January 20th, 2014
በሱዳን፣ ግብጽና ኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረዉ የሶስትዮች ንግግር መበተኑን አስመልክቶ ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት እንዲሁም የፓርላማ አባል፣ የግብጽን አቋም «የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅ» እንደሆነ በመግልጽ፣ መንግስት የወሰደዉን አቋም ደገፉ።
በአባይ ግድብ ዙሪያ እንኳን የተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓርላማ አባል የሆኑት እርሳቸዉም በቂ መረጃ እንደሌላቸዉ የገለጹት አቶ ግርማ፣ «የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከዚህ አንፃር በጭፍን የአባይን ግድብ እንዲደግፉ እንጂ መረጃን መሰረት አድርገው ትንተና እንዲሰሩ እና የራሳቸውን ምክረ ሃሳብ እንዲሰጡ እድል የላቸውም፡፡ ለዚህ ጉዳይ የሚፈለጉት ልማታዊ የሚባሉት ጋዜጠኞች ብቻ ናቸው እነርሱም መንግሰት የሚለውን እንደ በቀቀን መድገም ነው የሚጠበቅባቸው፡» ሲሉ በመንግስት ሜዲያዎች የሚነዙ ፕሮፖጋንዳዎችን አማረዋል።
የሰባአዊ መብት ከተከበረ፣ በአባይ ፕሮጀክት ዙሪያ የተሸፋፈነዉን የተደባበቀ ገሃድ ወጥቶ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ከተዘረጋ፣ ግብጾችን ከመለማመጥ በዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ብቻ ግድቡን ሊገነቡት እንደሚችሉ የገለጹት አቶ ግርማ አገዛዙ በዉጭ ያሉት ለማቀፍ እምሰረታዊ ለዎጦች እንዲያደርግ አሳሰበዉል።
«በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ይህን ግድብ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሊገነቡት የሚችሉበት አቅም እንዳለ ተገንዝቦ ግብፅን አንገት የሚያስደፋ መንገድ ከመቀየስ ይልቅ አሁንም በውጭ የሚገኙትን ዜጎች መከፋፈል ተገቢ አይደለም የሚል እምነት አለኝ» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ የጻፉት።
«የመንግሰት ሹማምንት የአባይ ግድብን ያህል ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው ተቃዋሚና ገዢ ፓርቲ የሚል ክፍተት መፍጠር እንደሌለባቸው ሲነገራቸው፣ በተግባር የሚሰሩትን ሀቅ ወደ ጎን ትተው ጉዳዩን በሙሉ ፕሮፓጋንዳ ያደርጉታል» ያሉት አቶ ግርማ፣ የኢሕአዴግን አግላይ ተቃዋሚዎችን የመግፋት ኃላ ቀር ባህሪን ለማሳየት ሞክረዋል።
«ግብፆች የአባይ ጉዳይ ሲነሳ የፖለቲካ ልዩነታቸውን ትተው እንደ ግብፅ ሲያስቡ እኛን መለያየት ለምን ያስፈልጋል? የአባይ ግድብ ፕሮጀክት በተግባር የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮጅክት አንዲሆን የፖለቲካ ድባቡ ላይ ያጠላው የፕሮፓጋንዳ አዚም ሊገፈፍ ይገባል፡፡ አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን መጠቀም ተፍጥሯዊ መብቷ ነው ይላል፡፡ ይህ የማይገሰስ መብት ላይ ምን ፕሮፓጋንዳ ያስፈልጋል ? የዛሬው መልዕክቴ ዋና ማጠንጠኛ በሀገር ጉዳይ እንዳንግባባ አዚም ያደረገብን ማን ነው? የዚህ አዚም መፍቻ ቁልፍ መተማመን እና ሀገራዊ ዕርቅ ይመስለኛል» ሲሉም በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የፖለቲክ ልዩነቶች ሳይኖሩ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ላይ መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል።
Monday, 20 January 2014
ጡት የሚያሳይ፣ በሕዝብ ገንዘብ የተሰራ ሃዉልት !
