Tuesday, 31 December 2013

በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ”ና በሁለት ተጨማሪ መጽሀፎች ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

|
Democracy-and-Development-in-Ethiopia-Standing-Book1 brehanu nega
በፖለቲካው ዓለም ጉልህ ስፍራ ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አዲስ መጽሃፍ ያነበብኩት ዘግይቼ ነው ፤ ለመዘግየቴ ሶስት መሰራታዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፣ አንዱና ዋናው ዶ/ሩ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ስላቀረቡ በመጽሀፉ ውስጥ እምብዛም አዲስ ነገር ያቀርባሉ የሚል እምነት ስላልነበረኝ ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ዶ/ሩ ራሳቸው በከፊል የጠቀሱት ነው፣ “ በአገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር አባል መሆኑን ሲመለከት፣ ከቅንጦትም ባሻገር በተወሰነ ደረጃ “ የስራ ፈትነት” ወይንም የበለጠ ጠርጣራ ( cynic) ለሆነ ሰው “ በተግባር ስራ ለመስራት ካለመቻል “ የመጣ፤ ተግባራዊ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ሊመስል ይችላል” የሚለው ነው። ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ፣ ፋሽን በሚመስል መልኩ በአገር ቤት የሚኖሩ ፖለቲከኞች በተከታታይ መጽሃፎችን በማሳተማቸው ለእነሱ ቅድሚያ ለመስጠት በመፈለግ ነው።

ዶ/ር ብርሃኑን ያነበብኩት ሁለቱ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች -ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ” እንዲሁም ኢ/ር ሃይሉ ሻውል “ ሕይወቴ እና የፖለቲካ እርምጃዬ” በሚሉ ርዕሶች ያሳተሙዋቸውን መጽሃፎች ካነበብኩ በሁዋላ በመሆኑ፣ በሶስቱም ስራዎች ላይ መጠነኛ ንጽጽር ለማድረግ አስችሎኛል።

ዶ/ር መረራ ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ ያለውን የአገራችንን ፖለቲካ ግሩም በሆነ መንገድ አቅርበዋል፤ መጽሃፉ ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች የተካተቱበት በመሆኑ ፣ በቋንቋና በዓርትዖት በኩል የሚታይበትን ጉልህ ችግር አይተን እንዳላየን እንድናልፈው ያስገድደናል።
  መጽሀፉ በጥሩ ዓርታዒ እንደገና ቢታረምና ቢታተም “ የተዋጣላቸው” ከሚባሉት የአገራችን መጽሀፎች ተርታ የመመደቡ እድል ከፍተኛ ነው።
ዶ/ር መረራ የአገራችንን ህልውና እየተፈታተነ የመጣውን፣ በ1960ዎቹ ተዘርቶ በእነ አቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ተኮትኮቶ ያደገውን የብሄር ፖለቲካ መነሻ ፣ ያመጣውን ግሳንግስ እና የግሳንግሱን ማራገፊያ መፍትሄ አስቀምጠዋል። መፍትሄ ብለው ያስቀመጡትም በመጽሀፉ የመጨረሻ ገጽ እንደሚከተለው ሰፍሯል፣ “ …ለታሪክም ለህዝብም አስቀምጬ (ማለፍ) የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ ፣ አብዛኛው የትግራይ ሊሂቃን “ ስልጣን ወይም ሞት” ብሎ ስልጣን ላይ የሙጥኝ እስካለ ድረስ ፣ አብዛኛው የአማራ ሊህቃን በአጼዎች ዘመን የነበረውን የበላይነትን መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የሕልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ የኦሮሞ ሊህቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠና የምትወጣ አይመስለኝም።
 በሌላ ቋንቋ ለነዚህ መሰረታዊ በሽታዎቻችን መድሃኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈጽሞ የምታገኝ አይመስለኝም።”
 ( ገጽ 264)። ምንም እንኳ “አብዛኛው” የሚለው ቃል አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችል ቢሰማኝም ፣ ዶ/ሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በትኩረት ሊታይ እንደሚገባው ሳላስታውስ አላልፍም፤ በተለይ” እነዚህ የሶስቱ ብሄሮች ሊህቃን ህልማቸውን እንዲተው ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሚለው ጥያቄ ለእኔ ቁልፍ ይመስለኛል። ዶ/ር መረራ በዚህ ዙሪያ የተብራራ መልስ ቢሰጡ ኖሮ መጽሃፋቸውን የበለጠ ሙሉ ማደረግ ይችሉ ነበር እላለሁ።

የኢንጂነር ሃይሉ መጽሀፍ የአገራችንን የፖለቲካ ችግር ከግለሰቦች ባህሪ ጋይ ያያዘው በመሆኑ ብዙም ክብደት የሚሰጠው ሆኖ አላገኘሁትም፤ ንድፈሃሳባዊ ትንተናዎች ይጎድሉታል፣ የተዓማኒነት ችግሮችም አሉበት( በተለይ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ስለነበረው የሽምግልና ሂደትና ከዚያ በሁዋላ ስለተፈጠሩት ኩነቶች) ፤ ለተተኪው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት ስለመኖሩም በእጅጉ እጠራጠራለሁ፤ በእርግጥ ኢ/ር ሃይሉ ብዙ ውጣውረዶችን አልፈው እስካሁን በህይወት ለመቆየት መቻላቸው እድለኛ ሰው እንደሆኑ በመጽሃፋ ለማየት ችለናል፣ አገራቸውን የሚወዱ ሰው መሆናቸውንም አስገንዝቦናል። ኢ/ር ሃይሉ የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን መንገድ በመከተል መጽሀፉን በሌላ ሰው በማስጻፋቸው ስለጸሃፊነት ችሎታቸው አስተያየት ለመስጠት አያስችልም ።

የዶ/ር ብርሀኑ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” የሚለው ርዕስ ዘጊ ወይም ለማንበብ የማይጋብዝ ነው፤ በትምህርቱ አለም የዘለቁና የጥናትና ምርምር ወረቀቶችን ለማንበብ ፍላጎት ያላቸው ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር፣ እንደ እኔ አይነቱ ተራ አንባቢ በርዕሱ ማልሎ መጽሀፉን ለማንበብ ስለመነሳሳቱ እጠራጠራለሁ።
  መጽሀፉ ውጫዊ ገጽታው ባያማልልም ውስጣዊ ይዘቱ ግን ድንቅ ነው። እንደምንም የጀመርኩትን መጽሀፍ እየተጨነቁና እየፈራሁ፣ እያዘንኩና ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ፣ እግረ-መንገዴንም የጸፊውን እይታ፣ የትንታኔ እና የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታ እያደነቁኩ ጨርሸዋለሁ። መጽሀፉን እንደጨረስኩ የተናደድኩበት ነገር ቢኖር ጻሃፊው የኢትዮጵያን ችግሮች እንዲያ አድርገው ካቀረቡ በሁዋላ መፍትሄውን በይደር በመተዋቸው ነው።

ከዚህ ቀደም የአገራችንን ሁለተናዊ ችግሮች ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተፈጥሮና የህዝብ ብዛትን በአንድነት አጣምሮ፣ በአገራችን ህልውና ላይ የደቀኑትን ፈተናዎች ቅልብጭ አድርጎ ያሳየ ከገብረህይወት ባይከዳኝ “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” በሁዋላ የተጻፈ መጽሀፍ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ይህን ስል ሌሎች ድንቅ የፖለቲካ መጽሃፎች አልተጻፉም እያልኩ አይደለም፤ የዶ/ር ብርሃኑን መጽሀፍ ለየት የሚያደርገው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮችን ለይተው በማውጣት እርስበርስ ያላቸውን ትስስር ከግሩም ትንተና ጋር ሁሉም ሊረዳውና ሊጠቀምበት በሚችለው መንገድ ማቅረባቸው ነው ። (የምጣኔ ሀብት ትምህርት ( economics) የማይገባው ሰው እንኳ ቢሆን፣ መጽሀፉን አንብቦ ስለአገራችን ኢኮኖሚ ለመረዳት አይሳነውም።) መጽሃፉ የባራክ ኦባማን The Audacity of Hope እንዳስታወሰኝ ብገልጽ ያጋነንኩ አይመስለኝም፣ አጋነኸዋል የምትሉኝ ካላችሁም ” አንብቡትና ሞግቱኝ።

