24 Jan 2014 | 6:08 pm
ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት፣ ከልማትና መልካም አስተዳዳር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከራሳቸው ከእስረኞች ነው። ለኢሳት ከተላከው ስም ዝርዝር ለመረዳት እንደተቻለው አብዛኞቹ እስረኞች አርሶ አደሮች ቢሆኑም፣ 5 የሃይማኖት አባቶች፣ 7 መምህራን፣ 6 ነጋዴዎች፣ 25 ተማሪዎች፣ 22 በልዩ ልዩ የመንግስት ስራ ላይ የሚገኙ፣ 5 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል።
ከእስረኞች መካከል 27ቱ እድሜያቸው ከ60 እስከ85 የሚጠጋ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከ50 በታች ናቸው።፡ በጸታ ደረጃ ደግሞ 7ቱ ሴቶች ናቸው። በትምህርት ደረጃም ፒ ኤች ዲ፣ ማስተርስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ምሁራን ታስረዋል።
ካልተሰሩት ነገር ግን ከስራ የተሰናበቱ 6 ፖሊሶች በዝርዝር ውስጥ ሲካተቱ፣ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከስራ መባረር እስከ ወር ደሞዝ ቅጣት እንደደረሰባቸው ተመልክቷል። 17 ሰዎች ደግሞ የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው በተለያየ ቅጣት ተለቀዋል።
የስም ዝርዝሩ ከሰኔ 28/2005 ዓ.ም እስከ ጥር 13/2006 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የታሰሩና የተከናወኑ ድርጊቶችን የሚዘረዝር ነው።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ በእስር ላይ የሚገኙት የቁጫ ነዋሪዎች ከ400 በላይ ይደርሳሉ
Friday, 24 January 2014
የእነ አንዱዓለም አራጌ ቀጠሮ ተምታታ፤ ፍርድ ቤቱ ለጥር 30 ቀጥሯቸዋል፤ ሬጅስትራር በበኩሉ ጥር 24 ቀን 2006 ዓ.ም መቅረብ አለባቸው ይላል- ፍኖተ ነጻነት
January 24th, 2014
በነአቶ አንዱአለም አሬጌ ስም ያለው የክስ መዝገብን በሚመለከት በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተከሳሽ ጠበቆችና ከቤተሰቦች ጋር ብንቀርብም ፍርድ ቤቱ ቀጠሮው ትላንት ስለ ማለፉ ተናግሯል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አጀንዳቸው ላይ የያዙት ዛሬ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ.ም መሆኑን ቢገልፁም በዳኛ አዳነ ንጉሴ፣ ዓሊ መሐመድ፣ አልመው ወሌ እና ሙስጠፋ አህመድ የተሰየመው ችሎት በበኩሉ የቀጠሮው ቀን ትላንት ማለፉን ተናግረዋል፡፡
ችሎቱ ቀጠሮው ዛሬ እንኳ ቢኆን መዝገቡ እጅግ ሰፊ በመሆኑ ውሳኔው እየተጻፈ በመሆኑ ምክንያት ለጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል፡፡
በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር ቀጠሮው ዛሬ መሆኑን አምኖ ነገር ግን ለከሳሽ አቃቤ ህግ መጥርያ ያልተላከ በመሆኑ ለአቃቤ ህግ ድጋሚ ትዕዛዝ ለማፃፍ ጥር 21 ቀን 2006 ዓ.ም ችሎት እንድቀርቡ አዟል፡፡ ከሬጂስትራሩና ከፍርድቤቱ ቀጠሮ የትኛው ትክክል እንደሆነም ለማወቅ አልተቻለም፡፡
በሌላ በኩል አንድነት ፓርቲ ለክትትል ያመቸው ዘንድ የእስክንድር ነጋን የሰበር ሰሚ ይግባኝ ለማጣራት ሙከራ ቢያደርግም በእስክንድር ስም የቀረበ አንዳችም ይግባኝ እንደሌለ ሬጂስትራሩ አረጋግጧል፡፡ ባለቤቱን ጨምሮ ሎሎች አስተያየት ሰጪዎች ግን እስክንድር ያለ ጠበቃ ለመከራከር ይግባኝ ማለቱን አምነዋል፡፡
መንግስት ለአቶ አንዱአለም አያሌው ያቆማቸው ጠበቃና በሽብር ድርጊት ተጠርጥረዋል የተባሉትን ሰዎች ክስ የመሰረተው የመንግስት ዓቃቤ ህግ ከሀገር መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