January 20th, 2014
የኦሮሚያ ክልል የቱሪዝምና ባህል ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሞሃመድ ጂሊ፣ የአኖሌ ሃዉልት እንደተሰራና በመሰራቱም ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው፣ ገዛ ተጋሩ በተባለ የፕላቶክ ክፍል ቀርበው ገለጹ።
የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች በአርሲ የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል የሚባለዉ ወሬ፣ የቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ በጻፉት መጽሃፍ ከመጻፉና በአንዳድን አክራሪ የኦሮሞ ድህረ ገጾች ላይ ከመዉጣቱ መቀር፣ በታሪክ ባለሞያዎች የተደገፈ፣ ተፈጸመ የተባለውን መፈጸሙን የሚይሳይ መረጃ እስከአሁን አልቀረበብም።
ሆኖም የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ ዉሸት ሊሆን የሚችል ወሬን ተመርኩዞ ፣ በትክክል በተረጋገጠዉ በበደኖ እና አርባ ጉጉ፣ በተፈጸመ ግፍና ጭካኔ ዙሪያ ማስታወሻ ሃዉልቶች ሳይሰሩ፣ በሕዝብና በሕዝብ መካከል ጥላቻ ሊያሰፍን የሚችል፣ የሴት ልጅን ጡቱ የሚያሳይ ሃዉልት በአርሲ መሰራቱ ፣ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ። በበደኖ በኦነግ ታጣቂቶች ነፍሰ ጦር ሴቶች ሁሉ ሳይቀሩ፣ በሕይወት አይኖቻቸውን ተሸፍነዉ የጠልቀ ገድል ዉስጥ እንዲወረወሩ መደረጉ የሚታወቅ ነዉ። በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ.ኢሕአዴግ ታጣቂዎች አቀነባባሪነት፣ በአርባ ጉጉ አርሲ በርካታ ዜጎች በተኙበት ቤታቸው እንዲቃጠል ተደርጎ አልቀዋል።
አንዳንድ የኢሕአዴግ ደግፊዎች፣ «የኦሮሚያ ክልል ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ነዉ። ፌደራል መንግስት እዚህ ዉስጥ ጣልቃ አይገባም። ነበገሩም የለበትም። ክልሉ እንጂ» በማላት ሃላፊነት ላለመዉሰድ እየሞከሩ ነዉ።
«በተለይም የአርሲን ሕዝብ ጨምሮ፣ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከድህነት ጋር እየታገለ ባለበት ወቅት፣ በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ፣ ከሕዝብ ካዝና ተሰብስቦ፣ ይህ ሃዉልት መሰራቱ፣ ኢሕአዴግ/ኦሕደድ ምን ያህል ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ፣ ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ዜጎችንም ወደኋላ እየጎተተ እንደሆነ የሚይሳይ ነዉ» ሲሉ የገለጹት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ኢትዮጵያዉያን በተለይም ኦሮሞ ነን የሚሉ ከበስተጀርባ ያለዉን ተንኮል እንዲያስተዉሉ መክረዋል።
ኦሕደድ እና በዉጭ እየጮሑ ያሉ አክራሪዎች፣ ኦሮሞዉ በተቀረዉ ሕዝብ እንዲጠላ እያደረጉት ነዉ » ያሉት እኝህ ተንታኝ፣ የኦሮሞዉ ማህበረሰብ በአካባቢዉና አብረዉት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር እድሉ የተሳሰረ እንደመሆኑ፣ የሚያፋቅርና የሚያሰባስብን አጀንዳ የሚያራምዱትን እንጂ፣ አካራሪዎች ማስተናጋድ እንደሌለበት ይናገራሉ።
በአርሲ፣ በሕዝብ ገንዘብ የተሰራዉን ጡት የሚያሳይ ሃዉልት ለማየት እዚህ ይጫኑ !

ድሃን የምትወድና የምትረዳ ሴት፣ ርዮት፣ ሽብርተኛ ስትባል !