የዚህ መጽሀፍ ትልቁ መልእክት፣ ለእኔ እንደገባኝ፣ “የአገራችን ችግር ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በመገንባት ይፈታል” የሚለው አስተሳሰብ እንደሚታሰበው ቀላል አለመሆኑንና ከአሁኑ መፍትሄ ካልተበጀለት በሁዋላ ላይ ይዞት የሚመጣው ችግር ቀላል አለመሆኑን ማሳየት ነው ። የብሄር ፖለቲካው በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ፣ በአገራችን ልማትን ለማምጣት የሚገጥሙ ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ችግሮች፣ ከአካባቢ ውድመትና ከህዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ በመጽሀፉ በዝርዝር ቀርቧል። በአሁኑ ጊዜ በአገራችን እየታየ ያለውን የገቢ አለመመጣጠንም 1500 ብር የሚያወጣውን የአንድ መለኪያ ውስኪ ግብዣ በምሳሌነት በማንሳት በደቡብ አፍሪካ እንደታየው በአገራችንም ለወደፊቱ ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ጣጣ ጸሀፊው በደንብ አሳይተውናል።

መጽሀፉ የውጩ ፖለቲካ በአገራችን ፖለቲካ ላይ የሚያሳርፈውን ተጽዕኖ እንዲሁም የአለማቀፉ የንግድ ስርዓት በኢትዮጵያ እድገት ላይ ያለውን ተጽእኖ ቢያካትት ኖሮ የበለጠ ድንቅ ይሆን እንደነበር አስባለሁ ። ከዚያ በተረፈ ግን መፍትሄዎቹ በሌላ ክፍል እንደሚቀርቡ መገለጹ በመጽሀፉ ላይ በቂ ክርክር እንዳይነሳ ያደረገው ይመስለኛል። በመጽሀፉ በቀረቡት ችግሮች እና ትንተናዎች ላይ ተቃውሞ የሚኖረው ሰው ይኖራል ብየ አላስብም፣ ተቃውሞ የሚነሳው ችግሮችን ለመፍታት በሚቀርቡት የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ እንደሚሆን በመገመት ቀጣዩ መጽሃፍ አወያይ ( አካራካሪ) ይሆናል እላለሁ።

ስለአገራቸው እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ሁሉ መጽሀፉን እንዲያነቡት እመክራለሁ ( የዶ/ር መረራንም ጨምሮ)። በተለይ በሰላማዊው የትግል ሜዳ ለመፋለም የሚያስቡ ጀማሪም ሆኑ ነባር ፖለቲከኞች የብርሀኑን መጽሀፍ በማንበብና በምርጫ ክርክር ወቅት ይዞ በመቅረብ ( የመፍትሄው መጽሀፍ ቶሎ እንደሚደረስ በመገመት) ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፤ ስልጣኑን ይረከባሉ ብዬ ባላስብም።

Monday, 30 December 2013

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

December 30, 2013
ሁኔ አቢሲኒያዊ



ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡

 በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡
 በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡:
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ '

በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡
 አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!

ደም ሰጥቶ ነፃነት የተከለከለ ህዝብ (ሽሬ) – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

(የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች - ፎቶ ከአብርሃ ደስታ)



ሽሬ ከመቀሌ በስተ ሰሜን ምዕራብ በ320(?) ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ከተማ ናት። በአውቶቡስ ጉዞ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት ይወስዳል (እኛ ስምንት ሰዓት ፈጅቶብናል)። ከመቀሌ ማይመኽደን፣ አጉላዕ፣ ዉቅሮ፣ ነጋሽ፣ እንዳተካ ተስፋይ፣ ፍረወይኒ (ስንቃጣ)፣ማይመገልታ፣ እዳጋሓሙስ፣ ዓዲግራት፣ አሕዘራ፣ ሴሮ፣ እንትጮ፣ ማርያም ሸዊቶ፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ዉቅሮማራይ፣ ሰለኽለኻ አቋርጠን ሽሬ እንዳስላሴ ገባን።

ሽሬ ለም መሬት ነው። ሰፊና ሜዳማ የእርሻ መሬት አለ። ህዝቡ እንግዳ አክባሪ ነው። ሽሬ የሆነ ደስ የሚል ነገር አለው። ግን ባከባቢው ብዙ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ። ይሄን ጉዳይ ሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። አሁን ግን ወደ የስብሰባው ጉዳይ እንግባ።
ዓረና መድረክ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ወሰነ። ስብሰባው የሚያዘጋጅ የዓረና ቡድን ወደ ከተማው ተላከ። በከተማው ስብሰባ ለማድረግ የሚያስችል ፍቃድና መሰብሰብያ አዳራሽ እንዲሰጠን ጠየቅን። ከአንድ ቀን በኋላ ስበሰባ ማድረግ እንደምንችል ፈቅደው አዳራሽ ግን እንደተያዘ ነገሩን። አዳራሽ መከራየት እንደምንችል ካልሆነ ደግሞ በሆነ ሜዳ ማካሄድ እንደምንፈልግ ነገርናቸው። ከአንድ ቀን በኋላ ተነጋግረው አዳራሽ ፈቀዱልን (ሜዳ ላይ ስብሰባ ከተደረገ ለነሱ ጥሩ አለመሆኑ ያውቁታል)።
አዳራሽ ካስፈቀድን በኋላ ሓሙስና ዓርብ ቀሰቀስን። ከአስር ሺ በላይ በራሪ ወረቀት ተበተነ። በማይክሮፎን ተጠቅመን መረጃው ለህዝብ አዳረስን። የከተማው ካድሬዎች በእግርና በመኪኖች እኛን እየተከታተሉና የሽሬ ህዝብ ለኛ ያለው ስሜት ይሰልዩ ነበር። ያኔ ካድሬዎቹና ሰላዮቹ በኛ ላይ ያደረሱት ምንም ተፅዕኖ አልነበረም። የተቀደደብን ወረቀትም ጭራሽ አልነበረም (በሌሎች አከባቢዎች ካድሬዎቹ ወረቀት ተቀብለው የሚቀዱ ነበሩ)። ዓርብ ቤት ለቤት ቀሰቀስን።

ካድሬዎቹና ሰላዮቹ የህዝቡን ጥሩ አቀባበል ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት አደረጉ። ዓርብ ከሰዓት የከተማው የካቢኔ አባላት ተሰብስበው በጉዳዩ ተወያዩ። ዓርብ ማታ (ከምሽቱ አንድ ሰዓት) የከተማው ከንቲባ አቶ መረሳ አታክልቲና ምክትል ከንቲባው መምህር ሃይለ አዳነ ወደ ማዘጋጃቤት ጠርተው ቅስቀሳ ማቆም እንዳለብን ነገሩን። ስላደረግነው ቅስቀሳ በቂ መረጃ መሰብሰባቸው፣ በጉዳዩ ካቢኔ መሰብሰቡና እስካሁን የተደረገ ቤት ለቤት ቅስቀሳ በቂ መሆኑ መግባባት ላይ መደረሱ ተነገረን።

እኛም ተቃወምን። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ደግሞ ‘ስለ ቅስቀሳው በቂነት የምናውቀውና የምንወሰነው እኛ ራሳችን እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ ቅስቀሳችን እንቀጥላለን’ አለ። ምክትል ከንቲባው በጣም ተናዶ ‘አንደኛ ስትቀሰቅሱ መሳደብ አቁሙ’ አለ።

 ‘መቼ ነው የተሳደብነው’ ስለው ‘ግዕዙይ ምምሕዳር’ ብላችኋል አለኝ። ለካ በማይክሮፎን ስንቀሰቅስ የስብሰባው አጀንዳዎች እንዘረዝር ነበር። ከአጀንዳዎቹ አንድ ስለ ‘መልካም አስተዳደር እጦትና መፍትሔው’ የተመለከተ ነበር። በትግርኛ ‘ግዕዙይ ምምሕዳርን መፍትሒኡን’ ይላል። አስገደም አስከትሎ ‘ግዕዝይናኮ ሙስና ነው።

