወታቸው ስታልፍ እንደ እንሰሳ ቆዳቸው መገፈፉ፤ ሳይሞቱ በገደል ሲጣሉና ሕጻን ሽማግሌ ሴት ወንድ ሳይለይ በጅምላ የማለቃቸውን ሃዘን ሳንረሳው ዛሬ ደግሞ ዳግም የጠብ አጫሪነቱን፡ በምን ታደርጉኛላችሁ እብሪት ተወጥሮ በባንዳው አለምነው መኮነን አስፈፃሚነት ለክልሉ ህዝብ ያለውን ከፍተኛ ንቀት ሬት ሬት በሚሉና አጥንትን የሚሰረስሩ ስድቦችን በመጠቀም አንካችሁ አሉ። አለምነው መኮነን የረጨውን መርዝ እስኪ አስቡት ወገን? ማንን ተማምኖ፡ የልብ ልብ ተሰምቶት ይመስላችኋል ይህ የመርገምት ልጅ ይህን ያህል ልሃጩን በጨዋው የአማራ ህዝብ ላይ የሚተፋበት? አረመኔውን የፋሽስት አገዛዝ አደለምን። ኧረ ግን አማራው እስከመቼ በዚህ የፋሽስት ስርአት እየተገደለ፡ እየተሰደደና እየተዋረደ መኖርን መረጠ? ኧረ ዝምታው ምንድነው? ግን እስከመቼስ ይሆን?
ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!
ፋሽስቱ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በተከታታይ በማድረስ ላይ ያለዉ በደል፤ ግፍና ዉርደት የወያኔ ዘረኞች ሊነግሩን አንደሚፈልጉት የአማራዉ ጉዳይ ነዉ ተብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።ይህ ዛሬ በአማራዉ ላይ እየፈጸመው ያለው ዘርን የማዋረድና የማጥፋት ርካሽ ስራ ነገ በእያንዳንዳችን ላይ የሚደርስ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። የወያኔ ወንጀል አሁን የተጠነሰሰ ሳይሆን ወያኔ ገና ደደቢት በረሃ ላይ ሲጠነሰስ አብሮት የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ። ወያኔና ዘረኛ ስርአቱ እስካልተወገዱ ድረስ ይህ የተጀመረው አማራን የማዋረድ፡ የመጨፍጨፋ፣ የማፈናቀልና የማሳደድ ዘመቻ፣ ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም። ወያኔ አማራዉን ካዳከምኩ ሌላዉ አያቅተኝም በሚል ዘረኛ ስሌቱ ዛሬ አማራዉ ላይ አተኮረ እንጂ በወያኔ የተደበደ ፣ የታሰረ፣ የተሰደደ፤ የተፈናቀለ ፤እንዲራብ የተደረገ፤ የተዋረደና የተገደለ ኢትዮጵያዊ ስፍር ቁጥር የለዉም። ዛሬ  የአማራው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየማቀቀ ነው። ስለዚህ ችግሩ የአገርና የወገን የህልውና ጉዳይ እንጅ  የፖለቲካ ጨዋታ ባለመሆኑ የወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ጾታ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ በመስጠት አለበት ባይ ነኝ። በአማራው ህዝብ ላይ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜው አሁን ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።
በወያኔ ዙሪያ ተሰብስባችሁ የሥርዓቱ ጠባቂና ተጠቃሚዎች የሆናችሁ በሙሉ ባሳለፋችሁት የግዛት ዘመናችሁ የአማራውን ዘር ብትሰድቡትም፡ ብትገድሉትም፡ ብታስሩትና ብታስርቡትም፤ ብታሰድዱትም፤ ሀብት ንብረቱን ብትዘርፉትም፤ በአገሩ በኢትዮጵያ የመኖር መብቱን ብትገፉትም ሕዝቡ መሃሪ ነውና ዛሬውኑ የሕዝቡን ትግል ብትደግፉና ብትቀላቀሉ ይሻላል።  በተለይ አማራ ሆናችሁ ብአዴን የሚባል የፋሽስቱ ወያኔን የጥፋት ክንፍ ስታገለግሉ፡ እስከ ዛሬ በሆዳችሁ ስትገዙ የኖራችሁ እንደ አለምነው መኮንን አይነት የእፉኝት ልጆች ሕዝባችሁን የማዋረድና፤ የማድማት ተልኮዋችሁን አቁማችሁ፤ ወያኔ በወገኖቻችሁ ላይ እየፈጠረ ያለው ችግር ተሰምቷችሁ፤ ህዝባችሁን ይቅርታ ጠይቃችሁ፤ አሁኑኑ ለትግሉ ምላሽ በመስጠት መከታ በመሆን አዝሎ ያሳደጋችሁን ህብረተሰብ ከባርነት ቀንበር ታላቅቁት ዘንድ ወገናዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። ለውሳኔው አለማርፈዳችሁን በዚሁ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ ጭምር እወዳለሁ።