January 20th, 2014
ጃኑዋሩ 22 ቀን 33ኛ አመቷን ታከብራለች። በሃይ ስኩል የእንግሊዘኛ አስተማሪ ነበረች። በሕገ መንግስቱ ላይ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም፣ በተለያዩ አገር ውስጥ በሚታተሙ ሜዲያዎች ትጽፋለች። «እነርሱ እንዲጻፍ ከሚፈልጉት ዉጭ እንዲጻፍ የማይፈልጉት ባለስልጣናት፣ የሃሰት ክስ መሰርተዉ፣ ዳኛ ለተብዬዎች መመሪያ ሰጠዉ፣ መሰረተ ልማቶችን ለማፍረስ አሴራለች፣ ሽብርተኛ ናት» ብለዉ ፈረዱባት።

ይች ሴት ርዮት አለሙ ትባላለች። ጡቷ አካባቢ ችግር ስላለበት ክትትል እንደሚያሰልጋት እየታወቅም ክትትል ለማግኘት አልቻለችም። ከሁለት አመት ተኩል በላይ፣ ባላጠፋችዉ ጥፋት፣ ኢሕአዴግን ስለተቃወመች ብቻ፣ እየማቀቀች ነዉ። የርዮት ወንጀል አገሯ፣ ሕዝቧን መዉደዷ ነዉ።
ርይቶ አለሙ፣ ከጋዜጣኛ ነብዩ ሃይሉ ጋር በአዲስ ፕሬስ፣ ከጋዜጣኛ ስለሺ ሃጎስ ጋር በ ቼንጅ መጽሄት ላይ ሰርታለች። ነብዩና ስለሺ፣ በአንድነት ራዲዮ ስለርዮት አለሙ፣ ከሚያወቁት ያጋሩንን ጥቂቱን ላካፍላችሁ።
ያዉ በአገራችን ባለዉ የዘር ፖለቲካ ምክንያት «የትግራይ ልማት ማህበር»፣ «የአማራ ልማት ማህበር» የሚባሉ አሉ። እነዚህ ማህበራት በየቦታዉ ለልማት ሥራ በሚል ገንዘብ ያሰባስባሉ። የአማራዉ ልማት አማራ የሚላቸዉን ነዉ የሚያነጋግረዉ፣ የትግሬዉ ደግሞ ትግሬዎችን።
አንድ ጊዜ የትግራይ ልማት ማሕበር ርዮት በምታስትምረበት ትምህርት ቤት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ትኬቶች ይሸጣል። አንዱ ትኬት 30 ብር ነበር። በትግራይ፣ መቀመጫ አጥተዉ በመሬት ላይ ተቀምጠዉ የሚማሩ ተማሪዎች የሚያሳይ ቪዲዮ አሳዩ። ርዮት «ይሄማ መሆን የለበትም» ብላ በቪዴዎ የታዩ ተማሪዎችን ለመርዳት ወሰነች። እርሷ ብቻ 300 ብር አወጥታ አሥር ትኬቶች ገዛች። ሌሎች ጓደኞቿም እንዲገዙ ግፊት አደረገች። ምንም እንኳን ትግሬ ባትሆንም፣ የትግራይ ልማት ማህበሩ ያነጣጠረው ትግሬዎች ላይ የነበረም ቢሆን፣ እርሷ ግን ያየቸው የተማሪዎችን ዘር ሳይሆን፣ ስብእናቸዉን እና ኢትዮጵያዊነታቸውን ነበር።
ርዮትን ያሰሩ ሰዎች፣ «መሰረተ ልማትን ለማፍረስ ፣ በሰዎች ላዩ ጉዳት ለማድረግ የምትፈልግ ፣ አሸባሪ ናት» ነዉ የሚሉን። እንግዲህ በትግራይ ያሉ ተማሪዎች ይመስክሩ።
በአገራችን ትልቅ የኢኮኖሚ ችግር እንዳለ የሚታወቅ ነዉ። ጥቂቶች እላይ ሲመጠቁ፣ አብዛኛዉ ኑሮ ከብዶት፣ በቀን አንዴ እየተመገበ ነዉ የሚኖረዉ። ርዮት አስተማሪ እንደመሆኗ በተማሪዎቿ አካባቢ ያለዉን ችግር ታዉቃለች። ብዙ ጊዜ በጠኔ ሲወድቁ አይታለች። ብዙዎች እንደ ታላቅ እህት ችግራቸውን ያጫዉቷታል። አቅሟ በፈቀደ መጠን ከማስተማር በተጨማሪ ተማሪዎቿን የምትረዳ ፣ የተከበረችና የተወደደች ምህሩ ነበረች። በጣም ችግረኛ ለሆኑ፣ አሥራ ሁለት ተማሪዎች፣ የሚለብሱት ዩኒፎርም በየአመቱ የምታሰፋ ነበረች።
ርዮትን ያሰሩ ሰዎች፣ «መሰረተ ልማትን ለማፍረስ ፣ በሰዎች ላዩ ጉዳት ለማድረግ የምትፈልግ አሸባሪ ናት » ነዉ የሚሉን። እንግዲህ በአዲስ አበባ ያሉ፣ ርዮት እንደ ታልቅ እህት የረዳቸቸዉን የደገፈቻቸው ተማሪዎች ይመስክሩ።
አንድ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ሆነ። አንድ በጣም ጎበዝ የሆነ፣ ተማሪዎ፣ የማትሪክ ዉጤት እንደጠበቀዉ አልመጣለትም። የመንግስት ተቋማት መመደብ አልቻለም። በዚህም ምክንያት በጣም ተስፋ ቆርጦ እራሱን ወደ ማጥፋት ደረጃ ደረሰ። ይሄንን ስትሰማ ቤተሰቦቹን አነጋገረች። ያለዉን ነገር አስረዷት። በጣም ድሃዎች እንደመሆናቸው፣ ልጃቸውን የግል ትምህርት ቤት ከፍለው ሊያስተምሩት እንደማይችሉ ነገሯት። ይህን ወጣት፣ ወጭዉን በሙሉ ሸፍና፣ ዩኒቲ ኮሌጅ ገብቶ እንዲማር አደረግቸው።