ስለ ሙስና እንነጋገራለን’ አለ (ሙስና በትግርኛ ግዕዝይና ነው)። ምክትል ከንቲባውም ‘ታድያ ሙስናኮ መንግስታችን ህወሓት እየተታገለው ነው ያለው፤ እናንተ ምን አገባቹ’ አለ።
ርእሱ ለመቀየር ሞከርኩ። ‘እስከ ስብሰባው ቀን ድረስ ብንቀሰቅስ ችግሩ ምንድነው’ ብዬ ጠየቅኩ። ከንቲባው ‘አንደኛ ህዝቡ በቅስቀሳው ደስተኛ አይደለም፤ ሊረብሽ ይችላል። ሁለተኛ ነገ ቅዳሜ ነው፤ የገበያ ቀን ነው። ሦስተኛ እስካሁን በቂ ቅስቀሳ ተደርጓል’ የሚሉ ሦስት ምክንያቶች አቀረበ። እኛም ለሦስቱ ምክንያቶች መልስ ሰጠን። ‘አንደኛ ህዝቡ አይረብሽም፤ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል። ሁለተኛ በሕጉ መሰረት ከገበያ ቦታ አምስት መቶ ሜትር ርቀን ነው የምንቀሰቅሰው። ሦስተኛ እኛ በፈለግነው ግዜ ቅስቀሳው እንጀምራለን፣ እናቆማለን’ አልን።

ቅስቀሳው ማቆም እንዳለብን፣ የካቢኔ ዉሳኔና ትእዛዝ መሆኑ ነገሩን። ትእዛዝ ከሆነ በፅሑፍ እንዲያሳውቁን ጠየቅን። በፅሑፍም አሳወቁን። ፅሑፉ ለሚደርስብን ችግር የከተማው አስተዳደር ሐላፊነት እንደማይወስድ ይጠቁማል። ፀጥታ የማስከበር ሐላፊነት የመንግስት ተግባር ነው፤ የኛ ስራ አይደለም ብለን ቅዳሜም ቅስቀሳችን ቀጠልን። ምንም ችግር አልደረሰብንም።

እሁድ ጠዋት በተፈቀደልን አዳራሽ አከባቢ በማይክሮፎን ህዝቡን ስለ ስብሰባ ማስታወስ ጀመርን። መቀስቀስ እንደሌለብን ፖሊስ ነገረን (ፖሊስ ቅስቀሳው ለማስቆም መታዘዙ ነግሮናል)። መቀስቀሱ አቁመን ወደ አደራሹ ሄድን። ከሁለት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ሰዎች ተሰባስበዋል። አደራሹ ግን ዝግ ነው። ዘበኛው እንዲከፍትልን ጠየቅን። ‘አልታዘዝኩም’ አለ። ከድር ወደተባለ አለቃው ደወልኩ። አዳራሹ መክፈት እንዳለበት ነገረው። ባደራሹ በር ሁለት ሰዎች አሉ። ‘ጥብቃ ነን’ አሉ። ግን የህወሓት ካድሬዎች ናቸው።


በሩ ተከፈተ። ህዝብ ለመግባት በር ላይ ሲደርስ ሁለቱ ካድሬዎች ወደ አደራሹ የሚገባ ሰው የቀበሌ መታወቅያ በእጁ የያዘ ብቻ መሆኑ አወጁ። ህዝቡም ‘መታወቅያ አናሳይም’ አለ። ‘መታወቅያ ካላሳያቹ አትገቡም’ ተባለ። ጭቅጭቅ ተጀመረ። ‘በህዝብ ስብሰባ ለመሳተፍ መታወቅያ አያስፈልግም’ ብዬ ለሁለቱም ካድሬዎች ነገርኳቸው። ‘መታወቅያ ያስፈልጋል ተብሏል’ አሉኝ። ‘ህዝቡ መፈተሽ ያለበትኮ ፖሊስ እንጂ እናንተ አይደላችሁም’ አልኳቸው። ካድሬዎቹ የአዳራሹ በር ዘጉት።

ወደ ከንቲባው ደውዬ ህዝብ በፖሊስ ብቻ እየተፈተሸ፣ የቀበሌ መታወቅያ ሳይጠየቅ እንዲገባ ለማድረግ ሕጋዊ ፖሊስ እንዲመደብልን ጠየቅኩት። እሱም ፖሊስ እንደማይመድብ፣ የቀበሌ መታወቅያ ያለው ብቻ መግባት እንዳለበትም ነገረኝ። እኔም እንደዛ ከሆነ ስብሰባው ከአዳራሹ ዉጭ እንደምናደርገው ነገርኩት። ‘አይሆንም’ አለኝ።

‘መታወቅያ ያልያዘ አይገባም’ ስለተባለ ስብሰባው ባደራሹ በር ለማድረግ ተስማማን (ልብ በሉ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ እንደማይመድብና ለሚፈጠረው ችግር ሐላፊነት እንደማይወስድ ነግሮናል)። አደራሽ ዉስጥ ገብቶ የነበረ ሰው እንዲወጣ አደረግንና ስብሰባው ባደራሹ በር አከባቢ ባለው ሜዳ ጀመርን። በጣም ብዙ ህዝብ ነበር (በሺዎች የሚቆጠር)።

የከተማው አስተዳዳሪዎች መጡ (ከንቲባው፣ ምክትል ከንቲባው፣ የፕሮፓጋንዳ ሐላፊው … እስከ ቀበሌ ተጠሪዎች ተሰባስበው መጡ። ስብሰባው ማቋረጥ እንዳለብን ነገሩን። ከፈለጋቹ እሰሩን እንጂ ህዝብ ጠርተንማ ስብሰባ አናቋርጥም አለን። እኛ ከከተማው አስተዳዳሪዎች ጋር እንጨቃጨቃለን። የዓረና ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርሀ ግን ንግግር ማድረግ ጀመረ። አለመግባባቱ ግን እየከረረ መጣ። ባከባቢው ደንብ የለበሰ ፖሊስ አልነበረም። የደህንነት ሰዎች ግን መዓት ነበሩ።

አንድ የፖሊስ አዛዥ መጣ። ‘ስርዓት ያዙ’ አለን። ‘ስብሰባ እያካሄድን ነን’ አልን። ‘እዚህ ስብሰባ እንድታደርጉ አልተፈቀደላችሁም’ አለ (ትክክል ነበር፤ በሜዳ ስብሰባ ለማድረግ አልተፈቀደልንም)። ‘ግን ህዝቡ በካድሬዎች ወደ አዳራሽ እንዳይገባ እየተከለከለ ነው’ ብለን ለፖሊሱ ነገርነው። ፖሊሱ ‘አሁን ወደ ተፈቀደላቹ አዳራሽ ግቡ’ ሲለን ህዝቡ ለመግባት ሰልፍ ያዘ።

‘ህዝቡ መታወቅያ እየተጠየቀ ነው’ ብለን ለፖሊሱ አሳወቅን። (ከከንቲባውና ጓደኞቹ ጋር የምናደርገው ንትርክ ግን እየከረረ ነው)። ፖሊስ ‘መታወቅያ አያስፈልግም። እየፈተሻቹ አስገቡት’ አለ። ከንቲባው ‘ያለ መታወቅያማ ሰው አይገባም’ አለ።

 ፖሊሱና ከንቲባው ተጨቃጨቁ። ከንቲባው ተቆጣው። ከዛ ፖሊሱ እኛንና የህወሓት አባላትን መሸምገል ጀመረ። አስገደ ገብረስላሴ ‘አትረብሹን’ አለ (አስገደ ተናዶ ነበር)። መታወቅያ የያዘ ብቻ ሰልፍ ስይዝ መታወቅያ ያልያዘ ጥግ ያዘ። አንድ የደህንነት ሐላፊ ነው የተባለው ሰው መጥቶ ለሚፈት ሹ ካድሬዎች ‘የቀበሌ መታወቅያ ያለው ሳይሆን የዓረና መታወቅያ ያለው ብቻ ነው የምታስገቡ’ የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ።
‘ስብሰባው’ኮ የህዝብ እንጂ የዓረና አባላት ብቻ አይደለም’ አልኩና ሁኔታው በፌስቡክ ለመዘገብ ወደ ኢንተርኔት ካፌ ገባሁ። በአደራሹ በር አከባቢ የተሰበሰው የሽሬ ከተማ ህዝብ ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነበር እነ አቶ ከንቲባ። ግን በጣም ብዙ ስለነበር በቀላሉ መበተን አልተቻለም። እንዳውም ጭቅጭቁ ለምስማት ይጠጋ ነበር።

