Friday, 3 January 2014
የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ (ከፈቃዱ በቀለ)
መግቢያ
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ “ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በህወሀት ውስጥ የሚገኙ አክራሪ የሚባሉት ቡድኖች የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ሙስና ለመከላከል ብቃቱ ጎሏቸዋል በሚል እንደተነጋገሩና ጉዳዩ በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ክፍል ሲታይ ቆይቶ በመጨረሻም ይፋ ተደርጎ” ሶስቱም ጄኔራሎች በያዙት ማእረግ ሃለፊነታቸው ቀንሶ እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል። ይሁን እንጅ ጄ/ል ሞላ እና ጄ/ል ሳህረ ከጄኔራል አበባው ጋር በአድማው የተሳተፉት ሆን ተብሎ ጄ/ሉን ከስልጣን ተፎካካሪነት ለማስወጣትና ፍትሀዊ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን ለተቀሩት የሰራዊቱ አባላት ለማሳየት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል ሳሞራን ይተካሉ ተብለው የሚታሰቡት በቅርቡ የሌ/ጄ ማእረግ ያገኙት ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ናቸው። የተለያዩ ወታደራዊ አዛዦችን በማነጋገር ስለነበረው ሙሉ ድራማ ከዜናው በሁዋላ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።
የወያኔን “አንድ ለአምስቶች” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው
January 3, 2014
ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው በ“አንድ ለአምስት” አደረጃጀትእያደራጀው ነው። ይህ አደረጃጀት ስታሊን ለሠላሳ ዓመታት ሶቭየት ኅብረትን፤ ኤንቨር ሆዣ ደግሞ ለአርባ ዓመታት አልባኒያን ጠፍረው የገዙበት ስልት ነው። በዚህ የአገዛዝ ስልት መሠረት እያንዳንዱ ሰው በመዋቅር ተይዞ አራቱ ለአንዱ መረጃ የሚያቀብሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።
ሕዝብን በድርጅት አባልነት ስም በመዋቅር ማስገባት ለአንባገነኖች የሚሰጠው ዋነኛ ጥቅም የማኅበረሰብን ስነልቦና መስበሩ ነው። ይህ አወቃቀር ዜጎች የአምባገነኑን መንግሥት ኃይል ከመጠን በላይ አግዝፈው፤ እራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል። ዜጎች፣ “መንግሥት እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥሮ ያውቃል” በሚል የፍራቻ ቆፈን እንዲያዙ ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ጓደኛውን እንዲጠረጥር በማድረግ አምባገነኖች የስለላ ተቋማቸዉ ጠንካራና ሁሉን-አዋቂ እንዲመስል ያደርጉታል።
ይሁን እንጂ የማኅበረሰብ ስነልቦና ካልተሰበረ፤ በፍራቻ ፋንታ በራስ መተማመን ከዳበረ ማንም ያደራጀው ማን ነፃ ህሊና ያላቸው አባላት ድርጅቱን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ይጠቀሙበታል። አሁን በደረስንበት ሁኔታ ይህንን በአገራችን ተግባራዊ የማድረግ ሰፊ እድል አለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ፍራቻ እራሱን ነፃ እያወጣ ነው። ወያኔ ከስታሊንም ሆነ ከኤንቨር ሆዣ በተለየ መንገድየአመለካከትና የርዕዮተዓለም ጉዳይ የሚያሳስበዉ ሀይል አይደለም።ቢያሳስበውም የሕዝብን ቀልብ የሚይይዝበት ምንምነገር የለውም። ይህ ባህሪይዉ ነዉ ነው ወያኔ በእጅጉ የተጠላ ኃይል እንዲሆን ያደረገው።
እንዲህ በግዴታ እንጂ በእምነት ያልተሰባሰቡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተመሳሳይ ፀረ-ወያኔ አቋም ያላቸው ሰዎች በአንድ “አንድ ለአምስት” ሕዋስ ውስጥ የመገኘታቸው አጋጣሚ የጎላ ነው። እነዚህ አባላት በግልጽ ከተነጋገሩበት ሕዋሱን ለፀረ-ወያኔ ትግል ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በመሆኑም ወያኔን ለመጨቆኛ መሣሪያነት ያዋቀረውን “አንድ ለአምስት” ራሱ ወያኔን መታገያ ብሎም ማዳከሚያ መሣሪያ ማድረግ ይቻላል። “አንድ ለአምስትን” በሽፋንነት በመጠቀም ውስጥ ውስጡን መጀራጀት በስፋት ልንይዘዉና ልንሰራበት የሚገባ ስትራቴጄ ነው።
የወያኔ “አንድ ለአምስት” የኑሯችን አካል እየሆነ መጥቷል። በአንዳንድ ቦታዎች አለመደራጀት ሥራ የሚያሳጣ እየሆነ ነው። በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ወያኔ ጉያ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች ካሁን በኋላ መሥራት ያለባቸው ወያኔን ከውስጥ ሆኖ የማዳከምን ሥራ ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ “አንድ ለአምስት” አመቺ የሆነ መዋቅር አይገኝም።
በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7 ሕዋሳቶቹን በሁሉም ቦታ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤በዚህም መሠረት የግንቦት 7 ሕዋሶች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ባልተማከለ መልኩ በብዛት እየተመሠረቱ ነው። ከዚህ ህዋሳቶችን ከመዘርጋት ሥራ ጎን ለጎን ህዝቡ በያለበት የወያኔንየራሱንመዋቅር በመጠቀም ወያኔንና ስርዐቱን መገዝገዝ አለበት።
ይህንን ለማድረግ የግንቦት 7ን መመሪያ መጠበቅ አያስፈልግም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ መንገድተግባራዊ ሊያደርገው የ የሚችለዉ ነገር ነው።
በመሆኑም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ “አንድ ለአምስቶችን” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!