እንግዲህ አስቡት ወገኖቼ፣ እንደ ርዮት አለሙ አይነት የተከበሩ፣ አገር ወዳድ፣ ለሰው የሚያዝኑ ኢትዮጵያዉያንን ነዉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሽብርተኞች እያለ ወደ ቃሊቲ የሚወረወረው። ዜጎች መልካም በሰሩ፣ የአገርንና የወገንን ጥቅም ባስቀደሙ፣ ለሕዝብ ክብርና ነጻነት በቆሙ፣ ፍትህን በሰበኩ፣ የአገሪቷ ባለስልጣናት የሚሰሩትን ስህተቶችን በደሎች ባጋለጡ ለምንድን ነዉ የሚታሰሩት ? ኢትዮጵያስ እስከምቼ ለልጆቿ ሲኦል ትሆናለች ?
አንዳንድ ሰዎች በጣም ክፉ ከመሆናቸው የተነሳ ሌሎች ሲሰቃዩ የሚደስቱ አለ። እነዚህ በዉስጣቸው ያለው የሕሊና ድምጽ የማይቃጭልባቸዉ ፣ ርህራሄና ሃዘኔታ የሚባል ነገር የሌላቸው፣ ለስብእና ክብር የማይሰጡ ናቸው። ኢሕአዴግ እየተመራ ያለ በእንደነዚህ አይነት ሰዎች ነዉ። እነዚህ ሰዎች የራሳቸዉን የጠላቻ እርካታ ለማጥገብ ሲሉ በሚሰሩት ግፍ፣ ኢሕአዴግን ወደ ገደል እየወሰዱኢት ነዉ።
የርዮት አለሙ መታሰር እንደ ፓርቲ ኢሕአዴግ ለሚያደርጋቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ምንም አይጠቅምም። በፖለቲካም የበለጠ እንዲጠላ ነዉ እያደረገው ያለዉ። የኢሕአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የሚመሯቸውን አክራሪዎች ገፍተዉ እንዲያስወጡ እመክራቸዋለሁ። በአስቸኳይ ርዮት አለሙ እንዲሁም ሌሎች የሕሊና እስረኞች መፈታት አለባቸው። ቀናት እየጨመሩ በሄዱ ቁጥር ነገሮች እየተወሳሰቡ ነዉ የሚመጡት። ኢሕአዴግ እየመነመነ፣ እነርዮት አለሙ ደግሞ ተወዳችነታቸው እየጨመረ ነዉ የሚመታዉ።
ርዮት አለሙ፣ አሁን ብትታሰርም፣ ሚሊዮኖች የርዮት አፍ ሆነዉ ድምጻቸዉን ያስተጋባሉ። የሚሊዮኖች የፍትህ ድምጽ የአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ግድግዳን እያለፈ፣ ባለስልጣናቱ በተኙበት ይሰሙታል። ያለ ምንም ጥርጥር ርዮት አለሙ፣ እንደ ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንድቅ አላማ በላይዋ ላይ ለብሳ በክብር ከቃሊቲ ትወጣለች።
በርዮት ዙሪያ በአንድነት ራዲዮ የቀረበዉን ለማዳመጥ የሚከተለዉን ይጫኑ !

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!
January 20, 2014
ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል።
ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን።
ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩ ያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።
“የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡
በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-” ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም! በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!