ከደቂቃዎች በኋላ ተመለስኩ። አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ወጥቶ በማይክሮፎን መናገር ጀመረ። ‘የሽሬ ህዝብ ታፍነሃል…’ ምናምን ይላል። ከዞኑ ፅሕፈት ቤት ሦስት ሰዎች በፍጥነት ጮክ ብለው እየተናገሩ ወደ ተሰበሰው ህዝብ ተቀላቀሉ። የከተማው አስተዳዳሪዎችና ተጠሪዎች እንዲሁም የደህንነት ሰዎች አሰባስበው አስር ዓመት የማይሞላቸው ህፃናት አስከትለው ‘ሆ’ አሉ። እየጮሁ ዓረናና የዓረና አባላትን መሳደብ ጀመሩ። ‘ዓረና ሻዕቢያ ነው! ዓረና ኪራይ ሰብሳቢ ነው! ዓረና አሸባሪ ነው! እያሉ ይጮኃሉ።
አስገደ ገብረስላሴ ፎቅ ላይ ሁኖ ይናገራል። የሚናገረውን ነገር ህዝቡ እንዳይሰማው ለማድረግ ድምፅ እየጨመሩ ‘አስገደ ሌባ’ እያሉ መጮህ ተያያዙት። ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ተበተነ (ጥጉ ጥጉ ያዘ)። አከባቢው እነሱ ብቻ ተቆጣጠሩት። ፎቅ ላይ ሁነን ቪድዮ ለማንሳት ሞከርን። መጨረሻ እየጮሁ ወደ ዞን አስተዳደር ህንፃ ገቡ። ስብሰባው ተስተጓጎለ።

ረብሻው ይመሩት የነበሩ ሦስት ሰዎች ሲሆኑ ሁለቱ ተፈናቃይ ኤርትራውያን (ግን በማዘጋጃቤት የተቀጠሩ)ና አንድ የደህንነት ሐላፊ ናቸው። ግን ለምንድነው ኤርትራውያን ለህወሓት የሚደግፉ? የሽሬ ህዝብ ህወሓትን ያልደገፈ አርትራውያን ለምን? የሽሬ ህዝብ ግን በሁኔታው እጅግ መገረሙ ከሠዓት በኋላ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

ስብሰባው ተጀምሮ ተስተጓጎለና ወደ ቢሮአችን አመራን። ህዝቡ ‘አይዟቹ’ ይለን ነበር። ከዛ እኔ ወደ ዓድዋ አመራሁ። የማገኛቸው የዓረና አባላት ለማደራጀት ነበር። ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓድዋ ነበርኩ። ዓድዋ ሁኜ ስለ የሽሬ ስብሰባ ለመፃፍ ፈለግኩ። ግን ደክሞኝ ነበር። የተወሰነ መረጃ ለመስጠትና ዓድዋ ከተማ እንደምገኝ ለማሳወቅ ትንሽ ፃፍኩኝ። ግን እንተርኔት ደካማ ስለነበር ፖስት ማድረግ አልቻልኩም። ፅሑፉ ግን በፍላሽ ይዠው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ ወደ መቀሌ ጉዞ ጀመርኩ። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መቀሌ ገባሁ። ዓድዋ ሁኜ የፃፍኩት በመቀሌ ከተማ ለጠፍኩት። ለካ ፅሕፉ ‘ዓድዋ ነኝ ያለሁት’ የሚል አለው።

 (ልብ አላልኩትም ነበር። ያስታወስኩት አሸናፊ የተባለ ጓደኛዬ ሲነግረኝ ነው። ደክሞኝ ነበር። ድካሙ አሁንም አልወጣልኝም)።
‘የምጥሰጠን መረጃ ታማኝ ከሆነ ለምን በፎቶ ወይም ቪድዮ አታስደግፈውም’ የሚሉ አስተያየቶች ይነሳሉ።

 ግን ፎቶ ወይም ቪድዮ የማልለጥፍበት ወይ የማላነሳበት ምክንያት አለኝ። በውቅሮ ከተማ ስብሰባ ስናደርግ ካድሬዎች ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍ ይመልሱ ነበር። ካድሬዎቹ ህዝብ ሲመልሱ በካሜራ እንቀርፃቸው ነበር።

 ባጋጣሚ ግን የከተማው ፖሊስ ኮማንደር ሰው ሲመልስ ቀረፅነው (ከሌሎች ካድሬዎች ጋር)። የፖሊስ ኮማንደሩ ‘ያለ ፍላጎቴ ቀርፀውኛል’ ብሎ ፖሊስ ጣብያ ወሰደን። ካሜራው በፖሊስ ተያዘ። አባሎቻችን ተንገላቱ፣ የተቀረፀ ቪድዮ አጠፉት፣ በዛ ሂደት የዉቅሮ ስብሰባችን ሳንቀርፀው ቀረን።

ከዉቅሮ ትምህርት ወስደን ቀረፃ የምናካሂድ በስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ብቻ ነው። በማይጨው ከአደራሽ ዉጭ አልቀረፅንም። በተምቤን ካድሬዎቹ በአደራሹ በር አከባቢ ተሰፍስፈው ሲያስቸግሩን በሞባይል የምቀርፃቸው መስዬ ባከባቢው አለፍኩ። የተቀረፁ የመሰላቸው የዓብይ ዓዲ ከተማ ፖሊስ ኮማንደር (ክብሮም)ና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱኝ። ‘ያለ ፍቃዳችን ቀረፅከን’ አለኝ። ‘አልቀረፅኩም’ ብዬ ሞባይሌን በባለሙያ ተፈተሸ። ምንም አልቀረፅኩም። ተለቀቅኩ።


ከዚህ በመነሳት በሽሬም እንዳያስተጓጉልን በመስጋት ከአዳራሽ ዉጭ ቪድዮ ለመቅረፅ ይሁን ፎቶ ለማንሳት አልፈለግንም ነበር። ግን ስብሰባው መስተጓጎሉ ከተረዳን በኋላ ግን ሁኔታው በቪድዮ ቀርፀነዋል፣ ፎቶም አንስተናል። የነበረን ሐሳብ ግን ስብሰባው ተጀምሮ የሚካሄደው ዉይይት ለመቅረፅ ያለመ ነበር። የተሳታፊዎች ፍቃድ ከሆነ ማቅረብ እችላለሁ። በሚቀጥለው መታወቅያ ያልያዙ ሰዎች ጥግ ይዘው ሲጠባበቁ የሚያሳይ ነው።

ባጠቃላይ በሽሬ ያደረግነው ቅስቀሳ ዉጤታማ ነበር። ስብሰባው (ተጀምሮ ሳያልቅ) በድል ተጠናቋል ማለት ይቻላል። ህወሓቶች ግን የህዝቡ የተቃውሞ መንፈስ በጣም አስደንግጧቸዋል። ሁሉም በስብሰባው እንዲሳተፍ ቢፈቀድለት ኑሮ ወደ ሁለት ሺ ሰው ይሳተፍ ነበር የሚል ግምት አለን። ግን ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ ተነፈገ።

የፈለገውን ሐሳብ በነፃነት እንዳያራምድ ተደረገ። ህዝብ አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ መከልከል ህዝብን ማፈን ነው። ታድያ ህዝብ እንዲህ ከታፈነ ለምን ነበር ይህን ሁሉ መስዋእትነት የከፈለው? የሽሬ ህዝብ ደሙ የሰጠ ለነፃነቱ አልነበረም እንዴ? ደም የሰጠ ህዝብ ነፃነት ይከለከላል?

ለማንኛውም የሽሬ ህዝብ የካድሬዎችን ማስፈራርያ ሳይበግረው በስብሰባው ለመሳተፍ መጥቷል። ህዝቡ በስብሰባው እንዳይሳተፍ የተደረገው በማስፈራራት ሳይሆን የአደራሹን በር በመዝጋትና ስብሰባው እንዳይካሄድ በመረበሽ ነበር። ህዝቡ ግን ለውጥ ይፈልጋል። በቅስቀሳው ወቅት ብዙ አባላት አፍርተናል። ስብሰባው ቢካሄድ ኑሮ ደግሞ የበለጠ ይሆን ነበር። በሐሳብ መከራከር የሰለጠነ መንገድ ነው። ህወሓቶች ዓቅም ካላቸው በህዝብ ፊት ቀርበው ከኛ ጋር ይከራከሩ። ስብሰባ መረበሽ ጀግንነት አይደለም። ጀግንነት ተከራክሮ ማሸነፍ ነው።

በትግራይ ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ የሚል መንግስት እንዴት በዓረና ስብሰባ ይደነግጣል? ህወሓት የህዝብ ድጋፍ ካለው ለምን ዓረና ከህዝብ እንዳይገናኝ እንቅፋት ይፈጥራል? ህወሓት ዓቅም እንደሌላቸው አረጋግጠዋል። በሽሬ ከተማ ህወሓት ምንም ድጋፍ እንደሌለውም አረጋግጠናል። የሽሬ ህዝብ በጣም የተበደለ ነው።

ይህን ሁሉ መስዋእትነት በነፃነት የመሰብሰብ መብት ካላስገኘ ታድያ ፋይዳው ምንድነው? ህወሓት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚያምን ቢሆን ኑሮ ይህን ያህን አይፈራም ነበር።

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው













ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።

በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።

ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል

በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።

የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል።

 መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

Ethiopians in South Sudan seek help

Ethiopian emigrants that reside in the Unity State of South Sudan are stating that they are found in war zone and are at risk.

Six Ethiopians working in the State’s main road construction said they have been hiding inside heavy machineries for the past two days. They said two Ethiopians have been killed while three were wounded.

Although the total number of Ethiopians that have been killed so far is unknown, according to the Voice of America (VoA) Amharic service, 30 Ethiopians have been killed until the December 26, 2013.

The Ethiopian migrants have told ESAT that their government has not reached out to them so far. They said they are puzzled that when the government of Kenya and Uganda have evacuated their citizens from South Sudan, the Ethiopian government did not do.

Four Ethiopian women who have been raped in the Jonglei State of South Sudan have received medical treatment in the United Nations Hospital in Juba.

Meanwhile, According to the Inter-Governmental Authority on Development (IGAD), spearheaded by leaders of seven East African countries, South Sudanese President SalvaKiir expressed hiscommitment to cease fire in the recently war-ravaged country.

 Uhuru Kenyatta, the Kenyan President, said, “Let it be known we in IGAD will not accept the unconstitutional overthrow of a duly and democratically elected government in South Sudan.”
More than 1,000 people have been killed in fighting between the government and rebels since 15 December when violent clashes began in the capital, Juba.

Thursday, 26 December 2013

ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!

ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!

December 25, 2013 Leave a comment

ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ።
ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ።
በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል።
በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል።
በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።

ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።
በዚህ ዙሪያ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የአንባስደሩን አማካሪ ዲፕሎማት አቶ ዘላለም እና አንባሳደር መሃመድ ሃሰንን ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም !
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
posted by Aseged Tamene

ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠው

ሰማያዊ ፓርቲ በአስቸኳይ የግንፍሌውን ጽ/ቤት እንዲለቅ ትእዛዝ ተሰጠው::
ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከ አራት ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰቦች ጋር በመምጣት ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው ሲል አሳስቧል:; ቤቱን ገዛሁት የሚለው ትግሪኛ ተናጋሪ ግለሰብ ቤቱን የገዛሁት ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አመራሮቹ ላይ ዝቷል::
ይህ ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በማይመለከተው ጉዳይ በመግባት ከዚህ በፊት ልቀቁ ተብላችሁ በተደጋጋሚ እንደተነገራችሁ መረጃው አለኝ በማለት በአመራሮቹ ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ዛቻ በመዛት ሄዷል:; በወቅቱ ይዞት የነበረው ተሽከርካሪ ጥቁር የደህነንት መኪና የሆነች ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ሲሆን የታርጋ ቁጥሩም ኮድ 2-89176 የሆነ ነው::
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በመነን አከባቢ ተከራይቶት የነበረውን ጽ/ቤት ገና ሳይገባበት በዝግጅት ላይ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ፖለኢሶች እና ቅጥረኞች ተባብረው በተቀናጀ አፈና ቢሮውን መንጠቃቸው ይታወቃል:: የነጠቁትንም ቢሮ ለካድሬያቸው በመስጠት ፔንሲዎን ከፍቶ እየሰራበት ይገኛል

Sunday, 22 December 2013

Wednesday, 18 December 2013

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

December 17, 2013
ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው  ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው ለሚረገጠው በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።Ginbot 7 Popular Force logo
የዋልድባ መነኩሳት ገዳማችን  አትድፈሩ አታፍረሱ በማለታቸው እየተገረፉ ለዘመናት ፈጣሪያቸውን ከሚማጸኑበት ለሃገርና  ለህዝብ ምልጃ ከቆሙበት ገዳም በዘር መመዘኛ እየተለዩ  እንደቆ ሻሻ ተጠርገው የተባረሩበት ፣ እምነታችን አትንኩ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  መሪዎቻቸው በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው  ወህኒ መውረዳቸው አንሶ  ወንድሞቻችን ይፈቱ በማለት  ሰላማዊ  ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻቸን በወያኔ ነፍሰ- ገዳዮች  በአረመኔያዊ ጭካኔ የተጨፈጨፉት በዚሁ አመት ነው። ወያኔ በህዝብ መሃከል በዘራው የዘር መርዝ የተነሳ በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮች ከጉራ ፈርዳና ከቤንሻንጉል፣ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ምስራቅ ሃረርጌ  አካባቢ  እንዲፈናቀሉና በገዛ ሃገራቸው መድረሻ ቢሶች  እንዲሆኑ የተደረገው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ነው። ጋምቤላዎች ሙርሲዎች አፋሮችና ሌሎችም ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች የተጨፈጨፉበት፣በልማት ስም ለመጡ የውጭ ወራሪዎችና ወያኔ ለፈጠራቸው ቱጃሮች ቦታ እንዲለቁ ተደርጎ ቀደምቶቻቸው ለዘመናት ከኖሩባቸው ቀየዎች እንዲነቀሉ ተደርገው እንደ አልባሌ ነገር የትም እንዲበተኑ የማድረጉ ሂደት ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው በዚሁ አመት ነው። በዚሁ አንድ አመት በወያኔ የሃገሪቱ ገዥዎች በህዝብ ላይ የተፈጸመው  ጭካኔና ወንጀል ተዘርዝሮ  የሚያልቅ አይደለም።
ይህ ወያኔ  ሰራሽ ሃገር በቀል የውርደትና  የስቃይ ህይወት አልበቃ  ብሎ ወያኔ ከሳውዲ የጨለማ ዘመን ገዥዎች ጋር በመተባበር ወንድሞቻችን በሳውዲ አውራ ጎዳናዎች ላይ እንዲታረዱ እህቶቻችን በቡድን በተደራጁ የሳውዲ ጎረምሳዎች  እንዲደፈሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ  ለኢትዮጵያውያን ያለውን እጅግ የከረረ ጥላቻ በአደባባይ ያሳየበት አመት ነው። እንዲህ አይነቱ የጅምላ ግፍና  ውርደት ከመከሰቱ በፊት ህዝባዊ ሃይሉ በአረብ ሃገር በባርነትና  በስደት የሚገኙ እህትቶቻችንን ወንድሞችችን ስቃይ  ስቃዩ አድርጎ በመውሰድ “ላንቺ ነው” በሚለው ድርጅታዊ መዝሙሩ “በባለጌ  አረቦች መዳፍ ውድ ክብራቸው ለጎደፈው እህቶቻችን፣ በአረቦች የባርነት ቀንበር ጀርባቸው ለጎበጠው  ወገኖቻችን እንደርስላችኋለን፣ የተሰባሰብነው  ደማችን የሚፈሰው የመከራ ቀናችሁን ለማሳጠር ነው” የሚል ቃል ኪዳኑ ሰጥቶ  ነበር። የድርጅታችንን ምስረታ አንደኛ  አመት ስናከብር ልባችንን ደስታ ሳይሆን ሃዘን እንዲሞላ የሚያደርገው ይህ ቃል ኪዳናችን ለማክበር የጀመርነው ጉዞ ከድርጅት ምስረታና ከድርጅታዊ ዝግጅት አልፎ   በኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻና ንቀት  የተነፋውን የወያኔን እብሪት በማስተንፈስ የወሰዳቸው ተጨባጭ የአለኝታነት እርምጃዎች ባለመኖራቸው ነው።

ምንም እንኳን ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል እራሱን እንደ ድርጅት አቁሞ  ኢትዮጵያውያንን አሰባስቦ  መራራው ትግል የሚጠይቀውን የፖለቲካ  የወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ አስታጥቆ  በወያኔ  ላይ ለመዝመት የጀመረውን ጉዞ የሚያስቆመው ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ብናውቅም የህዝብ ስቃይ ለግዜው መቀጠሉ የህባዊ ሃይሉን አባላት ማሰቃየቱ አልቀረም። በወያኔ  ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው ወገናችን ህዝባዊ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ እድሜ  የሚያሳጥሩ ፈጣን እርምጃዎችን እንዲወስድ በከፍተኛ  ጉጉት እየተጠባበቀ እንደሆነ  እናውቃለን። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች በተጠንቀቅ እንደቆሙ እናውቃለን። እነዚህ ዜጎች ከሁሉም የእምነት የቋንቋ  የጾታ የእድሜ  የኑሮና  የማህበረሰብ ስብጥር የሚያካተቱ  እንደሆኑ እናውቃለን። በሃገሪቱ ታሪክ ተሰምቶና  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የወታደር ልብሱን  እየጣፈ እንዲለብስ፣  የወታደር ጫማውን መቀየሪያ አጥቶ  ሸበጥ እንዲያደርግ የተገደደውን፣  የወያኔ ጀነራሎች በስልጣንና  በዘረፋ ሲያብጡ በድህነት እንዲሟሽሽ የተፈረደበት የሃገሪቱ ሰራዊት በዘር በእምነት ሳይለያይ ከህዝባዊ ሃይሉ ጎን ለመቆም አሰፍስፎ  የቆመ  እንደሆነ  እናውቃለን። ይህ ሃገራዊ እውነታ ለህዝብ የገባነውን ቃልኪዳን የለምንም ጥርጣሬ  ማስከበር እንደምንችል በሙሉ ድፍረት እንድናውጅ የሚያስችለን ሃቅ ነው።
የወያኔ ጀንበር እየጠለቀች የኢትዮጵያ  ህዝብ ጀንበር እየፈካች የመሄዱ ጉዳይ እንደማይታጠፈው  የመንጋትና  የመምሸት የተፈጥሮ ህግ ነቅነቅ የማይል እንደሆነ ግንቦት7 ጠንቅቆ ያውቃል።  እውቀታችን ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ ኣይደለም። ግፍ ፍትህን አሸንፎ፣ እውነት በሃሰት ተደፍቃ፣ ጥላቻ ፍቅርን፣ አድሎ እኩልነትን፣ ሃገራዊ ክህደት ሃገር መውደድን፣ ባንዳነት አርበኛናትን ለዘላላሙ ቀብረው የሄዱበት የሃገራችንና  የሰው ልጆች ታሪክ የለምና የወያኔን አይቀሬ ሞት ለመተንበይ  ልዩ ጥበብ አያሻንም። ይህን እኛ ብቻ ሳንሆን በዘረፋና በጥላቻ  የደነዘዘ ህሊና ያዳበሩት የወያኔ  ባለስልጣናትም ያውቁታል። ያለእኔ  ጀግና የለም፣ ያለእኔ  አልሞ  ተኳሽ የለም በሚል እብሪት በመጻደቅ የሚታወቁት ወያኔዎች በመቶ ሽዎች በሚቆጠሩ ወታደሮች ተከበው፣  በታንክ በአይሮፕላን በሚሳይል ታጅበው ከሚኖሩበት ቤተመንግስትና ቪላዎች ውስጥ ብርክ እንዲይዛቸው ያደረገው ለመሆኑ፣  ሳር ቅጠሉ ግንቦት ሰባት እየመሰላቸው ሲበረግጉ እንደሚያመሹ፣  የግንቦት ሰባት አባላት እያሉ ከድርጅታችን ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች እያሰሩ ሲያሰቃዩ ፣  ከምላሳቸው ላይ ግንቦት 7  የሚል ስም ተፈናጦባቸው  እንደሚውሉ በራሳቸው ሚድያ  ወያኔዎች ራሳቸው እያሳዩን እያስደመጡን ነው። ከዚህም አልፎ በዚህ አንድ አመት ውስጥ  የህዝባዊ ሃይሉን መሪዎች በመግደል ድርጅቱን ለማኮላሸት ይቻላል በሚል ወያኔ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችና ድርጅቱን ከውስጥ ለመቦርቦር ያሰማራቸው ሰርጎገቦች ተራ በተራ ተልእኳቸው እየከሸፈ በህዝባዊ ሃይሉ እጅ እየወደቁ ወይም ተልእኳቸው እንደማይሳካ ሲረዱ እየፈረጠጡ ወደ ወያኔ ሲመለሱ አይተናል።
ያለፈው አንድ አመት ተመክሯችን ስለወያኔ  ብቻ ሳይሆን ስለራሳችንም ጥንካሬና  ድክመት ብዙ ነገሮች ያስተማረን ኣመት ነው። የቀደምቶቻችን የጀግንነት የአርበኛነት ቅርስ በመላ ህዋሳቸው የተሸከሙ  ለኢትዮጵያ እና  ለህዝቧ ሲሉ ደማቸው ለማፍሰስ ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ ብቻ ሳይሆኑ አርቀው የሚያዩ  በርካታ ልጆች  ሃጋሪቷ ያሏት መሆኑን ያረጋገጥንበት አመት  ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ  ድርጅታችን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቸኛው የመንግስት ስልጣን ባላቤት የማድረጉን ታሪካዊ ራእዩን ለመሳካት የሚያደረገው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ጋር የሚደረግ እንደሆነ  በሚገባ  የተረዳነው  በዚሁ የአንድ አመት የድርጅታችን እድሜ  ነው። ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል ወያኔ በማህበረሰባችን ውስጥ ከዘራቸውና የሃገሪቱን ዜጎች እንዲበክሉ ካደረጋቸው የዘረኛነት የአድሎ  ከህዝብና  ከሃገር ጥቅም በፊት የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የሱሰኛነትና የሙስናና ሌሎችም አደገኛ ባህሎች ጋር ነው።
ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ  ደጋግሞ  እንደገለጸው ትግላችን አንድ መንግስታዊ ስርአት ወድቆ ሌላው የመንግስት ስርአት በመጣ ቁጥር የህዝብ ተስፋ እየጨለመ  “አዲስ ከመጣው ስርአት ያላፈው ያረጀ ስርአት በግፈኛነቱ በዘራፊነቱ ያነሰ ነበር” የሚል የግፈኛና የዘራፊ ስርአቶች ንጽጽር ላይ የቆመ አሳዛኝ የህዝብ ህይወት እንዲያበቃ ነው። ደርግን ያየ የአጼውን ስርአት እንከኖች ረስቶ ንጉሱ ይሻሉን ነበር ያለበት፣ ወያኔን ያየ የደርግን አስከፊ ዘመን ረስቶ መንጌ በስንት ጣሙ ያለበት አሳዛኝ ሁኔታ ከወያኔ መውደቅ በኋላ በሃገራችን እንዳይደገም ነው ትግላችን። የኢትዮጵያ ህዝብ የውድ ልጆቹን ህይወት ገብሮ ወያኔን በማስወገድ የሚያመጣው ስርአት ከወያኔ ብሶ ህዝብ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ቅስም ሰባሪና አዋራጅ የታሪክ ቅጥልጥሎሽ  እንዳይቀጥል ማድረግ ህዝባዊ ሃይሉ የተመሰረተበት፣ አባላቱ መከራ ለመቀበልና መስዋእትነት ለመክፈል በረሃ የገቡበት ዋናውና ብቸናው ምክንያት ነው። ትግላችንን መራራ የሚያደርገው ከበሰበሰውና የአንድ ጀምበር የህዝብ ቁጣ ከታሪክ ቆሻሻ የመጠያ ስፍራ ከሚከምረው  የወያኔ ስርአት ጋር ብቻ ሳይሆን በወያኔ ቦታ የሚተካውን ስርአት ከአድሎና ከዘረኛነት ከዘረፋና ሃገራዊ ክህደት የጸዳ፣ ዳግም ለኢትዮጵያውያን ውርደትና እንግልት ምክንያት እንዳይሆን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ሳይቀር የማያቋርጥ ትግልን ማድረግ የግድ ስለሚል ነው። ህዝባዊ ሃይሉ የአመጽ ትግል የሚያደርግ፣ የመሳሪያው ብዛትና  የሰራዊቱ ቁጥር እያደገ  የሚሄድ ሃይል መሆኑን ስለምንረዳ  ይህን ሃይል ገና ከጅምሩ ከብዙ እንከኖች እያጸዱ ማደራጀት ካልተቻለ  በሃገርና በህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ  የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጠንቅቀው የተረዱት ሃቅ ነው። ይህ ግንዛቤ የሰራዊቱን አባላት በጥንቃቄ መመልመልን፣ ማሰልጠንንና መገንባትን የግድ የሚል ነው።
ይህ ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል እጅግ መራራ ነው። ታሪካዊ ስህተቶችን ላለመድገም የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአካልና የመንፈስ ጽናትን፣ ሃቀኛነትን፣ ታማኝነትን፣ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትግል ነው። የወያኔ ስርአት ከሃገር ግድያው በተጨማሪ ትውልድን ለመግደል ሆን ብሎ ያስፋፋቸው እኩይና ጎጂ ባህሎችና ልምዶች ምን ያህል ማህበረሰባችንን እንደጎዱት ህዝባዊ ሃይሉ ባላፈው አንድ አመት እድሜው በሚገባ የተረዳው ጉዳይ ሆኗል። ህዝባዊ ሃይሉ የሚመኘውን የኢትዮጵያ ትንሳኤና ተሃድሶ እውን ለማድረግ እነኝህ  ወያኔ ሆን ብሎ  ያስፋፋቸውን የባህልና የሞራል ብክለት ማጽዳት የግድ እንደሆነ የተረዳ አካል ሆኗል።
ትግላችን መደፍረስን መጥራትን፣ መንተክተክን መስከንን የትግሉ ሂደት አካል አድርጎ  የሚጓዝ ነው።   ትግሉ የሚልመጠመጠውን እንደቀስት ቀጥ ብሎ ከሚራመደው፣ በካፊያው የሚንቀጠ ቀጠውን ለዶፉ ደንታ ከሌለው፣ ዝናር በቅፌን ከምሩ ተኳሽ  የሚለይ መራራ ትግል ነው። ያለፈው አንድ አመት ይህን አስተምሮናል። ህዝባዊ ሃይሉ ትግሉ ቀላል ነው የሚል ከእውነታ ጋር ያልተያያዘ ቃል ለህዝብም ሆነ ህዝባዊ ሃይሉን ሊቀላቀሉት ለተዘጋጁት ወገኖቹ አይናገርም። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል ለተሰለፉ በሽዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ትግሉ የሚጠየቅውን የሞራል የስብእና ጥብቅነት፣ከፍተኛ  የሃገርና የወገን ፍቅር፣ ጥልቅ የሆነ የመስዋእትነት ፈቃደኛነት የሚጠይቅ መሆኑን ከማስረዳት አንቦዝንም። ህዝባዊ ሃይሉ ለህዝብ ቃል እንደገባው ከወያኔ  ጋር የምናደርገው ትግል በጥበብ በእውቀት በጥናት በጥንቃቄ የምናደርገደው ነው። ነጻነት ያለመስዋእትነት እንደማይሳካ ብናውቅም ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። የውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።
ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ የድርጅት ምስረታ  መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ  ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ነው። በዚህ ረገድ የተሰራው ስራ አጥጋቢ ውጤት አስገኝቷል። ስልጠናው፣ ድርጅት ማጠናከሩና  ማጥራቱ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሃይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባላፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የሃገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት አመት መሆኑ ነው። በዚህ የህዝባዊ ሃይላችን የአንደኛ አመት ምስረታ  ክብረ በአል ወቅት ወገንም ጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ብቻ ነው።
ውድመት ለዋናውና  ለብቸኛው የኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያችን ጠላት ለሆነው የወያኔ ገዥ ጉጅሌ!
ድል በወያኔ ግፈኛ ስርአት አበሳውን ለሚያየው የመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ!
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል
Ginbot 7 Popular Force
www.ginbot7pf.org
Tel: +44 208 123 0056 begin_of_the_skype_highlighting +44 208 123 0056 FREE  end_of_the_skype_highlighting
email: pr@ginbot7pf.org

Tuesday, 17 December 2013

Thursday, 12 December 2013

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት…

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት…

December 11, 2013
ነቢዩ ሲራክ
Ethiopian woman in Saudi Arabia, Jiddah Ethiopian embassy
ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ ያየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ “አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር ላይ የሆነችው ሃገር ቤት ለመሄድ ወረቀቷ አልቆ እያለ “ሃገር ቤት አልሄድም!” በማለቷ እነረደሆነ ተነግሮኛል ። “በመጠለያው የነበሩት ሰነዳቸው ባሳር በመከራ አልቆ ሲሸኙ ወደ ሃገር ቤት አልሸኝም ብላ ረብሻ ከማንሳት አልፎ ከተዘጋጀው መኪና ወርዳ ይህን የምታየው ሚኒባስ መስታውት ሰብራዋለች! ከዚያን ቀን ወዲህ አትበላም አትጠጣም ፣ እኛንም የገረመን ይሄ ነው! ምን ታደርጋለህ! ” ነበር ያሉኝ …
ይህ ከተነገረኝም “ወዲህ ሃገር ቤት አልገባም!” ያለችው እህት ለቀናት በቆንስሉ በር አልጠፋችም። ከተቀመጠችበት ወንበር ጀርባ ባለው ግድግዳ “ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ እና የወጣውን የሳውዲ ህግ መስፈርት የማታሟሉ ወደ ሃገር ግቡ !” የሚለው የቆንስል ማስታወቂያ ይታያል ። ከአጠገቧ በፕላስቲክ ኪስ የታጨቀ ጓዟን አስቀምጣ ፣ በሆዷ ቁርአን ታቅፋ አንገቷን ከመድፋት ባለፈ በአካባቢው አዛን ስትሰማ የዘወትር ጸሎቷን (ሰላቷን) ወንበሯን ፈቀቅ አድርጋ እንደምትሰግድ አንድ ዘወትር እንቅስቃሴዋን የሚከታተል ወዳጀ አጫውቶኛል… እንዲህ ሆና ኮርመት ብላ ውላ ታድራለች! ቀን ጸሃይ ሲወቃት ፣ ማታ ወበቁ ይፈራረቅባታል ! ካየኋት ቀን ጀምሮ ወደ መጠለያው እንድትገባ ብዙ ሁነን ብንማጸናትም አልተሳካልንም …
ከሃገሯ በጤና የመጣችው እህት ችግር ውጋቷን እንድንጋራ ስንጠይቃት አትመልስም! ወደ ሃገር ቤት እንድትገባ በጅዳ ቆንስል ልትሸኝ ቢሞከርም አልተሳካም። የ”ሃገር ቤት ግቢ!” ” አልገባም!” አለ መግባባት ፍርሻ ከመምጣቱ በፊት አንዳንዴ ኦሮምኛና ብዙ ጊዜ ግን የተሰባበረ አረብኛ እየቀላቀለች መናገር ይቀናት እንደነበር አንድ “በመጠለያው እያለች አውቃታለሁ!” ያሉ ወንድም አጫውተውኛል። ያን ሰሞን ወደ መጠለያው እንድትገባ ተለምና ብትገባም በመጠለያው ውስጥ ካሉ ግፉአን ጋር ግብ ግብ ፈጥራ መውጣቷን ሰምቻለሁ!
ይዚህች ግፉዕ እህት ሰላም የነሳና አዕሮዋን ያወከ የውስጥ ህመም ሚስጥር አይታወቅም! ትሰማለች ፣ ለመናገር አልፈቀደችም! ባሳለፍናቸው የበር ላይ ውሎዋ ትንፍሽ ብላ ስትናገር ቢያን እኔ እስከ ዛሬ አልሰማኋትም ! ውስጧ እንጅ ውጭ አካሏ የተጎዳ አይመስልም! ከሁሉም የሚገርመው ይህች እህት ጤናዋ ታውኮ እንኳ ሃገር ቤት ከወገኖቿ ጋር መቀናቀል ሞት መስሏታል ! ሌላው አስገራሚ ሂደት የዚህችን መልከ መልካም እጣ ፈንታ የምንመለከትም ህጋዊ ሰነድ የሌለን ብዙዎች የሳውዲን መንግስት የምህረት ቀቢጸ-ተስፋ ሰንቀን ጤናችን ተጠብቆ እያለ” በሰላም ሃገር ቤት ግቡ!” የሚለውን የመንግስትና የወገን ምክር መቀበል አቅቶናል! እንዴት ነው ነገሩ …?
አንድየ ይታረቀን ከማለት ባሻገር ምን ይባላል :) ብቻ እሱ ያቅልለው እንጅ የሚሰማ የሚታየው ይከብዳል ! … ያማል … ያማል!

HRC confirms Human Rights abuses in Benishangul-Gumuz ESAT News

HRC confirms Human Rights abuses in Benishangul-Gumuz

ESAT News
December 11, 2013
The Human Rights Congress (HRC) of Ethiopia has confirmed that human rights and physical abuses have been committed against thousands of Ethiopians who have been evicted from different zones of the Benishangul-Gumuz region for belonging to the “Amhara ethnic origin”.
HRC also stated that around 10, 000 citizens residing in the region have been told that they were not “natives of the region” and were forcefully evicted from the region as of April 23, 2013.

The Congress has also stated that it has confirmed from the complaints and testimonies of the representatives of the evictees that children and women, females and the helpless have been going through enormous predicament due to lack of adequate food and drink.

It also stated that it had been able to investigate the scale of the problem and the general situation of the evictees.   The report states that the evictees are currently in a difficult situation and for example in some areas such as the Kamashe Zone; the properties of the returnees have been confiscated making it impossible for the returnees to restart their life.

HRC’s investigators have been able to confirm from the words of the victims that their ethnic origin has been mentioned as a reason and they have been refused and discriminated access to credits, seeds and fertilisers.

The number of evictees from the Baruda Kebele and its environs of the Bulen Woreda in Metekel Zone were around 5000 that were later spread out in Chagni town of the Amhara region. During their investigation, HRC’s researchers have found that there were over 500 people who were dispersed in different areas of the town.

The victims also told the Human Rights organisation that they have harassed, threatened and arrested for telling the abuses and hardships they have sustained during the eviction.

An application letter signed by over 140 evictees and other documents sent to the Congress reveal that they have went through a lot of suffering, abuse and discrimination at the hands of regional officials and local populace.

Evictees from Baruda Kebele have told the Congress that their properties have not yet been returned to them, they are being attacked, have got no support, are denied access to agricultural inputs for originating from “that ethnic group”.

ESAT’s reporter has also confirmed that although Ethiopians of the Amhara ethnic origin that have been evicted from the Benishangul-Gumuz region have been returned back to the region last year, they still have not received any form of help from the government and are even facing different forms of administrative abuses.

Wednesday, 11 December 2013

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ

(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ።

ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

የሶማሊ ክልል ለመከላከያ አዛዦች አዛዦች የመክበሪያ ቦታ መሆኗን ምንጮች አስታወቁ

በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት  ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ  ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና በክልሉ ቁጥር አንድ ሀብታም የሚባሉት /ወ/ት ሀዋ የሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ሁለተኛ ሚስትና የልጅ እናት ሲሆኑ፣ ግለሰቧ ከተራ ጫት ነጋዴነት በአንድ ጊዜ በብዙ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ለማጋበስ የቻሉት በፍቅር ጓደናቸው አማካኝነት መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰራተኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
ጄኔራል ዮሐንስ ከወ/ት ሀዋ ጋር የተዋወቁት በኮሎኔልነት ማእረግ የምእራብ ጎዴ አዛዥ በነበሩበት ወቅት ሲሆን፣ በወቅቱ ክልሉ ያወጣውን የምእራብ ጎዴን የካናል ጠረጋ የመከላከያ ሰራዊት እንዲያሸንፍ በማስደረግና የሰራዊቱ አዛዥም ስራውን ወ/ት ሀዋ ኩባንያ አቋቁመው በሰብ ኮንትራትነት እንዲሰጣቸው በማድረግ በአንድ ጊዜ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ እንዲያገኙ አድርገዋቸዋል።
በጄኔራል ዮሀንስና በወ/ት ሀዋ መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት እየደራ ሲሄድ፣ ወ/ት ሀዋ ከፍተኛ ሀይል እየተሰማቸው ከታክስ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የሚያቀርቡባቸውን የክልል ሰራተኞችን ሳይቀር የመከላከያን መኪኖች ይዞ በመሄድ በማስፈራራት ከግብር ራሳቸውን ነጻ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ምንጮች ይናገራሉ።
ወ/ት ሀዋ ከፍቅር ጓደኛቸው ከጄ/ል ዮሐንስ ጋር በመሆን ባቋቋሙት ኩባንያ በጅጅጋ ሁለት ታላላቅ ፎቆችን የገነቡ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ያለምንም ጫረታ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት የፈሰሰባቸውን ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸዋል።
ከፕሮጅቶች መካከል የቀብሪ ደሀር የውሀ አቅርቦት፣ የደገሀቡር የውሀ አቅርቦት፣ ጅጅጋ መምህራን ማሰልጠኛ ማስፋፊያ፣ የክልል የትምህርት ቢሮ ፕሮጀክት፣ ጅጅጋ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታና ሌሎችንም ውድ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። ምንም እንኳ /ወ/ት ሀዋ ግንባር ቀደም ሆነው ሀብቱን ቢቆጣጠሩትም ከጀርባ ሆነው የክልሉን ፕሮጀክቶች የሚያሰሩት ጄኔራል ዮሐንስ መሆናቸውን ምንጮች ይናገራሉ።
ጄ/ል ዮሐንስ በአዲስ አበባ ቦሌ መድሀኒያለም አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ፎቅ አሰርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ውስጥ አሁን በመከላከያ አዛዥነት የሚንቀሳቀሱ አንድ የህወሀት የመከላከያ ኮሎኔል የክልሉ ፕሬዚዳንት የትውልድ ቦታ ላይ አንድ የውሀ ፕሮጀክት እንዲሰሩ የ120 ሚሊዮን ብር ተፈራርመው ስራውን ከጀመሩ በሁዋላና አስፈላጊው ክፍያ ከተፈጸመ በሁዋላ ፐሮጀክቱ አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል። ባለፈው ወር ለእኝሁ ኮሎኔል 22 ሚሊዮን ብር ከክልል መስተዳደር ወጪ ተደርጎ እንደተከፈላቸውም ምንጮች ገልጸዋል።
ሰሞኑን በተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዝግጀቶችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የሽያጭ እቃዎችን እስከማቅርብ የሚደረሱ ስራዎችን ከህወሀት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በኮንትራት ወስደው ከፍተኛ ትርፍ እንዳገኙበት እነዚሁ የመስተዳድሩ የአስተዳደር ሰራተኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ጽሬዚዳንት ለማነጋገር ወደ ጽህፈት ቤታቸውው ስልክ ብንደውልም አልተሳካልንም።